tgoop.com/Terbinos/12689
Last Update:
📌 ዓርብ || ሰሞነ ሕማማት
••የዕዳ ደብዳቤያችን በጌታችን በእየሱስ ክርስቶስ ለመጨረሻ ጊዜ የተደመሰሰበት ፣ ከአጋንንት አገዛዝ ነፃ የወጣንበት ዕለት ስለሆነ " የድኅነት ቀን " ይባላል።
••
••
ጌታችን ጠዋት በሥስት ሰዓት ተገረፈ ፣ በስድስት ሰዓት ተሰቀለ። ጌታችን በውኃው ተጠምቀን ፣ ደሙን ተቀብለን የእግዚአብሔር ልጆች እንኾን ዘንድ ከቀኝ ጎድኑ ጥሩ ውኃ ፣ አፈሰሰልን።
••
በዐሥራ አንድ ሰዓት ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከመስቀል አውርደው ሽቶ እየረበረቡ በድርብ በፍታ ገንዝተው ቀበሩት። ነፍሱ ወደ ሲኦል ወርዳ ነፍሳትን ነፃ አወጣች። በዚህ ጊዜ ብርሃነ መለኮቱ በሲኦል ተገለጠ። ስለዚህም " #ንሴብሖ_ለእግዚአብሔር " እየተባለ ይዘመራል። ከሆሳዕና አንስቶ ተከልክሎ የነበረው ኑዛዜ ይናዘዛል ፣ ጸሎተ ፍትሐት ይደረጋል።
👉🏻 የስቅለት ዓርብ ይባላል፦ ጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ቤዛ ሆኖ በመልዕልተ መስቀል ላይ ተሰቅሎ የዋለበት ዕለት ነውና የስቅለት ዓርብ ይባላል።
••
👉🏻 መልካሙ ዓርብ ይባላል፡- ከጌታ ስቅለት በፊት በተለይም በሮማውያን ህግ የወንጀለኛ መቅጫ ምልክት የነበረውን መስቀል ጌታችን በደሙ ቀድሶ የምህረት፣ የሕይወት አርማ፣ የዲያቢሎስ ድል መንሻ ስላደረገው፤ በሞቱ መልካሙን ሕይወት ስላገኘን መልካሙ ዓርብ ይባላል።
••
👉🏻 እባካችሁ ለሌሎች አካፍሉት ክርስቲያናዊን ወደዚህ ይጋብዙ‼️
•••••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tgoop.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
BY ❤️ የአማኑኤል ልጆች ❤️
Share with your friend now:
tgoop.com/Terbinos/12689