tgoop.com/TIBEBnegni/2503
Create:
Last Update:
Last Update:
💥💥አይዞሽ ኢትዮጵያዬ💥💥
አንች ትልቅ ሀገር
በአባቶቸ አጥንት
በአባቶቸ ደም ፀንተሽ የቆየሽው ፡፡
ምን? አድርገሽ ይሆን
በአጥፊዎች ሰበዝ የምትታመሽው ።
በምን ?ሀጢአትሽ ነው
ወልደሽ ባሳደግሽ የምትነከሽው::
የበረከት ምድር: የታሪክ ማህደር
ኤትዮጵያ ሀገሬ ::
ስልጣን አገኝ ብለው
በእንባ ያራጬሽ
በደም ያጨቀዩሽ ገለውሻል ዛሬ::
አይዞሽ እናታለም :
አይታለፍ የለም ይሄም ጊዜ ያልፋል ::
ከችግርሽ በላይ
ባርኮ የፈጠረሽ ፈጣሪ ይገዝፋል ::
አይዞሽ ኢትዮጵያየ
ሳቅሽን ያጠፋው
ለቅሶሽን ያበዛው
መከራሸ ቢያመኝም ::
ይሁን ቻል አድርጊው
ከመከራው በፊት ትንሳኤ አይገኝም::
01/03/13
Samuel Adane
@Sam2127
💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚
ሌሎች እንዲለወጡ ምክንያት እንሁን
፡በፍቅር እንኑር
💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
BY ሰው መሆን...
Share with your friend now:
tgoop.com/TIBEBnegni/2503