Telegram Web
Forwarded from Hawassa University
Upcoming Event at Hawassa University

26th Students' Graduation Ceremony on the Weekend!

Congratulations Class of 2025!

Hawassa University
Ever to Excel!
ውድ የቤታችን ድምቀቶች
እነሆ ተናፋቂዋ ቀን ደርሳለች

የልፋታችሁን ውጤት የምታዩበት ተውዳጁን ባርኔጣ የምትጭኑበት ፣ በጥቁሩ ካባ የምትዋብበት
ለዚህች ውብ ቀን እንኳን በሰላም አደረሳችሁ።

በደስታችሁ ምንግዜም ደስ ይለናል

👩‍🎓እንኳን ደስ አላችሁ 👨‍🎓

#ኑ_የቆምንበትን_መሠረት_እንፈትሽ
#የተሻለ_ትውልድ_ለተሻለች_ኢትዮጵያ
#የምክንያታዊ_ለራዕዮች_ስብስብ
@RvcClub
8
ክዋክብቶቻችን ሲያንፀባርቁ የእኛም አይኖች በደስታ ይበራሉ ።

🏅ወርቅ የሆነችው የቀድሞ ፕሬዝዳንታችን አይናዲስ ታረቀኝ ከትምህርት ክፍሏ እጅግ ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ የወርቅ ሜዳልያ 🏅 ተሸላሚ ሆናለች።

ኮርተንብሻል አይንዬ

#ኑ_የቆምንበትን_መሠረት_እንፈትሽ
#የተሻለ_ትውልድ_ለተሻለች_ኢትዮጵያ
#የምክንያታዊ_ለራዕዮች_ስብስብ
@RvcClub
33👏9👍1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የምስራች

እንኳን ደስ አላችሁ

ተናፋቂዋ ቅዳሜያችን ከነ ሞቅታዋ በእያንዳንዳችን በስክሪን ከተፍ ልትል ነው።

ከሰኔ 21/2017ዓ.ም ጀምሮ ሞቅ ደመቅ ያሉ መሰናዶዎችን በመያዝ በ Google meet መተግበሪያ በቀጥታ መተላለፍ ይጀምራል።

ከርሶ የሚጠበቀው ሰዓቱን ጠብቀው የሚለቀቀውን መስፈንጠሪያ (link) መጫን ብቻ ።

በጉጉት እንጠብቃችኋለን

📍🗺 አድራሻችን RVC Telegram channel ።

🕰 ከምሽቱ 2:30 ጀምሮ

  የቴሌግራም ቻናላችንን ላልተቀላቀላቹ ከታች ባለው ሊንክ መቀላቀል እንዳይረሳ።

📌 ሰዓት ማክበር የምክንያታዊ ባለራዕይ ወጣት መገለጫ ነው።


#ኑ_የቆምንበትን_መሠረት_እንፈትሽ
#የተሻለ_ትውልድ_ለተሻለች_ኢትዮጵያ
#የምክንያታዊ_ባለራዕዮች_ስብስብ
@RvcClub
@RvcClub
11👏2
በዚህ ሳምንት በምክንያታዊ ባለራዕዮች ስብስብ :-

ክረምትን......ለእረፍት ወይስ ለ"ብቁ"ነት?

1, ስኬታማ የክረምት ጊዜ ምን ምንን ያካትታል ትላላችሁ?

2,በአሁኑ ክረምት በማድረግ ላይ ያላችሁት ወይም ለማድረግ ያሰባቹት ተግባር ምንድንነው?

3,ክረምትን አስመልክቶ ሙያ ነክ ወይም እውቀት መጨበጫ ስልጠና ብታካፍሉን?

4,በስራ አለም እና በትምህርት ላይ ላለ ሰው የክረምቱ ጣዕም ልዩነት ይኖረው ይሆን?

5,የስራውን አለም የተቀላቀላችሁ፣ ተማሪዎች ክረምትን ምን በማድረግ ቢያሳልፉ ጥሩ ነው ትላላችሁ?

በጉጉት እንጠብቃችኋለን

📍🗺 አድራሻችን RVC Telegram channel ።

🕰  ከምሽቱ 2:30 ጀምሮ

  የቴሌግራም ቻናላችንን ላልተቀላቀላቹ ከታች ባለው ሊንክ መቀላቀል እንዳይረሳ።

📌 ሰዓት ማክበር የምክንያታዊ ባለራዕይ ወጣት መገለጫ ነው።


#ኑ_የቆምንበትን_መሠረት_እንፈትሽ
#የተሻለ_ትውልድ_ለተሻለች_ኢትዮጵያ
#የምክንያታዊ_ባለራዕዮች_ስብስብ
@RvcClub
@RvcClub
3
እነሆ ሐሙስ

ከብዙ መጠፋፋት እና መነፋፈቅ በኋላ በቤታችን ተሰብስበን መፀሀፍትን የምንመረምርበት ወይ ደሞ በመፅሐፍት የምንመረመርበት ግዜው ደርሷል።

ወቅቱ ሆነና ከትንሿ ቤታችን ብንርቅም ቴክኖሎጂ ባበጀልን መተግበሪያ ሰብሰብ ልንል ዝግጅታችንን ጨርሰናል።

ወትሮም ለክረምት የተማሪ እና የመጽሐፍት ፍቅር ይደራል ።

ማንበብ ሱሳችን የሆንን እኛ ደግሞ ኑ በቤታችን ሃሳብ እንቋደስ ። ተካፍሎ መብላት እና ተካፍሎ ማንበብ ባህላችን ነውና እንላለን ።

📚 ለዳሰሳ የተመረጠው ግጥም: "የእርሷ ስም " ከተሰኘው የግጥም መድብል  "ሽማግሌ ላኪልኝ" የሚለውን ስራ

✍️ ደራሲ :-
የሀዋሳ ዩንቨርስቲ ተማሪ እና የRvc ቤተሰብ ከነበረው የህግ ባለሙያ ዳዊት ጥዑማይ

ከ 2:30 ጀምሮ
📍በ Google Meet

📌 ስራውን በ book review የቴሌግራም ግሩፕ ላይ ያገኙታል ።

ሰዓት ማክበር የምክንያታዊ ወጣት መገለጫ ነው።

@rvcclub
@rvcbookreview
👍41
በዚህ ሳምንት በምክንያታዊ ባለራዐዮች ስብስብ :-

ማንበብ ለምን ?

1.የምናነበው ለምን አላማ ብለን ነው? እውን ወደ አላማችንስ እየወሰደን ነው ብላችሁ ታስባላችሁ?

2.ስናነብ መረጃውን ለመያዝ ብቻ  ወይስ ችግር ለመቅረፍ ተጠቅመንበት እናውቃለን ?

3. እስከመቼ ነው ማንበብ ያለብን ብላችሁ ታስባላችሁ ? (እስክንሞት ከሚለው ውጪ በምክንያት )

4. የንባብ ቅደም ተከተል ካለው ብናነሳው። ለምሳሌ ከልብወለድ-ፍልስፍና የቱ ይቅደም

5, ለእናንተ የምንዜም ምርጥ 3 መፅሃፍት የትኞቹ ናቸው ?
( ከሃገር ውስጥም ከውጪም )

በጉጉት እንጠብቃችኋለን

📍🗺 አድራሻችን RVC Telegram channel ።

🕰  ከምሽቱ 2:30 ጀምሮ

  የቴሌግራም ቻናላችንን ላልተቀላቀላቹ ከታች ባለው ሊንክ መቀላቀል እንዳይረሳ።

📌 ሰዓት ማክበር የምክንያታዊ ባለራዕይ ወጣት መገለጫ ነው።


#ኑ_የቆምንበትን_መሠረት_እንፈትሽ
#የተሻለ_ትውልድ_ለተሻለች_ኢትዮጵያ
#የምክንያታዊ_ባለራዕዮች_ስብስብ
@RvcClub
@RvcClub
👍41
BOOK AWARD 🏆
መልዕክት ከቤተሰባችን

"ወዳጆቼ ላሳያችሁኝ ድጋፍና ማበረታታት በጣም አመሰግናለሁ 🙏 ድምፅ መስጠት ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም በማጋራት ከጎኔ ለሆናችሁ በሙሉ እ/ር ያክብርልኝ🙏🙏

ክቡር ልጆች መጽሐፌ እንዴት እንዴት ብላ የመጨረሻ ዙር እንደደረሰች አግራሞት ጭራብኛለች። አሁን የእናንተን ድጋፍ ትፈልጋለች።

የመጨረሻ ዙር ደርሶማ ....የለም ወደኃላ!!

እናንተ እያላችሁ እንደምታኮሩኝ አምናለሁ! አልያ ተኗኗርናታ 😂😂😂

ድምፅ ለመስጠት 30 ሰከንድ ብቻ፤ ሊንኩን ተጫኑ ፣ 5 ቁጥር ላይ ክቡር ልጆች ይምረጡ Submit የሚለውን መጫን አበቃ።
👇
https://docs.google.com/forms/d/1YDUXGpLnx-mlnK1ipGyhkQeiEtjx-Al10rYepswpdjI/

አመሰግናለሁ🙏
ብርሃኑበላቸው አሰፋ
እነሆ ሀሙስ

የመረጥነውን መፅሃፍ እስከምንጨርስ እስኪ ደግሞ በግጥም ብቅ እንበል ብለን ተከስተናል።

📚 አብረን ዝም እንበል

✍️ ክብር ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን

📌 ስራውን በ book review የቴሌግራም ግሩፕ ላይ በ pdf ያገኙታል ።

📆 ነገ ሐሙስ 3 /11/ 2017 ግጥሙን በጋራ የምንዳስስ ይሆናል ።


መልካም የንባብ ጊዜ

@rvcclub
@rvcbookreview
አብረን ዝም እንበል

ከሰው መንጋ እንገንጠል
ለአንድ አፍታ እንኳን እንገለል
በእፎይታ ጥላ እንጠለል
ዝም ብለን አብረን ዝም እንበል፡፡
ምነው አዋሽ ማዶ ቆቃ፣ እሸለቆው ግርጌ ሽሽተን የቆቃን ሰቆቃ ሰምተን
ሲቃውን ሲሰብቀው አይተን ሰቀቀኑን ተወያይተን የምሽት ጀንበር ቢውጠን ?
ውሀ እንደዱታ ሲተምም፣ በድን ሸለቆ ሲናገር
በሰማይ ፈረስ ተጭኖ፣ ከአጽናፍ አጽናፍ ሲንደረደር
ሲያጉተመትም ሲያስገመግም፣ በዓይነ - ሕሊና ለመመስከር
ሳንጨነቅ ሳንገደር
ለማንም ምንም ሳናዋይ፣ ሳንናገር ሳንጋገር
ከዓይንሽ ከልብሽ ከልቤ፣ አዋሽ ማዶ አብረን እንብረር ..
...........................................

ብቻ ዳግመኛ ሞት ሳንሞት፣ አዲስ ቀን ሳይጨልምብን
ድፍን ደመና ሳይቋጥር፣ ክረምት ውርጅት ሳይወርድብን
ኮከባችንን ሳንጠራ፣ ሳንቆጥርባት ሳትቆጥርብን
ሞራችንን ሳናስነብብ፣ ሳናሳያት ሳታይብን
ጨረቃን መስከሪ ሳንል፣ ሳናውቅባት ሳታውቅብን አዋሽ ማዶ ቆቃ በርረን፣ ባክሽ ጀምበር ትጥለቅብን..

ጸጋዬ ገብረ መድኅን (ባለ ቅኔ ሎሬት) ቆቃ 1961 ዓ.ም
በዚህ ሳምንት በምክንያታዊ ባለራዕዮች ስብስብ :-

1. 'Ego' ማለት በእናንተ እይታ ምን ማለት ነው?

2.'Ego' ህይወታችን ላይ ምን አይነት ተጽዕኖ ይፈጥራል ፤ እናንተስ በህይወታቹ በ Ego ምክንያት ያጣችሁት አልያም ያገኛችሁት ነገር ምንድነው?

3. በራስ ማበልፀግ (personal growth)፣ በጓደኝነት፣ በስራ ቦታ፣ እንዲሁም በፍቅር ግንኙነት መሃል 'Ego' ቢኖር ምን አይነት ተጽዕኖ ይፈጥራል?

4. ውሳኔ ለመወሰን 'Ego'ን ማካተት አለብን? ለምን?

በጉጉት እንጠብቃችኋለን

📍🗺 አድራሻችን RVC Telegram channel ።

🕰  ከምሽቱ 2:30 ጀምሮ

  የቴሌግራም ቻናላችንን ላልተቀላቀላቹ ከታች ባለው ሊንክ መቀላቀል እንዳይረሳ።

📌 ሰዓት ማክበር የምክንያታዊ ባለራዕይ ወጣት መገለጫ ነው።


#ኑ_የቆምንበትን_መሠረት_እንፈትሽ
#የተሻለ_ትውልድ_ለተሻለች_ኢትዮጵያ
#የምክንያታዊ_ባለራዕዮች_ስብስብ
@RvcClub
@RvcClub
3
🚀 Online Training Alert!

Topic: Using Social Media Effectively for Professional Development

📍 Venue: Virtual - https://www.tgoop.com/HUMCSC
🕒 Time: 3:00 LT
📆 Date: Sunday, July 13, 2025
🎙️ Trainer: Yihun Abebe

Join us as we explore how to:
Build a strong professional presence online
Network strategically using social platforms
Leverage content to attract opportunities

🎯 What You’ll Gain:

✔️ Practical tools for branding yourself
✔️ Strategies to grow your career network
✔️ Insights to stand out in your field

Don't miss this empowering session! 💻

#ProfessionalDevelopment #SocialMediaForGrowth
#MutualCareAndSpport
2025/07/13 02:54:35
Back to Top
HTML Embed Code: