tgoop.com/TIBEBnegni/2501
Last Update:
💙ይህች ምድር ያንተናትና ተስፋ አትቁረጥ!
💜አንተ ልዩ ሆነህ የተፈጠርከው በፈጣሪ ፈቃድ ነውና ምንም ሳታማርር ህይወትህን ኑራት። ባለህ እየኮራህ ህይወትህን አጣፍጣት። ሰዎችን ለመምሰልና የነሱ ግልባጭ ለመሆን አትጣር።
✨የአንተ ንጹህና እጹብ ድንቅ ያልታየ ማንነት የሚወጣው በራስህ መተማመን፣መኩራትና እራስህን ማክበር ስትጀምር ነውና። በዙሪያህ ምንም አይነት ዝነኞች ትልቅና ልዩ ሰዎች ቢኖሩም በአንተ ውስጥ ያለው ልዩ ስጦታ ግን ከሁሉም ይለያል!
ይልቃል! ይበልጣል!
✨እነዚህ ልዩ ያልካቸው ሰዎች በአፈጣጠራቸው የተለዩ ሆነው ሳይሆን ይህንን ምስጢር ስላወቁትና ስለተገበሩት ብቻ ነው ከሌሎች ተለይተው አሁን ያሉበት የደረሱት። አንተም እንደነሱ የደረሱበት እንደውም ከነሱበላይ መስጠት መስራትና ማበርከት ከፈለክ ወደ እኔ ጠጋ በልና ጆሮህን ስጠኝ እኔም ሚስጢሩን ሹክ ልበልህ። "እራስህን ሁን! እራስህን አክብር! እራስህን ውደድ!" እራስህን እንደማትወደው እንደማታከብረውና እንደማትሆነው ስታስብ ከማይመረመረው ከፈጣሪ እውቀት ጋ እየተደራደርክ ነውና ሁለቴ አስብ።
☯ሰዎች ከሚሉህ በላይም ፈጣሪ ሲፈጥርህም ምክንያት አለውና የሌለህን ትተህ ያለህን ዋጋ ስጥ። በሌለህ ነገር ስለምታገኘው ሳይሆን ባለህ ነገር ስለምትለውጠው ተመራመር። በሌለህና ባልተጨበጠው ነገር ትልቅ ነገር ለመስጠት ከማሰብ ይልቅ ባለህ ነገር ትንሽ ነገር ለመስጠት ሞክር። ያኔ አንተ ውስጥ የተደበቀው ከሌሎች የተለየው ድንቅ ፍልቃቂ ማበብ ይጀምራል።
✨ብርሀንህ በዓለም ሁሉ ይሰፋል። ስምህም በሰዎች ልብ ውስጥ ይነግሳል።በምድር ላይ በኖርክበት ዘመን ሁሉ ዘመንህ የጣፈጠ ይሆንልሀል።
💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚
ሌሎች እንዲማሩ እና እንዲለወጡ ምክንያት እንሁን ፡፡በፍቅር እንኑር ፡፡
💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
BY ሰው መሆን...
Share with your friend now:
tgoop.com/TIBEBnegni/2501