Telegram Web
ኦንላይን (Online) የከፍተኛ ትምህርት ለመስጠት የሚያስችል ረቂቅ አዋጅ መዘጋጀቱ ተገልጿል

የከፍተኛ ትምህርት መማር የሚያስችላቸውን መስፈርት አሟልተው ሳሉ በተለያዩ ምክንያቶች መማር ያልቻሉ ዜጎች የኦንላይን የትምህርት አሰጣጥ ዘዴን እንደ አማራጭ መንገድ በመዘርጋት ባሉበት ሆነው እንዲማሩ ለማስቻል እየተሰራ መሆኑን የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡

በኦንላይን የትምህርት አሰጣጥ ዘዴ በመጀመሪያ፣ በሁለተኛና ሦስተኛ ዲግሪ ደረጃ ትምህርት ለማስተማር ለሚፈልግ ተቋም የእውቅና ፈቃድና እድሳት ለመስጠት፤ ክትትል ድጋፍና ቁጥጥር ለማድረግ ረቂቅ መመሪያም ተዘጋጅቶ ግብአት መሰብሰብ መጀመሩን ነው ኤጀንሲው የገለጸው፡፡

ከዚህ ቀደም በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ኦላይን ተማሩ በሚል ይቀርቡ የነበሩት ማስታወቂያዎች ፍቃድ የሌላቸው እንደሆኑና በኢትዮጵያም በኦላይን ለማስተማር ፈቃድ የተሰጠው ተቋም እንደሌለ ሲገለጽ እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡
@timhirt_minister @timhirt_minister
የዛሬው የትምህርት ፕሮግራም

06/09/2012 14/5/2020

3:00 _ 3:30 Maths 11

3:40 _ 4:10 Biology 10

4:20 _ 4:50 Chemistry 7 Oro

5:00 _ 5:30 Physics 8

5:40 _ 6:10 History 11

6:20 _ 6:50 Biology 7 Oro


ከሰዓት በኋላ

8:00 _ 8:30 Chemistry 7

8:40 _ 9:10 Chemistry 12

9:20 _ 9:50 Physics 8 Oro

#Share
https://www.tgoop.com/joinchat-AAAAAE0QKKtUOAYfYSfXug
#EthiopiaFightsCOVID19

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ለኢትዮጵያ ኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ 10 የሙቀት መለኪያዎችን አበረከተ፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች ለኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከላከያ ከተበረከቱለት የሙቀት መለኪያዎች (Infrared Thermometer) ውስጥ አስሩን ለጉባኤው አበርክቷል፡፡

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማርያም ስጦታውን ሲያበረክቱ ጉባኤው ዜጎች በወረርሽኙ እንዳይጠቁና በጥንቃቄ መንፈሰ ጠንካራ እንዲሆኑ በማስተማር፣ በማረጋገት፣ በማጽናት እያደረገ ያለውን ተግባር አድንቀው አሁንም ግንዛቤ የመፍጠሩና የጥንቃቄ መልዕክቶቹን ማስተላለፉ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

በስነስርዓቱ የኢትዮጵያ ኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሃፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ ስለስጦታው አመስግነው ጉባኤው የሰው ልጆች ህይወትን ለማዳን ከማህበረሰቡ ጋር ተስማምቶ የወረርሽኙን መከላከያ እርምጃዎች እየወሰደ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በዝግጅቱ ማጠቃለያ ፕሮፌሰር ሂሩት እንዳሉት የስጦታው ዋና ዓላማ "በዚህ አስቸጋሪ ወቅት አንድነታችን እና መተሳሰባችንን ከሌላው ጊዜ በበለጠ እንደሚያስፈልግ ለማሳየትና ሌሎች ተመሳሳይ ድጋፍ እንዲያደርጉ ተነሳሽነት ለመፍጠር" ነው ብለዋል፡፡
@timhirt_minister
@timhirt_minister
#ወሎ_ዩኒቨርሲቲ

#ለመደበኛ እና ኤክስቴሽን ድህረ-ምረቃ ተማሪዎች በሙሉ።
@timhirt_minister
@timhirt_minister
አራቱ የፀረ ኮሮናቫይረስ የ’’መ’’ ህጎች

መቆየት
መራራቅ
መሸፈን
መታጠብ

• ህግጋቱን ተግባራዊ በማድረግ በሽታውን እንከላከል።
@timhirt_minister
@timhirt_minister
📺#የትምህርት_ፕሮግራም_በአፍሪ_ኸልዝ 📡

ቀን 06/09/2012 ዓ/ም

ትምህርት በቤቴ!
የአርብ የቀን 06/09/2012 ዓ/ም ትምህርት በቤቴ የቴሌቭዥን የስርጭት መርሃ ግብር


🔴 ፕሮግራማችሁን ጠብቃቹ እንድትከታተሉ ስንል እናሳስባለን።
@timhirt_minister
@timhirt_minister
እናንተ አሸንፉ እኛ እንሸልማቹሀለን
@timhirt_minister
@timhirt_minister
የአፄ ዘርዓ ያዕቆም የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን ድጋፍ አደረጉ::

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 የሚገኘው የአፄ ዘርዓ ያዕቆብ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን 61 ለሚሆኑ አቅም ለሌላቸው ወገኖች ከወር ደሞዛቸው በማዋጣት የምግብ ግብዓት ድጋፍ አድርገዋል። ድጋፍ ከተደረገላቸው አካላት መካከል በተማሪዎች ምገባ ሥራ ላይ ይሳተፉ የነበሩ እናቶችም ይገኙበታል።


በሥፍራው የተገኙት የክፍለ ከተማው ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፍቃዱ ካሳሁን የዚህ ትምህርት ቤት መምህራን ካለን እንካፈል በማለት ይህን በጎ ተግባር ማድረጋቸው እጅግ ያስመሰግናል። አሁን የመጣብንን በሽታም መከላከል የምንችለው እንዲህ በህብረት ስንተጓገዝና ስንሠራ ነዉ ብለዋል። ሥራ አስፈጻሚዉ አክለዉም በቀጣይም መተጋገዙ ይቀጥል፣ አቅም የሌላቸውን ሰዎች ከእኛ ውጪ ማንም ሊደግፋቸው ሰለማይችል ባለሃብቶችም በየ ቦታው ይህን በጎ ተግባር ማድረጋቸው እንደቀጠለ ተናግረዋል።

ሥራ አስፈጻሚው አቶ ፍቃዱ ይህን ላደረጉት የትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ምስጋናም አቅርበዋል።
@timhirt_minister
@timhirt_minister
ቀን 7 / 09 / 2012 ዓ/ም

የየካ ክፍለ ከተማ ወላጅ ተማሪዎች ህብረት ተማሪዎች በቤታቸው ሆነው በትምህርታቸው ላይ እንዲያተኩሩና ራሳቸውን ከቫይረሱ እንዲጠብቁ አሳሰበ::

የየካ ክፍለ ከተማ የወላጅ ተማሪዎች ህብረት በግልና በመንግስት ት/ቤቶች ሲማሩ ለነበሩና በክፍለ ከተማው ውስጥ ለሚገኙ ተማሪዎች በቤታቸው ሆነው እንዲያጠኑና ራሳቸውን ከኮቪድ-19 እንዲጠብቁ አሳስቧል::

ህብረቱ ከግንቦት 4-7/2012 ዓ/ም ድረስ የቤት ለቤት ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ ማከናወኑን የህብረቱ ፕሬዚደንት አቶ አለማየሁ ጆርጋ ገልፀዋል:: ቅስቀሳው በ14ቱም ወረዳዎች ህዝብ በሚበዛባቸው አካባቢዎች ለ4 ተከታታይ ቀናት መደረጉን ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል::

መንግስትና የተለያዩ አካላት ወረርሽኙን ለመከላከልና የዜጎችን ህይወት ለመታደግ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ባለበት በዚህ ወቅት አንድም ተማሪ የቫይረሱ ተጠቂ መሆን እንደሌለበት ህብረቱ ጥሪ አስተላልፏል::

ተማሪዎች ከቤታቸው ባለመውጣት የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ በአፍሪ ሄልዝ ቴሌቭዥንና በኤፍ.ኤም 97.4 ራዲዮ ላይ የሚተላለፉ የትምህርት ፕሮግራሞችን በአፅንኦት እንዲከታተሉ ህብረቱ አሳስቧል:: ወላጆች ልጆቻቸው በትምህርት ላይ መሆናቸውን መከታተልና ድጋፍ መድረግ እንዳለባቸውም ነው ህብረቱ ያሳሰበው::
@timhirt_minister
@timhirt_minister
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከጥቂት ወራት በፊት ዩንቨርሲቲዎቻችን ይህን መሰል ሁኔታ ላይ ይገኙ ነበር ፤ ኮሮና ከመምጣቱ በፊት ዩንቨርሲቲዎቻችን በተለይም ብሄር ተኮር ግጭት በርትቶ እንደነበር እሙን ነው።

ይሄ ክፉ ወረርሽኝ ሲገታ ዩንቨርሲቲዎቻችን እንደቀድሞው የስጋት ማዕከላት ይሆኑ ይሆን ወይስ ኮሮና ተማሪውን ወደ ልቦናው ይመልሰዋል?
@timhirt_minister
@timhirt_minister
#MOSHE

የተቋረጠው ትምህርት ሲቀጥል ጫና እንዳይፈጥር የሚያስችል ጥናት እየተደረገ ነው


በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የተቋረጠው ትምህርት ሲቀጥል ጫና እንዳይፈጥር የሚያስችል ጥናት እየተደረገ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

በዚህም የተቋረጠው የትምህርት ዘመን በምን መልኩ መቀጠል እንዳለበት የሚያጠና ቡድን ተደራጅቶ እየተሰራ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ኢትዮጵያ መግባቱን ተከትሎ ከተወሰዱ እርምጃዎች ውስጥ አንዱ የትምህርት ቤቶች መዘጋት ሲሆን ከመጋቢት መጀመሪያ አንስቶም በአገሪቱ ያሉ ትምህርት ቤቶች ዝግ ሆነው ቆይተዋል።

የትምህርት ሚኒስቴር የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር ወይዘሮ ሐረጓ ማሞ በወረርሽኙ ምክንያት ትምህርት ቤቶች ላልተወሰነ ጊዜ ዝግ እንዲሆኑ በመወሰኑ ተማሪዎች በሬዲዮና ቴሌቪዥን እየተማሩ ይገኛሉ ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
@timhirt_minister
@timhirt_minister
የዛሬው የትምህርት ፕሮግራም

10/09/2012 18/5/2020

3:00 _ 3:30 Bio 9

3:40 _ 4:10 chem 11

4:20 _ 4:50 phy 12

5:00 _ 5:30 math 8

5:40 _ 6:10 Bio 7

6:20 _ 6:50 Chem 11


ከሰዓት በኋላ

8:00 _ 8:30 Phy 10

8:40 _ 9:10 Phy 7

9:20 _ 9:50 Math 8 Oro
@timhirt_minister
@timhirt_minister
#ሰበር_ዜና

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 35 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል!

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 1,775 የላብራቶሪ ምርመራ 35 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 352 ደርሷል፡፡
@timhirt_minister
@timhirt_minister
TUESDAY , 19 05 2020 , Tv schedule
@timhirt_minister
@timhirt_minister
AFAAN ORO.MODEL AMHARIC K 8-.pdf
243.8 KB
AFAAN AMAARAA

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የተዘጋጀ የአፋን ኦሮሞ የ 8ኛ ክፍል አማረኛ ሞዴል ፈተና እንደሚከተለዉ የቀረበ ሲሆን ተማሪዎች እራሳችሁን እንድትፈትሹበትና ወላጆችም ተገቢዉን እገዛ እንድታደርጉላቸዉ እና በአግባቡ ፈተናዉን መውሰዳቸዉን እንድታረጋግጡ እንጠይቃለን፡፡
@timhirt_minister
@timhirt_minister
AMHARIC MODEL EXAM GRADE .8 .pdf
322.1 KB
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የተዘጋጀ የ 8ኛ ክፍል አማርኛ ሞዴል ፈተና እንደሚከተለዉ የቀረበ ሲሆን ተማሪዎች እራሳችሁን እንድትፈትሹበትና ወላጆችም ተገቢዉን እገዛ እንድታደርጉላቸዉ እና በአግባቡ ፈተናዉን መውሰዳቸዉን እንድታረጋግጡ እንጠይቃለን፡፡
@timhirt_minister
@timhirt_minister
ENGLISH MODEL EXAM GRADE 12.pdf
709.5 KB
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የተዘጋጀ የ 12ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና እንደሚከተለዉ የቀረበ ሲሆን ተማሪዎች እራሳችሁን እንድትፈትሹበትና ወላጆችም ተገቢዉን እገዛ እንድታደርጉላቸዉ እና በአግባቡ ፈተናዉን መውሰዳቸዉን እንድታረጋግጡ እንጠይቃለን።
@timhirt_minister
@timhirt_minister
2025/07/12 00:34:15
Back to Top
HTML Embed Code: