tgoop.com/Re_ya_zan/2323
Create:
Last Update:
Last Update:
ንጋት...
ሲነጋ አይኖች ሲከፈቱ፣ አዲስ ቀን ብቅ ያለ ይመስላል። ነገር ግን ንጋት ሁሌ አዲስ ተስፋ አይደለም። የትናንቱን ኮተት ሰብስቦ የሚመለስ፣ ፀሀይ መውጣቷ ብቻ የሚለየው ዳግማው ትናንትም ይሆናል። እድሜያችንም የነዚህ ቀናት ጥርቅም ነው። ዳግማዊ ትናንቶች በየቀኑ ሲደጋገሙ ህይወታችን ወጥ ይሆናል። ዛሬዎችን ማጣት ህይወትን ይበልጥ አሰልችና የሚያስመርሩ ያደቸዋል። በነዚህ ቀናት ስናልፍ አልፎ አልፎ ብቅ የሚሉ አዳዲስ ንጋቶች፣ አዲስ ቅርፅ ያለው ዛሬን ሲሰጡን ትላልቅ የደስታ ቀናት እናልፋለን። የደስታ ቀናችንንም አንድ ብለን ከቆጠርናቸው ብዙ ዳግማዊ ትናንቶች ጋ ደምረን አንድ እርምጃ እንደተንቀሳቀስን ሁሉ.... ዳግም ወደቆጠራ ተመልሰን ሁለት እንላለን። እድሚያችንም ይበልጥ ያጥርብናል። ብዙ የተቃጠለ እድሜም እንዳለ ይሰማናል። ዳግማዊ ትናንቶችን መደምሰስ ባንችልም ግን ከትናንቱ የተወሰነ ልዩነት ለማምጣት ብለን እስካልተነሳን ድረስ አዳዲስ ዛሬዎች ይበልጥ እየራቁን ይመጣሉ። ስለዚህ ቢያንስ ትናንትን ከዳግማዊ ትናንት ለመለየት የቀኑን አጀማመራችንን እንለውጠው ወይንም አጨራረሳችንን። አንድን ቀን ሁለቴ ላለመኖር ያክል ብቻ…
@Re_Ya_zan
BY TEAM HUDA
Share with your friend now:
tgoop.com/Re_ya_zan/2323