tgoop.com/Tenshu6793/155
Last Update:
የረጀብ ወር እና ልቅናው
==== ⨳ ===== ⨳ ====
*
*•══༻◉••﷽••◉༺══•*
🌺 إِنَّ عِدَّةَ الشُّهُورِ عِندَ اللَّهِ اثْنَا عَشَرَ شَهْرًا فِي كِتَابِ اللَّهِ يَوْمَ خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ مِنْهَا أَرْبَعَةٌ حُرُمٌ ۚ ذَٰلِكَ الدِّينُ الْقَيِّمُ ۚ فَلَا تَظْلِمُوا فِيهِنَّ أَنفُسَكُمْ ۚ 🌺
🌺የወሮች ቁጥር አላህ ዘንድ በአላህ መጽሐፍ ውስጥ ሰማያትንና ምድርን በፈጠረበት ቀን ዐሥራ ሁለት ወር ነው፡፡ ከእነሱ አራቱ የተከበሩ ናቸው፡፡ ይህ ቀጥተኛው ሃይማኖት ነው፡፡ በእነርሱ ውስጥም ነፍሶቻችሁን አትበድሉ፡፡🌺
🔮 ሱረቱል ተውባ 9፥ 36
*
በሒጅራ ካላንደር ሰባተኛ ወር መግባቱን ያበስራል ወርሃ ረጀብ... እንዲሁም በኢስላም ከተመረጡት አራት ወራቶች አንዱ ሲሆን የተቀሩትም ዙል ቃኢዳ ፣ ዙል ሂጃ እና ሙሀረም ናቸው... እነዚህ ወራት ከእስልምናም በፊት በነበሩ የመካከለኛው ምስራቅ አረቦች ይከበሩ እንደነበር መዛግብቶች በሰፊው ይተርካሉ...
*
💚💕 ኢማም አልጋዛሊ ሙካሸፍ አል ቁሉብ አል አክበር የተሰኘው ኪታባቸው ላይ ... ረጀብ ... "አት_ተርጂብ" ከሚለው ቃል የመጣ ሲሆን 'ተከበረ' ወይንም 'ተላቀ' ማለት ነው ... ረጀብ በሌላ ስሙ "አል-አሰብ" በመባል ተጠርቷል... ይህንንም ያሰኘው የአላህ እዝነት ፣ ፀጋና ይቅርታ ከወንጀላቸው ለተፀፀቱ እና በኢባዳ ለሚዘወትሩ ባሮቹ የሚፈስበት እና የሚንቧቧበት ወር በመሆኑ ነው ... ከዚህ በተጨማሪም "አል-አሲም" ወይንም ደንቆሮው ተብሎ ተገልጿል የዚህም ምክንያቱ ወሩ በቀደምት አረቦችም የተከበረ እና ውጊያ(ግጭት) የማይፈቀድበት በመሆኑ ነው ብለው ከትበዋል ...
*
💚💕 ኢማም አልጋዛሊ በዚሁ ኪታብ ላይ ረጀብ የሚለው ቃል ከሶስት ፊደላት የተዋቀረ ሲሆን ... ራ - ራህማ (እዝነት) ፣ ጂም - ጂናያህ /ጁርም (ወንጀል / ሀጢያት) ፣ ባዕ - ቢር (ቸርነት) የሚለውን የሚወክሉ ሲሆኑ ...💚💕 አላህ ሱብሀነሁ ወተአላ 'ወንጀላችሁን በእዝነቴና በቸርነቴ መሀከል ነው የማስቀምጠው' ማለቱ ነው የሚል ማብራሪያም አስፍረዋል ...
*
💚💕 ኢማም ሙሳ ካዚም እንደተናገሩት ... "ረጀብ ጀነት ውስጥ ያለ ከወተት የነፃ ከማር የጣፈጠ ወንዝ ስም ነው... በዚህ ወር ነብሳቸው ከወንጀል የፆመች በበጎ ስራ የተጠመደች ሰዎች የተመነዳች ናት..." ይላሉ .
*
💚💕 አሽረፈል ኸልቅም ﷺ " ረጀብ የአላህ ወር ነው... ሸእባን የኔ ወር ነው... ረመዳን የዑመቶቼ ወር ናት..." ማለታቸው ይታውቃል... የወራት ሁሉ ባልተቤትነት የአላህ ቢሆንም እቺ ረጀብ የተባለቺው ወር በውስጧ የያዘቺው ፀጋ እና ፍፁምነቷ የአላህ ወር አሰኝቷታል...
*
💚💕 ኢማሙ ሻፊዒይ ረህመቱሏሂ ዐለይህ "ኡም"በሚባለው መፅሀፋቸው ስለ ሁለቱ ዒዶች በሚያወራው ርዕስ ውስጥም ይህንን ብለዋል
በአምስት ሌሊቶች ዱዐእ ተቀባይነቱ የጎላ ነው ይባል እንደነበረ ደርሶናል፣ እነርሱም:–
1) የጁሙዐ ሌሊት
2) የዒደል አድሀ ሌሊት
3) የዒደል ፊጥር ሌሊት
4) #የረጀብ_ወር_የመጀመሪያው_ሌሊት
5) የሸዕባን 15 ሌሊት ናቸው።
*
አዕሪፎቹ እንዳመላከቱት ረጅብ የሚዘራበት ወር ሲሆን ፤ ሻዕባን የዘራነውን የምናጠጣበት፤ ረመዳን ደግሞ ምርቱን የምናጭድበት ነው ... በረጀብ ያልዘራ ፣ በሻዕባን ያላጠጣ በረመዳን ሊያጭድ አይችልም ... ከላይ እንደተጠቀሰው የረጀብ ወር የመጀመሪያው ሌሊትም ብዙ ትሩፋት ያሉበት ለይል ነውና ገላ
# "አሚር ት'ንሹ"
በቴሌግራም
❀ይ🀄️ላ🀄️ሉን!
➢🍀🍀🍀
👇👇👇
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
BY ❤ ፈ ዳ ኢ ሉ
Share with your friend now:
tgoop.com/Tenshu6793/155