tgoop.com/Terbinos/12682
Last Update:
👉 ኪርያላይሶን፦
ቃሉ የግሪክ ሲሆን አጠራሩ « ኪርዬ ኤሌይሶን » ነው፡፡ « ኪርያ » ማለት « እግዝእትነ » ማለት ሲሆን « ኪርዬ » ማለት ደግሞ « እግዚኦ » ማለት ነው፡፡
••
ሲጠራም « ኪርዬ ኤሌይሶን » መባል አለበት፡፡ ትርጉሙ « አቤቱ ማረን »ማለት ነው፡፡ « ኪርያላይሶን » የምንለው በተለምዶ ነው፡፡ ይኼውም ኪርዬ ከሚለው « ዬ » ኤላይሶን ከሚለው ደግሞ « ኤ » በመሳሳባቸው በአማርኛ « ያ »ን ፈጥረው ነው፡፡
••
👉 ናይናን፦
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ « መሐረነ ፣ ማረን » ማለት ነው፡፡
••
👉 እብኖዲ፦
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ « አምላክ » ማለት ነው፡፡ « እብኖዲ ናይናን » ሲልም « አምላክ ሆይ ማረን » ማለቱ ነው
••
👉 ታኦስ፦
የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙ « ጌታ ፣ አምላክ » ማለት ነው፡፡ « ታኦስ ናይናን » ማለትም « ጌታ ሆይ ማረን » ማለት ነው፡፡
••
👉 ማስያስ፦
የዕብራይስጥ ቃል ሲሆነ ትርጉሙ « መሲሕ » ማለት ነው፡፡ « ማስያስ ናይናን » ሲልም « መሲሕ ሆይ ማረን » ማለት ነው
••
👉 ትስቡጣ፦
« ዴስፓታ » ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም ደግ ገዥ ማለት ነው
••
📌 አምነስቲቲ ሙኪርያቱ አንቲ ፋሲልያሱ ፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም « ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ - አቤቱ በመንግሥትህ አስበኝ » ማለት ነው፡፡
••
📌 አምንስቲቲ ሙዓግያ አንቲ ፋሲልያሱ፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን « ተዘከረነ ኦ ቅዱስ በውስተ መንግሥትከ -ቅዱስ ሆይ በመንግሥትህ አስበን » ማለት ነው፡፡
••
📌 አምንስቲቲ ሙዳሱጣ አንቲ ፋሲልያሱ፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም « ተዘከረነ እግዚአ ኩሉ በውስተ መንግሥትከ - የሁሉ የበላይ የሆንክ ወይ በመንግሥትህ አስበን » ማለት ነው፡፡
••
👉🏻 እባካችሁ ለሌሎች አካፍሉት ክርስቲያናዊን ወደዚህ ይጋብዙ‼️
••
👉🏻 https://www.tgoop.com/Terbinos
👉🏻 https://www.facebook.com/terbinos
BY ❤️ የአማኑኤል ልጆች ❤️
Share with your friend now:
tgoop.com/Terbinos/12682