tgoop.com/TEWAHIDOETHIOPIA/337
Last Update:
ግንቦት 8
ታላቁ አባ ዳንኤል
ይህ ቅዱስ አባት ስም አጠራሩ ክቡር ነው። በሁሉ ነገሩ የተቀደሰ የገዳማውያን መብራትም ነው። ከተረፈ ንጹሕ ሕይወቱ ጣዕመ መንግሥተ ሰማያትን አይቷልና። አባ ዳንኤል በትውልድ ግብጻዊ ሲሆን ዓለምን ንቆ (መንኖ) ገዳም የገባው ገና በወጣትነቱ ነው።
ጊዜውም ዘመነ ጻድቃን (በአምስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን) ነበር። በገዳመ አስቄጥስና በደብረ ሲሐት ይታወቃል። ታላቋ መካነ ቅዱሳን ገዳመ ሲሐት ዛሬም ድረስ በስሙ የምትጠራ ሲሆን ለዚህም ምክንያቱ እጅግ ለብዙ ዘመናት በውስጧ ተጋድሎ ፍሬ ስላፈራባት ደቀ መዛሙርትን በቅድስና ስለ ወለደባት ነው።
ስለዚህም ዛሬም ድረስ "አባ ዳንኤል ዘደብረ ሲሐት" ተብሎ ሲጠራ ይኖራል። ሌላኛው ስሙ ደግሞ "ዘገዳመ አስቄጥስ" ይሰኛል። ገዳመ አስቄጥስ የታላቁ ቅዱስ መቃርስ ርስት ሲሆን በዓለም በስፋትም ብዙ ቅዱሳንን በማፍራትም አንደኛ የሆነ ገዳም ነው።
በዚህ ገዳም ላይ አበ ምኔት ሆኖ የሚሾሙ አበው ሁሌም የብቃት መዓርግ ላይ የደረሱ ሲሆኑ ክብራቸው ከፓትርያርክ በላይ ነው። አባ ዳንኤልም ከብዙ የቅድስና ዓመታት በኋላ በአስቄጥስ ገዳም አበ ምኔት ሆኖ ተሹሞ እልፍ አእላፍ መነኮሳትን በጽድቅ መንገድ መርቷል።
ቅዱሱ ከትጋቱ የተነሳ ለምግብና ለእንቅልፍ ጊዜ አልነበረውም። ቀን ቀን መነኮሳቱን ሲናዝዝ፣ ድውያንን ሲፈውስ፣ ሥርዓተ ገዳምን ሲቆጣጠር ይውላል። ልክ ሲመሽ ጭው ወዳለውና ስውራን ወደ ሚገኙበት በርሃ ይወጣል።
በዚያም ሙሉውን ሌሊት የተሰወሩ አባቶችን ሲፈልግ ያድር ነበር። በዚህም ምክንያት የብዙ ስውራንን ገድል የጻፈ ሲሆን ባረፉ ጊዜም ገንዞ በመቅበር በረከታቸውን ተሳትፏል። ታላቅ ሙያንም ፈጽሟል።
እርሱ ገንዞ ቀብሮ ዜናቸውን ከጻፈላቸው ሥውራን ቅዱሳንም እንደ አብነት እስራኤላዊቷን ቅድስት ዓመተ ክርስቶስን (ለሠላሳ ስምንት ዓመት ራቁቷን በሥውር የኖረች) እና ቅድስት በጥሪቃ ንግሥትን (መንግሥቷን ትታ በሥውር የኖረች ናት።) መጥቀስ እንችላለን።
ከዚህ ባለፈም አባ ዳንኤል በሰው ዘንድ የተናቁትንም ማክበርን ያውቅበታል። ለምሳሌ በሴቶች ገዳም "እብድ" ናት ተብላ በበር የተጣለችውን ቅድስት አናሲማን፣ በእስክንድርያ ከተማ ሊቀ ጳጳሳቱ ሳይቀር "እብድ" ነው ብለው የናቁትን ቅዱስ ምሕርካን እብድ ሳይሆኑ ራሳቸውን የሠወሩ ቅዱሳን መሆናቸውን ገልጧል።
አባ ዳንኤል ሐዋርያዊም ነበር። በጊዜው ጦማረ ልዮን የሚባል የኑፋቄ ደብዳቤ ይላክ ነበርና ለዚህ ኬልቄዶናዊ ኑፋቄ በትጋት ምላሽ ይሰጥ ነበር። አንድ ቀንም በንጉሥ ትዕዛዝ ኑፋቄው በእርሱ ገዳም ሊነበብ ሲል ቅዱሱ ከወታ...
BY ተዋህዶ ኢትዮጵያ-TEWAHIDO ETHIOPIA
Share with your friend now:
tgoop.com/TEWAHIDOETHIOPIA/337