Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የመጀመርያውን ዙር 30 ተማሪዎች ና 11 ወላጆች ስንመርጥ በምክንያት ነው፡፡
ለቀጣይ ሽልማት ብቁ እንዲሆኑ ይህንን መልዕክት ይከታተሉ፡፡
#Share
@timhirt_minister
@timhirt_minister
ለቀጣይ ሽልማት ብቁ እንዲሆኑ ይህንን መልዕክት ይከታተሉ፡፡
#Share
@timhirt_minister
@timhirt_minister
በአዲስ አበባ አራት የግል ትምህርት ቤቶች ለአንድ ዓመት ታገዱ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርት ጥራት ሙያ ብቃት ምዘና ማረጋገጫ ባለስልጣን ዛሬ በሰጠው መግለጫ በአዲስ አበባ አራት ትምህርት ቤቶች በቀጠቀዩ ዓመት ተማሪዎችን ተቀብለው እንዳያስተምሩ ታግደዋል።
ባለሰልጣኑ ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የትምህርት ቤት ክፍያቸውን ከ50 እስከ 75 በመቶ እንዲቀንሱ መመሪያ ቢያስተላልፍም ትምህርት ቤቶቹ ግን 100 ፐርሰነት ክፍያ አስከፍለው ነው።
ለአንድ ዓመት ከታገዱት ትምህርት ቤቶች መካከልም 3ኤም ትምህርት ቤት፣ገነት መሰረተ ክርስቶስ፣ሮማን አካዳሚ እና ለምለም ትምህርት ቤቶች በ2013 ዓመት ተማሪ እንዳይቀበሉ ተወስኖባቸዋል።

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ማኅበረሰብ አባላት ከደሞዛቸው በማዋጣት ለአካባቢው ኅብረተሰብ ድጋፍ አደረጉ
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ማኅበረሰብ አባላት ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ ከደሞዛቸው ላይ ከ25 እስከ 100 ፐርሰንት በማዋጣት በዞኑ በሚገኙ 22 ወረዳዎች ውስጥ ለሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች የተለያዩ ድጋፎችን አድርገዋል።
በተለይ በዛሬው ዕለት በቡታ ጂራ ከተማ አስተዳደር እና በመስቃን ወረዳ ለሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ አድርገዋል።
ለቡታ ጂራ ከተማ አስተዳደር 30 ኩንታል ዱቄት እና 9 ኩንታል ሩዝ፣ 571 ሳሙናዎችን (በነጠላ)፣ 500 ሊትር ዘይት ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን ለመስቃን ወረዳ ደግሞ 26 ኩንታል ዱቄትን ጨምሮ የተለያዩ ድጋፎችን አድርገዋል።
የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ አባላት ድጋፉን ያደረጉት ከደሞዛቸው ላይ ከ25 እስከ 100 ፐርሰንት አዋጥተው በድምር እስከ ሁለት ሚሊዮን ብር በመለገስ መሆኑ ታውቋል።
ከዚህ በተጨማሪም ከዩኒቨርሲቲው በጀት ላይ ሌላ 2 ሚሊዮን ብር ለድጋፍ ወጪ መደረጉ ተገልጿል።
ከድጋፉ በተጨማሪም የአካባቢውን ኅብረተሰብ ከኮቪድ-19ን ከመከላከል በቀጣይ ምን መደረግ አለበት በሚለው ጉዳይ ላይም ውይይት ተደርጓል።
ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የኮሮና ቫይረስን ከመከላከል አኳያ ግንዛቤ ማስጨበጥን ጨምሮ የተለያዩ ሥራዎችን ሲሠራ መቆየቱም ተገልጿል።
ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ ለሚገኙ ቁጥራቸው ወደ 178 ለሚሆን የጤና ባለሙያዎች ቫይረሱን ከመከላከል አኳያ ግንዛቤ መስጠቱን እና ለይቶ ማቆያዎችን ከማዘጋጀት አኳያም ተሳትፎ እንደነበረው ተገልጿል።

አንዳንድ የትምህርት ተቋማት ከሁለተኛ ዲግሪ በላይ ያሉትን ተማሪዎቻቸውን ትምህርት ማስጨረስ መጀመራቸው ተገለፀ
ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሁለተኛና የሦስተኛ ዲግሪ ተማሪዎቻቸውን ትምህርት ማስጨረስ መጀመራቸው ተጠቆመ፡፡ የመጨረሻ ዓመት የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች ደግሞ ከየትምህርት ተቋሞቻቸው የሚላኩላቸውን የትምህርት ሰነዶች እያነበቡ እንደሚቆዩ ተገልጿል፡፡
በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል ዶክተር ኤባ ሚጀና በኮቪድ 19 ቫይረስ ወረርሽኝ በሽታ ምክንያት በዚህ ወቅት ይካሄድ ስለነበረው የከፍተኛ ተማሪዎች የምረቃ መርሃ ግብር ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለፁት፣ በኮቪድ 19 ቫይረስ ወረርሽኝ በሽታ ምክንያት የሁለተኛና ሦስተኛ ዲግሪ ትምህርት በቴክኖሎጂ በመታገዝ ትምህርቱን እንዲከታተሉና ከአማካሪዎቻቸው ጋርም የሚገናኙበት ምቹ ሁኔታ በመኖሩ ትምህርታቸውን በማጠናቀቅ ላይ ይገኛሉ፡፡
የምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ባይኖርም አንዳንድ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን ትምህርት ማስጨረስ እንደ ጀመሩ አመልክተው፣ በዚህም ጅማና ሐሮማያ ዩኒቨርሲቲዎች ይጠቀሳሉ ብለዋል፡፡ ትምህርታቸውን ያልጨረሱ ተማሪዎችም እንደሚኖሩ ጠቁመዋል፡፡
ተማሪዎቹ ትምህርታቸውን ለመጨረስ የቻሉት በተመቻቸው የቴክኖሎጂ የማስተማሪያ ዘዴ በአግባቡ መጠቀም በመቻላቸው፣ እንዲሁም በተማሪውና በአማካሪዎቻቸው ጥንካሬ እንደሆነ የጠቆሙት ዶክተር ኤባ፣ የትምህርት ተቋማቱም በየጊዜው አስፈላጊውን ክትትልና ግምገማ በማድረግ ውጤታማ መሆኑ መቻላቸውን አመልክተዋል፡፡
የመጨረሻ ዓመት የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎችን በተመለከተም ዶክተር ኤባ እንዳብራሩት፣ በወረርሽኙ ምክንያት ባለመማራቸው፣ አንዳንዶችም የመጀመሪያ መንፈቅ (ሴሚስተር) ፈተና ለመውሰድ ዝግጅት ላይ እያሉ ወረርሽኙ በመከሰቱ ምክንያት ባለመፈተናቸው በዚህ ክረምት ትምህርታቸውን የሚያጠናቅቁ ተማሪዎች አይኖሩም፡፡
እነርሱን በተመለከተ መደረግ ስላበት ነገር በየሳምንቱ ከየትምህርት ተቋማቱ የትምህርት አመራሮች ጋር ግምገማ እየተደረገ እንደሚገኝ አመልክተው፣ ወረርሽኙ ቢገታ ወይም ቢቆም መደረግ ስላለበት ሁኔታ ከወዲሁ ዝርዝር ዕቅድ ያዘጋጁ የትምህርት ተቋማት መኖራቸውን ገልፀዋል፡፡
ዝርዝር ዕቅዱ ተማሪዎች ትምህርታቸውን ምን ላይ እንዳቆሙ እና ካቆሙበት በመቀጠል ደግሞ በምን ያህል ጊዜ ውስጥ በመሸፈን ትምህርታቸውን ማጠናቀቅ እንደሚችሉ የሚያሳይ እንደሆነም አስረድተዋል።

የቅድመ ምረቃ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች ሳይማሩ እንደማይመረቁ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ
ለሳይንስና ከፍትኛ ትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ የሆኑና በስራ ላይ ያሉ 44 ዩኒቨርሲቲዎች ከመጋቢት ወር የመጀመሪያ ሳምንት ጀምሮ የገጽ ለገጽ የመማር ማስተማር ሂደታቸውን ማቋረጣቸው ይታወሳል።
የሳይንስና ከፈተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ፥ በቅድመ-ምረቃ መርሃ ግብር በቴክክኖሎጂ ትምህርት ማስቀጠል ባለመቻሉ ተማሪዎች ሳይማሩ አይመረቁም ብለዋል።
“በቴክኖሎጂ የቅድመ-ምረቃ ትምህርት ማስቀጠል ከሞላ ጎደል አልተቻለም፤ እያንዳንዱ ተማሪ በየቀኑ፣ በየሳምንቱ የሚማረውን እያነበበ፤ ምዕራፍ በምዕራፍ፣ ሞጁል በሞጁል ተምሮ ምዘና እየተደረገለት አልቆየም።
በዚህ ረገድ ያልመጣን፣ የትምህርቱን ይዘት ያላጠናቀቀን ተማሪ ተምሯል ብሎ ወስዶ፤ ይህንን ኮርስ ጨርሰሃል፣ በዚህ መልኩ ተገምግመሃል እና ይህንን ውጤት አግኝተሃል ብሎ ውጤት ሰጥቶ ማስመረቅ በትምህርትም በአሰራርም ወንጀል ነው፤ መሰል አካሄድ አይፈቀድም፤ እንደዚህም አይሆንም!” ብለዋል።
የድህረ ምረቃ የሁለተኛ እና የሶስተኛ ዲግሪ መርሃ-ግብር በቴክኖሎጂ ማድረስ በመቻሉ ይመረቃሉ ከሚል ድምዳሜ ተደርሷል።

የዛሬው የትምህርት ፕሮግራም
21/09/2012
29/5/2020
3:00 _ 3:30 Bio 12
3:30 _ 4:10 Phy 9
4:20 _ 4:50 Bio 11
5:00 _ 5:30 Phy 7 Oro
5:30 _ 6:00 Math 11
6:00 _ 6:30 Hist 12
ከሰዓት በኋላ ⏰
8:00 _ 8:30 Bio 8
8:40 _ 9:10 Geo 11
9:20 _ 9:50 Math 7
@timhirt_minister
@timhirt_minister
21/09/2012
29/5/2020
3:00 _ 3:30 Bio 12
3:30 _ 4:10 Phy 9
4:20 _ 4:50 Bio 11
5:00 _ 5:30 Phy 7 Oro
5:30 _ 6:00 Math 11
6:00 _ 6:30 Hist 12
ከሰዓት በኋላ ⏰
8:00 _ 8:30 Bio 8
8:40 _ 9:10 Geo 11
9:20 _ 9:50 Math 7
@timhirt_minister
@timhirt_minister
ትምህርት ሚኒስቴር!
•ማንኛውም የግል ተማሪ ወራዊ ክፍያው 75% መሆን አለበት።
•ለመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች ምንም አይነት ምዘና፣ ከ ሴሚስተር ወደ ሴሚስተር ወይ ከአመት ወደ አመት መዘዋወር ወይም ማስመረቅ አይቻልም።
•ተማሪዎች ወደ መማር ማስተማር ሲመለሱ በቂ የሆነ ትምህርት ይሰጣል።
•የ2ኛ ና 3ኛ ዲግሪ ተመራቂ ተማሪዎች በኦንላይን ትምህርታቸውን ተከታትለው መመረቅ እንዳለባቸው ተገልጿል።

የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮች እና ሠራተኞች "# ደም # በመለገስ # ህይወት # እናድን " በሚል መሪ ቃል በሚኒስቴር
መስሪያ ቤቱ ቅጥር ግቢ ተገኝተው ደም ለግሰዋል፡፡
***************************************
የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሠራተኞች ከዚህ ቀደም ደም የመለገስ ልምድ ያላቸው ሲሆን አሁን በተለይ ያለንበትን አስቸጋሪ
ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ 19) ወረርሽኝ ምክንያት የደም መለገስ ሁኔታው እየቀነሰ
በመምጣቱ ለእናቶችና ደም ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ለመድረስ በማሰብ ደም እየለገሱ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ደም መለገስ ከዜጎች የሚጠበቅ የውዴታ ግዴታ በመሆኑም የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አመራሮች እና ሠራተኞች ለሁለት
ቀናት በሚቆየው የደም ልገሳ መርሃ-ግብር እንደሚሳተፉም የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ዘግቧል፡፡

በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሕክምና ሳንይንስ ኮሌጅ ሕይወት ፋና ሆስፒታል 3 የሕክምና ኢንተርን ተማሪዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘው በለይቶ ማቆያ ውስጥ ይገኛሉ።
ከተማሪዎቹ የ6ኛ አመት ሕክምና ተማሪዎች ሲሆኑ ከበሽተኛ ጋር በነበራቸው ንክኪ በሽታው እንደተገኘባቸው ተገልጿል።
ከተማሪዎቹ ጋርም ንክኪ የነበራቸው ሌሎች የሕክምና ተማሪዎችም በዩኒቨርሲቲው ውስጥ በተዘጋጀላቸው ለይቶ ማቆያ ( ኳረንቲን ) ውስጥ ይገኛሉ።
በኳረንቲን ውስጥም አስፈላጊው ክትትል እየተደርገላቸው እንደሚገኝ የነገሩን ሲሆን በሕብረተሰቡ መካከል ግን ስለበሽታው ምንነት እና ኳረንቲን ስለመግባት ያለው ግንዛቤ እጅግ በጣም አናሳ መሆኑን ጠቁመውናል፡፡

#ATTENTION‼️
ይሄ የትምህርት ሚንስቴር Offical ቻናል አይደለም ነገር ግን ከትምህር ሚንስቴር የፌስቡክ ገፁ ላይ ያገኘናቸውን መረጃ በሙሉ ለእናንተ በቀጥታ እናደርሳለን::

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
How Cement is Made?
@timhirt_minister
@timhirt_minister
የግል ትምህርት ቤቶች ከአምስት ሺህ በላይ ተማሪዎችን በነፃ እያስተማሩ ነው
የግል ትምህርት ቤቶች ኮቪዲ 19 ወረርሽኝ ያሳደረውን ጫና ማቃለል እንዲቻል አምስት ሺህ 99 ተማሪዎችን በነፃ እያስተማሩ እንደሆነ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት፣ ስልጠና ጥራት ሙያ ብቃት ማረጋገጫ ባለስልጣን አስታወቀ። አራት ትምህርት ቤቶችም ርምጃ እንደተወሰደባቸውም ተገልጿል፡፡
የባለስልጣኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ ወይዘሮ ሸዊት ሻንካ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንዳሉት ይሄን ክፉ ጊዜ በመደጋገፍና በመተጋገዝ ማለፍ አስፈላጊ በመሆኑ በከተማው በሁሉም ረገድ እየተደረጉ የሚገኙት ርብርቦች የሚያስመሰግኑ ሲሆኑ፤ በትምህርት ዘርፉም ከወላጅ ኮሚቴዎችና ከትምህርት ቤት አመራሮች ጋር በጋራ ውይይት በኮሮና ወረርሽኙ ምክንያት ገቢያቸው የቀነሰባቸውን ወላጆች በየትምህርት ቤቶች በመለየት ልጆቻቸውን በነፃ እንዲያስተምሩ መደረጉን ተናግረዋል።
የነፃ ትምህርት ተጠቃሚዎቹም ወንድ ሁለት ሺህ 499 እና ሴት ሁለት ሺህ 600 በድምሩ አምስት ሺህ 99 ተማሪዎች ሲሆኑ፤ ገቢያቸው የነጠፈባቸው በሰባት ክፍለ ከተሞች የሚገኙ ወላጆች መሆናቸውን ገልጸዋል።
መንግሥት ያደረጋቸውን ጥሪዎች ጆሮ ሰጥተው በማድመጥ በየተሰማሩባቸው ዘርፎች ለሕብረተሰቡ ችግር የአቅማቸውን አስተዋጽኦ በማበርካት አለኝታነታቸውን ለሚያሳዩ አካላት ምስጋና ሊቸራቸው ይገባልም ነው ያሉት።
ወይዘሮ ሸዊት እንደተናገሩት፤ በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ገቢያቸው የተቋረጠባቸው በርካታ የሕብረተሰብ ክፍሎች በመኖራቸው ከዚህ በፊት በግል ትምህርት ቤቶች ልጆቻቸውን ከፍለው ያስተምሩ የነበሩ ወላጆች ያን ማድረግ በማይችሉበት ሁኔታ ላይ ይገኛሉ።

🖍“አንድም የኢትዮጵያ ተማሪ በቻይና በኮሮና አልተያዘም”- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ
በቻይና ለትምህርት ከሄዱ የኢትዮጵያ ተማሪዎች መካከል አንድም ተማሪ በኮሮና ቫይረስ አለመያዙን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አስታወቁ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት በዛሬው እለት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ከምክርቤቱ አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች መልስ በሰጡበት ወቅት ነው፡፡
መንግስት በቻይና ትምህርት ላይ ላሉ ዜጎች የተወሰነ ገንዘብ መላኩንም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ገልጸዋል። የቻይና መንግስት ለኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ላደረገው እንክብካቤ ፕሬዚዳንት ሺ ዥንፒንግን አመስግነዋል ።በቻይና ቫይረሱ በተከሰተበት ወቅት ተማሪዎቹን መንግስት ይመልስ የሚሉ ጥያቄዎች ነበሩ፤ ነገርግን ተማሪዎቹ በቻይና እንዲቆሩ ማድረጋችን ትክክለኛ ውሳኔ ነበር ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በእንቦጭ አረም ዙሪያ ከሰሞኑ ምክክር አድርገዋል
ከሰሞኑ በተካሄደው ምክክርም የምርምር እና የመከላከል ሥራዎችን ወጥ በሆነ መንገድ ለመምራት የሚያስችል ስምምነት ላይ መደረሱን በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የምርምር እና ማኅበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት መርሻ ጫኔ (ፕሮፌሰር) ገልጸዋል፡፡
ፕሮፌሰሩ የከፍተኛ በትምህርት ተቋሟቱ የሚሰሩ የምርምር ውጤቶችን ወስዶ በሥራ ላይ የማዋል ኃላፊነት የሌሎች ተቋማት በመሆኑ ከዚህ ቀደም በሚስተዋሉ የምርምር ሥራዎችን ተረክቦ የመጠቀም ውስንነትም በቀጣይ ይቀረፋል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ፕሮፌሰር መርሻ ተናግረዋል፡፡
የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የምርምር እና ማኅበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር መንበሩ ተሾመ አረሙን በሰው ጉልበት ለማስወገድ በዘመቻ መልክ መጀመሩን አስታውቀው ዘመቻውም በክልሉ ያሉ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተቀናጀ ትብብር የሚመሩት እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡

How to Get Better at Math
@timhirt_minister
@timhirt_minister
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
Limits and Continuity
@timhirt_minister
@timhirt_minister
#እንጅባራ_ዩኒቨርሲቲ ያመረተውን 2.3 ሚሊዮን ብር የሚገመት የእጅ ማፅጃ ሳኒታይዘር ለተቋማት አከፋፈለ
ሰኔ 05/2012 ዓ.ም፣ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
ዩኒቨርሲቲው ለጤና ተቋማት፣ ለማረሚያ ቤት፣ ለጸጥታ አካላት እንዲሁም ለመንገድና ትራንስፖርት የሳኒታይዘር ምርቶቹን ያከፋፋለ ሲሆን፤ የርክክብ ሥነ-ሥርዓቱም የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮችና የተረካቢ ተቋማት ኃላፊዎች በተገኙበት ተከናውኗል፡፡
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክና ምርምር ም/ፕሬዚደንት አዕምሮ ታደሰ(ዶ/ር) በርክክቡ ሥነ-ሥርዓት ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ዩኒቨርሲቲው የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ተከትሎ በተለያየ ጊዜ ሲሰራቸው ከነበሩ የማኅበረሰብ አገልግሎት ስራዎች በተጨማሪ 5,600 ሊትር ሳኒታይዘር በማምረት ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በማሰራጨት የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ መሆኑን ገልፀዋል፡፡