tgoop.com/Tenshu6793/161
Last Update:
☘☘ የ ኛ ነብይ ﷺ💚💚
ፊተ ብሩህ ናቸው። ንጣት ከቅላት ጋር ተዋህዶ አስደማሚ ቀለም ችሯቸዋል። ኩልል ብሎ የሚፈሰው ላባቸው እንደ ሉል ፅዱና አንፀባራቂ ነው። ሲራመዱ ከዳገት ላይ የሚንደረደሩ ይመስላል።
♤اللهم صلي وسلم وبارك على نبينا محمد ﷺ
መሬቱን አይጫኑትም። ለመሬቱ የሚሳሱ ያስመስልባቸዋል። ዕይታቸው በብዛት ወደ መሬት ነው። ማንነትን ሳይለዩ መንገድ ላይ ለሚያገኙት ሁሉ ሰላምታን ያቀርባሉ። ከሩቅ ሲታዩ ያስፈራሉ። ሲቀርቧቸው ይፈቀራሉ።
♤اللهم صلي وسلم وبارك على نبينا محمد ﷺ
"ቀጭኑንም ሆነ ወፍራሙን ሐር በእጄ ዳስሻለሁ ነገር ግን እንደ ረሱልﷺመዳፍ ለስላሳ ነገር ዳብሼ አላውቅም። ሚስክና ዐንበርን አሽትቻለሁ። እንደ አላህ መልዕክተኛﷺመዓዛው የሚማርክን ነገር አሽትቼ አላውቅም" ይላል ኻዲማቸው አነስ ኢብኑ ማሊክ።ነቢዩንﷺበዓይነ ሥጋ ለማየትና ለማወቅ የታደሉት ሁሉ ወዲያው ነበር በውዴታቸው የሚጠመዱት፡፡
♤اللهم صلي وسلم وبارك على نبينا محمد ﷺ
ስለረሱልግመል ቀስዋ ፍቅር ትንሽ ላውጋችሁ። ከነቢ ህልፈት በኋላ ፍፁም ጤና ራቃት። ማንንም በጀርባዋ ለመሸከምም ሆነ ማንንም ለማጓጓዝ ፈቃደኛ አልሆን አለች። በሀዘን ኩርምት ጭምት አለች። እህል ውሀ መቅመስ ተሳናት። ለአንድ ወር ያህል አፏን ከምግብና ከእህል ከልክላ ሠነበተች።
♤اللهم صلي وسلم وبارك على نبينا محمد ﷺ
እጅግ ከማልቀሷ ብዛት ሁለት አይኖቿ ታወሩ። መገን ፍቅር!ወዲጄ እየነገርኩህ ያለሁት ስለሚስቶቻቸው አልያም ስለባልደረቦቻቸው አይደለም። ስለ ቀስዋእ ግመል ነው።በናፍቆት፣ በሀዘን፣ በለቅሶ፣ በረሃብ፣ ብዛት ተጎሳቁላ "ያለ ረሱልﷺህይወት ለምኔ" በማለት በ14 ዓመቷ በናፍቆት እንደተንገበገበች ይህቺን ጠፊ ዓለም ተሠናበተች።
♤اللهم صلي وسلم وبارك على نبينا محمد ﷺ
አሚር ትንሹ
በቴሌግራም
❀ይ🀄️ላ🀄️ሉን!
➢🍀🍀🍀
👇👇👇
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
BY ❤ ፈ ዳ ኢ ሉ
Share with your friend now:
tgoop.com/Tenshu6793/161