Warning: Undefined array key 0 in /var/www/tgoop/function.php on line 65

Warning: Trying to access array offset on value of type null in /var/www/tgoop/function.php on line 65
2924 - Telegram Web
Telegram Web
Forwarded from Tesfa
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
The PASSION_OF_CHRIST በአማርኛ ቋንቋ ስቃይ የሚበዛበት የኢየሱስ ክርስቶስ ፊልም

ለመልዕክት 📩
@TikvahOrthodoxbot

ለመቀላቀል ...👇
✦✺ @tikvahorthodox ✺✦
✦✺ @tikvahorthodox ✺✦
''ክርስቶስ ተንስአ እሙታን ▸ በዐቢይ ኃይል ወስልጣን ፤ አሰሮ ለሰይጣን አግአዞ ለአዳም ፤ ሰላም ▸ እምይእዜሰ ፤ ኮነ ▸ ፍስሐ ወሰላም''

''ክርስቶስ በታላቅ በኃይልና ስልጣን ከሙታን ተነሳ ፤ ሰይጣንን አሰረው አዳምንም ነጻ አወጣው ፤ ስለዚህም ከእንግዲህ ወዲህ ፍፁም ሰላም እና ደስታ ሆነ''

እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ።

በዓሉ የሰላም የፍቅር እና የአንድነት በዓል ይሁንልን አሜን።

ለመልዕክት 📩
@TikvahOrthodoxbot

ለመቀላቀል ...👇
✦✺ @tikvahorthodox ✺✦
✦✺ @tikvahorthodox ✺✦
"ትንሳኤ ክርስቶስ"
ዝማሬ ዳዊት On Telegram
👉 ትንሳኤ ክርስቶስ
🎤 በሊቃውንት አንደበት

ለመልዕክት 📩
@TikvahOrthodoxbot

ለመቀላቀል ...👇
✦✺ @tikvahorthodox ✺✦
✦✺ @tikvahorthodox ✺✦
Forwarded from Tesfa
ትንሳኤ.pdf
84.1 KB
ለመልዕክት 📩 @TikvahOrthodoxbot

ለመቀላቀል ...👇
✦✺ @tikvahorthodox ✺✦
✦✺ @tikvahorthodox ✺✦
ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም ...

ለመልዕክት 📩 @TikvahOrthodoxbot

ለመቀላቀል ...👇
✦✺ @tikvahorthodox ✺✦
✦✺ @tikvahorthodox ✺✦
ለመልዕክት 📩 @TikvahOrthodoxbot

ለመቀላቀል ...👇
✦✺ @tikvahorthodox ✺✦
✦✺ @tikvahorthodox ✺✦
​​#የመልካም_ወጣት_መገኛ

Share በማድረግ ለመጥፋት የተዘጋጁ በጎችን ከመንጋው እንዳይለዩ ታደጓቸው።

መልካም ወጣት ማለት ከኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሀይማኖት ወጥተህ መናፍቃን አዳራሽ መክተም አይደለም።

መልካም ወጣት ማለት ክርስቶስ የተሰቀለበትን መስቀል ከአንገትህ ላይ በጥሶ መጣል አይደለም። መልካም ወጣት ማለት ቅድስት ድንግል ማርያምን መካድ ማለት አይደለም።
መልካም ወጣት ማለት ለሰዎች ይታዩ ዘንድ በምድር ላይ ባለጠግነትንና ዝነኝነትን ማካበት አይደለም፥ በምድር ላይ ሁሉ የከንቱ ከንቱ ነው።

#ይልቁንስ መልካም ወጣት ማለት ወንጌል ነው፦
ወዳጄ ወንጌል ማለት በሽንገላ ከንፈር ኢየሱስ ያድናል ማለት አይደለም። ወንጌል ማለት ክርስቶስን አምኛለውኝ ብሎ በግላዊ ግብር ለክርስቶስ ያለመታመንም ማለት አይደለም። ወንጌል ማለት መከራ መስቀልን መሸከም ነው። ወንጌል ማለት ክርስቶስ የተጓዘበትን የኩርንችት መንገድ በደስታ መራመድ ነው ። ወንጌል ማለት ለመሀተብህ ትሞታለህ ሲባል ከስጋው ይልቅ ነፍስን አስበልጦ ቀድሞ መሰለፍ ነው። ወንጌል ማለት ስለክርስቶስ ፍቅር ስጋህን እና ምኞትህን ገድለህ ለሞተልህ አምላክ መሰጠት ነው። ወንጌል ማለት ነፍስን መግደል በማይችሉት ፈርዖኖች ፊት በክብር ማሸብሸብ ነው ።

ወንጌል የምታወራው ልብ ወለድ ሳይሆን የምትላላክለት መወደድ ትዕዛዝ እንጅ። ወንጌል ማለት ክርስቶስ በደሙ የዋጃት ቤተክርስቲያን ክብር ላይ ዕጣ ሲጣጣሉባት እንደ 44 ታቦት ብላቴናዎች ቀድሞ የመገኘት ጥሪ ነው። ወንጌል የምትታዘበው እና ከአውደምህረት ላይ የምትወረውረው የማትኖርበት ቃል አይደለም። የምታልፍበት የመከራ ኮረብታ እንጅ ።

ከእዚህ አማናዊ ወንጌል ከሆነው ህዝብ ተማር። በጣም ተማር። ልጆቻችሁን ወንድም እኅቶቻችሁን "መልካም ወጣት አዳራሽ" የምትልኩ ኦርቶዶክሳውያን ጊዜያዊ መላ ፍለጋ ልጆቻችሁን ለዘለዓለማዊ ሞት አሳልፋችሁ እየሰጣችሁ እንደሆነ ዕወቁ። አዎ ልክ ነው ዘፋኙ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ነው፥ አዎ ልክ ነው ሰካራሙ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ነው፥ አዎ ልክ ነው ሱሰኛው ኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ነው፥ አዎ ልክ ነው ተሳዳቢው፥ ተራጋሚው፥ ተደባዳቢው፥ አመጸኛው የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ነው ነገር ግን ቤተ ክርስቲያኒቷ እና ሀይማኖቷ አጥብቀው ያወግዛሉ።

የአባ ዘጋስጫ ሀይማኖት ፥ የአባ ኤፍሬም ሀይማኖት ፥ የቅዱስ ያሬድ ሀይማኖት፥ የቅድስት አፎሚያ ሀይማኖት፥ የአቡነ ተክለ ሀይማኖት፥ ገብረ መንፈስ ቅዱስ፥ አቡነ አረጋዊ ሀይማኖት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ነው፥ ትልቅ እምነት እና ከክርስቶስ ቀጥሎ በክርስቶስ መንገድ የሄዱ ቅዱሳን የተጠሩባት ሀይማኖት (1ቆሮ᎐11:1) እኔ ስጠራበት በመጥፎ ስራዬ ላፍር በሀይማኖቴ ግን ልኮራ ይገባል።

ይህ ሰበብ ሊሆነን አይገባም፥ እኔ መልካም ወጣት እንድሆን መናፍቅ መሆን በፍጹም አይጠበቅብኝም!!

ኦርቶዶክሳውያን ሰባክያነ ወንጌል፣ ማኅበረ ቅዱሳንና ሌሎች መንፈሳዊ ማኅበራት፣ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ኦርቶዶክሳዊውን ወጣት የመጠበቅ ኃላፊነትና አደራ ከጌታ የተሰጣችሁ ነውና ትውልዱን ከጥፋት ለመጠበቅ ምን መሥራት እንዳለባችሁ አስቡበት።

"ደግሞ ሁለተኛ፦ የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ ትወደኛለህን? አለው። አዎን ጌታ ሆይ፥ እንድወድህ አንተ ታውቃለህ አለው። ጠቦቶቼን ጠብቅ አለው።" (ዮሐ 21:16-17 )

@ytewahido_lijoch ❤️
​​#ቅዱስ_ገብርኤል

እንኳን ለታላቁ መልአክ ለቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ አደረሰን!!!

በቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት ሐምሌ 19 የቅዱስ ገብርኤል አመታዊ በዓል ነው፡፡ ይህ ቀን ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ቅድስት እየሉጣንና ልጇን ቅዱስ ቂርቆስን ከሞት አደጋ እንደታደገበት የሚታሰብበት ዕለት ነው። የሐምሌ 19 ስንክሳርና የሐምሌ ወር ድርሳነ ገብርኤል እንዲህ ተርከውታል፡፡

በዘመነ ሰማእታት ከሐድያን ነገሥታትና መኳንንት በክርስቲያኖች ላይ መከራ አጽንተውባቸው ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት ብዙዎች ሰማእትነትን ሲቀበሉ የተቀሩት አገር ጥለው ተሰደዱ። እየሉጣም የሦስት ዓመት ህፃን የነበረውን ቅዱስ ቂርቆስን ይዛ ሸሸች በዚያም የሸሸችውን መኮንን አገኘችው ሰዎችም ነገር አሰሩባት ወደእርሱ አስቀረባት እና ስለ አምልኮ ጠየቃት እርሷም መኮንን ሆይ ዕድሜው ሦስት አመት የሆነው ህፃን አለ አማልክቶችህን ማምለክ መልካም እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ ያስረዳን ዘንድ እሱን ጠይቅ አለችው፡፡

ህፃኑም ወዳለበት ጭፍራውን ልኮ ወደእርሱ አስመጣው ህፃኑም ፊቱ ብሩህና ደስተኛ እንደሆነ አየውና አንተ ደስተኛ ህፃን ሆይ እንዴት ነህ አለው፡፡ ህፃኑም መልሶ አዎ ለኔ ተጠብቆልኛል ላንተ ግን ሐዘንና ለቅሶ ጥርስ ማፋጨትም ነው፡፡ መጻሐፍ ለዝንጉዎች ተድላ ደስታ የላቸውም ብሏል እና አለው፡፡ እግዚአብሔር ኃይልና ንግግርን ሰጥቶታልና ብዙ ተናገረ በዚያም ያሉትን እስካስደነገጣቸው ድረስ ንጉሱን መኳንንቱንና ጣኦታቱን ረገማቸው፡፡ከብርታቱም የተነሳ አደነቁ፡፡

መኮንኑም በአፈረ ጊዜ በያይነቱ በሆነ ስቃይ ታላላቆች የማይችሉትን ታላቅና አስጨናቂ የሆነ ስቃይን አሰቃየው እናቱንም ከእርሱ ጋር አሰቃያት፡፡ እግዚአብሔርም ያለ ምንም ጉዳት ያነሳቸው ነበር፡፡ ብዙዎች አህዛብም ይኸንን አይተው አደነቁ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስም አምነው በሰማእትነት አረፉ፡፡ የሰማእትነትንም አክሊል ተቀበሉ፡፡ በህፃኑም ላይ የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ አደረበት፡፡ ታላላቅ ድንቆችና ተአምራቶችንም አደረገ ብዙዎች በሽተኞችንም አዳናቸው፡፡

መስፍኑም በውስጡ ሰም፣ ጨው፣ ባሩድ፣ ሙጫ የዶሮ ማር፣ እርሳስ፣ ብረት፣ ቅንጭብ፣ ቁልቋል ጨምራችሁ ታላቅ የብረት ጋን አንጡልኝ ብሎ ጭፍሮቹን አዘዛቸው፡፡ ጭፍሮቹም እንዳዘዛቸው ካአደረጉ በኋላ ያዘዝከንን ሁሉ ፈጽመን እሳቱ ነዶ ፈልቷል፡፡ ድምፁ እንደነጐድጓድ ይጮኸል ወላፈኑም እንደጸሐይ ነጸብራቅ በሩቁ ይጋረፋል፡፡ የፍላቱም ኃይል በ14 ክንድ ያኽል ከፍታ ወደ ላይ ይዘላል፡፡ እንግዲህ በውስጡ የሚጣሉትን እዘዝ አሉት በዚህ ጊዜ ህፃን ቂርቆስና እናቱ እየሉጣ በክርስቶስ ስም ስለሚያምኑ አስረዋቸው ነበርና ከፍላቱ ሊጨምሯቸው ከእስር ቤት አወጧቸው፡፡

በዚያም ፍላቱ ወደላይ በሚዘል ብረት ጋን ውስጥ ለመጨመር ሲወስዷቸው የነዚህን ቅዱሳን አሟሟት ያዩ ዘንድ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች እንዲሰበሰቡ አዘዛቸው፡፡ በዚህን ጊዜ ቅድስት እየሉጣ የፍላቱን ጩኸት በሰማችና ባየች ጊዜ ተሸበረች፡፡ ተዘጋጅቶላት ከነበረው ክብር ልታፈገፍግ ሞከረች፡፡ ልጇ ቅዱስ ቂርቆስ ግን እናት ሆይ ከዚህ የብረት ጋን ግርማ የተነሳ አትፍሪ ድንጋጼም አይደርብሽ አናንያንና አዛርያን ሚሳኤልንም እግዚአብሔር ከእቶነ እሳት እንዳወጣቸው ሁሉ እኛንም ከዚህ ከብረት ጋን ሊያወጣን ችሎታ ያለው መሆኑን አትጠራጠሪ፡፡

እናት ሆ ከዚህ ከሚያልፈው ዓለም ጭንቅና መከራ ለመዳን ስትይ በማያልፈው ዘላለማዊ እሳት ለመቀጣት ትመርጫለሽን ይኽስ አይሆንም ይቅርብሽ፡፡ በአሁኑ ጊዜ እግዚአብሔር በመካከላችን አለና ይረዳናል፡፡ እናት ሆይ ሶስናን ከእደ ረበናት /መምህራነ አይሁድ/ ዳንኤልን ከአፈ አናብስት ያዳነ እርሱ እኛንም ከጋን ፍላት ያወጣናል፡፡ ይልቁንም እግዚአብሔር በዚህ የብረት ጋን ውስጥ ግዳጃችንን ልንፈጽም ፈቅዶ ከሆነ ኢዮብ ንብረቱንና ገንዘቡን ልጆቹንና ሚስቱን በመጨረሻም የተፈጥሮ አካሉን ባሳጣው ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ እግዚአብሐር ሰጠ እግዚአብሔር ነሳ እግዚአብሔርም እንደወደደ አደረገ ከማለት በስተቀር ምንም የተናገረው ነገር እንደሌለ ሁሉ እኛም የሱን ዓላማ በመከተል ይኽንን መከራ ልንታገስ ይገባናል፡፡

ነገር ግን እናቱ በዚህ ምክር ልትጽናና ባለመቻሏ ቅዱስ ቂርቆስ ዐይኑን ወደ ሰማይ አቅንቶ አቤቱ አምላክ ሆይ ይችን ባሪያህን ከርስትህ የምትለያት ከሆነ ከባለሟልነትህ መጽሐፍ ፋቀኝ፤ አቤቱ አዝመራውን አቃጥለ ፍሬውን ልትባርክ ትወዳለህን ይኽን እንዳታደር ግን ቸርነትህ ትከለክልኸለች አቤቱ እንጨቱን ቆርጣችሁ አንድዱት ቅጠሉን ግን ጠብቁት ብለኽ ልታዝ መለኮታዊ ባሕሪህ አይደለም፡፡ ነገር ግን እንጨቱንም ቅጠሉንም በአንድ ጠብቁት ብለኽ ታዝዛለኽ እንጂ፡፡ እንግዲህ በዚህ ምክንያት ይኽንን ያየ ሁሉ ማዳን የሚችል አምላክ ቢኖራቸውስ ኖሮ ከእሳት ባልሸሹም ነበር ብሎ አይጠራጠር፡፡

አቤቱ ዲያብሎስም ከባለስልጣኑ ይልቅ እኔ በረታሁ ቅዱሳኖቹንም ድል ነሳኋቸው ብሎ እንዳይመካ ከመንጋውም አንድ በግ ቀማው በማለት እንዳይደነፋ ለእናቴ ጽኑ የሆነ ኃይለ መንፈስ ቅዱስን ስጣት ብሎ በጸለየ ጊዜ ዲያብሎስ ከእየሉጣ አጠገብ ብን ብሎ ጠፋ፡፡ ከዚህ በኋላ ቅድስት እናቱ በሰማያዊ መንግሥት አባት የሆንከኝ ልጄ ሆይ ጌታኽ ኃይልን ሰጥቶኛልና የሚጠብቀንን ገድላችንን ፈጽመን ድል እናድርግ እነሆ በብረት ጋን ውስጥ የሚነደውን እሳት በማይበት ጊዜ በለምለም /በምንጭ/ ላይ እንደሚወርድ ጠል ሆኖ አይቸዋለሁና አለችው፡፡

#ይቀጥላል

ለመልዕክት 📩 @TikvahOrthodoxbot

ለመቀላቀል ...👇
✦✺ @tikvahorthodox ✺✦
✦✺ @tikvahorthodox ✺✦
​​👆የቀጠለ

እኒኽም ቅዱሳን ይኽንን በሚነጋገሩበት ጊዜ በውስጡ አንገትን የሚቆለምም ልብንም የሚያቀልጥ ሆድን የሚሰነጥቅ ሥርን የሚበጣጥስ መሳሪያ ካለበት የብረት ጋን ውስጥ ጨመራቸው፡፡ ከዚህ በኋላ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወረደና የብረቱን ጋን እሳት አጠፋው፡፡ ከቅዱሳኑም አንዳቸውንም ሳያቃጥላቸው የብረቱ ጋር ማቃጠሉና መፍላቱ ጸጥ አለ፡፡

ወንድሞቻችን ሆይ እንግዲህ በጭንቃቸው ጊዜ ገድላቸውን እስኪፈጽሙ ድረስ ይህ መልአክ ከሰማእታትና ከጻድቃን ጐን እንደማይለይ እወቁ ለኃጥአንም ኃጢአታቸውን ይቅር ይላቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ይጸልይላቸዋል፡፡ እኛም የዚህ የሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል በዓሉን እያከበርን አማላጅና ወዳጅ እናድርገው። በዚህም በሚመጣውም ዓለም ሊረዳን ይችላልና፡፡

ዳግመኛም መስፍኑ ሐሳቡ ሳይሳካለት ስለቀረ 14 የሾሉና የጋሉ የብረት ችንካሮች አምጥተው ሰባቱን በእናቱ በኢየሉጣ አካል ሰባቱን በራሱ በቂርቆስ አካል ማለት ሁለቱን በጆሮዎቹ ሁለቱን በዐይኖቹ ሁለቱን በአፍንጫዎቹ አንዱን በልቡ ይቸነክራቸው ዘንድ ጭፍሮቹን አዘዘ፡፡ ዳግመኛም የህፃኑን የእራስ ቆዳ ገፈው እሳት ውስጥ ይጨምሩ ዘንድ አዘዘ፡፡

አሁንም መልአኩ መጥቶ ይህንን መከራ ከእርሱ አራቀለት፡፡ ቀጥሎም በመቃን ውስጥ ጨምረው በገመድ እንዲጎትቱት አዘዘ፡፡ በዚህም ጊዜ መልአኩ አዳነው፡፡ ሕዝቡም ይህንን ሁሉ ተአምር ባዩ ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰገኑት ቅዱስ ገብርኤልንም አከበሩት፡፡ ቅዱስ ቂርቆስና ቅድስት እየሉጣ ብዙ መከራ ከተቀበሉ በኋላ ጥር 15 በሰይፍ ተመትተው ስማትነትን ተቀብለዋል።

የሊቀ መላእክት የቅዱስ ገብርኤል ፣ ቅዱስ ቂርቆስና የእናቱ የቅድስት እየሉጣ ተራዳኢነት ጸሎት አይለየን። ከዚህ በኋላ ሕፃኑን አስፈልገው ቢጠይቁት ነቢዩ ዳዊት የተናገረው ኃይለ ቃል መንፈስ ቅዱስ ተገልጾለት፤ ‹‹የአሕዛብ ጣዖታት የወርቅና የብር የሰው እጅ ሥራዎች ናቸው፡፡ የሚታመኑባቸውም ሁሉ እንደ እነርሱ ይሁኑ›› መዝ. ፻፴ በማለት ሲዘልፏቸው አገር ገዥው ሰምቶ ተቆጣና የብረት ጋን አስመጥቶ ውኃ ሞልቶ ከዕቶን እሳት ላይ ጥዶ ልዩ ልዩ ማገዶዎች በመጨመር ነበልባሉ ከመጠን በላይ ሆነ፡፡ የብረት ጋኑም ድምፅ እንደ ክረምት መብረቅና ነጎድጓድ እስኪያስፈራ ድረስ አስነድዶ ሕፃኑን ከነእናቱ ወስዳችሁ ጨምሩአቸው ብሎ አዘዘ፡፡

በዚህ ጊዜ ቅድስት ኢየሉጣ በጣም ፈራች፡፡ የእግዚአብሔር ሥራ እፁብ ድንቅ ግሩም ረቂቅ ነው፡፡ ገና አፉን ያልፈታ የሦስት ዓመት ሕፃን ‹‹እናቴ ሆይ! ገድላችን እንፈጽም ዘንድ ጨክኝ በርቺ›› አላት፡፡ ቅድስት ኢየሉጣም ‹‹ልጄ የነፍስ አባት ሁነኝ›› አለችው፡፡ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስም ከዘመናቸው ሳይደርስ፣ ታሪካቸውን ሳይማር የሠለስቱ ደቂቅን ታሪክ መንፈስ ቅዱስ ገልጾለት ‹‹አናንያን፣ አዛርያንና ሚሳኤልን ያዳነ አምላክ ያድነናል›› ቢላት ፍርሃቱ ሊለቃት ባለመቻሉ፣ ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ጸለየ፡፡

‹‹ጌታ ሆይ! የወይኑን ፍሬ ስትሻ ግንዱን ታጠፋለህን? እንደዚህስ ሁሉ እኔን አድነህ እናቴን ታጠፋታለህን?›› ብሎ በጸለየጊዜ መንፈስ ቅዱስ አደረባትና መንግሥተ ሰማያትን በዓይነ ሥጋ እንድታይ አደረጋት፡፡ ከዚህ በኋላ ፍርሃቱ ለቀቃትና ‹‹ልጄ ሆይ! ከዛሬ ጀምሮ መምህሬ፣ አባቴ፣ መካሪዬ እልሃለሁ እንጂ ልጄ አልልህም›› ብላ በጭካኔ ከልጅዋ ጋር ወደ ፈላው የብረት ጋን ገባችበት፡፡

በዚህ ጊዜ ሕፃኑ ቂርቆስ አናንያን፣ አዛርያንና ሚሳኤልን ያዳነ አምላክ ያድነናል ያለውን ቃል ለመፈጻም እግዚአብሔር አምላክ መልአኩ
ቅዱስ ገብርኤልን ላከላቸው፡፡ መልአኩም በትእምርተ መስቀል እሳቱን ቢባርከው እንደ በረዶ ቀዝቅዞላቸዋል፡፡ በመልካቸውም እንደ ፀሐይ አበራ፡፡ ከእግር ጥፍራቸው እስከ ራስ ጠሩራቸው አንድም ሳይጎዳቸው በደህና ወጡ፡፡

በመጨረሻም ሕፃኑ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ እንዲህ አለ፡፡ ይህን ያህል ገድል ተጋድዬ ምን ዋጋ ትሰጠኛለህ ቢለው፣ ጌታ በልብህ ያለውን ሁሉ እሰጥሃለሁ አለው፡፡ ዳግመኛም ሥጋህ በምድር ላይ እንዳይፈርስ እንዳይበሰብስ በኤልያስ ሠረገላ ላይ አኖርሃለሁ አለው፡፡

ስለሆነም በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያናችን መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ለእናታችን ለቅድስት ኢየሉጣ እና ለሕፃኑ ለቅዱስ ቂርቆስ ያደረገውን ይህን ታላቅ ተአምር ድንቅ ሥራ በማሰብ ከዋዜማው ጀምራ እግዚአብሔርን ስታመሰግን ትውላለች ታድራለች፡፡

የመልአኩ የቅዱስ ገብርኤል በረከት ተራዳኢነት ከሁላችን ጋር ይኑር አሜን፡፡

ለመልዕክት 📩 @TikvahOrthodoxbot

ለመቀላቀል ...👇
✦✺ @tikvahorthodox ✺✦
✦✺ @tikvahorthodox ✺✦
ቂርቆስ እየሉጣ
ዝማሬ ዳዊት
#ቂርቆስ_እየሉጣ

ቂርቆስ እየሉጣን ያወጣ ከእሳት
እኛንም አድነን/2/ ሊቀ መላዕክት
እኛንም አድነን/2/ ገብርኤል ሊቀ መላዕክት

ለመልዕክት 📩 @TikvahOrthodoxbot

ለመቀላቀል ...👇
✦✺ @tikvahorthodox ✺✦
✦✺ @tikvahorthodox ✺✦
ገብርኤል አማልደን
ዝማሬ ዳዊት
#ገብርኤል

ገብርኤል አማልደን ከአምላካችን /2/ 
እንዳንጠፋ እንዳንሞት በነፍሳችን 
አደራህን ቁምልን ከጎናችን /2/

ለመልዕክት 📩 @TikvahOrthodoxbot

ለመቀላቀል ...👇
✦✺ @tikvahorthodox ✺✦
✦✺ @tikvahorthodox ✺✦
ሕፃን ወእሙ
ዝማሬ ዳዊት
#ሕፃን_ወእሙ

ሕፃን ወእሙ /4/ 
ክልዔሆሙ ፈጸሙ ገድሎሙ/4/

ለመልዕክት 📩 @TikvahOrthodoxbot

ለመቀላቀል ...👇
✦✺ @tikvahorthodox ✺✦
✦✺ @tikvahorthodox ✺✦
ሁላችንም ይህ ቻናላችን ወደ ተሻለ እድገት እንዲደርስ እና ቃለ እግዚአብሔርም በስፋት እንዲዳረስ አንድ አሻራ እናሳርፍ።

መልካም ወጣት ለመሆን የተዋህዶ ልጅ መሆን በቂ ነው ። ይህ የተዋህዶ ልጆች መሰብሰቢያ ፥ የሰማይ ጉባኤ ነው ። ኑ ወደ ቤታችን እንግባ ።

- ጥቁር እንግዳ
- የተዋህዶ ልጆች
- ምስክርነት
- ዝማሬ ፥ ምስጋና
- መንፈሳዊ ጉዞ
- ተዋህዶን እንወቅ
- ይህንን ያውቃሉ ?
- ሚስጥሬን ላካፍላችሁ !
- ስብከቶች

ብቻ ብዙ ብዙ ፥ ተዋሕዶ ተዋሕዶ የሚሸቱ መርሐ ግብሮችን ይዘን መጥተናል ።

ለእናንተ የ #10 second እና የ #10 ሳንቲም ስራ ነው ። ለኛና ለቻናላችን እድገት ግን በጣም ትልቅ ነገር ነው ።

ከታች ባለው link ላይ Ok በማለት subscribe ያድርጉ ...👇👇👇

https://youtube.com/channel/UCPuJFLFnMdWNOij1TdVKHOA

እግዚአብሔር አለማችንን እና ህዝቦቿን ይባርክ ፤ አሜን ...🙏

@ytewahido_lijoch ❤️
​​​​🌼 ልጄ ሆይ እንደ ዘመኑ አንተም ተለወጥ

ልጄ ሆይ....... ወጣትነት ፈትኖህ፤ለስጋህ አድልተህ፤ነፍስህን አቀጭጨኻት ከአለም የኖርክበትን ዓመትህን ጥለኸው በንሰሐ እንደ ዘመኑ አንተም ተለወጥ።

ልጄ ሆይ ..... በአዲስ አመት ለአምላክህ የሚገባህን ግብር ትፈፅም ዘንድ በፍቅሩ አፀድ እንድትገኝ ካለመታዘዘ ተለወጥ።

ልጄ ሆይ ....... በአፈር ከሚሸነፈው ስጋዊ ዘርህ ወጥተህ ሰማያዊነትን ከሚያለብስህ ከማይጠፋው ሰማያዊ ዘር ክብረት ታደርግ ዘንድ ሰውን ካለመውደድ ጥላቻ ተለወጥ።

ልጄ ሆይ ...... በምክንያቶች ተደልለህ አፅዋማትን ዘለህ፤ምስጋናን ነፍገህ፥አገልግሎትን ንቀህ ከአለም ጫጫታ ውስጥ የዘፈቀውን ማንነትህ እንዳያጠፋህ እንደ ዘመኑ አንተም ተለወጥ።

ልጄ ሆይ ...... ዲያቢሎስ በቃል እንዳያስትህ፤በማማለል እንዳይጠልፍህ የመንጋውን ጠባቂ ቃልን ስማ፤ የመታዘዝን በረከት ታገኝ ዘንድ ከትምህክትህ እንደ ዘመኑ አንተም ተለወጥ።

ልጄ ሆይ .....ቀናት ሳይሆን መንፈስህ ይለወጥ፤ፀሐይ ሳትሆን የህይወት ጀንበርህ ይለወጥ።

ልጄ ሆይ ......ዕለታት አይሰልጥኑብህ፤ ዘመናት እስከ ሞትህ ጥግ ድረስ እስኪገፉህ ሳትጠብቅ አንተም እንደ ዘመንህ ተለወጥ

ልጄ ሆይ .....የእግዚአብሔር ፍቅር ለተከፈተ ልብ ቸር ነው ። ርህራሄው ጥልቅ ነው ። በአምሳሉ ፈጥሮሃል እና እንዳትጠፋ አንድያ ልጁን ለሞት አሳልፎ እስከመስጠት የደረስ ጥልቅ ፍቅር አሳይቷል ። ስለዚህ ከዘመንህ ቀድመህ ተለወጥ።

ልጄ ሆይ ...አዛኝቷን ተለማመን፤መላአኩን ተማለደው ፤ቀደምት ቅዱሳን አባቶችህን ጥራ፤ ፃድቃንን ዘክር እንጅ ላለመለወጥ ተማምለው ቀናት ብቻ ከሚለወጥባቸው ሰልፈኞች ተርታ አትገኝ ።

በንስሐ ወደ በረቱ የምንመለስበት ዘመን ይሁንልን! አሜን

🌻 መልካም አዲስ አመት ይሁንልን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

ለመልዕክት 📩 @TikvahOrthodoxbot

ለመቀላቀል ...👇
✦✺ @tikvahorthodox ✺✦
✦✺ @tikvahorthodox ✺✦
2025/01/06 12:48:27
Back to Top
HTML Embed Code: