tgoop.com/Re_ya_zan/2322
Last Update:
....የሆነ ጥሩ ቀን ላይ ደግሞ... መውደድ... ከፍቅር ቃላት ውጪ የሚገለፅበት ብዙ መንገድ እንዳለው ድንገት ብልጭ ይልልሃል። አለም ስለተስማማበት የተግባር አገላለፅ ሳይሆን... ከቃላት መካከልም በቦታቸው ተብለው፣ በኋላ ላይ ልብ ስትላቸው ከሌላው ልቀው ስለሚገኙት ነው የምልህ። ለምሳሌ... የእናትህን "ጨርሰህ ካልበላህ ወየውልህ!" አይነት... የአባትህን "የት ነው ያመሸኸው?" አይነት... ከተግሳፅ ውጪም ሌሎች ውስጣቸው መውደድን የደበቁ አገላለፆች... አንዳንዴ "ይቅርታ"ን... አንዳንዴ "እወድሃለው"ን ተክተው እንዳሳደጉህ ትዝ ይልህና ፈገግ ትላለህ።
....ከሁሉም ደግሞ... ጉዳዩ የአኽላቅ ተምሳሌት የሆኑት ተወዳጅ ሀቢብ ስለመረጡት አገላለፅ ሲሆን ሚዛኑ ፍፁም ሌላ ታሪክ ይሆናል። እናታችን ዓኢሻ (ረ.0) ጋር ከሚቆዩባቸው ቀናት በአንዱ እንግድነት ከመጡ ሶሃቦቻቸው ጋር ተቀማምጠው ሳለ፣ ከሚስቶቻቸው አንዷ በአንድ አገልጋይ ወደሳቸው ምግብ ወዳስላከችበት ወደዛ ቀን እንሳፈር። ዓኢሻ በድርጊቱ ተበሳጭታ የአገልጋዩዋን እጅ ትመታታለች፣ ምግቡም ከነ ሰሃኑ መሬት ላይ ወድቆ ይሰበራል። ታዲያ እንደማንኛውም አባወራ ያዙኝ ልቀቁኝ በሚያስብለው በዚ አጋጣሚ ላይ ሃቢቡና ቀለል አድርገው "እናታቹ ቀንታ ነው" በሚል ፈገግ በሚያደርግ ማስተባበያ ሸፍነውላት፣ ምግቡንም በምግብ፣ ሰሃኑንንም በሰሃን እንዳስተኩ ይነገራል። "እናታቹ ቀንታ ነው"... ምን አይነት ሰኪና... ምን ያለ ሂክማ ነው! አላልክም?... የማን ጭንቅላት ላይ እንዲ ሁሉን በአንድ የያዘ አገላለፅ ይመጣል? አንድም ንዴቷ እሳቸውን የመውደድ መሆኑን ሲረዱላት የሷን መውደድን.... አንድም እንግዶቹ ስሟን ይዘው እንዳይሄዱ ሲሰትሯት የሳቸውን መውደድን.... "ስለምወድሽ መውደድሽን ተረድቼ አልፌልሻለሁ" አይነት.... ማንስ ቢወዳቸው፣ ቢቀናባቸው መች ይገርማል?.... "በሳቸው ውስጥ መልካም መከተል (ምሳሌ) አለላችሁ" የተባልነውን ልዩ ሰው መከተልን.... ካስተማሩን ብዙ ብዙውን መተግበርን ራህማኑ ይወፍቀን።
@Re_Ya_zan
BY TEAM HUDA
Share with your friend now:
tgoop.com/Re_ya_zan/2322