tgoop.com/Tenshu6793/206
Last Update:
" እልፍ አላፍ ኩርኩሞች የቀመሱ ዕራሶች
ዳባች የፍቅር እጆች እንጂ ዕይሹም ትራሶች "
❤ ትንሹ አሚር ❤
🌿 🌿 🌿 ለይለቱል ጁመዕ 🌿 🌿 🌿
❤️ አሶላት ወሰላም አለይክ
ወል አሊ ወሶ ሃበቲ
ያ ሸምሰን ፊል መዲነቲ 💚
💚ለሓይባው ብራና ገልጦ
ጀማሉን ዳኢም አፍጥጦ
ተዳልጦ ያው ገባለት
💚ሰምተነው ከጌቶች መንደር
ጣፈጠን አይኑን መንደርደር
እያደር ስሙን ማንሳት
💚የዱንያው የኡኺራ ሹሙ
ደባብሱኝ አባ ቃሲሙ
ሂያሙ መስሎኛል ሞት
💚ናፍቆቱ ሆድ እያስባሰ
የስንቱ ገላ ፈረሰ
ታረሰ በሚያምረው ዛት
💚 ና በል ኮርጅ ከነዛ
ኮራጁም አይደል የዋዛ
ኢጃዛ ለሱ እስኪሰብት
💚 ግንባሩ ማ ኑር አውድማ
ፈሶበት የጀማል ጣዝማ
ለይላም ሰልማ ሞቱለት
💚በአሏህ ስም ሃዩል ቀዩውوሙ
በጀዋዱ በከሪيሙ
ለኺድማው በል ግባለት
💚ግንባሩ ያስኋባ ደውሩ
የጣፈጠበት አዝካሩ
ሥር ሥሩ ኮልኩሎለት
💚ጠጉርሁን ኡሙ ሰለመት
አኑራው ውሃ ነክራበት
ታማሚው ሊሽረበት
💚ጠጉርሁ ደምቆ አደመቀን
ዘለላው ሲባል ሸወቀን
ላሳር ቀን ነው መድሃኒት
💚ጠጉሩማ ሙእጂዛው ዞማ
ደረቱን ዞራ ገልድማ
አንገቱን ሸፋፍናለት
💚አይኑማ ሱብሃነል ቁዱوስ
አርጎታል ጁምዐ ኢድ عሩውስ
በል አድሩስ አጭስለት
💚ጠጉርሁን ሰይድ ኻሊዱ
አንግቦት ለጦር ሲሄዱ
ሽንፈት ሚባል ጠፋበት
💚አይኑማ ይብቃህ ለገድሉ
በአሏህ ዛት ልቆ መኳሉ
ተገልጦለት አስችሎት
💚 ከንፈሩህ የኑር ተምር
ለ አሚነት ሲዘምር
ሲያሽር ያንቱስ ውልደት
💚አይኑማ ቢያየኝ ከጦይባ
በኢናያው ተጀዝባ
ተጣጥባ ነፍሴ ላትስት
💚ሺ ዩሱፍ ሺ ሸምሰል ጀማል
በዛቱህ ሺ አቅማር ኸትሟል
በጀላላው ደብቆት
💚ጉንጭሁ ንጥር ነው ሰፈፍ
ሃሳን አይቶት ቢንሰፈሰፍ
ያ አሽረፍ ሲል ኖረለት
💚ጀማሉህማ ሃቂቃው
ያሏህ ሂጃብ ባይጠብቀው
ያቃጥል ነበር ከውናት
💚እሱ ነው እሱ ነው በቃ
ሩሁል ከውን ለዉጁድ ጭቃ
አይበቃ ያለርሱ ህይወት
💚ትከሻውማ መስፋቱ
ምናሉውሁ ከአስርቱ
ጉያችን ስንፈራ ሞት
💚 እጅሁ ያሏህ ጁድ ድንኳን
ላደም መህር ለሃዋ መልኳን
የሁሏን ሃቋን ሰጣት
💚እጅሁ ለኑህ ለኸሊል
የአማን የከረም ኢክሊል
የጀሊል ካዝና ስጦት
💚 ባያልቅም እንኳ መደዱ
ደካማን ቁዋ ማስካዱ
ዝሎበት ሊቆምለት
💚እግሩማ ተው የግሩ ጫማ
ነጠላው ረግጧል ስማማ
በዐርሹ ራስ ሰፍሮበት
💚እጅሁ ለኑህ ለኸሊል
የአማን የከረም ኢክሊል
የጀሊል ካዝና ስጦት
💚በሲዲቅ ሷሂበ ተስዲቅ
መን ሳረ ቀልቡሁል ሙህሪቅ
አስለሙ ኩሊል አብያቲ
💚 ሶላት ሰላም ተጦያይባ
ስትዘምር ከወደጦይባ
ነሲሙ ትንፈስሎት
❤️አሶላት ወሰላም አለይክ
ወልአሊ ወሶሃበቲ
ያ ሸምሰን ፊል መዲነቲ💚
اللهُمَّ صَلِّ عَلَى حبيب ربي. وطب قلبي مولانا محمد وعلى آله ،،وارزقنا الحُب مع الأدب،،،ويسر لنا الوصول بلا تعب لحضرة حبيبك شريف النسب...
#ትንሹ አሚር
በቴሌግራም
❀ይ🀄️ላ🀄️ሉን!
➢🍀🍀🍀
👇👇👇
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
BY ❤ ፈ ዳ ኢ ሉ
Share with your friend now:
tgoop.com/Tenshu6793/206