Telegram Web
Forwarded from ኢዮርቅስ (Z Man Tad)
መሞት ሲያምረኝ ..ሞት ይወደድ እና ንሮ ዝፍጥ ይላል ፤
መኖር ሲጣፍጠኝ ፥ ኑሮ ይወደድ እና ሞት ጥንቡን ይጥላል ፡፡
እድሌ ነው መሰል ፥ ይነቅዛል የያዝሁት ፤
ደግሞ ሌላ ጊዜ ፥ ይገሽባል የጣልሁት ፤
ራሴን አጠሁት ፥ ወድቆ በሚነሳ ለክቸ እያየሁት ፡፡

ርካሹ እኔ......ውዱ እኔ......!!!

@eyorkis
@eyorkis
💙መስታወትህ ወዴት አለ?

💡አንዳንድ ሰው ራሱን አያይም፣ ራሱን ለመፈተሽ ጊዜ አይወስድም። አንዳንድ ሰው የሌሎች ድካም፣ ጥፋት፣ ስህተት እንጂ የራሱ ድክመት አይታየውም።ይህ ሰው የሌሎች ሰዎች መልካም ገጽ፣ በጎ ሃሳብ፣ ጥሩ ሰው መሆን አይታየውም።ይህ መልካም ፀባይ አይደለም።

ሁሌም ራሳችንን እየፈተሽን ስህተታችንን እናርም።

💎ሰው ሁሌም የሚፈልገው ነገር በዝቶ ይታየዋል። ጉዳዩ በዝቶ ሳይሆን ነገሩ የትኩረት ጉዳይ ነው። የሰዎች ድክመት ላይ የሚያተኩር ድክመታቸው በዝቶ ይታየዋል። የሰዎች መልካም ጎን ላይ የሚያተኩር መልካምነታቸው በዝቶ ይታየዋል። ጉዳዩ ያለው ከትኩረትህ ላይ ነው። ታድያ የትኩረት ነጥብህን መምረጥ ያንተ ፋንታ ነው። በጎው ላይ አተኩር!

💡አንተ ግን ሁሌም ከሰዎች ውስጥ መልካም ገጻቸውን ፈልገህ አንጥረህ ተመልከት፣ ጥሩነታቸውን በማድነቅ ገንባ፣ ከአፍህ መልካም ቃል ይውጣ፤ መልካም ዘር ዝራ።

💎ሰው የሚዘራውን ያጭዳልና መልካም ዘር ዝራ። ልብ በል! ክፋት፣ ጥላቻ፣ ቂም፣ ቅሬታ አይጠቅሙህም። ይልቅስ ይጎዱሃል፣ በሽታ ያመጡብሃል፣ ወደታች ይስቡሃል። ግዴለም ሁሌም ፍቅር ዝራ፣ ለሰዎች መልካም ልብ ይኑርህ።

💡የከፈትከው አካውንት ሳይዘጋ፣ ሂሳብህን ሳታወራርድ ምድራዊ ቆይታህ አይጠናቀቅም። የዘራሃትን ሁሉ ታጭዳታለህ። እናስ ጥሩ ዘር ብትዘራ አይሻልም?

💎ጥሩ ዘር፣ ሳንካ አልባ፣ ጉድለት የሌለበት ዘር ነው። ይህንን ዘር በውስጥህ ዝራ። መስታወት ፈልግና ራስህን እይ፤ ሃሳብህን አጥራ፣ ንግግርህን መርምር፣ ራስህን በመልካም ዘር አንጽ።

መልካም ዘር ዘርተን መልካም ምርት እንፈስ።

💙ፍቅር የዘራ ፍቅር ያገኝል። ጥላቻ የዘራም ጥላቻ ያመርታል። ቅሬታ የተከለ ቅሬታ ይለቅማል። መልካም ዘር የዘራ መልካም ፍሬ ያጭዳል።

💎ማንም ምንም ቢልም፣ ሁሌ በየጠዋቱ በመስታወት ራሳችንን እንደምናይ እና ጉድለታችንን እንደምናርም ሁሉ ራሳችንን በየዕለቱ እየፈተሽን በመልካም ዘር እናንጽ።

📍ሰው የዘራውን ያጭዳልና መልካም ዘር በውስጥህ ዝራ!

ራሳችንን በበጎ እናንጽ! Invest on yourself!

Toughe G. kebede

ውብ አሁን❤️
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
ግን አንድ ሰው አለ

እርጅና ሲጫንሽ
እድሜ ተጠራቅሞ ፤ እንዳስም ሲያፍንሽ
ሽበት እንደ አመዳይ
በጭንቅላትሽ ላይ
በድንገት ሲፈላ
ያይንሽ ከረጢቱ ፤ በእንቅልፍሽ ሲሞላ
ምድጃ ዳር ሆነሽ ፤
መጻፍሽን ከፍተሽ
ያለፈውን ዘመን ፤ገልጠሽ ስታነቢ
የኔን ቃል አስቢ ፤
ስንቶች አፈቀሩት፤ በሀቅ በይስሙላ
የገጽሽን አቦል፤ የውበትሽን አፍላ
ግን አንድ ሰው አለ፤
ከሌሎች ወንዶች ጋር፤ ያልተመሳሰለ
በእጹብ ድንቋ ፤ ነፍስሽ ፍቅር የነደደ
የመልክሽ ጸደይ ሲያልፍ
ልክ እንደ መስቀል ወፍ
ጥሎሽ ያልነጎደ፡፡


[ በእዉቀቱ ስዩም ]

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
⚡️ችግር!
የእምቅ ብቃትህ ብቸኛ መውጫው ቀዳዳ!

“ያልገደለኝ ነገር ሁሉ ያጠነክረኛል” ይላል ምንጩ ያልታወቀ የከረመ አባባል፡፡ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለማለፍ ፈቃደኛ እስካልሆንክ ድረስ የብቃትህን ጥግ ሳታውቀው ታልፋለህ፡፡ የሰው አቅሙና ብቃቱ የሚወጣው በሚያልፍበት አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ነው፡፡

🌗ብዙ ሰዎች አሁን ከድሮው ሕይወታቸው የተሻለ ኑሮን እየኖሩና የአሁኑ ዘመን ከበፊቱ በብዙ እጥፍ እየበለጠ እንኳን፣ “ድሮ ቀረ!” ሲሉ የሚደመጡት የበፊቱ አስቸጋሪ ዘመን በጊዜው ፈትኗቸው ቢሆንም እንኳን ተደብቆ የነበረውን እምቅ ብቃታቸውንና ድብቅ ብርታታቸውን እንዳወጣው ያውቃሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች ዛሬ የሆኑትን የሆኑት፣ ዛሬ የሚችሉትን የቻሉት፣ ዛሬ የገባቸው ነገር የገባቸው . . . ከእነዚያ ፈታኝ፣ ነገር ግን ድንቅ አመታት የተነሳ እንደሆነ ውስጣቸው ያውቀዋል፡፡

💫አንዳንድ ሰዎች አስቸጋሪ ሁኔታዎች ሲገጥማቸው የበለጠ እያዳበሩ የሚሄዱት “ችሎታ” ከዚያ ሁኔታ፣ ስፍራ፣ ግንኑነት … የመሸሽን ችሎታ ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ ግሩም የሆኑ “የሽሽት ባለሞያዎች” ወደመሆን ያድጋሉ፡፡ የስራና የትምህርት ዘርፍ ከበድ ሲላቸው እየለወጡ ውስጣቸው ግን ሳይለወጥ፣ የትዳር ሕይወት ችግር ይዞ ሲመጣ የትዳር ጓደኛን እየቀየሩ ባሪያቸው ግን ሳይቀየር፣ መንደር፣ ሰፈርና ሃገር አልመች ሲላቸው እየለወጡ አመለካከታቸው ግን ሳይለወጥ እንደነበሩ ይኖራሉ፡፡

🌗ምን ያህል አስገራሚ ብቃት እንዳለህ ማንም ሰው አያውቀውም፣ አንተው ራስህ እንኳን በቅጡ አታውቀውም፡፡ ይህንን ብቃትህን የሚያወጣው ጉዳይ “ችግር” ይባላል፡፡ ይህ ችግር የሚባል ነገር በሁለት ይከፈላል፣ 1) አስፈላጊ ችግርና፣ 2) አላስፈላጊ ችግር፡፡

💫አስፈላጊው ችግር የተለመደውን የሕይወት መስክ ይዘህ ስትጓዝ በተመሳሳይ ሁኔታ የሚያልፍ ሰው ሁሉ የሚጋራው ችግር ነው፡፡ ይህንን ችግር ከመሸሽ ይልቅ ስትጋፈጠው የውስጥህ ብቁ ማንነት ይወጣል፡፡

🌗አላስፈላጊ ችግር በእኛው የጥበብ ጉድለትና የተሳሳተ ውሳኔ የሚመጣው አይነት ችግር ነው፡፡ ይህን ችግር ሽሸው፣ እንዳይከሰትም የምትችለውን ሁሉ አድርግ፡፡ ሆኖም፣ አንዴ ከተከሰተ ግን ከስህተትህ ተማር፣ ውጤቱንም ተጋፈጥ እንጂ ለመደባበቅና ለመሸሽ አትሞክር፡፡

ዛሬ የምታልፍበት ችግር ነገ በብዙ ብቃት የምትወጣበት አስገራሚ እድል እንጂ ዛሬ የምትደክምበት ሁኔታ እንዲሆን አትፍቀድለት፡፡


@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
📍"እሴት ያለው ህይወት ኑር"

❤️ ተዘጋጀህም አልተዘጋጀህም ጉዳዩ አንድ ቀን ያበቃል።ከእንግዲህ የምትወጣ ፀሀይ አትኖርም። ደቂቃዎችም፤ ሰዓቶችም፤ቀኖችም የሉም።

🔷እነዚያ የሰበሰብካቸው ነገሮች ሁሉ የወደድካቸውም ይሁኑ የረሳሀቸው ወደ ሌላ ሰው ይተላለፋሉ።ሀብትህ፣ዝናህ እና ዓለማዊ ሀያልነትህ መንምኖ እዚህ ግባ የማይባል ይሆናል።ምን ምን የግልህ እንደነበረ ወይም ምን ምን ዕዳ ሊከፈል ይገባ እንድነበረ ልዩነት አያመጣም።

💙ቂምህ ፣አትንኩኝ ባይነትህ፣ኩምታዎችህና ቅናትህ ጨርሰው ይጠፋሉ። እንደዚሁም ተስፋዎችህ፣ፅኑ ፍላጎቶችህ፣ዕቅዶችህ፣ የስራ ዝርዝሮችህ ጊዜ ያለፈባቸው ይሆናሉ።በፊት በጣም አንገብጋቢ ይመስሉህ የነበሩት ድሎችና ሽንፈቶችም በንነው ይጠፋሉ።ከየት መጣህ? ደስተኛ ወይስ መከረኛ ኑሮ አሳለፍክ፤በመጨረሻ ልዩነት አይኖረውም።መልከ ቀና ነበርክ ወይስ ጥበበኛ ልዩነት አያመጣም። ፆታህና የቆዳህ ቀለም ሳይቀር እዚህ ግባ የማይባል ኢምንት ጉዳይ ሆኖ ይቀራል።

📍እንግዲያው (ላንተ) ልዩነት የሚያመጣው ምንድን ነው? የኖርካቸው ቀናት፣ የእሴታቸው ልክ እንደምን ሊመዘን ይችላል?ለወደፊት ዋጋ የሚኖረው ስኬታማ ውጤት ሳይሆን በሰዎች ልቦና የሚጠራቀምልህ እሴትህ ነው። ልዩነት የሚያመጣው ምን ምን እንደገዛህ አይደለም ለሰዎች ምን ምን እንዳበረከትክ ነው እንጂ
በመጨረሻ ልዩነት የሚያመጣው ችሎታህ ሳይሆን ጠባይህ ነው።

🔷ስንቶች መሰናበትህን እንዳወቁ ሳይሆን ፣ ለስንቶች አንተን
ያለማግኘት የሁልጊዜ እጦት እንደሚሆንባቸው ነው፡፡ የሚወዱህ
ሰዎች ውስጥ የሚቀረው ለምን ያህል ጊዜ እንደሚያስታውሱህአይደለም ፤ትውስታዎችህም አይደሉም ፤ እነማንን ለምን እንደምትታወሳቸው እንጂ::

📍እሴት ያለው ሕይወት መኖር ባጋጣሚ አይመጣም ፡፡ሁኔታዎች
የሚወስኑት ጉዳይ ሳይሆን፣ አንተ ራስህ መርጠህ የምትፈፅመው
ነው፡፡››



📖 ማስታወሻ ገፅ 223
ስብሃት ገ/እግዚኣብሄር
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️


ሌሎች እንዲማሩ ምክንያት እንሁን
እናካፍል ፡፡

@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
❤️You can't change the contents of life..
Yes you can always change the context..
Face it with cool..calm composure...
Without reacting or rebounding..
Discreetly giving your best.,.
Leaving the rest..going with the flow...
Till it blissfully reaches the shore...

🌘የህይወት ለውጦችን ከመቃወም ይልቅ ራስን አስተጋብሮ መራመድ ጥበብ ነው ። ሕይወት ካንተ ውጪ ሳትሆን ከእናንተ ጋር ትሁን፡፡

💫 ራስህን ስጋት አታድርግ፡፡ መልካም ሰው ማንንም አያማርርም ። ያለፍቅር ሕይወት ዋጋ የለውም ፡፡ ፍቅር የሕይወት ውሃ ነው ፣ ፍቅርን የሚያቅ ሰው የነፍስ መብራት ነው። ሁሉም ነገር እና ሁሉም ሰው ከማይታዩ ብዙ ህብረቶች ጋር የተሳሰረ ነው።

☀️ምን ዓይነት ፍቅርን መፈለግ እንዳለብህ አትጠይቅ…የምስራቃዊ ወይም ምዕራባዊ እያልክ ክፍፍል አትፍጠር፣ ያንተ ክፍፍሎች ወደ ብዙ መከፋፈል ከማምራት በቀር አንተን አይቀይሩህም፡፡ ፍቅር ስያሜ የለውም ፣ ትርጓሜ የለውም፡፡ንፁህ እና ቀላል ነው።

💫የሰዎችን ልብ አትስበር ፡፡ከአንተ ይልቅ ደካማ እንደሆኑ አርገህ ቁልቁል አትመልከት፡፡በአንደኛው የዓለም ክፍል ውስጥ ያለ ሀዘን መላውን ዓለም ሊያሰቃይ ይችላል ፣በዛው ልክ ደግሞ የአንድ ሰው ደስታ እና ፈገግታ መላውን ዓለም ፈገግ ሊያደርገው ይችላል።

☀️ አብዛኛዎቹ ግጭቶች እና ውጥረቶች በቋንቋ ምክንያት የሚከሰቱ ናቸው።ለቃላቶች በጣም ትኩረት አትስጥ ፣ በፍቅር ሀገር ውስጥ ቋንቋ የራሱ የሆነ ቦታ የለውም፣ ፍቅር ውብ ዝምታ ነው ፡፡

ሸምስ ታብሪዝ

❤️You can't change the contents of life..
Yes you can always change the context..
Face it with cool..calm composure...
Without reacting or rebounding..
Discreetly giving your best.,.
Leaving the rest..going with the flow...
Till it blissfully reaches the shore...

🌘የህይወት ለውጦችን ከመቃወም ይልቅ ራስን አስተጋብሮ መራመድ ጥበብ ነው ። ሕይወት ካንተ ውጪ ሳትሆን ከእናንተ ጋር ትሁን፡፡

💫 ራስህን ስጋት አታድርግ፡፡ መልካም ሰው ማንንም አያማርርም ። ያለፍቅር ሕይወት ዋጋ የለውም ፡፡ ፍቅር የሕይወት ውሃ ነው ፣ ፍቅርን የሚያቅ ሰው የነፍስ መብራት ነው። ሁሉም ነገር እና ሁሉም ሰው ከማይታዩ ብዙ ህብረቶች ጋር የተሳሰረ ነው።

☀️ምን ዓይነት ፍቅርን መፈለግ እንዳለብህ አትጠይቅ…የምስራቃዊ ወይም ምዕራባዊ እያልክ ክፍፍል አትፍጠር፣ ያንተ ክፍፍሎች ወደ ብዙ መከፋፈል ከማምራት በቀር አንተን አይቀይሩህም፡፡ ፍቅር ስያሜ የለውም ፣ ትርጓሜ የለውም፡፡ንፁህ እና ቀላል ነው።

💫የሰዎችን ልብ አትስበር ፡፡ከአንተ ይልቅ ደካማ እንደሆኑ አርገህ ቁልቁል አትመልከት፡፡በአንደኛው የዓለም ክፍል ውስጥ ያለ ሀዘን መላውን ዓለም ሊያሰቃይ ይችላል ፣በዛው ልክ ደግሞ የአንድ ሰው ደስታ እና ፈገግታ መላውን ዓለም ፈገግ ሊያደርገው ይችላል።

☀️ አብዛኛዎቹ ግጭቶች እና ውጥረቶች በቋንቋ ምክንያት የሚከሰቱ ናቸው።ለቃላቶች በጣም ትኩረት አትስጥ ፣ በፍቅር ሀገር ውስጥ ቋንቋ የራሱ የሆነ ቦታ የለውም፣ ፍቅር ውብ ዝምታ ነው ፡፡

ሸምስ ታብሪዝ

ሌሎች እንዲማሩ ምክንያት እንሁን፡፡
እናካፍል።
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
የቀበሮ ፀሎት
(ታገል ሰይፉ)
------
እባክህ አምላኬ- ብትሬን ቀባና
እኔም ልወዝወዘው-የሙሴን ጎዳና
ያላንዳች ፍርሃት-ያለምንም ችግር
ባህሩን ከፍዬ- ህዝቤን እንዳሻግር፡፡
*
አቤት የኔ ጌታ ይህም አያረካም
በቃልህ ታምኜ -ከሆንኩልህ መልካም
ለእኔም ፍቀድልኝ-ያብራምን ምልክት
ከምድር አሸዋ-ዘሬ እንዲበረክት፡፡
*
አቤቱ ምን ልሁን-ይህም አልጠቀመኝ
እስቲ እንደ ዮናስ-ህዝብ ፊት አቁመኝ
*
ትንቢቴን ሰምቶልኝ-ሀገር ይተራመስ
ሰው እህል ይጡም-ከብቱም ሳር አይቅመስ፡፡
ይህም አያረካም-ይልቅ እንደዳዊት
አንተን በሚፈራ-ብዙ ሺህ ሠራዊት
ዙፋኔ ተከቦ-በደስታ እንዳመልክህ
የዚህን ሰው ኮከብ -አውጣልኝ እባክህ
*
አደራህን ታዲያ- ጭንቅ አትወድም ነፍሴ
ልመናዬን ሰምተህ-ካደረግከኝ ሙሴ
መከራውን ማረኝ-ያርባ ዓመት ስደቱን
በሲና በረሃ-መራብ መጠማቱን፡፡
*
ነቢዩ ዮናስን -አርገህም ስትፈጥረኝ
የባህሩን ፍዳ- ያሳውን ሆድ ማረኝ፡፡
*
አብረሃምን ሆኜም-በደስታ ሳመልክህ
ልጅህን እረደው-አትበለኝ እባክህ፡፡
***
የዳዊትም ኮከብ-በኔ ላይ ሲወጣ
እባክህ አምላኬ -ጎልያድ አይምጣ፡፡

❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️

@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
💚
❤️ፍቅርና ጊዜ

💛ሁሉም አይነት ስሜቶች የሚኖሩበት አንድ ደሴት ነበር፡፡ የደስታ ስሜት፣የመከፋት ስሜት፣ እውቀት እና ሌሎቹ ስሜቶች ፍቅርን ጨምሮ፡፡ አንድ ቀን ታዲያ ደሴቱ ሊሰምጥ እንደሆነና ሁላቸውም ስሜቶች ሊያመልጡ የሚችሉበትን ጀልባ መስራት እንዲችሉ አዋጅ ተነገረ፡፡ በዚህም መሠረት ሁሉም ስሜቶች ጀልባቸውን ሲሰሩ ፍቅር ግን ደሴቱ እስኪ ሰምጥ ድረስ ጀልባ አልሰራም ነበርና ከሊሎቹ ስሜቶች እገዛ ለመጠየቅ ወሰነ፡፡

💙ሀብታምነት የሚባለው ስሜት በፍቅር በኩል ሲያልፍ “ሀብታም ሆይ ከአንተ ጋ ይዘኸኝ ልትሻገር ትችላለህ?” አለው ፍቅር፡፡ “አይሆንም፡፡ አልችልም በጀልባየ ውስጥ በርካታ ወርቅና መዳብ የያዝኩ በመሆኑ ለአንተ የሚሆን ቦታ የለኝም” ሲል ጥሎት ሄደ፡፡ ፍቅር አቶ ስግብግብን ሲያልፍ ተመለከተውና እንዲረዳው ጠየቀው፡፡ “አልችልም አቶ ፍቅር ጀልባየን ታበላሽብኛለህ አይሆንም ብሎ” ትቶት ሄደ፡፡ አቶ መከፋትን በቅርብ አገኘውና አሁንም ፍቅር አብሮ እንዲያሻግረው ጠየቀው፡፡ “ኦው! ፍቅር አዝናለሁ እኔ ብቻየን ነው መሆን የምፈልገው፡፡” ብሎ አሰናበተው፡፡ ደስታም ፍቅርን አልፎት እየሄደ በጣም በፈንጠዝያ ስሜት ላይ ስለነበር ፍቅር ሲጠራውም መስማት አልቻለም፡፡

💜ፍቅር ትዕግስቱን እያጣ በመከፋት ስሜት እንዳለ ባጋጣሚ “ፍቅር ና እኔ እወስድሃለሁ” የሚል ድምጽ ሰምቶ ሲዞር የተባረከ አዛወንት ነበር፡፡ “ጊዜው ነው” ወዳጀ ፍቅር ሲል እውቀት የተባለው ስሜት መለሰ፡፡

📍 “ጊዜ ማለት!?” ፍቅር በመደነቅ ጠየቀው “ነገር ግን ለምን ጊዜው ሊረዳኝ ቻለ?” እውቀት ፈገግ እያለ ምክንያቱም “የፍቅርን ዋጋ መረዳት የሚችለው ጊዜ ነው፡፡” ሲል መልስ ሰጠው፡፡

❤️በዚህ ዓለም ፍቅር ብቻ ነው ሠላምንና ታላቅ ደስታን ሊያመጣ የሚችለው፡፡ ባለጸጎች ስንሆን ፍቅርን ካራቅነው፣ ተፈላጊነታችን ሲጨምር ፍቅርን ከዘነጋን፣ ምናልባትም በደስታና በሀዘን ስሜት ስንሆንም ፍቅር ካጣን የማስተዋል ጊዜው ሲደርስ ነው የፍቅር ጥፍጥና የሚታወቀን፡፡

💞የልባችን ብርሀን የሚበራው በፍቅር ነውና ሁሌም ፍቅርን እናስቀድም፡፡

ምንጭ፡ Lovely Time.. Or Timely Love
❤️💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💙
ሌሎችን እናስተምር ።በፍቅር እንኑር!!!
እናካፍል
💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙

@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
It is never too late to do the right thing.And knowing what is right is not that difficult.
Just use your common sense.

❤️ልብህ ያሰበውን ጥሩ ነገር ከመፈጸም አትቦዝን። ሃሳቡ በውስጥህ አርጅቶ እስኪሞት አትጠብቅ። ሰዎች ምን ይሉኝ ብለህ አትፍራ። ሰዎች ብትሠራም ባትሠራም የሆነ ነገር ማለታቸው አይቀርም። ብቻ መጠንቀቅ ያለብህ አንድ ነገር አለ። ያም ነገር ድርጊትህ በጎ መሆን አለመሆኑን ማረጋገጥ ላይ ነው።

♦️ድርጊትህ ጥሩ መሆኑን ካመንክበት ለመተግበር ተጣጣር። ድርጊትህ ሙሉ በሙሉ ባይሳካ እንኳ በመሞከርህ ብቻ የህሊና እረፍት ታገኛለህ። በተከታታይ ከሠራህ ደግሞ እየሠራህ ማሻሻልህ አይቀርም።

ጥሩ ነገር ለማድረግ ምቹ ጊዜ አትጠብቅ። ምቹው ጊዜ ሃሳቡ ወደ ጭንቅላትህ የመጣበት ጊዜ ነው።

📍መማር ባለብህ ጊዜ ተማር፣ መሥራት ባለብህ ጊዜ ሥራ፣ መዝፈን ባለብህ ጊዜ ዝፈን፣ መዘመር ባለብህ ጊዜ ዘምር፣ መጻፍ ባለብህ ጊዜ ጻፍ፣ ማረፍ ባለብህ ጊዜ እረፍ።

ለማንኛውም ደመ-ነፍስህ የሚነግርህን ነገር ቸል አትበል።

Toughe G. kebede

💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚
ሌሎች እንዲማሩና እንዲለወጡ ምክንያት እንሁን፡፡ በፍቅር እንኑር !!!
💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙




@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
🕰ሰዎች ስለወቀሱን የማይርድ፤ ስለኮነኑን የማይወድቅ፤ ስለፈረዱብን የማይሞት፤ ስለጠሉን የማይፈራ፤ ስለተዉን የማይደክም መንፈስ በውስጣችን ሊኖር ግድ ይለናል። ከፈጣሪ የተሰጠን እውነተኛው ማንነታች ይህ ነው። ብዙዎቻችን ደካማ ስለተባልን ደክመናል፤ ሃጥያተኛ ስለተባልን ቆሽሸናል፤ ወንጀለኛ ስለተባልን ታስረናል።የሌሎች ሰዎች አስተያየትና መስፈርት ከእውነተኛው ማንነታችን አርቆናል፤ ሰላም ካለበት ስፍራ አውጥቶ የይሉኝታ ሰፈር ኗሪ አድርጎናል።

እውነት ነው ማናችንም ከተጽዕኖ ማምለጥ አንችልም። በመልካምም ሆነ በመጥፎ ሞርደ በየእለቱ መሞረዳችን አይቀርም። ማንነታችን የቤተሰባችን፤ የጓደኞቻችን፤ የአካባቢያችን የባህልና የእምነታችን ውጤት ነው። ሁሉም ነገራችን ላይ የአካባቢያችን ተጽዕኖ ያርፍበታል፤ ልክ ጣሪያ እንደሌለው ቤት በውጪ ያለው ሙቀትና ቅዝቃዜ፤ ዝናብና ንፋሱ፤ አቧራና ሽታው የራሳቸውን አሻራ ያኖሩበታል። በሌሎች ሰዎች ጉንፋን እኛ እናስነጥሳለን፤ በማህበረሰብ በሽታ እኛ የአልጋ ቁራኛ እንሆናለን፤ በሌሎች የእምነት ጥበት እኛ እንጨነቃለን፤። ለዚህ ነው ደስታችን በብዙ ነገሮች ተጽዕኖ ስር የሚወድቀው።

🕰ብዙ ውጫዊ ነገሮች አስደሳች ቢሆኑም ከጊዜ ጋር የተሳሰሩና ሃላፊ ናቸው። ዛሬ ያስደሰተን ጓደኛ ነገ ላይኖር ይችላል፤ ዛሬ ያጌጥንበት ውበት ነገ ይረግፋል፤ ዛሬ የተመካንበት አስተሳሰብ ነገ በቆመበት አይጸናም። ከውጪ የምናገኘው ማንኛውም አይነት ደስታ በመጣበት እግሩ ጥሎን መሄዱ አይቀርም። ከዛም አልፎ ዋጋ ያስከፍለናል። ከጊዜ ጋር የማይለዋወጥ ደስታን ለማግኘት ብቸኛ መፍትሄው ደስታና ሰላምን በውስጣችን መፈለግ ነው። እንደ ኩሬ ውሃ ያነሰች፤ እንደ ኩራዝ መብራት የቀጨጨች፤ እንደ ሰናፍጭ ቅንጣት የደቀቀችም ብትሆንም እንኳን ውስጣዊ ደስታን በልባችን መትከል ነው። ይህ ነው ማንም ሊነካውና ሊደፍረው የማይገባው ስፍራ።

❤️በዚህ ስፍራ ውስጥ ሙሉ ነን፤ እውነተኛ እኛነታችን የሚታየው በዚህ ስፍራ ነው። ወደ ውስጣችን ዘልቀን በዚህ ስፍራ ላይ ቆመን ህይወታችንን ብናየው፤ እንደምናስበው ደካማ አይደለንም፤ የሚጎድለን ብዙ አይደለም፤ ከምንም በላይ በፈጠረን አይን ውስጥ ውብና ንጹህ ነን። ታዲያ ከዚህ በላይ ምን አለ? ደስታና ሰላማችን በሰው እጅ ፤ ፍርድና ቅጣታችን በሰው ወንበር ፈጽሞ አይሁን!!!

💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚

ሌሎች እንዲማሩና እንዲለወጡ ምክንያት እንሁን።በፍቅር እንኑር!!!
💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙

@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
በልተን ፡ ተናግረን ፡ ሰርተን ፡ አልቅሰን ፡ስቀን የምንጨርሰው የኑሮ መስተጋብር ይኖር ይሆናል እንጂ
አለምንና በአለም ላይ ያለውን ሁሉ ኖረን አንጨርሰውም ፡በልኩ እና በአግባቡ መኖር አለብን፡፡ ቅጥ የሌለውና ገደብ የለሽ ፍላጎታችንን መስመር ልናበጅለት ይገባል፡፡ ሁሉም ነገር ስለኛ ተፈጠረ እንጂ እኛ ስለሁሉም አልተፈጠርንም እና ያየነው እና የሰማነው ሁሉ ሊገዛን አይገባም፡፡ ሁሉም ነገር ልክ ሲኖረው ያምራል፡፡ በልኩ ስትበላ ጤነኛ ትሆናለህ፡ በልክ ከጠጣህ አትስከርም ፡ በልክ ከተናገርክ ሰሚ ይኖርሀል፡ በልክ ከተጓዝክ አትሰናከልም፡፡ አብዝተህ ሰውን ከመውደድ ፡አብዝተህ ቅን እና መልካም ከመሆን ውጭ ፡፡ኑሮህን በሙሉ በልክ አድርገው። ያኔ ሰላምና የተረጋጋ ህይወት ይኖርሀል። አመስጋኝም ትሆናለህ፡፡ የተሰራው መንገድ ሁሉ መሄጃህ አደለም መድረሻህን የሚያሳምረውን መንገድ ብቻ ተጓዝ፡፡ መስመርህን አትሳት፡ አምሮህ ብዙ ጊዜ የሚጨነቀው ፡ከልክ በላይ ነገሮችን ለማሟላት ከመነጨ ፅኑ ፍላጎት የተነሳ ነው፡፡ በተሰጠህ እንጅ በሮጥከው ልክ አትኖርም፡፡ ደስታን ትፈልጋለህ?እንግዲያውስ ሁሉን ነገር በልክ አድርገው ፡ከተሰጠህ ላይ መስጠትን ልመድ፡፡ በዙ አትመኝ ፡ ያለህ እንዲባረክ ዘወትር አመስጋኝ ሁን!!!

ፈጣሪ ለሰው ልጆች ሁሉ ሰላም ፍቅር አንድነትን ያብዛ። አሜን

@sam2127
💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚
ሌሎች እንዲማሩና እንዲለወጡ እናድርግ
ያወቅነውን እናሳውቅ፡ በፍቅር እንኑር፡፡
💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙


@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
💛"Holding a grudge Doesn't make you strong; It makes you bitter. Forgiveness doesn't make you weak it sets you free" #forgive

ሁሌም በደልን ሳስብ አንድ ነገር ይመጣብኛል ፤ በአንድ ክፉ ሰው ስራ ስንት መልካም ሰዎች እድል ይከለከላሉ? በአንድ ሌባ ሰው ምክንያት ስንት ታማኞች እንደሌባ ይቆጠራሉ? በአንድ ከዳተኛ ምክንያት ስንት እውነተኛ አፍቃሪዎች እድል ሳይሰጣቸው ይገፋሉ? ....ምክንያቱም ይቅር ማለት ስለሚከብደን።

ይቅር ስንል ከበደሉን ሰዎች ይልቅ ቅልል የሚለን እኛን ነው። የተበደልነውን እያሰብን አቀርቅረን የምንኖር ከሆነ፤ ቁስላችንን ሊጠግኑ የሚችሉ፤ እንባችንን ሊያብሱ የሚችሉ፤ ካጎነበስንበት ቀና ሊያደርጉን የሚችሉ ሰዎች በአጠገባችን ሲያልፉ አናያቸውም። ይቅር ስንል ግን በሰው ልጆች ተስፋ አንቆርጥም።

💜ይህች አለም ክፉዎችንም ደጎችንም አሰባጥራ ይዛለች። በመጥፎ ሰዎች ስራ ግን ደጎች እንደሌሉ ይቆጠራሉ፤ ምክንያቱም መልካም ሰዎች በቂመኛ ሰው አይን ውስጥ ስለማይገቡ ነው። የበደሉንን እያሰብንን የሚክሱንን ባናርቃቸው መልካም ነው!!!

ይቅር በማለት እራሳችንን ነጻ እናውጣ!!!🙏

💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚
ሌሎችን እንዲማሩና እንዲለወጡ ምክንያት እንሁን፡፡አይከፈልበትም ፡ በፍቅር እንኑር።
💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙

ሚስጥረ አደራው


@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
💛Accept all of the things in your life that you regret; they happened, and they aren't going to change. What you can embrace and value about them, though, is the lessons they have throughout your life.

💜You have learned some important lessons, particularly in these circumstances.Those lessons, based on your experience, are molding you into the person you are now, and will also be the basis from which you give advice to others.

The wonderful feelings of happiness that good days provide, the intense experiences that bad days bring, the lessons of your worst days, and the memories of your best days are all valuable. They're shaping you into the person you are and will become.

💛 Live every day with absolute gratitude, respect, love and care because this is life and it will test you forever and a day. Love your life; you are here for a reason.Give a Heart if you are ready to accept all aspects of your life.

💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚
Pls Share For Your Be Loved Ones
💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙


@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
💙ይህች ምድር ያንተናትና ተስፋ አትቁረጥ!

💜አንተ ልዩ ሆነህ የተፈጠርከው በፈጣሪ ፈቃድ ነውና ምንም ሳታማርር ህይወትህን ኑራት። ባለህ እየኮራህ ህይወትህን አጣፍጣት። ሰዎችን ለመምሰልና የነሱ ግልባጭ ለመሆን አትጣር።

የአንተ ንጹህና እጹብ ድንቅ ያልታየ ማንነት የሚወጣው በራስህ መተማመን፣መኩራትና እራስህን ማክበር ስትጀምር ነውና። በዙሪያህ ምንም አይነት ዝነኞች ትልቅና ልዩ ሰዎች ቢኖሩም በአንተ ውስጥ ያለው ልዩ ስጦታ ግን ከሁሉም ይለያል!
ይልቃል! ይበልጣል!

እነዚህ ልዩ ያልካቸው ሰዎች በአፈጣጠራቸው የተለዩ ሆነው ሳይሆን ይህንን ምስጢር ስላወቁትና ስለተገበሩት ብቻ ነው ከሌሎች ተለይተው አሁን ያሉበት የደረሱት። አንተም እንደነሱ የደረሱበት እንደውም ከነሱበላይ መስጠት መስራትና ማበርከት ከፈለክ ወደ እኔ ጠጋ በልና ጆሮህን ስጠኝ እኔም ሚስጢሩን ሹክ ልበልህ። "እራስህን ሁን! እራስህን አክብር! እራስህን ውደድ!" እራስህን እንደማትወደው እንደማታከብረውና እንደማትሆነው ስታስብ ከማይመረመረው ከፈጣሪ እውቀት ጋ እየተደራደርክ ነውና ሁለቴ አስብ።

ሰዎች ከሚሉህ በላይም ፈጣሪ ሲፈጥርህም ምክንያት አለውና የሌለህን ትተህ ያለህን ዋጋ ስጥ። በሌለህ ነገር ስለምታገኘው ሳይሆን ባለህ ነገር ስለምትለውጠው ተመራመር። በሌለህና ባልተጨበጠው ነገር ትልቅ ነገር ለመስጠት ከማሰብ ይልቅ ባለህ ነገር ትንሽ ነገር ለመስጠት ሞክር። ያኔ አንተ ውስጥ የተደበቀው ከሌሎች የተለየው ድንቅ ፍልቃቂ ማበብ ይጀምራል።

ብርሀንህ በዓለም ሁሉ ይሰፋል። ስምህም በሰዎች ልብ ውስጥ ይነግሳል።በምድር ላይ በኖርክበት ዘመን ሁሉ ዘመንህ የጣፈጠ ይሆንልሀል።

💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚
ሌሎች እንዲማሩ እና እንዲለወጡ ምክንያት እንሁን ፡፡በፍቅር እንኑር ፡፡
💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙


@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
💙ወዳጄ ሆይ ባለሀብት ብዙ ያለው ሳይሆን ካለው ብዙ የሚሰጥ ነው።ከሚደልሉ አንደበቶች የሚመፀውቱ እጆች እጅግ ይልቃሉ ። ልግስና ማለት የኪሳችንን ቦርሳ መክፈት መቻላችን ብቻ ሳይሆን ልባችን መክፈት መቻላችን ነው።

💎ወዳጄ ሆይ የእውነት መሰረት ፍቅር ነው ።የፍቅር የመጀመርያ ምልክትና ርምጃ ልግስና ነው !የልግስና ጓደኛ ፍትሕ ነው ። የፍትሕ ፍሬ ደግሞ ስላም እና ሰዎችን መታደግ ነው ። ለሰዎች እርዳታን መሰጠት በእነሱ ውስጥ ፈጣሪን ማየት እና ማግኘት ነው።

💡ወዳጄ ሆይ ሰዎች በሚሰፈልጋቸው ግዜ እርዳ እነሱም በሚስፈልግህ ግዜ ይረዱሀል።ምንም ዓይነት የሕይወት ደረጃ ይኑርው፣
ከትኛውም እምነት ፣ ቀለም እና ዘር ይሁን፣
መልካምም ይሁን ክፉ ሁሉም ሰው በፈጣሪ የተፈጠረ መሆኑን አሰታውስ።

💡ወዳጄ ሆይ ለመልካም ስራ እጅን ለግስ "ልግስና የነፍስ ምግብ ነውና
ደስታ ለሚሰጥ አብዝቶ ይመለስለታል።
ጥሩ እርካታ ያገኘ ጥሩ ክፍያ እንዳገኘ ነው ።ባለንና በምናገኘው ነገር ኑሯችንን ስንመሰረት በምንሰጠው ነገር ደግሞ ሕይወታችንን እንመሰርታለን።

💎ወዳጄ ሆይ ለራስህ የምትፈልጋቸውን ሁሉ ለሁሉም ስጥ በትክክለኛው ስሌት ደስታን በሰጠኽው መጠን ትቀበለዋለህ።ደስታ በሰጠህ ግዜ እጥፍ ይጨመርልሀል።ሌሎችን መረዳት የመጀመርያው ንቃት እና ዕውቀት ነው፣ መንፈሳችንንም ወደ ላይ ክፍ ከፍ ያደርገዋል።

❤️መልካም ስራን ለመስራት የምንሰዋው ኃይል ለጊዜው ዋጋ ቢስከፍለንም በመጨረሻ ግን በውስጣችን የሚሰጠን የደስታ መጠን ግን እጅግ የላቀ እና የበዛ ነው! ! ! ታላቅ የሆነ ጥበብ እና ማስተዋልንም ይዞ ይመጣል ።

💡ወዳጄ ሆይ ደስተኛ የመሆን ቀላሉ መንገድ መልካም ነገር ማድረግ ነው ።ውብ ነገርን ተመርኩዘው የሰሩት ስራ ሁሌም ውብ ነውና።

💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚
ሌሎች እንዲማሩና እንዲለወጡ ምክንያት እንሁን፡፡ በፍቅር እንኑር ።
💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙

@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
💥💥አይዞሽ ኢትዮጵያዬ💥💥

አንች ትልቅ ሀገር
በአባቶቸ አጥንት
በአባቶቸ ደም ፀንተሽ የቆየሽው ፡፡
ምን? አድርገሽ ይሆን
በአጥፊዎች ሰበዝ የምትታመሽው ።
በምን ?ሀጢአትሽ ነው
ወልደሽ ባሳደግሽ የምትነከሽው::

የበረከት ምድር: የታሪክ ማህደር
ኤትዮጵያ ሀገሬ ::
ስልጣን አገኝ ብለው
በእንባ ያራጬሽ
በደም ያጨቀዩሽ ገለውሻል ዛሬ::

አይዞሽ እናታለም :
አይታለፍ የለም ይሄም ጊዜ ያልፋል ::
ከችግርሽ በላይ
ባርኮ የፈጠረሽ ፈጣሪ ይገዝፋል ::

አይዞሽ ኢትዮጵያየ

ሳቅሽን ያጠፋው
ለቅሶሽን ያበዛው
መከራሸ ቢያመኝም ::
ይሁን ቻል አድርጊው
ከመከራው በፊት ትንሳኤ አይገኝም::

01/03/13

Samuel Adane
@Sam2127

💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚
ሌሎች እንዲለወጡ ምክንያት እንሁን
፡በፍቅር እንኑር
💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙

@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
እኛነታችንን በደንብ አናውቀውም፡ ግን እኛ እኔ በሚል አጥር ውስጥ ተተብትበናል። መኖር እንመኛለን ግን የሌላው አለመኖር አያሳስበንም፡ መራብ አንፈልግም የሌሎች እርሀብ ግን አያመንም፡ ሰላም እንፈልጋለን ግን የሌሎች ሰላም እናናጋለን፡ መደሰት እንወዳለን
ግን ሌሎች እንዲያለቅሱ ምክኒያቶች ነን። በእውነት ምኑም ነገር አልገባንም፡ ብኩኖች ብቻ ነን ፡ ሸክላነታችን ያልገባን ፡ ነገን ለመኖር ዋስትና የሌለን ከንቱዎች፡ አፈርን ካፈር ለመለየት የምንዳክር ቂሎች ፡
ስጋችን የተለቀ ፣አስተሳሰባችን ያልታረቀ ፣ አካሄዳችን እና ምግባራችን የተናቀ ምስቅልቅሎች፡ ምኑም ነገር አልገባንም። ለክብርና ለዝና ፡ ለሀብትና አድሮ አመድ ለሚሆን ስጋችን ባሪያዎች የሆንን፤ የምንፈልገው አይገባንም ፡ የሚያስፈልገን አይታየንም፡ የውስጣችንን ባዶነት በጩህትና ባለባበስ ለመሸፈን የምንዋትት አሳዛኞች፡ ከፈጣሪ ትዛዝ ይልቅ የፍላጎታችን ባሪያወች ፡ ከፍቅር ይልቅ የጥላቻ ፈረሶች ፡ የሰውነት ክብራችንን ያጣን፣ ጥጋብ ምንሆነውን ያሳጣን ፣ ከቁጣው መቅሰፍት ያልወጣን
ጅሎች ሆነናል ፡፡ የምንናገረውን አናቅም፡ የምናምነውን እሱን አንሰማውም፡ የቃል ሰዎች ብቻ ነን፡ ፡
ሀጢታችን በፊታችን የተገለጠ ነው፡ ግን ክብራችን ይመስለናል ፡፡ እምናደርገውን አናስተውልም ፣ እየሆነ ያለው ሁሉ አይገባንም፡፡ የፈጣሪ እዳ አለብን ፡ እጃችን ባዶ ነው ፡ ለዛውም የተጨማለቀ ። አልገባንም ሀጢያታችን በዝቷል:: በከንቱ እየባዘንን ነው ፡ ውጤቱንም እያየነው ነው ፡፡ ከሩጫችን ረጋ እንበል፣እናስተውል ፣እንመለስ፣ ሰው እንሁን ፣ አስተሳሰባችንን ከሰውነት ሚዛን አናስወጣው ፡፡ አልረፈደም እንፀልይ ፡ የፈጠረን አምላክ ለይቅርታ የታመነ ነው።


ሰላም፣ ፍቅር፣ ጤንነት ፡ለሰው ልጆች ሁሉ ይሁን !

Samuel Adane
@sam2127
💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚
ሌሎች እንዲለወጡ ምክንያት እንሁን ፡፡
በፍቅር እንኑር ፡፡
💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙



@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
አለመናገሬን እናገረው ብየ መርጨ ባወጣም ፣
ዝምታየን ጥሶ
ነገሬን የሚውጥ ሰሚ እንደሁ አይመጣም ፣
እናም እንዳንዴ ባለ መናገር ውስጥ
መናገር ባይቻል ፣
ትርጉም ካጣ ጩኸት
እውነትን ያዘለ ዝምታ ይመቻል::

samuel Adane

01/09/13
🌿❤️🌿❤️🌿❤️🌿❤️🌿❤️🌿❤️🌿

@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
🕰ያወቅነው ግን ያላወቅነው!

Samuel Geda

📕 አንድ ሰው ከብዙ ዓመታት በኋላ ከቀድሞ የትምህርት ቤት ጓደኛው ጋር በመንገድ ይገጣጠማል፣ ለማመን እስኪያዳግተው ድረስ ጓደኛው አዲስና የቅርብ ሞዴል የሆነች መኪና እንደያዘ ይመለከታል። ታዲያ ወደቤት ሲመለስ ፊቱ በሃዘን ተሞልቶ ይተክዝና ያዝን ጀመር። እርሱ ወደ ኋላ እንደቀረ/እንደከሰረ አስቧልና። ይሁንና ያላወቀው ነገር ቢኖር፥ ጓደኛው የመኪና ሾፌር ሲሆን፣ ለመስክ ሥራ በአለቃው መኪና መላኩን ነው።
*
📙 ሮዛ ሁልጊዜም ፍቅር አትሰጠኝም/አታቀማጥለኝም/ በሚል ሰበብ ከባለቤቷ ጋር ትጋጫለች። ይኸውም፤ በመኪና ካደረሳት በኋላ እንደጓደኛዋ ሄለን ባል ከመኪና ወርዶ፡ ዞሮ፡ በር ከፍቶ እርሷን አለማውረዱን እንደምክንያት ታነሳለች። ሮዝ ያላወቀችው ነገር፡ የነሄለን መኪና፡ የፊት በሩ ላይ ብልሽት ስላለው ከውጪ ካልሆነ በስተቀር ከውስጥ መከፈት አለመቻሉን ነው።
*
📒 አንዲት ሴት ከረጅም ጊዜ ቆይታ በኋላ፣ የብዙ አመት ጓደኛዋን ልትጎበኝ በሄደችበት፡ ሶስት የሚያማምሩና ለዓይን የሚያሳሱ ልጆች ሲቦርቁ ዐይታ ስሜቷ ይረበሻል። የመጀመሪያ ልጇን ከወለደች በኋላ ለረጅም አመታት ሌላ ልጅ ለማርገዝ ብትጥርም ሳይሳካ /እየጨነገፈ/ ቀርቷልና። ይሁን እንጂ ያላወቀችው ነገር፡ የጓደኛዋ ልጅ በካንሰር በመያዙ መኖር የሚችለው ለአንድ አመት ብቻ ሲሆን ቀሪዎቹ ሁለቱ ልጆች ደግሞ የማደጎ ልጆች ናቸው።
* * *

📘ህይወት ሁሉንም አንድ ዓይነት በሆነ መንገድ የምታስተናግድ መድረክ አይደለችም። ካወቅነው ይልቅ የማናውቀው ብዙ ነው። ዐይነቱና መጠኑ ይለያይ እንጂ ሁሉም ሰው የራሱ ጉድለት አለው። ይሁንና ደስታ የምርጫ ጉዳይ በመሆኑ ሁሉም ሰው ግን በህይወቱ ደስተኛ አይደለም።

📗ይኸውልህ፤ ኤሊ ምን ዓይነት ሸክም እንደተሸከመች ካወቅክ ለምን በጥንቃቄ እንደምትራመድ አትጠይቅም። ከሚታየው ምቾት ባሻገር የማይታዩ ብዙ ሸክሞች፣ ከሚማርኩ ፈገግታዎች ጀርባ ብዙ የልብ ቁስልና ህመሞች እንዳሉ እወቅ። ከሩቅ ያማረ ኑሮ ሁሉ የስኬት ምልክት፣ ከውጭ የሚታይ አንጸባራቂ ነገር ሁሉ ወርቅ አይደለምና። ስለዚህ ያወቅነው 'ደስታውን' ሲሆን ያላወቅነው ደግሞ 'ጉድለቱን/ችግሩንና ድካሙን/' ነው።

"ለምን እኔ ብቻ?" እያልክ ትጠይቅ ይሆን?

እኩዮቼ አግብተዋል።
እኩዮቼ ልጆች አፍርተዋል።
እኩዮቼ ጥሩ ሥራ ይዘዋል።
እኩዮቼ ስኬት ተጎናጽፈዋል።
እኩዮቼ ውድ ቤትና መኪና አሏቸው።
እኩዮቼ በማኅበረሰቡ የተከበሩ ናቸው።
እኩዮቼ እንዲህ ናቸው፤ እንዲያ ናቸው...!!!

ትክክል ብለሃል። ይሁንና ይህንን ጨርሰህ መርሳትህ ያሳፍራል...

📕እኩዮችህ ሆነው በህይወት የሌሉትን።
እኩዮችህ ሆነው በህመም የሚሰቃዩትን።
እኩዮችህ ሆነው በአእምሮ መታወክ በማህበረሰቡ እንደ እብድ የተቆጠሩትን።
እኩዮችህ ሆነው መንገድ ዳር የሚያድሩትን።
እኩዮችህ ሆነው ወላጅ አልባ የሆኑትን።
እኩዮችህ ሆነው የለት ጉርስ ያጡትን።
እኩዮችህ ሆነው አንተ የምትኖረውን ኑሮ የሚናፍቁና ባንተ ህይወት የሚቀኑ መሰል የሰው ዘርን...ረስተሃል።

🔷ምናልባት የምትፈልገው ስፍራ ላይ አልተቀመጥክ ወይንም የምትመኘውን ነገር አላገኘህ ይሆናል፡ ይሁን እንጂ ከብዙዎች በላይ ደስተኛ ነህ። ስለዚህም ፈጣሪህን ባለህ ነገር አመስግን።

📒አንተ ለብቻህ የሆነብህ ነገር የለም። አንተ ጋር የጎደለህን ሌላው ጋር ስታይ 'ሁሉ የሞላለት' መስሎህ ነው። ባወቅኸው ልክ የሰውን ህይወት አትመዝን፣ የራስህንም አታቃል። ያወቅክ የመሰለህ ያላወቅኸው ብዙ አለና። ስለዚህ በምንም አይነት የህይወት ትግል ውስጥ ብትሆን ደስታን ምርጫህ አድርግ። ሰላምንም ውደዳት። ሁልጊዜም በፈጣሪህ ደስ ይበልህ!

ምንጭ:Book For all
@TIBEBnegni
@sam2127
አውጣን በሰመመን
~~~~~~~~~~~

ምን ይሉት ቀን መጣ
ምን አይነቱ ዘመን ፣
ምንሰማው ሁሉ
ምናየው ሁሉ ቁስል ሆኖ አመመን ፣
ፅናት አጣን እና ባንተ ልንታመን ፣
አድነን እያልን መጮሁ ደከመን ፣
አባክህ ጌታ ሆይ ከዚህ ማእበል ውስጥ
ታምር ፍጠርና አውጣን በሰመመን ፡፡


samuel Adane
@Sam2127
🌹🙏🌹🙏🌹🙏🌹🙏🌹🙏🌹
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
2025/02/24 16:36:35
Back to Top
HTML Embed Code: