tgoop.com/Tenshu6793/140
Last Update:
💚💚💚💚 የጀይላኒ ጀባታ 💚💚💚💚
• እነሆ ጀግና! እነሆ የመርካቶ ዛሂድ..! ዛሊከ ፈድሉላህ
<< ሙሐባ♡ እውነተኛ ቅዱሱን ፍቅር የኡ
ስታዝ ፈድሉ ሙሪዶች ጋር ፈልገው! >>
እንደ ቀልድ ዓመት...!
የበርካታ ሱቆች ባለቤት ሆኖ ቤት ቪላም ይሁን ኮንዶሚኒየም ቤት አልገዛም! መኖሪያው አንዋር መስጂድ ነበር።
ትልቅ ገቢ ኖሮት መስጂድ እየዋለ እያደረ ያውም መሀል መርካቶ ነጋዴዎች የመኪና አዳዲስ ሞዴሎችን በሚያቆሙበት ቢሊዮን ብሮች በሚንቀሳቀሱበት ነጋዴዎች መናሀሪያ መሀል መርካቶ... ገጠር ዛውያ ላይ ዛሂድ መሆን ቀላል ነው ምንም የዱንያ ብልጭልጭ ከእይታህ ይሰወራል... ኡስታዝ ፈድሉ እኮ መርካቶ መሀል ሆኖ 100 ካሬ ያልገዛ.. አዲስ የለበሰውን ቆንጆ ልብስ ከወር ቡሃላ መርካቶ ዙሪያ ያሉ ሚስኪኖች ለብሰውት ታየዋለህ...
ፆም ያበዛል የኸሚስና የኢሥነይን ቀበኛ ሱንይ ጿሚ ነው... በ24 ሰዓት አንዴ ሳይሆን በ72 ሰዓት አንዴ ብቻ ሊበላ ይችላል...
ሚንሁም መን ተረከ ሹርበን ወመእከላ
ሚንሁም መን ተረከ ዘውጀተን ወማላ
መስጂድን መኖሪያ ቤቱ ማድረጉ ብቻውን እንዳይገርምህ ትዳር አድርጎ የያዘው ደግሞ ከላሙላህን ቁርአንን ነበር። ስንትና ስንት ወዳጆቹ ቆነጃጅት ቢክራ ልጆቻቸውን እንዳርህ ጀባ ብለውታል ኡስታዝ ፈድሉ እንደ ሸይኽ አሕመድ አመዴ ውልም አላሉበት። ሚስት ሳይኖረው ብዙ ወጣቶችን የመኸር እየከፈለ ቤት እየተከራየ ብዙዎችን ባለትዳር አድርጓል...
ኡስታዝ ፈድሉ የረሱለላህን ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ፍቅር ልክ እንደ አሚና አረገዘ... ሀምዛ ኢብን ዓብዱልሙጠሊብ ለነቢ እንደተሰዋ ኡስታዝ ፈድሉ ለዲን ሙሐመዲያ ሸህዋውን ንብረት መያዝን ሰዋ። ሰልማን አል-ፋሪስ ለረሱለላህ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም 5 ግዜ በባርነት እንደተሸጠ ኡስታዝ ፈድሉ በዒልሙ ጥልቀት ኢማምና መሪ መሆን እየቻለ የቲሞችን ሚስኪኖችን ኻዳሚ በመሆን ነፍስያውን ሸጠ...
ሸዋል በሚወዳት የኢሥነይን ሌሊት ከአንዋር መስጂድ ወደ ዓለመል በርዘኽ መኖሪያ ሲቀይር ልብሶቹ ኪታቦቹ ገንዘቦቹን ሁሉ ለሚገባቸው ሰዎች አከፋፍሏል... ኡስታዝ ፈድሉ የሙሪዶቹ ሕይወት ላይ ከእናት ከአባታቸው በላይ ጠልቆ እየገባ ሕይወታቸውን እየቀየረ ያረገላቸውን ለማንም እንዳይናገሩ አደራ ይጥልባቸው ነበር...
ሪደላህን የአላህን ውዴታ በመሻቱ አላህ መውደድን ወዶት ረዲየላሁ ዓንሁ ወአርዳ ዓንሁ ናስ በሰዎችም አስወደደው።
ለስላሳ ለወጣቶች ገራም ለሴቶች ሩሕሩህ
ሀገር ከቀየረ ዓመት ሞለው... ታዲያ ሙሪዶቹ ደረሶቹ በየቀኑ ፋቲሐ ይቀሩለታል... ዛቱ ሙሐመድይ ሲፈቱ መለክይ መሆኑን ትንሽ ቀናት አብሮ ያሳለፈ ወዳጁ ለወር ሲናገረው ያንን ቂሳ ታገኛለህ...
ኡስታዝ ፈድሉ ቤት አይግዛ እንጂ በ11ዱም ክፍለ ከተሞች ያሉ ወዳጆቹ በውጭም ባገርም ባሉ ሙሒቦቹ ጋር በየቀልባቸው በየቤታቸው እየተወሳ አብሯቸው ውሎ አብሯቸው ያነጋል...
ሚስት አይኑረው እንጂ የዘመናችን ሴቶች ባላቸውን ከሚያፈቅሩት በላይ ኡስታዝ ተፈቅሯል እየተፈቀረ ነው... ይፈቀርማል ፍቅሩ ስጋዊ አይደለም አል-ሑቡል ሐቂቂይ...
በስጋ ልጅ አይኑረው እንጂ
እኔ አንተን እንጂ ~ አላውቅ አባቴን
በኡስታዝ ፈድሉ ረሳሁ ~ የቲምነቴን
የሚሉለት ከኮልፌ እስከ ፒያሳ ከተክለ ሀይማኖት እስከ ቦሌ... ደቦል ደቦል የሩሕ ልጆች አሉት።
ኡስታዝ ፈድሉ ق እንደ አባበክር ሲዲቅ ሙሉ ሀብት ንብረቱን ለዲኑ አዋለ። ወዲህ ደግሞ እንደ አባ-ዘር አል-ጊፋርይ.. አል-ፋቲሐ!
# ትንሹ አሚር
በቴሌግራም
❀ይ🀄️ላ🀄️ሉን!
➢🍀🍀🍀
👇👇👇
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
BY ❤ ፈ ዳ ኢ ሉ
Share with your friend now:
tgoop.com/Tenshu6793/140