Warning: mkdir(): No space left on device in /var/www/tgoop/post.php on line 37

Warning: file_put_contents(aCache/aDaily/post/SPMMC/--): Failed to open stream: No such file or directory in /var/www/tgoop/post.php on line 50
St.Paul's Hospital Millennium Medical College@SPMMC P.2846
SPMMC Telegram 2846
የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ፣ የአእምሮ ጤናና መረዳዳት

የመሬት መንቀጥቀጥ መሰረተ ልማቶችን፣ ሞቶችን፣ አካላዊ ጉዳቶችን ከማስከተሉ ባለፈ የአእምሮ ጤናን ክፉኛ ሊጎዳዉ ይችላል፡፡ ተጎጂዎች የሰዉ ህይወት ከመቀጠፉ፣ ከማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀዉስ የተነሳ ለከፍተኛ ፍርሃትና ጫና ሊጋለጡ ይችላሉ፡፡ በተቃራኒዉ ደግም ሰዎች ተባብረዉ ከቆሙ አደጋ የተሻለ የአእምሮ ጤናና ጫናን የመቋቋም ብቃት ላይ ሊያደርሳቸዉም ይችላል፡፡
ሰዎች የመሬት መንቀጥቀጥና መሰል ድንገተኛ አደጋዎች ሲያጋጥሟቸዉ ለበርካታ የአእምሮ ህመሞች የመጋለጥ እድላቸዉ ይጨምራል፡፡ ጉዳቱ ቀጥታ በራሳቸዉ ላይ ደርሶ፣ በሌሎች ላይ ጉዳት ሲደርስ ሲመለከቱ እና አደጋዉ በደረሰበት አቅራቢያ ባይገኙ እንኳ በቅርብ ቤተሰቦቻቸዉ ወይም በጓደኞቻቸዉ ላይ አደጋ እንደደረሰ በመስማት ብቻ ለድህረ አደጋ ሰቀቀን ሊጋለጡ ይችላሉ፡፡ ከአደጋዉ የተነሳ ከቤት ንብረታቸዉ ሲፈናቀሉ፣ በአደጋዉ ንብረቶቻቸዉ ሲወድሙባቸዉ፣ ስራቸዉን ሲያጡ፣ ማህበራዊ ትስስሮች(እድር፣ማህበር፣የእምነት ስፍራ…ወዘተ) ሲበጣጠሱባቸዉ ለከፍተኛ ድብርት፣ ለጭንቀት ህመም፣ ለሱስ ህመም፣ ራስን ለማጥፋት አደጋ ተጋላጭ ይሆናሉ፡፡ በተፈጥሮ አደጋ ጊዜ የሆስፒታል ድንገተኛ ክፍል ምልልሶች ይጨምራሉ፤ ሰዎች በአጠቃላይ ደስታን በማጣትና በዘርፋ ብዙ የጤና መቃወሶች ዉስጥ ያልፋሉ፡፡
በሌላዉ ጎን ደግሞ የተፈጥሮ አደጋዎች ሰዎች ህይወታቸዉን ለማቆየት በጋራ የመቆም ዉስጣዊ ግፊታቸዉን በመቀስቀስ በትብብር እንዲቆሙ ሊያደርጓቸዉም ይችላሉ፡፡ ሰዎች ተባብረዉ ሲቆሙና ሲረዳዱ የአእምሮ ጤናቸዉ ይሻሻላል፣ ማህበራዊ ትስስራቸዉ ይጠናከራል፣ ጫናን የመቋቋም አቅማቸዉ ይጎለብታል፡፡ እንደማህበረሰብ በቀደመዉ ዘመን የገጠሟቸዉን ጣላቶች በጋራ ተባብረዉ እንደመከቷቸዉ ሁሉ በዚህ ዘመንም የሚገጥሟቸዉን አደጋዎች በመረዳት፣ በመረዳዳት፣ በመተሳሰብና በርህራሄ በመተያየት ሊቋቋሟቸዉ ይችላሉ፡፡ ከአደጋ ጋር የተያያዙ የአእምሮ ህመም ተጋላጭነቶችን ከሚቀንሱ ነገሮች ዋነኛዉ በጉዳቱ ዉስጥ ላለፉ ወይም እያለፉ ላሉ ሰዎች የሚደረግ ማህበራዊ ድጋፍ ነዉ፡፡ በዚህ ረገድ ብርቱና መልካም ባህል አለን፤ ባህላችን ሰዉ ለሰዉ መድኃኒቱ፤ ካንድ ብርቱ ሁለት መድኃኒቱ፤ ሀምሳ ሎሚ ለሀምሳ ሰዉ ጌጡ ለአንድ ሰዉ ሸክሙ እንደሆነ አስቀምጦልናል፡፡ እንደሰዉ ዘር መቀጠላችን የሚወሰነዉ በመተባበራችን ነዉና በዚህ ክፉ ጊዜ ልንረዳዳና ተያያዘን ልንቆም ይገባናል፡፡ አደጋን ታሳቢ ካደረገ እንክንብካቤ መመሪያዎች በመነሳት ባለፍንባቸዉም ሆነ በምናልፍባቸዉ ሰቀቀኖች የሚከተሉትን ነገሮች ብንተገብርና ብንለማመዳቸዉ በብዙ እናተርፋለን፡፡
ደህንነት 
ሰዎች ዉጤታማ የሚሆኑትና በተሟላ አእምሯዊ ብቃት ላይ የሚሆኑት ደህንነት ሲሰማቸዉ ነዉ፡፡ ደህንነታቸዉ ሲናጋ በፍርሃትና ራስን በማዳን ሩጫ ይጠመዱና የሚጠቅማቸዉን ዉሳኔ አመዛዝኖ መወሰን ያቅታቸዋል፡፡ የሚመለከታቸዉ ሁሉ ከሁሉ በማስቀደም ለሰዉ ልጆች አካላዊ ደህንነት፣ስነልቦናዊ ደህንነት፣የስሜት ደህንነት፣ማህበራዊ ደህንነትና ሞራላዊ ደህንነት መጠንቀቅ ይኖርባቸዋል፡፡ በማንኛዉም ሁኔታ ዉስጥ ሲኮንና ሲታለፍ ለራስና ለሌሎች ደህንነት ንቁ መሆን የቅድሚያ ቅድሚያ ሊሆን ይገባዋል!
ታእማኒነትና ግልፀኝነት
አደጋዎች ሲኖሩ ብዙ ጥድፊያና ሩጫ መኖሩ የማይካድ ቢሆን የሚከወኑ ተግባራት ሰዎች እምነታቸዉን በሚጥሉበት መንገድ፣ ባልተሸፋፈና ግልፅ በሆነ መልክ ሊደረጉ ይገባቸዋል፡፡ እየሆኑ ስላሉ ጉዳዮች ከሚመለከታቸዉ ተቋማት ወቅታዊ መረጃ ፍሰቱን ጠብቆ መሄድ ይኖርበታል፡፡ እዉነተኛ መታመን እመኑን ከሚል የቃላት ጩኸት ሳይሆን ከተግባር ጥራት ብቻ የሚቀዳ መሆኑን እናስተዉል!
እርስ በርስ  መደጋገፍ፣ መተባበር 
የጋራ ታሪክ፣የጋራ ልምድና የጋራ ፈተና ያላቸዉ ሰዎች ህልዉናቸዉ የሚዘልቀዉ በጋራ መተባበርና መደጋገፍ ሲችሉ ነዉ፡፡ በሰዉ ልጅ ኑረት የአንዱ ህልዉና በሌላኛዉ ህልዉና ላይ የተመሰረተ ነዉና ከመገፋፋትና ከመጠፋፋት ይልቅ መደጋገፍን፣ መተባበርን፣ አብሮ መሰራትንና መገነባባትን የየዕለት ኑረታችን ማድረግ ግዴታችን ነዉ! ሌላኛዉ ወገናችን ሲሰቃይ ቆመን ካየን ነገ እኛ ስንሰቃይ የሚደርስልን አይኖርም፡፡ እንደጋገፍ! እንረዳዳ! እንተባበር! የተጎዱ ወገኖቻችንን ለማከም ሐኪም መሆን አይጠበቅብንም፤ ለሰዉ መድኃኒቱ ሰዉ ነዉና!
ትህትናና አለመፍረድ
ሰዉ እንደመሆናችን ባልገባንና ባልተረዳነዉ ጉዳይ በሌሎች ላይ ጣት ለመቀሰር ልንጣደፍ እንችላለን፡፡ ባህላቸዉን፣ ሀይማኖታቸዉን፣ ታሪካቸዉንና ልዩ ልዩ ልዩነቶቻችንን በማክበር በስቃይ ዉስጥ ከሚያልፉ ሰዎች ልምድ ለመማር መፍቀድና መዘጋጀት እንጂ ከኛ የተለየ ነገር ስለገጠማቸዉ ልንፈርድባቸዉ አይገባንም፡፡ ሰዎች በብዙ ስቃይ ዉስጥ የሚያልፉት ክፉ ስለሆኑ ወይም ፈጣሪ ስለፈረደባቸዉ ሳይሆን ስቃይ የህይወት አንዱ መልክ እንደሆነ እንረዳ፡፡ ከሰዉ ሰራሽ (መደፈር፣ፆታዊ ጥቃት፣ጦርነት፣ጠለፋ፣የእሳት አደጋ፣ግድያ፣የመኪና አደጋ…ወዘተ) ሆነ ከተፈጥሮ አደጋዎች (ጎርፍ፣የመሬት መንቀጥቀጥ፣ የመሬት መንሸራተት፣የመብረቅ አደጋ፣ርሃብና ድርቅ…ወዘተ) ጫና የተነሳ የሚረበሹ ሰዎችን ስናገኝ ወደ ባለሙያ እንላካቸዉ እንጂ አንፍረድባቸዉ! ማንም ከአደጋና ስቃይ የራቀ አይደለም!

ዶ/ርእሸቱ ጡሚሶ
የሥነ አእምሮ ሐኪም

tgoop.com/SPMMC/2846
Create:
Last Update:

BY St.Paul's Hospital Millennium Medical College

Share with your friend now:
tgoop.com/SPMMC/2846

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

According to media reports, the privacy watchdog was considering “blacklisting” some online platforms that have repeatedly posted doxxing information, with sources saying most messages were shared on Telegram. As of Thursday, the SUCK Channel had 34,146 subscribers, with only one message dated August 28, 2020. It was an announcement stating that police had removed all posts on the channel because its content “contravenes the laws of Hong Kong.” To upload a logo, click the Menu icon and select “Manage Channel.” In a new window, hit the Camera icon. Find your optimal posting schedule and stick to it. The peak posting times include 8 am, 6 pm, and 8 pm on social media. Try to publish serious stuff in the morning and leave less demanding content later in the day. With the administration mulling over limiting access to doxxing groups, a prominent Telegram doxxing group apparently went on a "revenge spree."
from us

Telegram St.Paul's Hospital Millennium Medical College
FROM American