Warning: mkdir(): No space left on device in /var/www/tgoop/post.php on line 37

Warning: file_put_contents(aCache/aDaily/post/Re_ya_zan/--): Failed to open stream: No such file or directory in /var/www/tgoop/post.php on line 50
TEAM HUDA@Re_ya_zan P.2326
RE_YA_ZAN Telegram 2326
እድሜ

ልጅነት የተለየ አለም አለው። ደስታ፣ ጨዋታ፣ መቦረቅ፣ መደባደብ… ከኛ ከትልቆቹ አለም እጅግ ይለያል። በጣም ጣፋጭ የማይገኝ የሚናፍቅ ጊዜ ነው "ኧረ ልጆች ልጆች እንጫወት በጣም፣ ከእንግዲህ ልጅነት ተመልሶ አይመጣም…" እያልን ትርጉሙን ሳናውቀው እየዘመርን ቦረቅንበት። ትልቅ መሆን እንደተመኘን ነፃነት ያለው እየመሰለን እየጓጓንለትም አደግን። ነገር ግን ስናድግ ትልቅነት እንዳሰብነው የሚናፈቅ አለም ሁኖ አላገኘነውም። ልጅ ሁነን እጃችን ላይ ትንሽ ነገር ከቧጨረን ሳምንቱን እንደ ህመምተኛ እጄን ነካብኝ፣ አያስበላኝም፣ አያስተኛኝም ብለን እንዳልቀበጥን ሁሉ፣ አሁን መች እንደቆሰለ ራሱ የማናውቀው ብዙ ቁስል ሰውነታችንን ሞልቶታል። መች እንደቆረጥነው ሳናውቅ ረጥቦን ስንመለከተው እየደማ እንደሆነ የምናውቅባቸው አጋጣሚዎች ጥቂት አይደሉም። በማደግ ውስጥ አለመታመም ኑሮ ወይስ የውስጣችን ህመም በዝቶ ይሆን ሲቆስል የማትታወቀን ባይገባኝም ትልቅነት ግን የሚያጓጓ ጊዜ አልነበረም።

በትልቅነት ውስጥ አዕምሯችን ይበሰልም አይብሰልም ሀላፊነቶችን የመወጣት ግዴታ ይኖርብናል። አሁን ላይ እያንዳንዱ ጥቃቅን ስህተት "ልጅ ናት አታውቅም" ተብሎ አይታለፍልንም። "ትልቅ አልደለች እንዴ?!" ብሎ ተቆጪው ወቃሹ ብዙ ነው። የስኬት መንገዶች ላይ ድሮ ልጅ እያለን የማናውቀውን "ምቀኛ" የሚባል ቃል እንማራለን። በየምንገዱ ማልቀስ ላገኙት ሁሉ መዘርገፍ የማያዋጣ ነገር ይሆናል። ድሮ ልጅ ስለሆንን "እንዳያስቡ!" ተብለን የተደብቅናቸውን ችግርና ፈተና የሚባሉ ነገሮችን በተግባር እንማራለን። ከዛም ትልቅነት ያስጠላናል፣ የምንነፋረቅበት እቅፍ ይናፍቀናል። ወደ ልጅነት መመለስን ብንሻም በምኞት ውስጥ ስንዋልል ቁሞ የሚጠብቅ እድሜ የለንም። ከኋላችን እርጅና ያሳድደናል አሁን ከምንኖረው የባሰ የሆነ እድሜ። ቁጭ ብሎ ወጣትነትን እያስታወሱ ራሳችንን የምንወቅስበት እድሜ። መለስ ብለን ስናስበው ብንመለስበት ብዙ ማሳካት የምንችልበት እንደሆነ እንዲሰማን የሚያደርግ፣ አሁን ብዙ ያደከመንን ፈተና "ለዚህ ነው?" ብሎ የሚያስንቅ እድሜ ወደፊት ይጠብቀናል። ምኞት ብቻ ሁነን መስሪያ ጉልበቱን የምናጣበት፣ ለነገ ብለን የገፋነው ሁሉ ተጠራቅሞ የሚጠብቅብን፣ አንገፋው ወደፊት የለን…አንሰራው አቅሙ የለን… እንዲሁ ሁነን እንባክናለን። ከዛም ለምን ወጣትነት ላይ ፈተና እና ችግር እንደሚበዛ ይገለጥልናል። የተሻለ የእርጅና ዘመን ላይ መኖር እንችል ነበር። ነገር ግን ነጋችንን ሳናቅድ ኑረነዋልና ያተረፍነው ነገር ምን እንደሆነ አይገባንም። ከዛም ዳግም ለምን ወጣትነቴን ሳልጠቀምበት የሚል ቁጭት እናስከትላለን። ይህን የሚያውቁ አዛውንቶችም በቻሉት መጠን ሊመክሩን ይጥራሉ። ሁሉም ባለፈበት እንድናልፍ አይመኝልንም። ትንሽ የሚንቀሳቀስ ወጣት ሲያዩ ይደሰታሉ። ሁሉም ወጣቱን ህዝብ ይፈልገዋል፣ ለስኬት አስፈላጊ እንደሁነ ስለሚያውቅ ያለፈውን እድል ወጣቱን ተጠቅሞ እንዲሳካለት ይለፋል። ምክንያቱም አስቦበትም ይሁን ሳያስብበት ሀላፊነትን የተሸከመው ወጣት እሱ ብቻ እንደሚያሳካው የሚያውቁት እድሜውን ያለፉት ብቻ ናቸውና። እናማ… ህመሙ፣ ችግሩ፣ ሀላፉነቱ ቢበዛም ሁሉን ችሎ ትልቅ ቦታ የሚደርሰው የወጣትነት ሀይል ያለው ብቻ ነውና ችለን ነጋችንን መገንባት ትልቁ ስኬታችን ነው። የእድሜያችን ፈተና ይህ ስለሆነ!

@Re_Ya_Zan

tgoop.com/Re_ya_zan/2326
Create:
Last Update:

BY TEAM HUDA

Share with your friend now:
tgoop.com/Re_ya_zan/2326

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

5Telegram Channel avatar size/dimensions There have been several contributions to the group with members posting voice notes of screaming, yelling, groaning, and wailing in different rhythms and pitches. Calling out the “degenerate” community or the crypto obsessives that engage in high-risk trading, Co-founder of NFT renting protocol Rentable World emiliano.eth shared this group on his Twitter. He wrote: “hey degen, are you stressed? Just let it out all out. Voice only tg channel for screaming”. Activate up to 20 bots Other crimes that the SUCK Channel incited under Ng’s watch included using corrosive chemicals to make explosives and causing grievous bodily harm with intent. The court also found Ng responsible for calling on people to assist protesters who clashed violently with police at several universities in November 2019. With the “Bear Market Screaming Therapy Group,” we’ve now transcended language.
from us

Telegram TEAM HUDA
FROM American