Telegram Web
ወዳጆች እንዴት ከረማችሁ 👋
ዛሬ ሽሙንሙኒት( ውበኛዋን )ቅዳሜን ልዳስስ ብቅ ብያለሁ ተከተሉኝማ...
መለያየት ባይኖር መተዋወቅ ምነኛ ድንቅ ነበር ያለው ማን ነበር ?
እኛም ታዲያ ግማሽ ሃዘን ግማሽ ደስታ ዝብርቅ ስሜት ውስጥ ሆነን ተመራቂ እህት ወንድሞቻችንን ልንሸኝ በጊዜ ነበር ዝግታችን የጀመርነው ።

ሁላችንም በመተጋገዝ ስንሰራ ቆይተን ሰዓቱ  ደረሰና መርሃግብራችንን በቡና መዓዛ ፣ በእጣኑ ሽታ አጅበን መርሃግብራችንን ጀመርን።

ተመራቂዎቻችን ልምዳቸውን ሲያካፍሉን RVC ቤት  መቼ እና እንዴት መጥተው ቤተሰብ እንደሆኑ ሲያወጉን  እንዲሁም የማይረሱትን ገጠመኝ ሲነግሩን በመሃል ደግሞ ግጥምና ሙዚቃ ፣ጨዋታ ትንሽ ደግሞ ወዝወዝም ብለን ትከሻ ተፈትሿል😁ብቻ በሳቅ ደምቀን አመሸን
ከዛ መለስ ስንል ደግሞ  ሁሉም ከተመራቂዎች ጋር ስላሳለፈው ጊዜ እያወራ መልካም እንዲገጥማቸው ሲመኝ የሁላችንንም ስሜት ተነክቶ  መለያየትን መራራቅን እየረገምን በመሃረብ ጠርዝ አይኖቻችንን አደራረቅን።

ከዛ ቀጥለን በእውቅና እና ሰርተፍኬት መርሃግብር ስራ አፅፈፃሚዎች ለነበሩ ፣ ንቁ ተሳታፊ እንዲሁም ቤተሰብ ሆነው ለቆዩ ተመራቂ ተማሪዎችን እና በኦፕን ማይክ ፕሮግራምም ተሳታፊ የነበሩ ልጆችን አመስግነን እውቅና ሰጠን።

ለቀድሞ ፕሬዝዳንታችን ደግሞ ቆንጆ ስዕል በስጦታ አበርከትንላት።

ለአመቱ የመጨረሻ የሆነውን ብሔራዊ መዝሙር በህብረት ዘምረን በህብረት ፎቶ ተነስተን ቅዳሜያችንን ሸኘናት።

ሰናይ የረፍት ጊዜ 🥰

📝በማክዳ ጸጋዬ

#ኑ_የቆምንበትን_መሠረት_እንፈትሽ
#የተሻለ_ትውልድ_ለተሻለች_ኢትዮጵያ
#የምክንያታዊ_ባለራዕዮች_ስብስብ
@RvcClub
11🥰2
Forwarded from HU STUDENT UNION OFFICIAL (Кαℓ 🫧)
Introducing the New AHAVAH Leadership Team

We’re so excited to welcome our newly appointed leaders — individuals who embody the spirit of love, service, and vision that AHAVAH stands for.

President: Hanan Mohammed
Vice President: Sara Sebisibe
Secretary: Amare Hamaro

At AHAVAH, we believe in building a brighter future for Ethiopia one where all children can truly enjoy their childhood, dream freely, and grow in love.

We are more than just a club we are a movement of heart-led youth who share love, act with intention, and serve with joy.
5
🔔 የመውጫ ፈተና የመጀመሪያ ቀን የኦንላይን ፈተና ውሎን ተከትሎ ከትምህርት ሚኒስቴር የተሰጠ ማሳሰቢያ፦

  ማንኛውም ተፈታኝ ፈተናውን ሲጨርስ Finish and Submit ሳያደርግ መውጣት የለበትም። ተፈታኙ ይህንን ማድረጉንም በፈተና ክፍሉ የተመደበ ባለሙያ ማረጋገጫ ሳይሰጠው እና ተፈታኙም ፈተናውን መጨረሱን በፊርማው ሳያረጋግጥ ከመፈተኛ ክፍል መውጣት አይኖርበትም።

በተለያየ ምክንያት ሲስተም ዘጋብን በማለት ፈተና ክፍል ውስጥ የሚቀመጡ ተፈታኞችን በተለያዩ መንገዶች የማጣራት ሥራ በመስራት አስፈለጊውን የእርምት ወይም አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰድ ይኖርበታል።

https://www.tgoop.com/HUGaDSSA_Official
በምክንያታዊ ባለራዕዮች ስብስብ ውስጥ ለነበራችሁ ተሳትፎ  የምስክር ወረቀት (certificate ) አሰርታችሁ  በወቅቱ ላልወሰዳችሁ ተመራቂ ተማሪዎች በሙሉ :-

ሰርተፍኬታችሁን እስከመመረቂያ ቀን ድረስ ብቻ በዋናው ጊቢ የተማሪዎች ኮምፕሌክስ ፣ ይሽሩን ኮፒ ቤት በአካል በመገኘት እንድትወስዱ እናሳስባለን ።

ከተጠቀሰው ጊዜ በኃላ ለሚቀርቡ ጥያቄዎች  ሃላፊነቱን የማንወስድ መሆኑን እንገልፃለን ።

#ኑ_የቆምንበትን_መሠረት_እንፈትሽ
#የተሻለ_ትውልድ_ለተሻለች_ኢትዮጵያ
#የምክንያታዊ_ለራዕዮች_ስብስብ
@RvcClub
Forwarded from H.U.P.S.A.
ስለ HUPSA ሰምተዋል?

የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሳይኮሎጂ ተማሪዎች ማህበር በቅርቡ የተቋቋመ ማህበር ሲሆን ጥራት ያለው እና ተግባራዊ የስነ-ልቦና እውቀትን በማስፋፋት ተማሪዎችን እንዲሁም ሰፊውን ማህበረሰብ ማገልገልን አላማው አድርጎ ሲንቀሳቀስ ቆይቷል።

ማንነታችንን፣ ስሜት፣ አስተሳሰብ እና ባህርያችንን፣ ግንኙነቶችን እና የማህበረሰባችንን ችግሮች በስነ ልቦና መነጽር ለመረዳት እንተጋለን። በጎ ስራም ዘላቂ አሻራ እንዳለው በመረዳት በነዚህ ሁሉ አብረን እንስራ እንላለን።

የስነልቦና ጉዳይ የሁላችንም ጉዳይ ነውና ሀሳቦቻችሁን እና ተሰጥኦዎቻችሁን ይዛችሁ ብቅ በሉ። ተጨልፎ ከማያልቀው ከሰው ልጅ ማንነት ጋር አብራችሁን ታገሉ።

ኑ ራሳችንን እንወቅ!

Telegram Instagram
5
2025/07/13 23:13:13
Back to Top
HTML Embed Code: