tgoop.com »
United States »
የሀዋሳ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም መራሔ ድኀነት ሰንበት ት/ት ቤት መንፈሳዊ ቴሌግራም ገጽ »
Telegram web »
Post 13497
የቅድስት ልደታ ለማርያም ሕንፃ ቤተክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የቡራኬ ሥነ ሥርዓት ተከናወነ።
የካቲት 8/2017 ዓ.ም ሀዋሳ-ኢትዮጵያ
በሀገረ ስብከታችን የሚገኘው የዶሬ ባፈና ቅድስት ልደታ ለማርያም ሕንፃ ቤተክርስቲያን በአቶ ዘነበ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እና አስተባባሪነት ግንባታው በአጭር ጊዜ ተጠናቆ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የሲዳማ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በተገኙበት ዛሬ ሥርዓተ ቡራኬው ተከናውኖ ጽላቱ በታላቅ ድምቀት ወደ ቤተ መቅደሱ ገባ።
ዶሬ ከሀዋሳ ወጣ ብሎ የሚገኝ አነስተኛ ከተማ ሲሆን በዚህ ከተማ የሚኖሩ ክርስቲያኖች የማምለኪያ ስፍራ ስላልነበራቸው ለ2 ዓመታት ያህል በኪራይ ቤት እየተሰባሰቡ በሲዳማ ሀገረ ስብከት መልካም ፈቃድ በሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ካሣሁን ወንዴ የሀዋሳ ወረዳ ቤተ ክህነት ዋና ጸሐፊ ሲማሩ የቆዩ ቢሆንም ቤተ ክርስቲያን ለማግኘት ላለፉት 17 ዓመታት ብዙ ዋጋ ከፍለዋል።
በፍቃደ እግዚአብሔር ህንጻ ቤተ ክርስቲያን ታንጾ ሊመረቅ ችሏል.
በዕለቱም ከብፁነታቸው በተጨማሪ የሲዳማ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መጋቤ ጥበባት ቀሲስ ሞላልኝ መርጊያ፣ሊቀ ብርሃናት ቀሲስ ተስፋዬ ስዩም የሀገረ ስብከቱ ሂሳብና በጀት ክፍል ኃላፊ፣በኩረ ትጉሃን ቀሲስ አማረ ግርማ የሀገረ ስብከቱ የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ ክፍል ኃላፊ፣ላዕከ ወንጌል ደግፌ ባንቡራ የሀዋሳ ከተማና ዙሪያ ወረዳ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቃውንተ ቤተ ክርስትያን ፣የሀዋሳ ከተማ እና የአካባቢው ምዕመናን ተገኝተዋል።
በመጨረሻም ብፁዕ አቡነ ዮሴፍም ለአካባቢው ክርስቲያኖች የእንኳን ደስ አላችሁ አባታዊ መልእክት አስተላለፈው ቤተክርስቲያኑን የሠሩ ያሰሩ ኮሚቴዎችን አመስግነው ቃለ ምዕዳን ቡራኬ ሰተው የመርሐ ግብሩ ፍጻሜ ሆኗል.
ነገ ቅዳሴ ቤቱ ይከበራል
@SaintGebrielSundaySchool

tgoop.com/SaintGebrielSundaySchool/13497
Create:
Last Update:

BY የሀዋሳ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም መራሔ ድኀነት ሰንበት ት/ት ቤት መንፈሳዊ ቴሌግራም ገጽ

Share with your friend now: