tgoop.com/Re_ya_zan/2328
Create:
Last Update:
Last Update:
እየደከምክ ግን ላለመውደቅ በመፍጨርጨር ውስጥ ሳለህ የማይደርስልህ፣ የማያስተውልህ ወዳጅ የወደቅክ ቀን ሊያስተዛዝንህ ብቅ ይላል። የመውደቅ እንጂ ይዞ የመቆየት ህመም የሚያም አይመስለው ይሁን አሊያ ስትወርድ አንድኛውን አላቅስሐለሁ ብሎ ይሁን ብለህ ጠርጥር። እንጂ መውረድህ እፎይታ ሰጥቶት ከንፈር ይመጥልኛል ስትል አትጠርጥር።
አውቃለሁ እያነባህ የደስታ የሚመስላቸው ሰዎች እንዳሉ፤ እየታገልክ ቀና ያልከውን ከኩራት የሚመድቡት እንዳሉ ይገባኛል። ያለፍከው መከራ ልብህን እንደወንፊት አሳስቶ ቶሎ እንደሚከፋህም።
ግን....
መታገልህን የሚረዳ፣ በቁም ውስጥህ እየተበላ እንደሆነ የሚያየው አሏህ አይበቃህም? ሊፈርድብህ ሳይሆን ሊሰማህ የተዘጋጀው አሏህ፤ ብስራቱን ሊሰድልህ ጥቂት ትቀርበው ዘንድ አንተን መጠበቁ አይበቃም ?
ትንሽ ታገስ። የተስፋን ክር የያዝክበቱ እጅህ ከጌታው የሆነን መረዳት እስኪያገኝ ድረስ ታጋሽ ሁን!
@Re_Ya_Zan
BY TEAM HUDA
Share with your friend now:
tgoop.com/Re_ya_zan/2328