tgoop.com/Re_ya_zan/2329
Last Update:
....አንድ የጌታሽ ዱንያ ላይ፣ ሁለቴ መጣን እንል ዘንድ ለትዝታ....
.
.
"ስካር
ከምሽቱ 6:07
<ኧረ ልጅቷ ዛሬ በጤናዋም አይደለች! ምን ነክቷት ነው።> ቅድም ጀምራ የምትስቀውን እንስት ግራ በመጋባት ውስጥ ያይዋታል። ስተፈልግ ደሞ እየሳቀች ታለቅሳለች። በአፏ አንድ ነገርን ከመደጋገም ውጭ ለሚጠይቋት ጥያቄ ምንም መልስ አልሰጥ ብላቸዋለች። <ሰክራ ነው> ብለው ጥለዋት ሄዱ። ከማንም በፊት ለድሮ ሚስጥረኛዋ ጨረቃ መናገር ነበረባትና እነሱ ከመሄዳቸው ወደ ሚስጥረኛዋ እየተመከተች መናገር ጀመረች።
< ሰማሻቸው ጨረቃዬ! ሰከረች አሉኮ ሃሃሃሃ ለነገሩ ምን ይበሉ እኔን ያሰከረኝ ነገር መች ገብቷቸው። ልክ ናቸዋ ሰክሪያለሁኮ፣ ግን ጠጥቼ አይደለም የሰከርኩት። እያሳቀ የሚያስለቅሰኝ ስካር የደስታ ስካር ነው። ለካ ደስታም ያሰክራል። ታውቂያለሽ! እስከዛሬ ተናድጄ፣ ታምሜ፣ አዝኜ፣ ተከፍቼ፣ ናፍቄ ነበር እንቅልፍ የማጣው ዛሬ ግን በተለየ ሁኔታ በደስታ ሰክሬ ነው።> ፈገግታ ምስልን የተላበሰችው ጨረቃ እሷም በደስታዋ የተደሰተች ትመስላለች። ንግግሯን ቀጠለች < ጨረቃ ግን አልገረመሽም! ብዙ ነገር በአንዴ እንደዚህ ብስራት በብስራት ሲሆን? በራስሽ ብስራት በጣም ተደስተሽ ደስታሽን የምታካፍያቸው ሁሉ ሲደሰቱ ስታዪ ደሞ ምን ያክል ደስታሽ እንደሚጨምር። ከዛም ደሞ እንሱን ያስደሰታቸውን ሲያካፍሉሽ፣ በነሱ ደስታ ስትደሰቺ ሱብሃንንን… ታውቂለሽ በአንድ ወቅት ለኔ ቅርብ የሆነው ወንድሜ "ችግሮች ጫፍ ሲነኩ መፈቻቸው ይቃረባል" ብሎኝ ነበር። ከቀናት በፊትኮ በዚሁ ሰአት ጭንቄን ላሰማሽ ተቀምጬ ነበር። የአሁኑ ደስታዬ ደሞ በቃ ጭንቅ ውስጥ ማለፍ ምንም አንዳልነበር ያሳየኛል። እና እንደዚህ ሁኖ በደስታ ብሰክር ይፈረዳል ወይ? ለካ አንዳንዴም ከማዘን ይልቅ የኢላሂ ባሪያ በመሆን ብቻ መደሰትም የሚገባ ነው። > ምላሽ ሳትጠብቅ እየተፍለቀለቀች ከተቀመጠችበት ተሳች። ከማንም በፊት ምስጋና ለሚገባው ጌታ መስገጃዋ ላይ ተደፍታ ልታመሰግነው!
" ألهم لك الحمدْ كما ينبغي لجلال وجهك و لعظيم سلطانك "
ረቡዕ 19/12/13"
@Re_Ya_Zan
BY TEAM HUDA
Share with your friend now:
tgoop.com/Re_ya_zan/2329