tgoop.com/Tenshu6793/154
Last Update:
የኢማን ተፅእኖ
💚💚 ሂስነይኖ💚💚
****
ቡርሃኑን ሙቢን በተሠኘዉና ኢማም ሙስሊም ባወሩት አጭር ታሪክ - አንድ ሰው በእንግድነት ነብዩ (ሶ.ዐ.ወ) ዘንድ አረፈ። እንግዳቸው ነዉና ፍየል እንድትታለብለት አዘዙለት፤ ሰውዬው ከታለበው ጠጣ፡፡ ሁለተኛም አዘዙለትና ጠጣ፡፡ ሶስተኛም አራተኛም አዘዙለት፡፡ ሰባቴ ድረስ ጠጣ። ሰውዬው እዚያው አደረ። በነቢዮ (ሶ.ዐ.ወ.) በረከት አላህ ልቡን ለእስልምና ከፈተለት። ሙስሊም ሆኖ አነጋ፡፡ እምነቱንም ይፋ አደረገ።
የአላህ መልዕክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) ጠዋት ላይ ወተት እንዲታለብለት አዘዙና ጠጣ፡፡ ሁለተኛ ታዘዘለት፡፡ መጨረስ አልቻለም። በዚህን ጊዜ የአላህ መልዕክተኛ ሁሌም ሲወሳ የሚኖር ቃል ተናገሩ፡፡ እንዲህ በማለት ፡- “ሙእሚን በአንድ አንጀት ነው የሚጠጣው፣ ካፊር ግን በሰባት አንጀት ነው የሚጠጣው፡፡”
በዚህ መልኩ የኢማንን ተፅዕኖ እናያለን። ያውም በአንዲት ሌሊት ልዩነት፡፡ ሰዉዬው ካፊር እያለ ትልቁ ጉጉት የነበረው ሆዱን መሙላት ነው። የተፈጠረበትን ዓላማ የማያውቅ ከእንሰሳ ያልተለየ ባህሪ ነበረውና። ሲሰልም ግን ወዲያው ተለወጠ፣ ከምግብ አንፃር ቁጥብ እና የተብቃቃ ሆነ፡፡ ጉዳዩ ምን ይሆን በዉስጡ የተቀየረው ነገር? ብሎ የሚያስጠይቅ ነው። ቀልቡ ዉስጥ የተለወጠ ነገር ይኖር ይሆን! አዎን ከካፊርነት ወደ አማኝነት ተቀየረ። በዚህ አጭር ጊዜ ዉስጥ ፈጣን ለውጥ ሊያመጣ የሚችለው ኢማን እንጂ ሌላ ምንም ሊኖር አይችልም።
اللهم_صل_على_سيدنا_محمد_وعلى_آله_وصحبه_وسلم
#✍️ አሚር ትንሹ
በቴሌግራም
❀ይ🀄️ላ🀄️ሉን!
➢🍀🍀🍀
👇👇👇
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
BY ❤ ፈ ዳ ኢ ሉ
Share with your friend now:
tgoop.com/Tenshu6793/154