tgoop.com/Terbinos/12662
Last Update:
❤️ ኪዳነ ምሕረት
•••
"ኪዳነ ተካየድኩ ምስለ ኅሩያንየ፦ ከመረጥኳቸው ጋር ቃል ኪዳን አደረግሁ" ብሎ እንደተናገረ ከብዙዎች ጋር ቃል ኪዳን አለው ። (መዝ ፡89-3) ምድርን ዳግመኛ በንፍር ውኃ ላይመታ ፣ ሥጋ ለባሽንም አንድ ጊዜ ፈጽሞ ላያጠፍ ለኖህ ቃል ኪዳን ገብቷል ። (ዘፍ፡9፥1-17) የምድር አሕዛብ በዘሩ እንዲባረኩ ለአብርሃም ቃልኪዳን ገብቷል ።( ዘፍ ፡22-18 ) ለይስሐቅና ለያዕቆብ ተስፍቸውን ነግሮአቸዋል ። ( ዘፍ፡26-4) ለቅዱስ ዳዊትም ምሎለታል ። (መዝ ፡89-3) የእነዚህ ሁሉ ቅዱሳን ኪዳን ፍፃሜ ያገኘው ግን በአምላክ ሰው መሆን ነው ።
•••
#የእመቤታችን ቃል ኪዳን ግን የለየት ያለ ነው ። ለየት የሚለው በሁለት ዐበይት ምክንያቶች ነው ። የመጀመሪያው እርሷ ምልዕተ ፀጋ መሆኗና ፍጽምት ርኅርኂተ ኅሊና ከመሆኗ የተነሳ ስለሰው ልጅች አብዝታ የማለደችና ክርስቲያኖች ሁሉ ይድኑ ዘንድ ከሌሎች በተለየ የለመነች በመሆኗ ነው ። እንኳን እግዚአብሔር ጨካኙ ዳኛ እንኳን አብዝታ ለለመነችው መበለት ያደረገውን እናውቃለን ። (ሉቃ 18-1-8) ሁለተኛ ምክንያት ደግሞ ወላዲተ አምላክ ለመባል የበቃች ከእርሷ በቀር ሌላ የሌለ በመሆኑ በዚህም መልዕልተ ፍጡራን ትሆን ዘንድ አምላክ ያከበራት በመሆኗ ልዩ ቃል ኪዳን ይገባላት ዘንድ የተገባት ናት ። ( "በዓላት" ዲያቆን ብርሃኑ አድማስ ገጽ 146-147 )
••••
ዛሬ 16 ለኪዳነ ምሕረት ወራዊ መታሰቢያ በዓል እንኳን አደረሳቹ ። !!! 🙏
BY ❤️ የአማኑኤል ልጆች ❤️
Share with your friend now:
tgoop.com/Terbinos/12662