Warning: Undefined array key 0 in /var/www/tgoop/function.php on line 65

Warning: Trying to access array offset on value of type null in /var/www/tgoop/function.php on line 65
- Telegram Web
Telegram Web
ልስላሴና እዝነት የተሰጠው ሰው ሁሉም ነገር ተሰጥቶታል🥰 አንዳንድ ፊቶች  ሲወቅሱን እንኳን  ያምራሉ እኮ ከፈገግታ ጋር የሚያስደብሩን ፊቶችንም አይተናል የነፍስ ነገር ይመስለኛል እዝነት ያለውና ለስለስ ያለ ስብዕና ይማርካል…  እየተጮኸብን እንኳን።

"ድርባ እና ብልኮ መች ጠፋ እና በሀገር
    አላስተኛ አለ እንጂ የትዝታ ነገር
     የናፍቆት ክፍቱ  የበደሉ በደል
ሲመሽ ነፍስ ይዘራል ስፈራ ሲደለደል"

           ✍️* አሚር ትንሹ *

በቴሌግራም
❀ይ🀄️🀄️ሉን!
🍀🍀🍀
👇👇👇
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
اللهُمَّ صَلِّ عَلَى حبيب ربي. وطب قلبي مولانا محمد وعلى آله ،،وارزقنا الحُب مع الأدب،،،ويسر لنا الوصول بلا تعب لحضرة حبيبك شريف النسب...
በቴሌግራም
❀ይ🀄️🀄️ሉን!
🍀🍀🍀
👇👇👇
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
ለይለቱል ጁመዕ

" ሰይዳችን ﷺ ላይ ሰለዋት ማውረድ ሙስተጃብ የሆነ ዱዓ ነው "

እሳቸው ላይ ሰለዋት ማውረድ ሀሳቡ የሆነ ያሰበውን ነገር ሁሉ ይደርሳል ከሰጋው ነገር ሁሉ ይጠበቃል። ጉዳዮቹ ይሳካሉ ። ህይወቱ ያምራል። ምላሱን አንቀሳቅሶ ሀጃዎቹን ሳይጠይቅ ይሳኩለታል። ሰለዋት ተቀባይነቱ የተረጋገጠ ዱዓ ነው

"ድርባ እና ብልኮ መች ጠፋ እና በሀገር
አላስተኛ አለ እንጂ,የትዝታ ነገር
የናፍቆት ክፋቱ የበደሉ በደል
ሲመሽ ነፍስ ይዘራል ስፈራ ሲደለደል"🥺

ሰ * ላ * ሜ

اللهُمَّ صَلِّ عَلَى حبيب ربي. وطب قلبي مولانا محمد وعلى آله ،،وارزقنا الحُب مع الأدب،،،ويسر لنا الوصول بلا تعب لحضرة حبيبك شريف النسب...

#አሚር ትንሹ

በቴሌግራም
❀ይ🀄️🀄️ሉን!
🍀🍀🍀
👇👇👇
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
🌼🌼 🌼 የጀይላን ጀባታ 🌼 🌼🌼

የአላዲን ምንጣፉ በሰማይ
.......ጋለበ ቢልም ተረቱ
.......ተረቱን አለም ለረቱ
.......ለሰማይ ለሚበረቱ
.......ገድል ታሪኳም ባይፅፍ
.......ማብረር ታውቃለች ምንጣፍ
.......አብርራኝ ነበር ምንጣፌ
......ወደኩኝ እንጂ በአፌ

ምንጣፌን ፊትህ ዘርግቼ....
አጥፌ ደግሞ ጠፍቼ....
አላዲን መሆን ብመኝም....
አለ ዲን አልሆነልኝም ....

...አፌ ሰበረው እምነቴን...
...ጌታዬ እንካ ፀሎቴን...
...ምላሴን ምንጣፍ አድርጋት...
...ከሰው ጋር ሲሆን አጥፌ...
...ካንተ ፊት ብቻ ልዘርጋት...

ትንሹ አሚር🙏

በቴሌግራም
❀ይ🀄️🀄️ሉን!
🍀🍀🍀
👇👇👇
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
🍀🍀🍀 ለይለተል ጁመዕ 🍀🍀🍀

የፈጣሪ ፍራቻ በሁለት ይከፈላል አለኝ ወዳጄ
                          👇
፩) ፈጣሪ ፍራቻ ጌታችን እንደ ጋንጊስተር.... ቅጣቱ የበረታ.....ከጥፋታችን ብዛት ጀሀነም (ገሃነም) ላለምውረድ ቅጣቱን ፍራቻ መገዛት  ሲሆን

፪) በፈጣሪህ ፍቅር መውደቅ የምትወደው ላለማጣት ፍራቻ ባጠፋህ ቁጥር ምህረት እና እዝነቱ ካንተ እንዳይርቅ መፍራት ነው.....ይህ ፍራቻ ከመጀመሪያው ሚለየው ያሀ እንዳይቀጣህ ስትፈራው ይህ ደግሞ ፍቅሩን እንዳታጣ መፍራት ነው


ጌታዬ ሆይ እንዳትቀጣቸው ከሚፈሩት ሳይሆን አፍቅረውህ ፍቅርህን እንዳያጡ ከሚፈሩት አድርገኝም አድርገን🙏🤲

#አሚር ትንሹ

በቴሌግራም
❀ይ🀄️🀄️ሉን!
🍀🍀🍀
👇👇👇
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
💚💚 አንሰንበት(ቀዩዋ ቀን)💚

በፍቅር ህይወት ውስጥ ሰምጠን፣
የናፍቆት ረመጥ ባህሩን አቋርጠን፣
በናፍቆት ያለፍነውን ቀናቶች ረስተን፣
አላፊ አግዳሚውን ሁሉንም ረስተን፣
በፍቅር በናፍቆት ሰምጠን ተቃቅፈን፣
በደስታ ብዛት ምናወራው ጠፍቶን፣
አይን ለአይን ካንቱ ጋር እየተያየን፣
አንደበታችን ተሳስሮ ቃላቶች ቢጠፋን፣
አፈቅሮታለው እንጂ ሌላ ቃል ጠፋን፣
መገናኘትን ስናስብ መለያየትን ፈራን፣
ቁጭ ብለን በመጅሊሳችን ስንጣራ አንቱን፣
እውን ሆኖ ማየት ነው ልክ እንደ ሀሳባችን፣
ጠይቀነዋል ከራህማን  ፈጣሪያችንን፣
አውግተን ጨርሰን ልንሄድ ወደ ሀረማችን፣
መገናኘት ፈራን ሲደርስ ሰዓታችን፣
ሰዓቱ እንዳይቆጥር ባለበት እንዲቆም፣
ግን ምን እናድርግ ማቆም አንችልም፣
ባለበት እንዲቆይ ብንፈልግም፣
ምኞት እንጂ እውን አይሆንም፣
ሰዓታችንም ደርሶ ልንለያይ ነው፣
የጠፋውን ናፍቆት ልንቀሰቅሰው፣
መገናኘት ስናስብ መለያየትን ምንፈራው።

# ትንሹዬ😍

በቴሌግራም
❀ይ🀄️🀄️ሉን!
🍀🍀🍀
👇👇👇
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
💚💚💚 ❤️ለይለቱል ጁመዕ❤️ 💚💚💚

ኢማሙ   ቡሠይሪ  በመናማቸው  ረሡሉሏህ ሰ.ዐ.ወ እንዲህ  ብለዋቸዋል  « መን  ፈረሃ  ቢና  ፈረህና  ቢሂ»  __ በእኛ  መወለድ  የተደሠተ  እኛም  በእሡ  ደስተኛ  ነን።
ኢማም  ጁነይዲ  ረሂመሁሏህ  እንዲህ  ብለውናል  « የመውሊድ  ኪታብ  ሲቀራ  የተገኘ  ፣ የረሡሉሏህን ሰ.ዐ.ወ ቀድር  ከፍ ከፍ  ያደረገ  በእርግጥ  በኢማን  ስኬትን  አግኝቶል። »
ኢማሙ  ሡዮጢ  ረሂመሁሏህ  እንዲህ  ብለውናል  « በቤቱ  የነብዮን  ሰ.ዐ.ወ  መውሊድ  የሚቀራ  ከችግርና  ከበላዕ  ይጠበቃል። ከሃሲድ  ተንኰል  ይድናል። የነኪርና  ሙንኪር  ጥያቄም  ይቀልለታል። »
ኢማሙ  ሻፍዕይ  ረሂመሁሏህ  እንዲህ  ብለውናል  « መውሊድ  ለማስቀራት  ወንድሞቹን  የሠበሠበ፣ ያበላና  እንግዶቹን  ያስተናገደ የውመል  ቂያማ  ከሹሃዳዎችና  ሷሊሆች  ጋ  ይቀሠቀሳል። በጀነት  ኒዕማም  ይቀማጠላል።»

اللهُمَّ صَلِّ عَلَى حبيب ربي. وطب قلبي مولانا محمد
وعلى آله ،،وارزقنا الحُب مع الأدب،،،ويسر لنا الوصول بلا تعب لحضرة حبيبك شريف النسب...

በቴሌግራም
❀ይ🀄️🀄️ሉን!
🍀🍀🍀
👇👇👇
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
ለይለቱል ጁመዕ

አንድን  አሪፍ  ሠኢድ  ልሁን  ሸቅይ  እንዴት  ላውቅ  እችላለሁ  ብሎ  አንድ  ወጣት  ጠየቃቸው። እርሳቸው  «  ሶለዋት  አለ  ነብይ  ካልክ  ሠኢድ   ነህ  ካላልክ  ሸቅይ  ነህ  አሉት»  ለዚህ  ማስረጃ  አለው  ወይ  አላቸው። አወ  አለው።« በነብዮ  ላይ አሏህና   መልዕክተኛው  ሶለዋት  እንደሚያወርዱ  ቁርአን  ነግሮናል። ሸቅይ  የሆነ  ሠው  ደግሞ  ከአሏህና  ከመላዕክታን  ጋ  በምንም  ባህራ  አይገናኝም። በምንም  አይነት  ስራ  አይጋራም  አሉት»  
ይልቅ  ሠኢድ  መሆን  ብቻ  አያኰራራም  ከሠኢድነት  በላይም  የሆነ  ደረጃ  አለ  እሡም  «አስዐድ  ነው»   የሠኢዶች  ሁሉ  የበላይ  ማለት  ነው  ብለው  ጨመሩለት። የሁለቱ  ልዮነት  ምንድን  ነው  ብሎ ጠየቃቸው።
ሠኢድ  በየቀኑ  ሶለዋት  የሚል  ሲሆን  በጣም  ሠኢድ  ሚባለው  ደግሞ  ሶለዋት  ሁሉ  ነገሩ  የሆነ  ነው። ምግቡም  ሆነ  መጠጡ  ሶለዋት  የሆነ።ሃሳቡም  ሆነ  ጭንቀቱ  ሶለዋት  የሆነ። የሚተነፍሠው  አየር  ሳይቀር  በሶለዋት  የደመቀ  ነው  የሠኢዶች  ቁንጮ  አሉት።
ይህን  ሲሉ  የወጣቱ  አይኖች  እምባ  አፈለቁ። እርሳቸውም  ይህ ከአይንህ  እምባ  መፍሠሡ  የሠኢድነት  ጅማሬ  ነው። ጥያቄውን  መጠየቅህም   የሠኢድነት  ምልክት  ነው  ብለው  አሠናበቱት።  በሶለዋት  የደመቀ   ሀያት  አሏህ  ይግጠመን።

اللهُمَّ صَلِّ عَلَى حبيب ربي. وطب قلبي مولانا محمد وعلى آله ،،وارزقنا الحُب مع الأدب،،،ويسر لنا الوصول بلا تعب لحضرة حبيبك شريف النسب...
በቴሌግራም
❀ይ🀄️🀄️ሉን!
🍀🍀🍀
👇👇👇
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
🍀 ለይለቱል ጁመዕ 🍀🍀

🦋ሠይደልዉጁድንﷺ በሕልም የማየት እድል የሚገጥማቸው ሙሒቦች..ውዱዕ አድርጎ መተኛት የዘወትር ልምዳቸው ያደረጉት መሆናቸው ይነገራል።
ይሄንን እድል ማግኘት የሚሻ ወዳጅ፣ውጫዊ አካሉ በውዱዕ..ውስጣዊ ማንነቱ ቀልቡን ደግሞ በፍቅር መፅዳት ይኖርበታል❞🩵 አሉ።

ኢማም አል-ጘዛሊ❨ረሂመሁሏህ❩

📿 ኸሚስዬ 📿
🦋በየትኛውም ሁኔታ ላይ ልሁን በሰይደልዉጁድ ﷺْ ላይ ሶለዋት ማብዛት እወዳለሁ..በተለይ የጁሙዐህ ቀኑን እና ሌሊቱ ላይ በጣም ብዝቼ እወዳለሁ🩵❞አሉ።

🦋 ሠይዲ ኢማም አል ሻፊዒይ ❮ረሂመሁሏህ❯🦋

اللهم صل علي سيدنا محمد الناصر المنصور صﻻة تنصرنا بها بما نصرت به الرسول وتحفظنا بها بما حفظت به الرسول وعلي آله وصحبه وجميع الانبياء والمرسلين كلما ذكرك وذكره الذاكرون وغفل عن ذكرك وذكره الغافلون
.. ومن تكن برسول الله نصرته إن تلقه الاسد في اجامها تجم نستنصر الله نستحفظه نستودعه ..
#صلوا_عليه_وسلموا_تسليم telku jjw

#ትንሹ አሚር
" እልፍ  አላፍ  ኩርኩሞች  የቀመሱ  ዕራሶች
ዳባች የፍቅር እጆች እንጂ ዕይሹም ትራሶች "
              ትንሹ አሚር

🌿 🌿 🌿 ለይለቱል ጁመዕ 🌿 🌿 🌿

  ❤️ አሶላት  ወሰላም አለይክ
        ወል አሊ   ወሶ ሃበቲ
     ያ ሸምሰን ፊል መዲነቲ 💚


💚ለሓይባው  ብራና ገልጦ
ጀማሉን ዳኢም አፍጥጦ  
                          ተዳልጦ  ያው ገባለት

💚ሰምተነው  ከጌቶች መንደር
ጣፈጠን አይኑን መንደርደር
                           እያደር  ስሙን ማንሳት

💚የዱንያው የኡኺራ ሹሙ
ደባብሱኝ አባ ቃሲሙ
                              ሂያሙ መስሎኛል ሞት
💚ናፍቆቱ ሆድ እያስባሰ
የስንቱ ገላ ፈረሰ 
                      ታረሰ  በሚያምረው ዛት

💚 ና በል ኮርጅ ከነዛ
ኮራጁም አይደል የዋዛ
                   ኢጃዛ ለሱ እስኪሰብት

💚 ግንባሩ ማ   ኑር አውድማ
ፈሶበት  የጀማል ጣዝማ 
                          ለይላም ሰልማ  ሞቱለት

💚በአሏህ ስም ሃዩል ቀዩውوሙ
በጀዋዱ በከሪيሙ
                       ለኺድማው በል ግባለት

💚ግንባሩ  ያስኋባ  ደውሩ
የጣፈጠበት አዝካሩ 
                     ሥር ሥሩ ኮልኩሎለት

💚ጠጉርሁን ኡሙ ሰለመት
አኑራው  ውሃ ነክራበት
                      ታማሚው   ሊሽረበት

💚ጠጉርሁ   ደምቆ አደመቀን
ዘለላው ሲባል ሸወቀን
                    ላሳር ቀን ነው መድሃኒት 

💚ጠጉሩማ   ሙእጂዛው  ዞማ
ደረቱን  ዞራ ገልድማ 
                 አንገቱን ሸፋፍናለት

💚አይኑማ  ሱብሃነል ቁዱوስ
አርጎታል  ጁምዐ ኢድ عሩውስ
                            በል አድሩስ አጭስለት

💚ጠጉርሁን ሰይድ ኻሊዱ
አንግቦት ለጦር ሲሄዱ
                       ሽንፈት ሚባል ጠፋበት 

💚አይኑማ  ይብቃህ ለገድሉ
በአሏህ ዛት ልቆ መኳሉ
                        ተገልጦለት  አስችሎት

💚 ከንፈሩህ  የኑር ተምር
ለ  አሚነት  ሲዘምር  
                       ሲያሽር  ያንቱስ ውልደት

💚አይኑማ  ቢያየኝ ከጦይባ
በኢናያው  ተጀዝባ
                    ተጣጥባ ነፍሴ ላትስት

💚ሺ ዩሱፍ  ሺ ሸምሰል ጀማል
በዛቱህ  ሺ አቅማር ኸትሟል 
                           በጀላላው  ደብቆት

💚ጉንጭሁ  ንጥር ነው ሰፈፍ
ሃሳን አይቶት ቢንሰፈሰፍ 
                       ያ አሽረፍ ሲል ኖረለት

💚ጀማሉህማ  ሃቂቃው
ያሏህ ሂጃብ  ባይጠብቀው 
                         ያቃጥል ነበር ከውናት

💚እሱ ነው እሱ ነው በቃ
ሩሁል ከውን ለዉጁድ ጭቃ
                           አይበቃ  ያለርሱ ህይወት

💚ትከሻውማ መስፋቱ
ምናሉውሁ ከአስርቱ 
                      ጉያችን ስንፈራ ሞት

💚 እጅሁ ያሏህ ጁድ ድንኳን
ላደም መህር ለሃዋ መልኳን
                           የሁሏን  ሃቋን ሰጣት

💚እጅሁ   ለኑህ ለኸሊል
የአማን  የከረም ኢክሊል 
                                  የጀሊል  ካዝና ስጦት

💚 ባያልቅም እንኳ  መደዱ
ደካማን ቁዋ  ማስካዱ 
                              ዝሎበት  ሊቆምለት 
💚እግሩማ   ተው የግሩ ጫማ
ነጠላው  ረግጧል  ስማማ 
                      በዐርሹ  ራስ ሰፍሮበት

💚እጅሁ   ለኑህ ለኸሊል
የአማን  የከረም ኢክሊል 
                                  የጀሊል  ካዝና ስጦት
💚በሲዲቅ  ሷሂበ ተስዲቅ
መን ሳረ ቀልቡሁል ሙህሪቅ
                            አስለሙ ኩሊል አብያቲ

💚 ሶላት  ሰላም  ተጦያይባ
ስትዘምር ከወደጦይባ 
                          ነሲሙ ትንፈስሎት

❤️አሶላት ወሰላም አለይክ  
ወልአሊ  ወሶሃበቲ 
      ያ ሸምሰን ፊል መዲነቲ💚

اللهُمَّ صَلِّ عَلَى حبيب ربي. وطب قلبي مولانا محمد وعلى آله ،،وارزقنا الحُب مع الأدب،،،ويسر لنا الوصول بلا تعب لحضرة حبيبك شريف النسب...
#ትንሹ አሚር
በቴሌግራም
❀ይ🀄️🀄️ሉን!
🍀🍀🍀
👇👇👇
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
Forwarded from  ፈ ዳ ኢ ሉ (@ Amir Reshad)
ረቢዕ ማለት ደግ ነው❤️❤️
የአህባቦቹ ሰርግ ነው❤️❤️

የመዲናዉ የሀዲስ አዋቂ ዶ/ር ሙሀመድ ኢብን አልዐለዊ በመካና በመዲና ለዘመናት የቆየዉንና እስከአሁንም በቤተሰባቸዉ የቀጠለዉን የታላቁን ነብይ የአሽረፈልኸልቅ የመዉሊድ ክብረበአል
አፈጻጸምን ሲገልጹ እንዲህ ብለዋል፡-
‹‹ደስታና ብርታት በሚሰማን በየትኛዉም ቀንና አጋጣሚ የነብዩንﷺ መዉሊድ እናስባለን… በርሳቸዉ የመወለድ ጸጋ እንደሰታለን…ይህ መደሰታችን ሰኞ ቀንና በተወለዱበት በወርሀ ረቢዐል አወል መጠኑ ይጨምራል❤️… ጤነኛ አዕምሮ ያለዉ ሰዉ ‹በኢስራእና በሚዕራጅ ባለቤት ለምን ትደሰታላችሁ?›› ብሎ ሊጠይቀን አይችልም፡!!!!ይህ ጥያቄ በአላህ ብቸኛ አምላክነትና በነብዩ ሙሀመድﷺመልዕክተኛነት ከመሰከረ ሙስሊም አንደበት ሊወጣ ይችላልን? እርባናቢስ ጥያቄ ስለሆነ መልስ አያሻዉም፡፡ ቢሆንም፡ ‹ሙእሚን ስለሆንኩ ነብዩንﷺ እወዳለሁ ፤ ስለወደድኳቸዉ በርሳቸዉ እደሰታለሁ፤ ደስታዬንም
ዘወትር እገልጻለሁ›ካልኩ በቂ ነዉ፡፡››
ይላሉ🥰🥰❤️

የሀገራችንን የመዉሊድ ሂደት ስናጠና ከላይ ሸኽ አልዐለዊ ከሰጡት ገለጻ ጋር ተመሳሳይ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ የነብዩﷺ ልደት በሳምንታዊ፣በወርሀዊ ወይም በቀናት ዑደት ዓመቱን ሙሉ ይታሰባል፡፡ ሆኖም በረቢዐል አወል ይህ ደሰታ ይጨምራል፡፡ ከወሩ ዉስጥ ከ9-12 ባሉት ቀናት ደግሞ
እርሳቸዉን የማሰቡና ገድላቸዉን በጋራ እያወሱ የመመሰጡ መጠን ይበልጥ ያይላል፡፡
በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በየትኛዉም የዓመቱ ቀን ድሆችን ደግሶ የማብላቱ ክንዉን መዉሊድ ይባላል፡፡ በእንዲህ ዓይነት ሶደቃዎች ላይ ምንጊዜም የነብያችንﷺ ገድል ይነበባል፡፡ በርሳቸዉ ላይ በብዛት ሶለዋት ይወረዳል፡፡ እርሳቸዉን የሚያወድሱና የሚያሞግሱ መንዙማዎች ምንጊዜም ይደመጣሉ፡፡ በዋነኛነት በእዉቁ ዓሊም በአህመደ ዳኒ (ዳንዩል
አወል) የተደራጀዉ ‹‹ራምሳ› እና ‹ተራ መንዙማ› የተሰኘ ሙሉ ዝግጅት ይቀርባል፡፡ ይህ የመዉሊድ ሂደት በሌሎችም የሀገራችን ክፍሎች የተለመደ ነዉ፡፡
ስለዚህ መዉሊድን በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ የሚከናወን ሂደት አድርጎ ማሰብ ስህተት ነዉ።

እንኳን ለቆንጅየው ለምርጡ ለጣፋጩ ነብዬ አለይሂ ሰላት ወሰላም ዊላዳ ወር ረቢዑል አወል አደረሳችሁ❤️❤️❤️❤️❤️

#ትንሹ አሚር

❀በቴሌግራም
❀ይ🀄️🀄️ሉን!
🍀🍀🍀
👇👇👇
💚💛❤️@Tenshu6793  💚💛❤️
💚💛❤️@Tenshu6793  💚💛❤️
💚💛❤️@Tenshu6793  💚💛❤️
Channel photo updated
Forwarded from  ፈ ዳ ኢ ሉ (@ Amir Reshad)
💚💚💚💚ረቢዕ💚💚💚💚

ምን ያማረ ባሪያ  አህመድ ሙሐመዱ
ለሙሪደ ሷዲቅ  የሰይሩ መደዱ
መደዱል ኹለፋእ ካንተው መገመዱ
ባንተው   ይኸየራል ለሲራጥም ሓውዱ
                       ጀዋዱ ጀዋዱ   መርከዙል አርሳሌ ሃሚሉ ሊዋኢ  ሸፊኡል አዘሌ
💜💚
ከጌታው ቡደላ  የጀነት መሽረብ
ይዤ  ልቀናጣ  መድሁን ልጘርብ
እያልኩት ልዝመተው  ሰይዱል ዐረብ
ቀምጥለህ ደልቀኝ ከጀዝብህ መረብ
                 ደዋእ ሙጀረብ   ለሩህም  አካሌ  ሃሚሉ ሊዋኢ  ሸፊኡል አዘሌ

ባቱ  በወንዶቹ  ሰክኖ ነው ያረፈው
ሐበሻም  ፊት ኋላ የተረፈረፈው
መርከቡ  ስንት አይሹን  ላጀብ የቀዘፈው
ከከውኑ ነጥሎት   ሳቁን እየላፈው
            መዱን ያንጣፈፈው አናም  ዳና ጫሌ

ሃሚሉ ሊዋኢ  ሸፊኡል አዘሌ
**💜💚
ሰላም ለሲዲቁ  ሃዱን ላጣው ሲድቁ
ለሙስጦፋው  ነበር መነሳት መውደቁ
ዋልሎ አቅሉን ሰርቆት   በቀንም ድቅድቁ
መገን   ወዶ ማበድ  መገን ኢህቲራቁ 
                አባ አሺሸቱ    የሓድራው ዘንፋሌ  ሃሚሉ ሊዋኢ  ሸፊኡል አዘሌ

አልቅሰን መች ወጣ ቀድ ጀራ ማ ጀራ
ሰላመት አባኮ   ያ መን ተፈጀራ
ፈጅሩል ጀማላቲ   ቢኩንሂን ላ ዩድራ
አስጠጉኝ  ከአህሉህ  እኔስ የለኝ ቁድራ
                   አደራ  አደራ   ሳይሽር ኑ ቁስሌ  ሃሚሉ ሊዋኢ  ሸፊኡል አዘሌ

አሏሁመ ሶሊ አላ ሙሐመዴ
ሰሂይቁል አንዋሬ ወልሚስኪ ወልዐንበር 
       ሃሚሉ ሊዋኢ  ሸፊኡል አዘሌ

❀በቴሌግራም
❀ይ🀄️🀄️ሉን!
🍀🍀🍀
👇👇👇
💚💛❤️@Tenshu6793  💚💛❤️
💚💛❤️@Tenshu6793  💚💛❤️
💚💛❤️@Tenshu6793  💚💛❤️
💖 💖 💖 💖 💖 💖 💖 💖 💖
✍️ ያ ራህመተል ሙነዘላ

«ወኢን  ቱጥዒሁ  ተህተዱ  »   _ መልዕክተኛውን   ከታዘዛቹሁ   ሂዳያን  ታገኛላቹሁ።
«አሏህና  መልዕክተኛውን  ታዘዙ  ትማራላቹሁ  »
«መልዕክተኛውን  የታዘዘ  አሏህን  እንደታዘዘ  ነው። »
አሏህ   ረሡሉን  መታዘዝ  ከራሡ  ጋ  አቆራኝቶ  ብዙ ቦታ አስቀምጦታል። የረሡሉን  ትዕዛዝ  መጣስ  የአሏህን  ትዕዛዝ  መጣስ  መሆኑን  አስረግጦ  ነግሮናል።
አቡ  ሁረይራ ( ረዐ) ባወሩት  ሀዲስ   ረሡሉሏህ  እንዲህ  ብለዋል። «  እኔን  የታዘዘ  አሏህን  ታዞል። እኔን   ያመፀ  አሏህን  አምፆል። እኔ  የሾምኩትን  መሪ  የታዘዘ  እኔን  ታዞል። እኔ  የሾምኩትን  መሪ  ያመፀ  እኔን  አምፆኛል። »
በሌላ  የአቡ  ሁረይራ( ረዐ)  ዘገባ «  ኡመቶቸ   በሙሉ  ጀነት  ይገባሉ  አልፈልግም    ያለ  ሲቀር  አሉ። ያረሡለሏህ   ጀነት  ግባ  ሲባል   አልገባም  ሚል  አለ  እንዴ  ተብለው  ተጠየቁ  ።እርሳቸውም    የታዘዘኝ  ጀነት ገባ  ያመፀኝ   አልፈልግም  አለ  አሉ  »

#ምርጥ ቂሳ

ላኪውን ለመንኩት ናፍቄው እንዳልቀር ምኑን አፈቀርኩት ካላየሁት በቀር😭

#ትንሹ አሚር

በቴሌግራም
❀ይ🀄️🀄️ሉን!
🍀🍀🍀
👇👇👇
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
💚💚💚 ለይለቱል ጁመዕ💚💚💚

አንድ  ሷሊህ  ሠው  መዲና  ከሀቢቢ አለይሂ ሰላት ወሰላም ቀብር  ፊት  ለፊት  ለሶላት  ያሃረመ  ሠው  በሚመስል  አቆቆም  ቁመዋል። የሆነ  ልጅ  እየሠገዱ  መሠለውና  ቂብላ   ስለተሳሳቱ  ላስተካክላቸው  ብሎ  ወሠነ። አባቴ  ሆይ  ቂብላ  ስተዋል  ብሎ  በእጁም  ጭምር   ታግዞ  እንዲያስተካክሉ  ነገራቸው። እርሳቸውም  « ልጀ  ሆይ  ቂብላ    ስቸ  አይደለም። ቂብላ  ብዙ  አይነት  ነው  ። ልክ  ነህ የሶላት  ቂብላ  ወደ ሀረም_መካ  ነው። የዱአ  ቂብላ  ደግሞ  ወደ  ሠማይ  ነው። የረጃዕ  -የተስፋ -  ቂብላ  ደግሞ  ወደ  ረሡሉሏህ አለይሂ ሰላት ወሰላም  ደሪህ  ነው። አሁን  እኔ የመጣሁት   ረጃዕ  ፈልጌ  ነው  ። ስለዚህ  ቂብላየ  ወደ  ሀቢቢ አለይሂ ሰላት ወሰላም ነው  አሉት።»
ሌሎችን  ቂብላዎች  ደግሞ  ሌላ  ጊዜ  እነግራሃለሁ   ብለው  ተሠናበቱት።

#ምርጥ ቂሳ
#ትንሹ አሚር
በቴሌግራም
❀ይ🀄️🀄️ሉን!
🍀🍀🍀
👇👇👇
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
"እናንተ ለወርቅና ለብራችሁ ከምትሰስቱት
ይበልጥ በእስትንፋሶቻቸውና በጊዜዎቻቸው
እጅጉን የሚጠባበቁና በጣም የሚሰስቱለት ሰዎችን
አግኝቻለሁ ልክ ከናንተ አንዱ ወርቁንም ሆነ ብሩን
በሚጠቅመው ነገር ላይ እንደሚያውለው ሁሉ እነርሱም
ከስትንፋሶቻቸው አንዱም ትንፋሽ ያለአላህ ትእዛዝ
        በጭራሽ አያባክኑም ጭራሽ  : :

🖤 ✍️  ከመንፈሴ አለም


      💚 የከውኑ ሞገስ

መች ያረጋል ሰብር ነቢን የሚወድ፣
ቢነቃም ቢተኛም ሲቀመጥ ሲሄድ፣
ቢቀራም ቢያቀራም ቢያርስም ቢነግድ፣
እሰውም ጋር ሲሆን ብቻውን ሲሄድ፣
አፉ ስራ አይፈታም እሩህም ጀሰድ፣
እላዩ ላይ ታስሮ የሀድራው ገመድ፣
ከቆመው ይቆማል ከሄደው መሄድ፣
አይፈራም አካሉ እራብና ብርድ፣
ቆላደጋ እያለ ሲባክን ሲያረግድ፣
ሰው አያቅለት ሙቀት ይሆን ብርድ፣
እንዴት ያለ መከራ አሳሩ ለጉድ፣
እሰው ጋር ቁጭ ብሎ እሱ በመንገድ፣
ስሙ ተለውጦ ከአቂሉ ዘንድ፣
ሲበላም ሲጠጣም ሲፆምም ሲሰግድ፣
ሲስቅም ሲያለቅስም ሲወጣም ሲወርድ፣
ይመስላል አንጀቱ ጨሶ የሚነድ፣
አሊም ጃሂል አይል ሴት አይልም ወንድ፣
የሰፈረ ግዜ የሙሀባው ጁንድ፣
ከርተት ከርተት ነው እስኪገባ ለህድ፣
ስራው ማንጎራጎር ሲወጣም ሲወርድ፣
የቀመሰ ይፍረድ ተው ዝም በል ጃሚድ።

اللهُمَّ صَلِّ عَلَى حبيب ربي. وطب قلبي مولانا محمد وعلى آله ،،وارزقنا الحُب مع الأدب،،،ويسر لنا الوصول بلا تعب لحضرة حبيبك شريف النسب...
በቴሌግራም
❀ይ🀄️🀄️ሉን!
🍀🍀🍀
👇👇👇
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
ሀሚሱ ሙባረክ

አንዳንድ ጊዜ ፈተናው ወደ መጨረሻው አይመጣም....
አንዳንድ ጊዜ ህመሙ ይጨምራል...
አንዳንድ ጊዜ እየጨለመ እና እየጨለመ ይሄዳል....
አንዳንድ ጊዜ መውጫ መንገድ ያለ አይመስልም....
ችግር እርስ በርሱ ይመጣና ቅጣቱ ቢሆንስ? ያስብላል.....
ፍቅር ሳይሆን የአላህ ቅጣት ቢሆንስ????

ነገር ግን አላህን እንድታወድስ እንድትናፍቅ ወደ እርሱ እንድትጮህ እና በእርሱ እና በእሱ ላይ ብቻ እንድትተማመን የሚያደርግህ ከሆነ ይህ እንዴት ቅጣት ሊሆን ይችላል?
                     ???? እንዴት????
ፍቅር ነው ንጹህ ፍቅር ሌላ ሊሆን አይችልም።

ሰሉ አለ ነቢ💚
ና እቆምኩበት ቆመህ
ጀማሉን ተመልከት
በጆሮህ አዳምጠው
የጀዝሙን መለከት
ግንባሩን እይና
በወጉ ተንከትከት
አይተነው እንኑር
ብንሞትም እንሙት🙏

ኸሚስኩም ሙባረክ😍

        صلوا عليه وسلموا تسليما  
اللهم_صل_على_سيدنا_محمد_وعلى_آله_وصحبه_وسلم
#አሚር ትንሹ

በቴሌግራም
❀ይ🀄️🀄️ሉን!
🍀🍀🍀
👇👇👇
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
💚💚💚 የ ሀሚሱ ጀባታ💚💚💚
አኢሻ ረዲየላሁ አንሀ ለነብያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እስቲ በእርሶ ላይ ካለፉ አስቸጋሪ ቀናቶች ውስጥ ከዋነኞቹ ንገሩኝ አለቻቸው እሳቸውም ከጣኢፍ አባርረውኝ   ወደ ቀርነል መማዚሎች የሄድኩ ጊዜ ነበር አሉአት  የዛን እለት በደሉ ሲበዛ እጆቼን አንስቼ
✿ጌታዬ ሆይ አልኩኝ ቅሬታዬን ለአንተ አቀርባለሁ የጉልበቴ/የአቅሜንም ማነስ ፡ አንተ ደግሞ የእኔም የተበዳዮች /የደካሞች ጌታ ነህ ወደ ማን ነው የምትተወኝ ወደ ጠላት ነውን እያሰቃየኝ ወዳለው ?
ወይስ ወደ አንተ ጉዳዬን የምትቆጣጠር ወደሆንከው  ጌታዬ በኔ ላይ ተቆጥተህ ካልሆነ ምንም ችግር የለውም አሳቸው እያሉ ነው የአንተ ቁጣ ከሌለበት በደሉ ሁላ ቀላል ነው
የአንተ ይቅርታ ለኔ ከሁሉም ነገር የተሻለ ነው ከዛም ተቀምጠው ዱአቸው ቀጠሉ በዚህ ሁኔታ ላይ እያሉ ሰይዲና ጅብሪል ወለይሂ ሰላም   አንተ ሙሀመድ ሆይ ከኔ ጋር ተራራ መላኢካ አላህ ልኮልህ ይዤልህ መጥቻለሁ ነብያችን ሲናገሩ ለመጀመሪያ ጊዜ ነበር ከጅብሪል ውጪ ሌላ መላኢካ ያየሁት ይላሉ  ከዛም የተራራው መላኢካ እነዚህን ሰዎች እነዚህን ሁለት ተራራ ላጣብቅባቸው    ሲላቸው   እሳቸውም ወደፊት ከእነዚህ ሰዎች ውስጥ ላኢላሀ ኢለላህ የሚል እንዲፈጥርልኝ እመኛለሁ ተዋቸው አትንካቸው ብለው መላኢካውን መልሰው ዱአ አደረጉ

ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም
" የአለሙ አይነታ የኸልቁ ጨረቃ
   ለአለማት እዘነት ነበሩ ጠበቃ "
በሰለዋት እንበርታ

#ትንሹ አሚር
በቴሌግራም
❀ይ🀄️🀄️ሉን!
🍀🍀🍀
👇👇👇
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
2025/01/04 08:31:09
Back to Top
HTML Embed Code: