tgoop.com/Tafakur_Mastenten/734
Last Update:
#እርግብ
እርግቦች በተፈጥሯቸው እጅግ ኢምንት Brain Size የተሰጣቸው ፍጡራን ናቸው፡፡ እርግቦች በጭንቅላት እርከን ከእንስሳት መካከል ከውራዎቹ መሐል ናቸው፡፡ ብልጥ ከሚባሉት እንስሣት ከድመት፣ ከውሻ፣ ከአይጥ፣ ከቺምፓንዚ፣ ከዶልፊን፣ ከአሣነባሪ፣ ከካንጋሩ፣ እና ከመሣሠሉት ጋር ሲነፃፀሩ ራሱ – እርግቦች – በቃ የዋህ መባላቸው እውነት ነው፡፡ አላህ ሱ.ወ ለእርግቦች የዋህነትን እንጂ ጭንቅላትን አልፈጠረባቸውማ፡፡ 1.2 ኪሎ ግራም ከሚመዝነው የሰው ልጅ ምጡቅ አዕምሮ ጋር የእርግቦችን ሚጢጢ አዕምሮ ካነፃፀርን – በቃ እኛ ሰዎች – ለእርግቦች – ጌታቸው ነን – ለማለት ይዳዳል፡፡
እርግቦች ጭንቅላት የላቸውም፡፡ ወይም ቴስታታቸው ኔፓ ነው፡፡ ግን ግን አንድ ነገር ልብ በል፡፡ በልጅነቱ እርገቦችን ያረባ፣ አሊያም የእርግቦችን ‹‹ኩኩ መለኮቴ›› ከጣራው ላይ እየሠማ ያደገ ማንም ሰው – የሚያውቀው አንድ ታላቅ የእርግቦች የተፈጥሮ ፀጋ አለ፡፡ የማፍቀር ፀጋ፡፡ እርግብ ሁሉ ያፈቅራል፡፡ አፍቃሪዎች ናቸው፡፡ ያለመሰልቸት ቀኑን ሙሉ አንዳቸው የሌላኛቸውን ላባ ሲያክኩ ይውላሉ፡፡ ወንዱ የሴቷን እንቁላል ይታቀፍላታል፡፡ አንዱ ገላውን ሲታጠብ ውሃ በሌላኛዋ ላይ ይረጫል – ለጨዋታ፡፡ አንዱ ምግብ ሲያገኝ በመንቁሩ እየነካካ ሌላውን ይጣራል፡፡ ወንድና ሴት እርግቦች ተሳስመው ውለው ቢያድሩ አይጠግቡም፡፡ በቃ እርግቦች የማፍቀር ፀጋ የተሰጣቸው – ዝም ብለው ለማፍቀር እና ለመፈቃቀር – ፍቅርን ለመስጠትና ለመቀበል ዝግጁ ሆነው የተፈጠሩ – የምድሪቱ ፍቅር እስከ መቃብር ፍጡራን ናቸው፡፡
👉 @Tafakur_mastenten 👈
BY ተፈኩር
Share with your friend now:
tgoop.com/Tafakur_Mastenten/734