tgoop.com/TIBEBnegni/2492
Last Update:
📍"እሴት ያለው ህይወት ኑር"
❤️ ተዘጋጀህም አልተዘጋጀህም ጉዳዩ አንድ ቀን ያበቃል።ከእንግዲህ የምትወጣ ፀሀይ አትኖርም። ደቂቃዎችም፤ ሰዓቶችም፤ቀኖችም የሉም።
🔷እነዚያ የሰበሰብካቸው ነገሮች ሁሉ የወደድካቸውም ይሁኑ የረሳሀቸው ወደ ሌላ ሰው ይተላለፋሉ።ሀብትህ፣ዝናህ እና ዓለማዊ ሀያልነትህ መንምኖ እዚህ ግባ የማይባል ይሆናል።ምን ምን የግልህ እንደነበረ ወይም ምን ምን ዕዳ ሊከፈል ይገባ እንድነበረ ልዩነት አያመጣም።
💙ቂምህ ፣አትንኩኝ ባይነትህ፣ኩምታዎችህና ቅናትህ ጨርሰው ይጠፋሉ። እንደዚሁም ተስፋዎችህ፣ፅኑ ፍላጎቶችህ፣ዕቅዶችህ፣ የስራ ዝርዝሮችህ ጊዜ ያለፈባቸው ይሆናሉ።በፊት በጣም አንገብጋቢ ይመስሉህ የነበሩት ድሎችና ሽንፈቶችም በንነው ይጠፋሉ።ከየት መጣህ? ደስተኛ ወይስ መከረኛ ኑሮ አሳለፍክ፤በመጨረሻ ልዩነት አይኖረውም።መልከ ቀና ነበርክ ወይስ ጥበበኛ ልዩነት አያመጣም። ፆታህና የቆዳህ ቀለም ሳይቀር እዚህ ግባ የማይባል ኢምንት ጉዳይ ሆኖ ይቀራል።
📍እንግዲያው (ላንተ) ልዩነት የሚያመጣው ምንድን ነው? የኖርካቸው ቀናት፣ የእሴታቸው ልክ እንደምን ሊመዘን ይችላል?ለወደፊት ዋጋ የሚኖረው ስኬታማ ውጤት ሳይሆን በሰዎች ልቦና የሚጠራቀምልህ እሴትህ ነው። ልዩነት የሚያመጣው ምን ምን እንደገዛህ አይደለም ለሰዎች ምን ምን እንዳበረከትክ ነው እንጂ
በመጨረሻ ልዩነት የሚያመጣው ችሎታህ ሳይሆን ጠባይህ ነው።
🔷ስንቶች መሰናበትህን እንዳወቁ ሳይሆን ፣ ለስንቶች አንተን
ያለማግኘት የሁልጊዜ እጦት እንደሚሆንባቸው ነው፡፡ የሚወዱህ
ሰዎች ውስጥ የሚቀረው ለምን ያህል ጊዜ እንደሚያስታውሱህአይደለም ፤ትውስታዎችህም አይደሉም ፤ እነማንን ለምን እንደምትታወሳቸው እንጂ::
📍እሴት ያለው ሕይወት መኖር ባጋጣሚ አይመጣም ፡፡ሁኔታዎች
የሚወስኑት ጉዳይ ሳይሆን፣ አንተ ራስህ መርጠህ የምትፈፅመው
ነው፡፡››
📖 ማስታወሻ ገፅ 223
✍ ስብሃት ገ/እግዚኣብሄር
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
ሌሎች እንዲማሩ ምክንያት እንሁን
እናካፍል ፡፡
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
BY ሰው መሆን...
Share with your friend now:
tgoop.com/TIBEBnegni/2492