tgoop.com/Terbinos/12711
Last Update:
⛪ ግንቦት 26 || አቡነ ሀብተማርያም
••
በገድል የተጠመዱ ኮከብ ገዳማዊ የጽድቅ የትሩፋት ሕይወታቸው እንደ ባሕር አሸዋ የበዛላቸው ታላቁ ጻድቅ አቡነ ሀብተማርያም ልደታቸው ነው።
••
የተወለዱት በመንዝ አውራጃ ልዩ ስሙ የራዊ በተባለ ቦታ ሲሆን የአባታቸው ስም ፍሬ ብሩክ የእናታቸው ስም ዮስቴና ይባላል፡፡ ሁለቱም በሕግ ጋብቻ ጸንተው ሕገ እግዚአብሔርን ጠብቀው ምግባር ቱሩፋት ሰርተው በስጽህና በቅድስና ይኖሩ ነበር
••
ለዮስቲና አንድ መናኝ መነኩሴ አግኝተዋቸው እግዚአብሔር በቅድስቲቱ ያለው ድብቅ ነገር ስለገለጠላቸው አንቺ ለምንኩስና የተፈቀደልሽ አይደለሽም
••
ወደ ቤትሽ ግቢ ጸሎቱ ለዓለም ሁሉ የሚጠቅም ሰው ሁሉ የሚማጸነው ስሙ፣ ገድሉ ትሩፋቱ በዓለም ሁሉ የሚነገርለት ወንድ ልጅ ትወልጃለሽ አሏቸው፡፡ የገድሉና የትሩፋቱ ዜና እስከ ዓለም ዳርቻ ይደርሳል በህይወተ ስጋ ሳለ በፈጣሪው እግዚአብሔር ፍቃድ የብዙዎችን ሰዎች ነፍሳት ከሲኦል ያወጣል እንደ መላእክትም ክንፈ ፀጋ ተሰጥቶታል፤ በሰው አካል ከስጋ ሆኖ ሳለ በተመስጦ ወደ ሰማይ የሥላሴን የአንድነትን የሦስትነትን ምስጢር ያያል አላት የእግዚአብሔርን ድንቅ ተዓምር የሰሙ ቅድስት ዮስቴናም እግዚአብሔርን እያመሰገኑ ወደ ቤታቸው ተመለሱ፡፡ የተናገረውን የማያስቀር አምላክ በቸርነቱ ጎበኛቸውና ነሃሴ 26 ቀን ጸነሱ፡፡
ግንቦት 26 ቀንም ደም ግባታቸው እጅግ
ያመረ ጻዲቅ ወለደች።
••
በእናተቸው ጀርባ ታዝለው ወደ ቤተክርስቲያን ሄደው በሕጻን አንደበታቸው ከቀዳሹ ካህን ጋር “እግዚኦ ማሐረነ ክርስቶስ” በማለት ...
BY ❤️ የአማኑኤል ልጆች ❤️
Share with your friend now:
tgoop.com/Terbinos/12711