Forwarded from ስኬት ለ ማትሪክ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Chapter 3—Kinematics Section 1
የምትከተለውና የምትተወው
“አንድን ነገር መቼ ትተህ መሄድ እንዳለብህ ማወቅ ጥበብ ነው፡፡ ያንን እርምጃ መውሰድ ደግሞ ቆራጥነት ነው፡፡ በጨዋነትና አንገትህን ሳትደፋ መሄድ ደግሞ
ማዕረግና ክብር ነው”
የሰው ጥበቡና ክብሩ የሚለካው በሚከታተላቸው ታላላቅ ነገሮች ብቻ ሳይሆን ትቶ ለመሄድ በወሰናቸው ነገሮችም ጭምር ነው፡፡ አንድ ሰው ወደፊት የሚደርስበት ከፍታ ከወዲሁ የሚታወቀው ምንም እንኳን መስዋእትነት ቢያስከፍለውም፣ ከአጠቃላይ የሕይወቱ መርህና የልህቀት ደረጃ ጋር ከማይመጥን ነገር ለመለየት ባለው ቆራጥነት ነው፡፡ አንድን የተሻለ ነገር በእጃችን ለመጨበጥ በመጀመሪያ የያዝነውን ነገር የመልቀቅ ጥያቄ ሊቀርብልን እንደሚችል መዘንጋት የለብንም፡፡
ለመክፈል ፈቃደኛ የሆንክለት መስዋእትነት ነገ የምትደርስበትንና በእጅህ የሚገባውን ነገር ጥራት ይወስነዋል፡፡ አንዳንድ ሰዎች ተራውንና ላላቸው ታላቅ የሕይወት ግብ የማይመጥነውን ላለመልቀቅ ሲሉ ከብዙ መልካም ነገር ይጎድላሉ፡፡ ለጊዜያዊው ሲሉ ዘላቂውን ይሰዋሉ፤ ለተራው ሲሉ የከበረውን ይጥላሉ፤ ላይ ላዩን ብቻ ለተብረቀረቀው ነገር ሲሉ ጥልቅና የውስጥ ውበት የተላበሰውን እውነተኛውን ችላ ይላሉ፡፡ እንደዚህ አይነት ሰዎች አንድን የላቀ ነገር ለማግኘት አናሳውን መስዋእት ማድረግ እንዳለባቸው የዘነጉ ጥበብ-የለሽ ሰዎች ናቸው፡፡
አገራችንን የሞሉትን የችግር ምንጮች ካየሃቸው ይህ አመለካከት የተጠናወታቸው ሰዎች ናቸው፡፡ የሚያስቡት፣ የሚናገሩትና የሚከተሉት ነገር ሁሉ ተራ የሆነባቸው ሰዎች በሕብረተሰቡ መካከል ለሚፈጠሩ ለአብዛኛዎቹ ቀውሶች መንስኤ ናቸው፡፡ እንደዚህ አይነት ሰዎች ለብዙሃኑ ጥቅም ሲሉ የራሳቸውን አጀንዳ መጣል የሚባለውን ሃሳብ በፍጹም የሚገነዘብ አእምሮ የላቸውም፡፡ ለአጠቃላይ ሃገራዊ ራእይ ሲሉ ጊዜያዊ ጥቅምንና መብተኝነት መልቀቅ የሚባለው ሃሳብ ፈጽሞ ሊታያቸው አይችልም፡፡
አንተ በምትወስደው እርምጃ ምክንያት ያለህበት ሕብረተሰብ ወደተሻለ ደረጃ እንደሚደርስ ብታውቅ ያንን ነገር ለማድረግ ዝግጁ ነህ? አንተ ለመተው ፈቃደኛ በሆንከው ነገር ምክንያት በሕብረተሰቡ መካከል ሰላም እንደሚሰፍን ብትገነዘብ ያንን ነገር ለመተው ምን ያህል ፈቃደኛ ነህ?
ሃሳቡን ስንደመድመው፣ የሕይወታችን ጥራት የሚለካው በምንተገብራቸው ነገሮች ብቻ ሳይሆን አንዳንዴም ለመተው በምንወስናቸውም ነገሮች እንደሆነም ማስታወስ ጥበብ ነው፡፡ የጥበባችን ልክ የሚመዘነው እከተለዋለሁ በምንለው ነገር ብቻ ሳይሆን እተወዋለሁ በምንለውም ነገር ጭምር ስለሆነ ማለት ነው፡፡ አስተዋይነታችን የሚለካው መያዝ-መጨበጥ አለብኝ በምንለው ነገር ብቻ ሳይሆን አንዳንድ ጊዜም ለመልቀቅ ፈቃደኛ በሆንነው ነገር እንደሆነ ለማስታወስ ይፈቀድልኝ፡፡ ብርታታችን የሚታየው ለመብቴ እቆማለሁ በሚለው ጠንካራ አቋማችን ብቻ ሳይሆን ለአጠቃላይ ሰላም ሲባል አንዳንዴ መብቴን እተዋለሁ በሚለውም አመለካከታችን እንደሆነ ይሰመርበት፡፡
@sewmehoneth

የሰዉ ሆዱ የወፍ ወንዱ አይታወቅም!!
ነገር ግን የሰዉን ማንነት በሚያስጨንቀዉ ጉዳይ መገመት ይቻላል!! አንዳንዱ ለመወደድ ሲሯሯጥ ተደብሮ ይዉላል.. አንዳንዱ የተወደደ መስሎት እዚያም እዚህም ሲሯሯጥ ይዉላል... አንዳንዱ በመልካምነቱና በደግነቱ ከሰዉ ልጆች ሁሉ መወደድን እየበላና እየጠጣ ይዉላል... አንዳንዱ ራሱን ለመለወጥና አጠገቡ ያሉትን በመርዳት ቁም ነገር ሲሰራ ይዉላል... አንዳንዱ ደግሞ በመንደር ወሬ ሲሻኮት ይዉላል... አንዳንዱ ከዛሬ ይልቅ ነገን በተስፋና በትጋት ሲጠብቅ ይዉላል.. አንዳንዱ ደግሞ አለ.... የሚያደርገዉ ጠፍቶተት ግራ ገብቶት በቀን ሲያልም የምዉል.. ብቻ ሁሉም ይዉላል 😂😁
ሁላችሁም ሰላም ዋሉልኝ!! 🙏

ስብከት በቆንጆ ሴት አፍ!
«ዘውድአለም ታደሠ»
በዚች ምድር ላይ ስኖር ልለምደው ያልቻልኩት ነገር ምንድነው? ዝናብ እየዘነበ በጠኋት መነሳት! ውይ! ምርር እኮ ነው ሚለኝ እውነት። ሲዘንብ ከአልጋ መውረድ ከስልጣን የመውረድ ያክል ይከብደኛል። ህይወት ለጥቂት ሰአት ትደብረኛለች!
ዛሬም እንደፈረደብኝ በጠኋት ተነስቼ ካፊያውን ተቋቁሜ ወደስራ አዘግማለሁ። ብርዱ አክቲቪስት ያሳቅፋል! :) ወደቤቴ ተመልሼ የመጣው ይምጣ ጥቅልል ብዬ ልተኛንዴ? የሚል ሃሳብ እየታገለኝ ስጓዝ ጠላታችሁ ክው ይበል የክላክስ ድምፅ ክው አረገኝ! (ይሄንማ ባዲስ መስመር ነው ምነግራችሁ)
ዞር ስል አጠገቤ እንደመስታወት የሚያበራ ጥቁር መኪና ቆሟል! መቼስ እነዚህ አሽከርካሪዎች እግረኛውን እንደጂፒኤስ ነው ሚጠቀሙበት መንገድ ሊጠይቀኝ ይሆናል ብዬ ጠጋ ስል የመኪናው መስታወት በቀስታ ወርዶ አንዲት ውብ ሴት ከውስጥ ብቅ አለች!! (ልክ መስታወቱ ሲከፈት መኪና ውስጥ የሞላው ውበት ወደውጪ የፈሰሰ ነው የመሰለኝ)
እንደድሮ ደራሲ ውበቷን እየተነተንኩ አላዝጋችሁም ባጭሩ ቁንጅና ብትወዳደር ብቻዋን ከአንድ እስከአስር ምትወጣ አይነት ሴት አርጋችሁ አስቧት! (ባለትዳሮች አታስቧት ይቅርባችሁ ሃሃ)
እኔ ደሞ ጥሎብኝ ያው የሴት ልጅ ውበት አድናቂ ነኝ ታውቃላችሁ። ቆንጆ ሴት ሳይ ለጥቂት ሰከንድ ሃውልት የሚያረገኝ ነገር አለ። ሴት ልጅ የኔ ሆነችም አልሆነች ቆንጆ ስትሆን ደስ ይለኛል በቃ! እዚህ ጋር ዋናው የውስጥ ውበት ነው ምናምን የሚል ምክር አልቀበልም። ወንድ ልጅ የሆነ ነገሯን ወዶ ካልቀረባት ውስጧን በምን አባቱ ያውቀዋል? ስንታይ የኤክስሬ ማሽን እንመስላለን እንዴ? ምን ትላለች እቺ!
«ወዬ ምን ልታዘዝ?» አልኳት በትህትና። እስቲ ወደፊት ሄድ ብለህ አስፓልቱ ላይ ተኛና ልግጭህ ብትለኝ ሁሉ ምስማማ ይመስለኛል :)
«አይ መንገዳችን አንድ ከሆነ ልሸኝህ» አለችኝ። ገና ልሸኝህ የሚለው ቃል ከአፏ ከመውጣቱ ጋቢና ገብቼ ተቀምጫለሁ :)
መኪና ውስጥ ለስለስ ያለ የሊሊ መዝሙር ይሰማል ... ውስጡ ገላዋ ላይ በበተነችው ማራኪ ሽቶ ታውዷል። መሪ ምታሽከረክርባቸውን ቀያይ ጥፍር ቀለም የተቀቡ ጣቶቿን አየኋቸው! ማሽ አላህ አለ አብዱ! እቺ ልጅ በሽንትቤት መኪና ሁሉ ሊፍት ብትሰጠኝ ደስ እያለኝ ነው ምሳፈረው :)
ከመዝሙሩ ጋር በለሆሳስ ትዘምራለች
«ልክ እንዳበደ ሰው
አይምሮውን እንዳጣ
አመሰግናለሁ ወዳንተ ስመጣ
የሌለኝን ሳይሆን ያለኝን እያየሁ
ተመስገን ተመስገን ተመስገን እላለሁ»
ትላለች ሊሊ! በአንድ ግዜ ንጭንጭና ድብርቴ ጠፋ! ገንዘብ ደስታን አይገዛም ምናምን ያለው ሰውዬ ማን ነበር? ብቻ ማንም ሆነ ማን የመሃል ጣቴን ሰጥቼዋለሁ :) ብራዘር የድህነት አስከፊነት የሚገባህ አንተ አጥንትን በሚሰረስር ብርድ ካፊያ እየዘነበብህ እንደገብረ ጉንዳን ታክሲ ጥበቃ ተሰልፈህ መስታወት ከፍተው በተወለወለ መኪና አስፓልቱ ላይ ፈልሰስ የሚሉ ሹፌሮችን ስታይ ነው! ያኔ አያቶቻችን ገንዘብ ካለ በሰማይ መንገድ አለ ያሉት ከመሬት ተነስተው እንዳልሆነ ይገባሃል!
መዝሙሩን በግማሽ ልቤ እየሰማሁ እሷ ላይ ተመስጫለሁ። እሷ መኪናዋን በእርጋታ እያሽከረከረች ትዘምራለች። ፊቷ ላይ ቢከፋፈል ለአፍሪካ የሚበቃ ሰላም አለ! በቃ ሰላም አስከባሪ ፊት ታውቃላችሁ? ስታዩት የተዋከበ ነፍሳችሁን የሚያረጋጋ ፀጥታ የሰፈነበት ፊት!! ትንሽ እንደተጓዝን ድንገት
«ጌታ ይወድሃል» አለችኝ!
«እኔም እወድሻለሁ ... ውይ የኔ ነገር... እኔም እወደዋለሁ ማለቴ» አልኩ ተደናብሬ
ከዛ ቀለል አርጋ ትሰብከኝ ጀመር። እኔም አንዴ ስብከቱን አንዴ የከንፈሮቿን እንቅስቃሴ እያደነቅሁ ዝም ብዬ ተከታተልኳት (ትምርቴን እንዲህ ብከታተል ይሄኔ ሰው ሆኜ ነበር :) )
እውነት ለመናገር ስብከት እንዲህ ገብቶኝ አያውቅም :D ከዚህ በፊት ብዙ ፕሮቴስታንቶች ሰብከውኝ ያውቃሉ። ግን እንዲህ ሮማንቲክ በሆነ መንገድ ስላልሰበኩኝ ነው መሰለኝ አስፈራሩኝ እንጂ አልማረኩኝም። አንዳንዶቹማ በአንድ እጃቸው መፅሃፍ ቅዱሳቸውን ይዘው የአንድ እጅ ሌባ ጣታቸውን ወደኔ እየጠቆሙ ዛቻ የሚመስል ስብከት ነው የሰበኩኝ። አለ አይደል
«ወየውልህ .... ብትድን ይሻልሃል .... ሲኦል ትገባታለህ ... እናትህ አፈር ትብላ ንስሃ ግባ» አይነት ስብከት! :D
እቺ ግን በቃ ሲኦል የለ ምን የለ ስለክርስቶስ ፍቅር ነው ምትሰብከኝ። ነፍሱን ላንተ ብሎ ሰጥቶሃል። ላንተ ያለው ፍቅር ጥልቅ ነው። ምናምን ስትለኝ ያው ውበቷም ተጨምሮበት እምባ ተናነቀኝ :D አረ አሁኑኑ ጌታን ተቀበል ተቀበል ሁሉ ብሎኛል። ከዚች ሴት ጋር አይደለም ገነት ሲኦል ራሱ መግባት ያዋጣል። አልኩ በልቤ :)
መጨረሻ ላይ ፈቃደኛ ከሆንክ ቸርች ልጋብዝህ? ስትለኝ አላቅማማሁም። እንኳን ቸርች ቀለል ያለ ጦርነት ላይ ብትጋብዘኝ ምንሽር ተሸክሜ የምሄድ ይመስለኛል። ሃሌሉያ!

🙏 ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አደራችሁ🙏
✍ እሰቲ ሰው ፈልጉ✍
📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖
አንደበተ ርቱእ - ቋንቋው ቀጥተኛ፣
ለሌላው አሳቢ - ያልሆነ ምቀኛ፤
፡
ከሸር ካሉባልታ - ከክፋት የራቀ፣
ጉራና ትምክህትን - በፍፁም የናቀ፣
አውቃለሁኝ ብሎ - ያልተመፃደቀ፤
፡
ሁሉንም አክባሪ - በሰው የማይኮራ፣
ለፍርድ የማይቸኩል - ቃሉ የተገራ፤
፡
ፍቅር ቁምነገሩ - ከወረት የፀዳ፣
በመከራ ሰዓት - ወዳጁን ያልከዳ፤
፡
ፈጣሪን አመስጋኝ - የሚኖር በወጉ፤
እርሱ ነው ሰው ማለት - እስቲ ሰው ፈልጉ፡፡
🙌መልካም ቀን ቸር ያውለን🙌
@sewmehoneth
✍ እሰቲ ሰው ፈልጉ✍
📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖
አንደበተ ርቱእ - ቋንቋው ቀጥተኛ፣
ለሌላው አሳቢ - ያልሆነ ምቀኛ፤
፡
ከሸር ካሉባልታ - ከክፋት የራቀ፣
ጉራና ትምክህትን - በፍፁም የናቀ፣
አውቃለሁኝ ብሎ - ያልተመፃደቀ፤
፡
ሁሉንም አክባሪ - በሰው የማይኮራ፣
ለፍርድ የማይቸኩል - ቃሉ የተገራ፤
፡
ፍቅር ቁምነገሩ - ከወረት የፀዳ፣
በመከራ ሰዓት - ወዳጁን ያልከዳ፤
፡
ፈጣሪን አመስጋኝ - የሚኖር በወጉ፤
እርሱ ነው ሰው ማለት - እስቲ ሰው ፈልጉ፡፡
🙌መልካም ቀን ቸር ያውለን🙌
@sewmehoneth
🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አደራችሁ🙏
የሰው ዋጋው ስንት ነው?
ዛሬ ጠዋታ ወደስራ ሳመራ በአይኔ ያየውትን አሳዛኝ ክስተት ላካፍላችሁ፡፡ ወቅቱ ክረምት በመሆኑ ጠዋትና ማታ ዝናብ መመታት የተለመደ ነው፡፡ ጠዋት እንደወትሮዬ ከትራንስፖርት እንደወረድኩ ወደ መስሪያ ቤቴ የምታደርሰኝን የ5 ደቂቃ የእግር መንገድ በፍጥነት መራመድን ተያይዣለው፡፡
ትንሽ እንደተጓዝኩ ግን ቃሊቲ ውሃ ልማት አልፍ ብሎ ኮርኪ ፋብሪካ ፊት ለፊት ብዙ ትራፊክ ፖሊሶች ብዙ ፖሊሶች በድንጋጤና በወከባ ቆመው ተመለከትኩ፡፡ ብዙ ትራፊኮችን በመመልከቴ እና በቦታው ብዙ የቆሙ ከባድ ተሽከርካሪዎችን በማየቴ ነገሩ ከህገ-ወጥ ጭነት ጋር የተያያዘ ነው ስል አሰብኩ፤ ግን በጣም በትልቁ ተሳስቼ ነበር፡፡
ወደ እነሱ እንደተጠጋውም በህይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ የሰው አስከሬን በአይኔ አየው፤ ለዛውም እንደ እንሰሳ ተቀጥቅጦና ተወግቶ ተገድሎ ደሙ ሙሉ መሬቱን ሸፍኖ፡፡ እርግጠኛ ባልሆንም በቦታው የነበሩ ፖሊሶችና ትራፊኮች ከውሃ መውረጃ ትቦ ውስጥ አውጥተን ካነበብነው መታወቂያው ላይ አገኘን ባሉት መረጃ ተማሪ ነው አሉ፡፡ መሬት ላይ ከጎኑ ወድቆ የተገኘ የላፕቶፕ ቦርሳም አለ፡፡
ብቻ ይሄ ሰው ወጣትም ይሁን ሽማግሌ፤ ህፃንም ይሁን አዋቂ፤ በጨለማ ተገሎ እንደ እንሰሳ መሬት ላይ ተጥሎ ስጋውን ዝናብ ሲደበድበው አድሯል፡፡
ይህን ሰው በግፍ የገደሉት የሰይጣን ሙሽሮች ምንም የተለየ ምክንያት ይኑራቸውም አይኑራቸውም ክቡር የሆነውን የሰው ነፍስ ያጠፉተ ለምድራዊ ጥቅም ፣ ቁስ ወይም ገንዘብ ሲሉ ነው፡፡
እውነት ግን የሰው ዋጋው ስንት ነው?
✔የሰው ነፍስ በደቂቃ ከሚጠፋ ገንዘብ ታንሳለችን?
✔የሰው ነፍስ ከአንድ ስማርት ፎን ታንሳለችን?
✔ የሰው ነፍስ ወድቆ ከሚሰበር ኮምፒውተር አንሳ ነውን?
ኧረ እንደው ሲጀምር የሰው ልጅ ከምንስ ጋር በምን መለኪያ ይወዳደራል?
✍ውድ ጓደኞቼ ጠባቂ አንድ አምላክ ቢሆንም እራሳችንም የተቻለንን ጥንቃቄ መውሰድ እንዳለብን ይሰማኛል፡፡ ኪሳችን ውስጥ ያለን 50 ብር ለመውሰድ ሊገለን ጩቤ የሚያወጣ ወሮ በላ ያለበት ዘመን ላይ ደርሰናልና በግዜ ወደየቤታችን እንግባ፡፡ ወንድማዊ ምክሬ ነው፡፡ ፈጣሪ ማስተዋል የሚችል አእምሮን ለሁላችን ይስጠን፤ እንደቀልድ በየሜዳው ደማቸው የሚፈሰውን እህት ወንድሞች ነፍሳቸውን በአፀደ ገነት ያኑር፡፡
🙌መልካም ቀን🙌
Join and share 👉 @sewmehoneth

"ጨረቃ መሆንክን ስታስብ ከዋክብቶችክን አትርሳ"
ጨረቃ እራሷን ችላ ብርሀን ትሰጥ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ውበቱ የሚፈካውና ደምቃ ማስገረም ደረጃ የምትደርሰው በከዋክብቶቿ ስትታጀብ ነው፡፡ እናም በመጠን ከእሷ የሚያንሱትን ከዋክብት ንቃ አትገፋቸውም፤ ይልቁን በዙሪያዋ አቅፋ ታቀርባቸዋለች እንጂ፡፡
አንተም በግልክ አዋቃ ፣ ባለፀጋ ፣ ዝነኛ ትሆን ይሆናል፡፡ ታዲያ ያኔ ማንም አያስፈልገኝም የሚል እሳቤ በውስጥክ ሊኖር አይገባም፤ በሀብትም ፣ በእውቀትም ሆነ በዝና ከአነት ዝቅ ብለው የሚገኙትን ልታርቃቸውም ሆነ ፊት ልትነሳቸው አይገባም፡፡ ይልቁን ልታቀርባቸው ነው ሚገባው፡፡ ምክንያቱም በዚች ምድር ብቻውን መንገድ ጀምሮ እሩቅ የተጓዘ የለም፡፡ ውበትክ የሚለካው በአብሮነት ውስጥ ነው፡፡ እናም ሰዎችን ማቅረብና አብሮ መኖርን ልመድ፡፡
ቀኑ ችግረኞችን የምንረዳበት፤ የታመሙትን የምንጠይቅበት፤ የተራቡትን የምንመግብበት፤ የታረዙትን የምናለብስበት ሰናይ ቀን ይሁንልን፡፡
🙌መልካም ቀን ቸር ያውለን🙌
Join and share👉 @sewmehoneth

😏 ወንዶች ግን ሲያስጠሉ!
«ዘውድአለም ታደሠ»
እንዴት አደራችሁ ክቡራትና ክቡራን? እኔ ከአፍሪካ አንደኛ ከአለም ሁለተኛ እንቅልፍ ተኝቼ ነው ያደርኩት! ባይ ዘ ዌይ እልም ያልኩ እንቅልፋም ነኝ። እንደውም ብዙ ሰዎች ለእንቅልፍ ያለኝን ፍቅር አይተው “ለምን ፓርላማ አትገባም?” ይሉኛል አንዴ ከተኛሁኮ ለምን መድፍ ላይ ሰክተው አይተኩሱኝም ንቅንቅ አልልም። እንደተኛሁ ቅልጥ ያለ ጦርነት መሃል ሁሉ ወስዳችሁ ብትጥሉኝ ተባራሪ ጥይት እስከወዲያኛው ካላሰናበተኝ በቀር ንቅንቅ የለም! የምር አሪፍ ተኚ ነኝ! ምናልባት ብዙም ስለማልጨነቅ ይሆናል። የሚገርም ሰላም አለኝ። ሃብት የለኝ ንብረት የለኝ አንድ ያለችኝ ነገር ሰላሜ ነች! እሷኑ ቆጥቤ እየተጠቀምኩ... ሃሃ ባሻዬ ዘንድሮኮ ሶላትና ሰላም የሌለው ሰው ነው እረፍት የነሳን!
እና እንዴት ናችሁ? እኔ ሰሞኑን ጂም እየተመላለስኩላችሁ ነው። ቆይ እቺን ወሬማ በደምብ ዘርዘር ላርጋት!!
ባለፈው ቦርጩ ጉልበቱ ጋር የደረሰ ጓደኛዬ ይሄ ነገር መሬት ከመንካቱ በፊት ጂም ካልተመዘገብኩ ብሎኝ አብሬው መሄድ! ከዛ ድንገት ቆንጅዬዋን የኤሮቢክስ አሰልጣኝ ማየት!! ከዛ ..... በቃ ምን ከዛ አለው የኔን ነገር ታውቁታላችሁ ያለፕሮግራሜ ተመዝግቤ ደምበኛ ስፖርተኛ ሆንኳ!
ጓዶች! የአሰልጣኟን ውበት ለመናገር አቅም ያንሰኛል! በተለይ የኋላ ታሪኳ (ማለቴ መቀመጫዋ) የአፍሪካ ህብረትን ያስቀምጣል። ከፊት ሆና “አንድ ሁለት” ስትል ሁላችንም ከኋላዋ ተሰልፈን እሷን እሷን እያየን እንደነገሩ ስንወራጭ አንዱንም በቅጡ ሳንሰራ ስፖርቱ ያልቃል። (በሷ ቤት ስፖርት አሰርታን ልቧ ውልቅ ብሏል)
በተለይ ሁሌ ከሷ ኋላ ሚቆመው ሰውዬ (ትራፊክ ነው አሉ) ሲያይ አይፎርሽም። በቃ የሆነ እያመለጠ ያለን መኪና ታርጋ የሚያነብ ነው ሚመስለው። እኔማ በመሃል አስቁሞ መንጃ ፈቃድ እንዳይጠይቃት ሁሉ ፈርቼ ነበር አቤት ሴቶችን ባየሁበት አይን ወንዶች ግን ስናስጠላ
ዛሬ ከጂም እንደወጣሁ መስቀል ፍላወር አካባቢ ወዳለች ካፌ ቁርስ ልበላ ሄድኩ። አስተናጋጆቹ ያምራሉ። (ያምራሉ ያምራሉ አበዛሁ ኣ? ምን ላርግ ሴት ልጅ አስቀያሚ ሆና አትታየኝም)
አስተናጋጆቹ ነጩን ሸሚዛቸውን ለብሰው ወዲያ ወዲህ ሲመላለሱ የሆነ ፋሽን ሾው እያሳዩ እንጂ ሰው እያስተናገዱ አይመስሉም ... ከመሃከላቸው አንዷ ዶን የጥርስ ሃኪም ቤት ማስታወቂያ ላይ እንዳለችው ሴትዮ ሰላሳ ምናምን ጥርሷን እያሳየች ወደኔ መጣች! ጥርሶቿ ከበረዶ ተቀርፀው የተደረደሩ ነው ሚመስሉት።
ጠጋ ስትለኝ ሽቶዋ አፍንጫዬን ሞላው (አስም በሽተኛ ብሆን ድፍት እል ነበር)
«ምን ልታዘዝ የኔ ጌታ» አለች ፈገግታዋን ሳታጓድል። አንቺን ማለት አማረኝ! አንዳንዴ የምንወደውን ሰው አንዱ ካፌ ቁጭ ብለን እንደምግብ ማዘዝ ብንችል እንዴት ጥሩ ነበር? አስተናጋጅ ጠርተን «ያቺን ቀይዋን ልጅ ከሁለት ማንኪያ ስኳር ጋር» ምናምን ብንል
ከሃሳብ እንደመባነን ብዬ «ቱና ሳንድዊች አምጪልኝ» አልኳትና አይኔን ወደሻይ ማሽኑ ስወረውር ቁመቷ ዘለግ ያለች ረዥምና ጥቁር ፀጉር ያላት ባሬስታ አንገቷን ጋደድ አድርጋ በሃሳብ ርቃ ሄዳለች ... የሆነ በሃሳብ ሰላም ባስ ላይ ተሳፍራ ተራራና ድልድዩን እያቆራረጠች ሐገሯ ምትገባ ነው ምትመስለው።
ዞር ስል አይኖቼ ካሼሪዋ ላይ አረፉ! ካሼሪዋ በዛ ያሉ ብሮችን በትኩረት ትቆጥራለች። ስትቆጥር ውብና ወፈር ያሉት ከንፈሮቿ በትንሹ ይንቀሳቀሳሉ። አይኖቼ በፍጥነት እጆቿ ላይ አነጣጠሩ ... በስማምምምም እጅ! እነዛን አሮጌ ብሮች መሆን አማረኝ! ለምን አሮጌ አንድ ብር አልሆንም በቃ ብር ብቻ መሆን አማረኝ! የጣቶቿ ቅጥነት የጥፍሮቿ ርዝማኔ .. አሁን በዚህ እጅ በጥፊ ቢመታ ሚከፋው አለ?
ከካሼሪዋ ላይ አይኔን ስመልስ ከጎኗ ተቀምጣ ሂሳብ የምትሰራ ተለቅ ያለች ሴትዮ ጋር አይን ለአይን ተጋጨሁ። (ባለቤቷ ሳትሆን አትቀርም) የሴትየዋ እድሜ ከነቫቱ እስከ 50 ይገመታል። ፊቷ ላይ የሚታየው በራስ መተማመንና መጠነኛ ኩራት ደስ ይላል። በቀጭኑ ያሰመረችው የአይኗ ኩል አይኗን የሁሉንም ቀልብ የሚስብና ማራኪ አድርጎታል። ፊቷ ላይ የተጋነነ ሜካፕ አይታይም። ያልተዝረከረከ ውበት ነው ያላት! አይኔን አንዴንኳ ሳላርገበግብ ሳፈጥባት ፈገግ ብላ ወደሂሳቧ ተመለሰች .... አቤት ፈገግታ ከእልፍ ሳቆች የሚሻል ውብ ፈገግታ! ልብን ቀጥ የሚያደርግ ተንኮለኛ ፈገግታ! በቃ ምን ልበላችሁ ሬስቶራንቷ ይህ ቀረሽ የማይባል ውበት ፈሶባታል!
ፊቴን ወደቀኝ ስመልስ ግን ጠላታችሁ ክውው ይበል አንድ እርጉዝ ጎሽ የመሰለ ድቅድቅ ጨለማ ፊት ያለው ሰውዬ ላይ አይኖቼ አረፉ! አቤት የደነገጥኩት ድንጋጤ! የሆነ ከገነት ወደሲኦል የተወረወርኩ ያህል ነው የተሰማኝ! በዚያ ላይ ያን የተረበሸ ከተማ የመሰለ ደስታ የራቀው ፊቱን አጨማዶ ሆዱን እያሸ የቀረበለትን ፍርፍር በችኮላ ይውጣል! ደግሞ የአፉ ስፋት ...በዚያ ላይ ቁጣው! ፊቱ ላይ የሚታየው ቁጣ እህል ሳይሆን ነገር እየበላ ነው ሚመስለው። ለመጉረስ አፉን ሲከፍት የአፉ ስፋት ውስጡ አልጋ ቡታጋዝ ምናምን ጣል ቢደረግበት ባለሁለት መኝታ ኮንዶሚኒየም ከነኪችኑ ይወጣዋል ደግሞ ችኮላው። ከራሱ ጋር እየተሻማ ነው ሚመስለው!
ብቻ ከዚያ ሁሉ ውበት አሽቆልቁሎ እዚህ ሰውዬ ላይ የጣለኝን እጣ ፈንታዬን እየረገምኩ ፊቴን ወደአስተናጋጇ መልሼ እንዲህ አልኳት ...
«አንድ ነገር ልጠይቅሽ የኔ ቆንጆ»
«ይቻላል የኔ ጌታ»
«ወንዶች ግን አያስጠሉም በናትሽ?»😂

በጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ ላይ የተሞከረው እና የተመከረው የግዲያ ሚስጥር፦
1. ልክ ለኦቦ ለማ መገርሳ ጠባቂዎች ሁለት ሁለት ሚሊዮን ብር የነብስ ወከፍ ክፍያ ሰጥቶ ለማስገደል እንደተሞከረው ሁሉ ለዶ/ር አብይ ጠባቂዎችም ሁለት ሁለት ሚሊዬን እንደሚሠጣቸው ቃል ተገብቶላቸው ለመግደል ተስማምተው ነበር።ዳሩ ግን ጠባቂዎቹ በዶ/ር አብይ ፍቅር የተሸነፉ ስለነበር የተነገራቸውን ሚስጥር ነግረውት ከሃገር ይወጣ ዘንድ ምክር ለገሱት።እሱ ግን ወገኖቼን ትቼ የትም ንቅንቅ አልልም የሚል አቋም ያዘ።ከዚያ ለባለቤቱ ነገረው ባለቤቱም ከሃገር መውጣት አለብን የሚል ድምዳሜ ላይ ደረሰች።ዶ/ር አብይ ግን በውሳኔው ፀንቶ የአብራኩ ክፋዮች ልጆቹ በጣም ስላሳዘኑት እነሱን አሜሪካን ሃገር አድርሶ እሱ ግን የህይወት መስዋትነት ለመክፈል እራሱን አዘጋጅቶ ወደ እናት ሃገሩ ተመለሠ።እንዳትረሱ ለመሞት ወስኖ ወደ ኢትዮጲያ ተመለሰ።
2. ከጠባቂዎቹ አንዱ ሊገድለው ተስማምቶ እሽታንም ተቀብሎ ነበር።ነገር ግን ገራገሩ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር
አብይ ለዚህ ጠባቂው ምንም ሳይነግረው የውጭ ትምህርት ጨርሶለት፤ ቨዛም ጭምር ያለቀ ስለነበር ለትምህርት ወደ ውጭ ሄደ።ጠባቂውም ከሄደ በኋላ ታቅዶ የነበረውን ሚስጥረ ግዲያ ለጠቅላያችን ነገረው።
3. ከሃረርጌ የኦሮሞ ህዝብ ጋር በሃረር ከተማ ምክክር ላይ በነበረ ግዜ የታጠቁ የመከላከያ አባላት ያለፍቃድ ወደ ስብሰባው ውስጥ ለምግባት ያደረጉት መከራ በጠባቂዎቹ ከሸፈ።
4. መሃል አዲስ አበባ፣አብዮት አደባባይ ላይ የተሞከረውን የግዲያ ሙከራ የምታስታውሱት የአደባባይ ማስጥር ነው።
5. አዲስ አበባ ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ቢሮ ፊትለፊት ያለ ህንፃ ላይ ስናይፐር ወድሮ የጠቅላዩን መውጫ እና መግቢያ ሲጠባበቁ እንደነበር የተደረሰበት ሃቅ ነው።
6. የመከላከያ አባላት ደሞዝ ጥያቄ ነው የሚል ጭንብል አጥልቀው ከነሙሉ ትጥቃቸው ወደ ቤተመንግስት የተመሙትም የመከላከያአባላት የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ናቸው።
እንግዲህ አስተውሉ ወንድሞቼ ከሞት ጋር ታግሎ እኛን ነፃ ያወጣን መሪ ነው።ሞቶ እኛን ያኖረን መሪ ነው።የዚህን
ሃገር ህዝብ ከወለዳቸው # ልጆች አስበልጦ እነሱን ሸኝቶ
ለመሞት ወስኖ የተመለሰ ታላቅ መሪ ነው።ነፍሱን አሲዞ
እንደልባችን አፋችንን እንድንከፍት ያረገና ጀግና መሪ
ነው። በህይዎቱ ላይ ወስኖ፤በሞት ውስጥ ታግሎ እኝን
ከእስር ያስፈታን ብርቅዬ መሪ ነው።
ታዲያ ዛሬ በህይዎቱ ቆምሮ ለኛ ህይወት የሰጠን መሪ ላይ ፊት ማዞርን ምን አመጣው? እንዴትስ ተቻለን፣ ከልጆቹ እኛን የመረጠ የክፈለ ዘመኑ ምርጥ መሪ ላይ መዶለቱንስ ከቶ ምን ወለደው? እና ወገኖቼ ደግመን ደጋግመን ብናሰላስል ተጠቃሚዎቹ እኛ እንጂ ዶ/ር አብይ እንዳልሆነ ብንገነዘብ መልካም ነው። አብይም የሰው ልጅ ነው ልሳሳት ይችላል ።
መልካም ጊዜ

የመፀዳጃ ቤት ወግ!
«ዘውድአለም ታደሠ»
መስሪያ ቤታችን ውስጥ ያሉት መፀዳጃ ቤቶች እንደብዙሃኑ የህዝብ መፀዳጃ ቤቶቻችን ከመፀዳጃነት ባለፈ እንደሃሳብ መስጫ ሳጥንነትም ያገለግላሉ። በርና ግድግዳው ላይ የማይፃፍ ነገር የለም። የኛ ህዝብ ሽንት ቤት ሲቀመጥ ወደደራሲነት የሚለወጠው ታሪክ አለ። አረ ሁን ብሎ ፓርከር ይዞ ሚገባ ሁሉ አለ።
በርግጥ ሰው ከበላና ከጠጣ ሽንት ቤት መቀመጡ አይቀርም። ሞዴል ሆነች ታዋቂ ዘፋኝ ፣ ቄስ ሆነ ፓስተር፣ ሃብታም ሆነ ደሃ ሁሏም በቀን ለተወሰነ ደቂቃ ሸኖ ቤት ዱቅ ትላለች። አንዳንዴ ሳስበው ሰውን እኩል የሚያደርገው ሞትና ሽንት ቤት ይመስለኛል
የመፀዳጃ ቤት ግድግዳና ፌስቡክም አንድ ናቸው። ሁሉም በነፃነት ሃሳቡን እንደወረደ ተንፍሶ ውልቅ ይላል።
ያው እኔም በገባሁ ቁጥር ግድግዳና በሩ ላይ የሚፃፉትን ፅሁፎች እያነበብኩ ዘና እላለሁ። አንዳንዴም ፃፍ ፃፍ አረጋለሁ :)
ዛሬ መስሪያ ቤት ያሉት ሶስቱም መፀዳጃዎች በራቸው ተዘግቶ ደረስኩ። ሽንት ቤቱ የግሌ ይመስል በሌላ ሰው ሲያዝ ለምን እንደምበሳጭ አይገባኝም :) ደሞ ክፋቱ የቤት አከራይና ሸኖ ግዜ አይሰጡም :) ሁሉም እንደተያዙ ባውቅም ጠጋ ብዬ የመጀመሪያውን በር አንኳኳሁ። በሃበሻ ባህል የሽንትቤት በር ማንኳኳት ማለት «ሰው አለ ወይ?» ማለት ሳይሆን «ሰውዬ ቶሎ ውጣ» ማለት ነው። ደጋግሞ ማንኳኳት ደግሞ «ሰውዬ የሽንትቤቱ መቀመጫኮ ስልጣን አይደለም ምን ይጎልትሃል?» ማለት ነው :)
የመጀመሪያውን በር ሳንኳኳ አንድ ሰላላ ድምፅ «ሰው አለ» አለኝ። ማንነቱን በድምፁ አወቅሁት። ምክትል ስራ አስኪያጃችን ነው። ይሄ ሰውዬ አንዴ ከገባ አይወጣም። እንደውም ግድግዳው ላይ በቀይ እስክሪብቶ ረጃጅም ግጥም ሚፅፈው እሱ ሳይሆን አይቀርም። :)
የሚቀጥለውን በር ሄጄ አንኳኳሁ። «ሰው አለ» አለኝ ወፈር ያለ ሻካራ ድምፅ። እሱንም በድምፁ ለየሁት። የእቃ ግዢ ክፍሉ ሃላፊ ነው። ፀባዩ እንደድምፁ ሻካራ ነው። በዚያ ላይ በገንዘብ ብክነት ብዙ ግዜ ተገምግሟል። ሆኖም የቀድሞው ማኔጀር ዘመዱ ስለነበር በማስጠንቀቂያ ነበር ሚታለፈው። አሁን ግን ማኔጀሩ ከቦታው ስለተነሳ እየጨነቀው ነው መሰለኝ ሽንት ቤት መመላለስ አብዝቷል። በየትኛውም ሰአት ብትመጡ የምታገኙት እሱን ነው። ልክ እንደ ናይት ክለብ ሽንት ቤት ሁሉ እየቀያየረ ይቀመጣል :) (እኔ ደሞ ሳጋንን ለነገ አልልም)
ሶስተኛውን ክፍል ሳንኳኳ «አለን» የሚል የሴት ድምፅ ሰማሁ። ጆሮዬን ስላላመንኩ ደግሜ አንኳኳሁ። «አረ ሰው አለ ጌታው መቼስ ተጠጋግተን አንቀመጥ» አለችኝ። ገኒ ነች። የመስሪያ ቤታችን ክሊዮፓትራ!
የወንዶች ሽንት ቤት መጠቀሟ ስለገረመኝ «ገኒ በሰላም ነው እኛ ጋር የመጣሽው?» ስላት እየሳቀች
«ዜድዬ እና ልፈንዳልህ እንዴ? ሴቶቹ እንደው አንዴ ከተቀመጡ ሽንት ቤቱ ለልማት ካልተፈለገ አይነሱ! ቢቸግረኝ እናንተጋር መጣኋ! መቼስ እቺን ሰራች ብላችሁ አትገመግሙኝም» ስትል ምክትል ማኔጄሩ ጮክ ብሎ
«ደና ዋልሽ ገኒ» አላት። (ያው ሰምቼሻለሁ ለማለት ነው)
«ደና ዋሉ አቶ ታምራት» አለች ደንገጥ ብላ
«እግዚሐር ይመስገን ስራ ጥሩ ነው?» አላት
«ጥሩ ነው ይመስገነው» አለች።
«እንዴት ነው ባለፈው ያዘዝኩሽን ስራ ጨረስሽ?» ሲላት ትግስቴ አለቀ።
«ሰውዬ ምን ነካህ? ሽንት ቤት ውስጥ ብዙ ስትቆይ ቢሮህ መሰለህ እንዴ?» ልለው አሰብኩና ከእንጀራ ገመዴ እንደሳር ሲነቅለኝ ታይቶኝ ዝም አልኩ!
ወዲያው ገኒ ወጣች! በስመአብ ዛሬ ደሞ እንዴታባቷ ነው ያማረባት? የሆነ ከሽንትቤት ሳይሆን ከስቲም ቤት የወጣች ነው ምትመስለው። ደሞ ሽቶዋ!
እጇን እየታጠበች ፈገግ ብላ «ሰላም ነው?» አለችኝ። ድምጿ ራሱ ሰላም አለው። እጆቿ አጥንት ያላቸው አይመስሉም። አለ አይደል በደም ተሞልተው በለስላሳ ቆዳ የተወጠሩ ነው ሚመስሉት።
ገኒ ውብ ነች! ውበቷን እንደመሰላል ብትጠቀም የትና የት እንደምትደርስ እናውቃለን። የድሮው ማኔጃራችን በፍቅሯ ጠብ ብሎ ሊጠብሳት ያልፈነቀለው ድንጋይ የለም። በቀን አስር ግዜ ነበር በሰበብ አስባቡ ቢሮው ሚያስጠራት። ምንም ሴልስ ኦፊሰር ብትሆንም ቢሮው አስጠርቶ ስለማይመለከታት ጉዳይ ያወራታል። አንድ ሰሞን የሻይ ሰአት ላይ የሚላትን እየነገረች ታስቀን ነበር። ቢሮው ባስቸኳይ ያስጠራትና
«እኔ ምልሽ ገኒ! የሰሜን ኮሪያና የአሜሪካን ፍጥጫ ከሙያሽ አንፃር እንዴት ታይዋለሽ?» ይላታል።
ሌላ ግዜ ደግሞ ከመሬት ተነስቶ «እንዴት ነው ሰሞኑን ፊትሽ ጥሩ አይደለም ያስቀየመሽ ሰራተኛ አለንዴ?» ይላታል። አዎ ብላ አንዱን ብትጠቁመውኮ ያለማስጠንቀቂያ ሊጭረው ነው :)
ብቻ ያቅሙን በስልጣኑም በፍራንኩም ሊያሰምጣት ሞክሮ ሳይሳካለት መስሪያቤቱን ለቀቀ!
(አንዳንዴኮ ቆንጆ ሴቶችን እንደጉሊት እቃ ገንዘብ ያለው ሁሉ ሚሸምታቸው ይመስለናል እንጂ ከአይናቸው ይልቅ እይታቸው ከከንፈራቸው ይልቅ ንግግራቸው የተዋበ እልፍ ሴቶች አሉኮ የምር)
አልዋሻችሁም አንድ ሰሞን እኔም ገኒን ልጠብሳት ተፍ ተፍ ብዬ ነበር። በርግጥ ከገኒ በፊትም መስሪያ ቤታችን የምትሰራ ሌላ ልጅም ወድጄ ነበር (ጥሎብኝ ፍቅር ያጠቃኛል መሰለኝ :D )
የመጀመሪያዋ «አይ ዜድዬ ጥሩ እህትህ ብሆን ይሻላል» ብላ ጨጓራዬን ላጠችው! ሴቶች ግን ካልፈለጋችሁ ለምን አልፈልግም እንደማትሉ ግራ ይገባኛል። «እናቱ እኔ ያሉኝንም እህቶች በአደራ ሚረከበኝ እያፈላለግኩ ነው። የምፈልገው ተጨማሪ እህት ሳይሆን ፍቅረኛ ነው» ብዬ ነካሁት :)
ገኒ ግን እህት ምናምን የሚል ግርግር ሳታበዛ «ዜድ you can't be my future husband» አለችኝ።
“why” ስላት
“because i know that u'r not ready for marriage እኔ ደሞ በዚህ እድሜዬ ተቃቅፎ ካፌ ለካፌ መዞር ምናምን አልፈልግም?” አለችኝ። አልተከራከርኩም! ሂሴን ውጬ ተሸበለልኩ ;)
ወደመፀዳጃ ቤት ገብቼ እንደለመድኩት በሩ ላይ የተፃፉትን አዳዲስ ፅሁፎች ማንበብ ጀመርኩ። ህዝቤ በግዜ ፃፍ ፃፍ አርጎ ወጥቶላችኋል።
«ወገን! የፖለቲካው ሁኔታ አያሳስባችሁም ግን?»
ከሚል ፅሁፍ ስር «አንተ የደላህ ነህ ልጄ። እኔ ምለው ደሞዝ አይወጣም እንዴ ወይስ እሱንም እንደምርጫው ይራዘም ሊሉ ነው?» የሚል መልስ ተፅፏል።
«ጌታቸው አሰፋ ውስጤ ነው» ከሚል ፅሁፍ ስር ደሞ «አደራ እዛው ይኑር እኛ መስሪያቤት እንዳትፀዳዳው» ብሎታል አንዱ ተንከሲስ!
አንድ የተበሳጨ ሰራተኛ ደሞ «ስራ አስኪያጁን አንድ ቀን እደፈጥጠዋለሁ» ብሎ ከፃፈው ስር
«አንተ የሰርቪሱ ሹፌር በቀለ ነህ አውቄሃለሁ» ተብሏል። ወረድ ብሎ «እናቴ ትሙት እኔ አይደለሁም» ብሏል በቄ :)
ጥግ ላይ ደሞ አንዱ የዋህ በእርሳስ «እባካችሁ ወገኖቼ ንስሃ ግቡ» ብሎ ፅፏል ። ከሱ ጎን
«እስቲ መጀመሪያ በግዜ እንግባ» የሚል መልስ ተፅፏል። (ይሄን መልስ የፃፈው ዘገየ እንደሆነ እርግጠኛ ነኝ። ዘገየ ቅምቀማ በጣም ከመውደዱ የተነሳ ቺክ ሲተዋወቅ ራሱ «ለምን ደብል ጅን በደረቁ እየጠጣን አናወራም?» ብሎ ነው ሚጀምረው)
ሌላ ሌላውንም ሳነብ ቆየሁ። ተረብ፣ ቀልድ ግጥም ሁሉም ነገር ተፅፏል። አንዳንዴ የስራ ባልደረቦቼ የባከኑ ደራሲዎች ሚመስሉኝኮ ለዚህ ነው። ጉዳዬን ጨርሼ ልወጣ ስል እኔም ስለተወሰወስኩ እስኪሪብቶዬን ከኪሴ አወጣሁና አንዲት ግጥም ፃፍኩ ..
ዶሮ ተወደደ
በጉ ተወደደ
በሬም ተወደደ
ብሎ ይተክዛል ፥ ሄዶ የጠየቀው
እኔን ምን ቸገረኝ ፥ ያገባ ይጭነቀው! :)
@sewmehoneth
Any comment 👉 @hundaolbot

መሽቷል ከስራ ወደቤት በባጃጅ እየሄድኩ ነው።ከኋላ ሦስት ሆነን
ተቀምጠናል።አጠገቤ የተቀመጡት ሁለቱም ስልካቸውን እየነካኩ ነው;ድንገት
የሆነ ሰአት ስቅ ስቅ ብሎ የሚያለቅ ሰው ድምፅ ተሰማኝ።ዞር ብዬ አጠገቤ
ያለችውን አየኋት ,ቀይ ነች የቀይ ዳማ በዛ ላይ የደም ገንቦ(የደስ ደስ አላት)
ስታለቅስ እንደቆየች ፊቷ ያስታውቃል። ይቺን የመሰለች ቆንጆ ማነው
ሚያስለቅሳት? አልኩ,ብዙ ነገር አሰብኩ የቤተሰብ ችግር አጋጥሟት ይሆን?
አሟት ይሆን እንዴ? ወይስ ከቤተሰብ ተጣልታ ይሆን? "እናት ምን ሆነሽ ነው
አልኳት"? ልትመልስልኝ አልፈለገችም ከስልኳ ላይ መልእክት ታነብና ደግሞ ቀና
ብላ ማልቀሷን ትቀጥላለች። በጣም ጨነቀኝ "በማርያም እናት ምን ሆነሽ ነው?
የምረዳሽ ነገር ካለ አልኳት?" ታውቂያለሽ "የምወደው boyfriendዴ cheat
አደረገብኝ dump አደረገኝ" ብላ ስለሁኔታው ነግራኝ ትከሻዬን ደገፍ ብላ
ማልቀሷን ቀጠለች, የፍቅሯን ጥልቀት ተረዳሁ,ላፅናናት ሞከርኩ ምን ያክል
ልቧን ቢሰብረው ነው እንደዚ የምታለቅሰው ብዬ አሰብኩ ሳላውቀው ልጁን
ጠላሁት
ሰፈሬ ደረስኩኝ ትችያት ወረድኩ ግን ሳስባት አመሸሁ
ቆይ ግን መታመን የማይችሉ ልቦች ለምን ፍቅር ይጀምራሉ? ለምን በሰው
ልብ እና ስሜትስ ይቀልዳሉ?
እና ምን ለማለት ኖ በፍቅር relationship ውስጥ መታመን የማይችል እዚህም
እዛም የሚያበዛ ሰው,የሰው ልብ መስበር ጀብድ የሚመስለው ሰው በአጠቃላይ
ሲጥ ይበል አቦ😜 በተለይ ልጅቷን ያስለቀስካት😁

Today, መንገድ ላይ I was a bit sick ena , I just needed a place
to sit ከዛ there was a ሊስትሮ around. እና "አሞኝ ነው ትንሽ ልቀመጥ"
ስላቸው። ጫማ የሚያስጠርገው ሰውዬ እንዴት እንደተነሳ። ሊስትሮው ደሞ "ነይ
ውሃ ላምጣልሽ?" ሰውየው ደሞ "የት ነው ምትሄጂው ስልክ ልደውልልሽ?"
ትንሽ አርፌ አመስግኜ I went to a pharmacy to buy painkillers. The
pharmasist was like, "ነይ እህቴ ቁጭ በይ፣ አሁን ትውጫለሽ?" She
gave me water and didnt even make me pay for it.
I went out and took a taxi. የረዳቱ ሃዘኔታ፣ አጠገቤ የነበረችው ልጅ ደሞ
she was like, "ቦታ ልቀይርሽ? ቦርሳሽን ልያዝልሽ?" ከታክሲ ስወርድ... Both
of them were like "ቀስ ብለሽ ሂጂ"።
They don't even know me eko, they are just መልካም ሰዎች!

አንዳንድ ነገሮችን ማብራራት ይከብዳል!!
ገበሬው በአቅራቢያው ያለ ጃምቦ ቤት በቀን አረቄ በጃንቦ ይጨልጣል።
አንድ ሌላ የሚያውቀው ሰው ይመጣና ይጠይቀዋል
" በዚ የስራ እና የምርት ሰዓት ግን እዚ መጠጥ ቤት ምን ታደርጋለህ?"
ገበሬው ጭንቅላቱን እያወዛወዘ
"አንዳንድ ነገሮችን ማብራራት ይከብዳል።" ይላል።
ሰውዬው ወንበር ስቦ እየተቀመጠ ገበሬውን ይጠይቀዋል
"ወዳጄ ምን ሆነህ ነው ንገረኝ፣ሲያወሩት ይቀላል"
"እሺ ካልክ...!" ብሎ ገበሬው ይጀምራል
"እሄውልህ ዛሬ ጠዋት ተነስቼ ግብርና በብድር የሰጠንን ነጯን ላም እያለብኩ
ነበር። አንድ እቃ እንደሞላው ግራ እግሯን አንስታ የታለበውን በሙሉ ደፋችው"
"እሺ ግን ይሄ እኮ ታድያ ብዙ አያስከፋም ለዚህ ሁኔታም አይዳርግም "ይላል
ሰውየው
"አንዳንድ ነገሮችን ማብራራት ይከብዳል።" ብሎ ገበሬው አሁንም ይተክዛል
...ጭማሪ አረቄም ያዛል።
"እሺ ከዛስ ምን ሆነ" ሰውየው አለሳልሶ ለማረጋጋት ይጠይቃል
ገበሬው እየጠጣ ንግግሩን ይቀጥላል
" ከዛ ያው ግራ እግሯን ከ አንዱ ቋሚ ጋር አሰርኩት"
"ከዛስ....?"
"ከዛማ ድጋሚ ተቀምጬ ማለብ ጀመርኩ....በሌላ እቃ ሞልቼ እንደጨረስኩ ቀኝ
እግሯን አንስታ ድጋሚ የሞላውትን እቃ ደፋችው"
ሰውዬው ከት ብሎ ስቆ "እንዴ ድጋሚ?" ይለዋል
ገበሬው አሁንም
"አንዳንድ ነገሮችን ማብራራት ይከብዳል " ይለዋል።
"ከዛስ ምን አረክ?" ሰውዬው በጉጉት ይጠይቃል።
"ያው ከዛ በጣም ተማርሬ ቀኝ እግሯንም ከሌላ ቋሚ ጋር አስሬ ማለብ
ጀመርኩ...የሚያሳዝነው ይቺ የተረገመች ላም ይሄኛውን በጥንቃቄ እንደጨረስኩ
በጭራዋ ደፋችው"
"ያሳዝናል በእውነቱ "አለ ሰውዬው ጭንቅላቱን እየነቀነቀ።
"አንዳንድ ነገሮችን ማብራራት ይከብዳል።" ብሎ ጭንቅላቱን በሃዘኔታ ይነቃንቃል
አሁንም ገበሬው
"ከዛስ?" ሰውዬው የገበሬው ችግር መጨረሻው አጓጉቶታል
"ከዛማ ሌላ ገመድ ፈልጌ ስላጣው ቀበቶዬን ፈትቼ ጭራዋን አስሬ እንደጨረስኩ
ሱርዬ ወለቀ፣በዝች ቅጽበት ሚስቴም ወደውስጥ እየገባች ነበር"
"አንዳንድ ነገሮችን ማብራራት ይከብዳል።"
...
...
..
መልካም እሁድ 😊
ምንጭ እንዳትሉኝ....

ㅤ:
ወጣትነት
ወጣትነት ፋሽን ተከታይ ዘናጭ ተሽቀርቃሪ መሆን ማለት አይደለም! ወጣትነት ራስን በሱሶች ማጠር ማለት አይደለም! ወጣትነት በምክንያታዊነት ሳይሆን በስሜታዊነት እየተነዱ ራስንና ሌላውን አደጋ ውስጥ መዝፈቅ ማለት አይደለም! ወጣትነት ብዙ ጃንቦ የጠጣ ጀግና ማን ነው መባባል ማለት አይደለም! ወጣትነት ብረት ገፍቶ ደረትን ማሳበጥ ማለት አይደለም! ወጣትነት ሺሻ ቤት ተቀምጦ ጭስ ማቡነን ማለት አይደለም!
፧
ወጣትነት በወሲብ ሱስ ከዚህም ከዚያችም ጋር በዝሙት ተወጥሮ መልከስከስ ማለት አይደለም! ወጣትነት በጥላቻ እና በዘረኝነት ተሞልቶ መታወር፣ መደባደብ እና መነታረክ ማለት አይደለም! ወጣትነት ተመልሶ የማይመጣውን ተፈጥሮ የሰጠችንን ታላቅ ሃይል በማይረባው ነገር ጊዜን ማቃጠል ማለት አይደለም! ወጣትነት ግዜያዊ ስሜትን ብቻ እያዳመጡ እንደፈረስ ጋሪ መነዳት ብቻ አይደለም! ወጣትነት በሀሜት፣ በአሉባልታ፣ በወሬ ሱስ፣ በአቃቂር፣ በተንኳሽነት፣ በቧልት መሞላት ማለት አይደለም!
፧
ወጣትነት ይሄንንም ያንንም ይቺንም ያቺንም መጀንጀን መጀናጀን ማጀናጀን ማለት አይደለም! ወጣትነት በባዶ ጭንቅላት ምርጥ አልባሳትን ለብሶ እየተጀነኑ በባዶ ኩራት ተወጥሮ መሬትን ለመርገጥ እየተጸየፉ መራመድ ማለት አይደለም! ወጣትነት በግዴለሽነት፣ በተስፋ መቁረጥ፣ ከነፈሰው ጋር መንፈስ ማለት አይደለም! ወጣትነት በራስ ወዳድነት መንፈስ መወጠር እና እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል ማለት አይደለም! ወጣትነት በማይረባው በቀበሌኛው አመለካከት መታጠር ማለት አይደለም! ወጣትነት ቁንጫ የምታክል እውቀት በመያዝ ይቺ እውቀት ብቻ ትበቃኛለች እያሉ አጉል መመጻደቅ ማለት አይደለም...
፧
ወጣትነት ባህር ነው ። ወጣትነት ውቂያኖስ ነው ። ወጣትነት አድማሰ ሰፊነት ነው ። ወጣትነት እውቀትን ለማስፋት የምንጋደልበት ሰአት ነው ። ወጣትነት በማስተዋል ብርሃን መሞላት ነው ። ወጣትነት ችግር ፈጣሪነት ሳይሆን ችግር ፈቺነት ነው ። ወጣትነት በዘረኝነት ተሞልቶ አማራ፣ ትግሬ፣ ኦሮሞ፣ ወላይታ...ቅብርጥሶ እየተባባሉ ቡድን በመስራት ስለ ቀበሌኛ አስተሳሰብ መስበክ ሳይሆን ወጣትነት ስለ ኢትዮጵያዊነት ከተቻለም አለም አቀፋዊ እይታን ማስፋት ነው ።
፧
ወጣትነት ፍቅርን እና አንድነትን መስበክ ነው ። ወጣትነት በዝሙት ባህር መንቦራጨቅ ሳይሆን ስሜትን የመግዛት ጥበብ ማዳበር መቻል ነው ። ወጣትነት ብርሃን ነው ። ወጣትነት ተስፋ አለመቁረጥ ነው ። ወጣትነት በቀናነት መሞላት ነው! ወጣትነት እስከመጨረሻው ጠብታ ህልምን ለማሳካት መፍጨርጨር ነው ። ወጣትነት ማንበብ ነው ። ወጣትነት መጠየቅ ነው ። ወጣትነት ስለዓለም፣ ስለ ህይወት፣ ስለ ጥበብ፣ ስለ እውቀት ብዙ ለማወቅ መጠማት ነው ። ወጣትነት ለሌሎች መኖር ነው ። ወጣትነት ለአገሬ ምን ልስራላት ብሎ ራስን መጠየቅ ነው ። ወጣትነት ስለነገ ትልቅ ህልም እና እቅድ መሰነቅ ነው ። ወጣትነት እሳት ነው ። ወጣትነት ቤንዚል ነው ። ወጣትነት ቅጠል ነው ። ወጣትነት ጤዛ ነው ። ወጣትነት ታክሲ ነው ። ወጣትነት ምርጫ ነው ። ወጣትነት በባህር ላይ ያለች ጀልባ መሆን ነው ። ወጣትነት የመቶ ሜትር ሩጫ ያህል ነው ። ወጣትነት ውስጥን ፈተናን ለማለፍ ማጀገን ነው ። ወጣትነት ከፍርሃት፣ አልችልም እና አይሳካልኝም የሚለውን እስር በጣጥሶ ማለፍ ነው ። ወጣትነት ለአንዳች ስኬት በኩራት እና በሞራል መራመድ ነው ... ።
፧
፧
ምንጭ ፦ " ኤጭ...! " መጽሐፍ ከገጽ 170-172 የተቀነጨበ
ደራሲ ፦ አዘርግ

«... የሃምሳ ብር መልስ ረስቼ ወርጄ ታክሲውን በላዳ እየተከተልኩት ነው
...የገባህበት እገባታለሁ እንጂ ኣንላቀቃትም
ወንድ ልጅ ዛሬ ገና ተደፈረ ! 😊😏
@sewmehoneth
...የገባህበት እገባታለሁ እንጂ ኣንላቀቃትም
ወንድ ልጅ ዛሬ ገና ተደፈረ ! 😊😏
@sewmehoneth
"ዛሬ ወደ ራሴ የሚመልሰኘ አስገራሚ ታሪክ ገጠመኘ፡፡"
በእልፍ አእላፋት ጥልፍልፍ መስመሮች የተሞላውን የዕጣ-ፈንታ ሰንጠረዥ የሰው ልጅ እንዴት ሊረዳው ይቻለዋል?.....ጥቂቱን እንኳን መረዳት መቻል ትልቅ ስጦታ ነው፡፡
ከዚያ የላቀ መረዳት ግን ተዓምር ነው ሊባል ይገባል፡፡
ከወራት በፊት በነበረኘ ግንዛቤ "የሁሉም ነገር ዕጣ-ፈንታ በፈጣሪ መዝገብ ተከትቧል፡፡"
የሚለውን ነገር በከፊል ስቀበል በከፊል ደግሞ አይዋጥልኘም ነበር፡፡ "የአንድ ሰው ነፍሰ ገዳይነት ቀድሞውንም በዕጣ ፋንታ መዝገቡ ላይ ተፅፎ ከሆነ ፣ ያሰው ከመወለዱ በፊት የተፃፈውን ዓይነት ሰው ከመሆን ውጪ አማራጭ ላይኖረው ነው፡፡ ታዲያ በምንም ዓይነት መልኩ ነፍሰ-ገዳይነቱን ሊገታው ካልቻለና ከተፃፈው ውስጥ ጠብ የሚል ነገር ከሌለ፣ እንደምን 'ነፍሰ-ገዳይ' ተብሎ ከገሃነም ይጣላል?" ብዬ ነው ምሟገተው፡፡
ከዚህም ሌላ አንደ ሰው ሲሞት፣ እንዲህ ቢያደርግ ኖሮኮ!...ወይም ይሔን ቢያደርግ ኖሮ ይተርፍ ነበር፡፡ ሲባል ሁሌም ምላሹ 'አይ!....ምንር ቢደረግ ፈጣሪ ቀድሞ ከቆጠረለት ቀን አንዲትም ሰከንድ መጨመር አይቻል!" የሚል ነው፡፡
ይሄ አባባል የሚገልፀው፣ የሁሉም ሰው ዕድሜ አስቀድሞ የተቆጠረና ከቀኗ ውልፍት አንደማትል ነው፡፡ ይሔም አንደማይዋጥልኘ ምክንያቴን አቅርቤ እሟገት ነበር፡፡
ምክንያቴም "እንደ ኢትዮጵያ ባሉት ደሃ ሃገራት የሰው አማካኘ እድሜ ከ40 አመት በታች ሲሆን፣ በስልጣኔ በገፋ ሀገራት ደግሞ የአማካኙ የሰው እድሜ 70 አመት ድረስ ይጠጋል፡፡ የሚል ነው፡፡ በደሃ ሃገራት በረሃብ ሳቢያ ሰው ያለዕድሜ ይረግፋል በቀላሉ ሊድኑ በሽታዎች በቂ ህክምና ባለመኖሩ ሳቢያ ብዙ ህዝብ ይጨርሳሉ፣ በዚህም ምክንያት የህዝቡ አማካኘ እድሜ አጭር ሊሆን ችሏል፡፡
በስልጣኔ በገፋ ሃገራት ደግሞ የተሟላ የምግብ አቅርቦት፣ በቂ ህክምና ማዕከል ስለሚገኘ፣ ህዝቡ በቀላሉ ሊድኑ በሚችሉ በሽታዎች ሳቢያ ለሞት አይደርስም፣ ለዚህ ነው አማካኙ እድሜ ከፍ ያለው፡፡
ታዲያ የእያንዳንዳችን ዕድሜ አስቀድሞ ስለተወሰነ ነው?? ወይስ እድሜን ከፍና ዝቅ ሊያደርጉ የሚችሉ ኢኮኖሚ ከቴክኖሎጂ ጋር ቁርኘነት ያላቸው ምክንያቶች ስላሉ ነው ይሔ የሆነው?? በማለት የሰው ልጅ እድሜ አስቀድሞ የተወሰነ ያለመሆኑን እሟገታለሁ፡፡
ፈጣሪ ፍፁም ዲሞክራሲያዊ በመሆኑ ለነፍሳችኝ በባህሪያት ከትቧል፡፡
እንደ ሕሊና አዕምምሮና ስሜት ሁሉን ፈቃድ የሚባል ባህሪን በነፍሳችን አትሟል፡፡
ይሔ ጥልፍልፍ ዕጣ-ፈንታ መዝገብ ጥልፍልፍ ጎዳና ቢሆንና እኛ ደሞ መኪና ብንሆን፣ ሹፌሩ ፈቃዳችን ነው፡፡
ይሔን መዝገብ የምንኖረው በፈቃዳችን በመረጥነው መስመር (ጎዳና) ይዘን በመጓዝ ነው፡፡
በፈቃዳችን ሹፌርነት የመረጥነውም መስመር(ጎዳና) ይዘን በመጓዝ ነው፡፡ በፈቃዳችን ሹፌርነት ከአንዱ ጎዳና ወደሌላው እየተጠማዘዝን ሁሉንም ጎዳናዎች በአንዴ መርገጥ ስለማንችል ከምንጓዝበት ጓዳና(ከመረጥነው መስመር) ውጪ ካሉት ሌሎች እልፍ አዕላፋት ሕይወት
ጎዳናዎች(ዕጣ-ፋንታዎች) ጋር ስንተዋወቅ ምን ሊመስሉ እንኳን እንደሚችሉ ፍንጣቂ ምስላቸው ሳይኖረን አልያ ከእነአካቴው መኖራቸውን እንኳን ሳናውቅ ተጀምረን እናበቃለን፡፡
በተከተልነውም ሆነ ባልተከተልናቸው የህይወት ጓዳናዎች ውስጥ የተለያዩ ገጠመኞች፣ የተለያዩ የዕድሜ ጣራዎች፣ የተለያዩ የሞት መንስኤውች ተፅፈዋል እላለሁ፡፡
ይሔ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ያመንኩበቶ መደምደሚያ ነው፡፡
እነዚህ ላይ "ከእኛ ፈቃድ ውጪ በሌሎች አስገዳጅነት ሳቢያ የሚገጥሙን ብዙ ነገሮች አሉ፡፡
አንድ ሰው መኪና ሲያሽከረክር ፍፁም ጥንቃቄ ቢያደርግም አንዱ ተክለፍልፎ መቶ ሊወጣበት ይችላል፡፡
እንዲ ያለውስ ነገር ምን ሊባል ነው?" የእኔ መልስ ግን "አሁንም ቢሆን ያንን ጎዳና ተከትለን የተጓዝነው በፈቃጃችን ነውና በዚያ ጎዳና ውስጥ የሚገጥሙን መልካምም ሆነ መጥፎ ነገሮች ሁሉ እናስተናግዳለን፡፡" የሚል ነው፡፡
ስለዚህ ነገሩን ሳጠቃልለው ነፍሰ ገዳዩም፣ ነፍስ ገዳይ ከመሆኑ በፊት ላይሆኖ የሚችልበት ብዙ አማራጭ የሕይወት ጎዳናዎች ነበሩት፡፡ የተከተለው ጎዳና ግን ለዚህ አብቅቶታል፡፡ ሟቹም በህይወት ሊቆይ የሚችልበት ብዙ መንገዶች ሊኖሩት ይችሉ ነበር፣ ነገር ግን በመረጠው ጎዳና እና በዚያ ጎዳና ውስጥ በተከሰቱ ነገሮች ሳቢያ ያ ሳይሆን ይቀራል፡፡
ከፈቃጃችን ውጪ የሚሆኑ ነገሮች ግን አሉ እላለሁ፡፡ መወለዴ በእኔ ፈቃድ የሆነ አይደለም፡፡
ከማን እንደምወለድ፣ የትሀገር እንደምወለድ፣ እና መች እንደምወለድ እኔ አልወሰንኩምና፡፡
ዮቶር :- ዓለማየሁ ደመቀ
ለንባብ እንዲመች ተደርጎ የተወሰደ
ማንኛውንም አስተያየታቹን በ @hundaolN
የሰው ግማሽ የለውም ግን ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል፡፡