tgoop.com/Re_ya_zan/2333
Last Update:
በ ህይወትሽ የትኛው የህይወትሽ ክፍል ቢደገም ትደግሚያለሽ?ብባል ድጋሚ እንኳን ሳላስብ 'አስራ ሁለተኛ ክፍልን!" ምል ይመስለኛል😊
በጣም ሰነፍ ነበርኩ ብያችኋለው? ብቻ ሰነፍ ነበርኩ ( አሁንም!😂) እና ለ ኢንትራንስ እንድናጠና ሚዘጉልን ጊዜያት እንዴት ያለ ቆንጆ የ እንቅልፍ እና የ ወሬ ሰአት ሆኖልኝ እንደነበር! ልናጠና ተሰብስበን ስናወራ ቀኑ እልቅ!... አጥንቶ እንደዋለ ሰው ቤት ገብቼ እራቴን በልቼ ለጥ!.....ግን ይሄ ምቾት ብዙ አልዘለቀም። በሌላ በኩል የ dicipline ማስተርስ ያላቸው ጓደኞቼ በየት ያስተኙኝ?😑 ቤት ድረስ እየመጡ እየጎተቱ ላይብረሪ! ወለም ዘለም የለም። ብቻ ከወሬው ፣ ከዝላዩ እና ከማይረሱ ትዝታዎቹ ጋር እንደዛሬም ነገር ባለመክረሩ በ አላህ ራህመት + በ ጓደኞቼ ፅናት በጥሩ ውጤት ግቢ ገባው።
ባለፎ የዘንድሮዎቹን አግኝቼ "እናንተ ላይ ከፍቷል ጊዜው መቼም.. እንዴት ነው ጥናት?" ስላቸው እኩል ሳቁና
"ትተነዋል ባክሽ" አሉኝ።የዛን ቀን ፊታቸው ላይ ያየሁት ተስፋ መቁረጥ አስደንጋጭ ነበር።already ቀድመው እንደሚወድቁ አምነው ተቀብለውታል።ደሞ ገና 11 ላይ 12 ሲወድቁ ምን እንደሚሰሩ ከሚያወሩ ለጋ ወጣቶች ጋር ማውራት ሲያስጠላ ወላሂ!!
ግን "ለዚህ ምክንያቱ ማንም ይሁን ማን መወቃቀሱን ትተን ዳይ ወደ መፍትሄ!" ያለው ሁርቃን(hurqan) ተቋም ፤ አምና በ አመርቂ ውጤት 12ተኛ ክፍልን አገባደው ወደ አንጋፋው አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የተቀላቀሉ ተማሪዎችን በመጋበዝ ፤ ለዘንድሮ ሙስሊም ሴት ተፈታኞች በ ሞራል ፣ በ ምክር እንዲሁም በ ልምድ ማጋራት( Experience sharing) ሊያሳሽቃቸው ዝግጅቱን እያገባደደ ነው።ሙስሊም ሴት ናችሁ?ለ ህይወታችሁ እድገት ቦታ አላችሁ? ባትሆኑም ሙስሊም ሴቶችን ማበርታት ትፈልጋላችሁ? እንግዲያውስ እንቀላቀል!
(12ተኛ የሆናችሁ ሴቶች ደሞ ግዴታ ነው!☺)
https://www.tgoop.com/HURQANN
BY TEAM HUDA
Share with your friend now:
tgoop.com/Re_ya_zan/2333