tgoop.com/Tewahedo12/21461
Last Update:
✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
አሜን
✍️ "በበጎ ሥራ ሁሉ ፍሬ እያፈራችሁ በእግዚአብሔርም እውቀት እያደጋችሁ፥
ለጌታ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እንለምናለን"
📖ቆላስይስ 1፥10-11
ቀናችንን በጸሎት እንጀምር
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
ጾመ ዮዲት
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
❖ ከፈቃድ አጽዋማት መካከል አንዱ የሆነውም ‹ጾመ ዮዲት (የዮዲት ጾም)› በዚህ በጳጉሜን ወር የምንጾመው ነው፡፡
❖ ዮዲት በናቡከደነጾር ዘመነ መንግሥት ትኖር የነበረች ስትሆን በንጽሕና ተጠብቃ፣ በጸሎትና በሕገ እግዚአብሔር የምትኖር ሴት ነበረች፡፡
❖ የፋርስ ንጉሥ ናቡከደነጾር በሠራዊቱ ተመክቶ ጠላት አጥፋ ድንበር አስፋ ካመነው እጅ መንሻ እየተቀበልህ ያላመነውን እያሳመንህ ና ብሎ ለጦር አበጋዙ ሆሎፎርኒስ ትእዛዝ ሰጠ፤ እርሱም እንደታዘዘው በኃይላቸው የታመኑ ፲፪(12) ሺህ እግረኞችንና በፈረስ የተቀመጡ ፲፪(12) ሺህ ጦረኞችን እየመራ ዘምቶ ካመነው እጅ መንሻ እየተቀበለ ያላመነውን እያሳመነ ብዙ ሀገሮችን እያጠፋ ሲሄድ ከአይሁድ ከተማ ደረሰ፤ በዚህም ብዙ ጥፋት በመድረሱ የእስራኤል ልጆች አለቀሱ፡፡
❖ በዚያን ጊዜ ንጉሡ ሥልጣኑን መከታ በማድረግ የእግዚአብሔርን ሕዝብ በግድ እያስገደደ እጅ መንሻ ይቀበል ነበር፤ የመንግሥቱን ትእዛዝ ያልተቀበለውንም እየገደለ፣ ጭፍሮቹ ኃያልነቱንና ገናናነቱን በአዋጅ በጦር አዛዦች ጭምር እያሳወጀ፣ በርካታ የጦር ሠራዊቶችን አሰልፎ ከአይሁድ ከተማ ገባ፡፡
❖ በዚያም ነዋሪዎችን በማስፈራራት የመንግሥቱን ትእዛዝ ያልተቀበሉትን ሁሉ እያሳደደ ስላስጨነቃቸው ማቅ ለብሰው፣ አመድ ነስንሰውና ድንጋይ ተንተርሰው ወደ ፈጣሪያቸው በመጮህ መለመን ጀመሩ፤ በጭካኔ የተሞላው የጦር አበጋዙ ሆሎፎርኒስም ይበልጥ እጅግ እንዲሠቃዩ ውኃ የሚቀዱበትን ስፍራ ተቆጣጠረው፤ በግዴታ ማርኮም እጅ እንዲሰጡ እንዳደረጋቸው በመጽሐፈ ዮዲት ላይ ተጽፏል፤ በአካባቢው ይኖር የነበረ ዖዝያን የተባለ አንድ ሰው የአባቶቻቸው አምላክ ጸሎታቸውን እንዲሰማቸው ለአምስት ቀናት በትዕግሥት ይጾሙና ይጸልዩ ዘንድ ሕዝቡን መከራቸው፤ እነርሱም በትዕግሥት ሊጠብቁ ተስማሙ፡፡
📖ዮዲ 2፥2-28፣ 4፥13
❖ ሕዝበ እስራኤል የናቡከደነጾርን ጦር ተዋግተው ለመርታት ካልሆነ ግን እጅ ለመስጠት ተመካከሩ፤ ነገር ግን ዮዲት እግዚአብሔርን የምትፈራ ብቸኛዋ ሴት እርሷ ነበረችና ምክክራቸውን ስትሰማ ለምን «እግዚአብሔር ያድነናል አትሉም» ብላ ገሠጸቻቸው፤ ማቅ በመልበስ፣ አመድ በመነስነስና ድንጋይ በመንተራስም ሱባኤ ገባች፤ በሦስተኛው ቀንም እግዚአብሔር አምላክ ሕዝቧን የምታድንበትን ጥበብ ገለጸላት፤ ዮዲትም እግዚአብሔር የሰጣትን ውበት ተጠቅማ ሕዝቧን ከጥፋት የምትታደግበትን ጥበብ ተረዳች።
📖ዮዲ 4፥13
❖ በአልባሳትም ተሸልማ፣ ሽቱ ተቀብታና ተውባ የጠላት ሠራዊት ወዳሉበት የጦር ሰፈር በድፍረት ተጓዘች፤ ሠራዊቱም ውበቷን አይተው እጅግ በመደነቅ «ይህችስ ለአለቃችን ትገባለች» ተባብለው ከጦር መሪያቸው ዘንድ ወሰዷት፤ ዮዲትም ቀድማ ከጠላቷ ማምለጫ መንገድ አዘጋጅታ ስለነበር የሠራዊቱ አለቃ ወደ ነበረበት ሥፍራ ከገባች በኋላ «ክቡር ጌታዬ ሆይ ርስት ተወስዶብኛል፤ እንድትመልስልኝ አስቀድሜ ደጅ ልጠና መጥቻለውና ርዳኝ፤ ትብብርህ አይለየኝ» ብላ ጠየቀችው፡፡
❖ የሠራዊቶቹ አዛዥም በዝሙት መንፈስ ታውሮ ስለነበር የጠየቀችውን እንደሚፈጽምላት ነገራት፤ ዮዲትም ባማረ ድንካን አስቀመጣት፤ በእግዚአብሔር ረዳትነትም ጥበቧንም ተጠቅማ ማምለጫዋን አዘጋጀች፡፡
📖ዮዲ 10፥23፣ 11፥23
❖ ዮዲትም ለቀናት በድንኳኑ ከተቀመጠች በኃላ የሠራዊቱ አበጋዝ የምሳ ግብዣ አዘጋጅቶ ከጎኑ አስቀመጣት፤ ከበሉና ከጠጡ በኋላም ሁሉን ሰው አስወጥቶ እልፍኙን በመዝጋት ከእርሷ ጋር ብቻውን ቀረ፤ ነገር ግን እንቅልፍ ጣለው፤ በዚያን ጊዜም ዮዲት ወደ አምላኳ በመጸለይ ፈጣሪዋ እንዲረዳት ለመነች፤ ከዚህ በኋላ የሠራዊቱን አለቃ ከራስጌው ሰይፉን በማንሣት አንገቱን ቀላችው፤ በድኑንም ከመሬት ጣለችው።
✍️"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል"
📖ምሳ 1፥33
✍️ " #ወአንቢበክሙ አንትሙ #ለዘኢያንበበ አይድኡ
➘ #እናንተ_አንብባችሁ_ላላነበበው_ንገሩ"
✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝
🙏 ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ፤ እኔም ለእናንተ ከአዘጋጀው በኃዋላ በድካሜ ብዛት ሳይገባኝና ሳይገባኝ በምጽፈው ድርሳንወ ገድላት መጽሐፍት ላይ የቃላት (የፊደል) ሕፀፅ ቢገኝ በጎደለው እየሞላችሁ በጠመመው እያቃናችሁ አንብቡ በረከት ተካፈሉ እላለሁ ከምንም ጊዜ በላይ ለሀገራችንና ለዓለም ሰላም እንዲሁም ለደካማው ወንድማችሁ እንድበረታ (የተጣልሁ) እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ
✍"ልብህን በእርጋታ አኑረው፤ የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር ዘገምተኛና ሰነፍ ሁን፤ ነገር ግን የቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድኅነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን"
📚ታላቁ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ይቆየን
───────────
Channel
🧲 https://www.tgoop.com/Tewahedo12
FB Like Page (የፌስቡክ ፔጅ)
🧲 http://facebook.com/Tewahedo12
YouTube Subscribe (ሰብስክራይብ)
🧲 https://www.youtube.com/channel/UCvYxUdv1D-5juH_P6iE7XXw
───────────
BY ✞ ተዋሕዶ ✞ 🇹 🇪 🇼 🇦 🇭 🇪 🇩 🇴
![](https://photo2.tgoop.com/u/cdn4.cdn-telegram.org/file/Q0KgX21J64Hyx99ooaghj45g1Ctv3NtAiaTy9j47Uv6wVj3ccXmErICLlItmlAxSiUQLh5B9QYvS9w40kRB6wxGKat8pasQ-pWPTDYKKJ6_kWSa_c9lJWT1z5tnZpKVPrcu66cgcnT0Mnv9OD63Bw_9sCeykGzNx6eYBnr7vVLzz1pcdnVc5Qd30TbTl7tacNJExHR6nLk7AkPur0o_psiJNa3o13tvmufnVJq60iv6cWarJTrKeLh45h12MEL1eIbta-8G87-anOQ2cQArjbFUmbacEHvU-PaUhXTZ0axKrA-SRJASSSciA2j4UEZDbQMBX0QREbiKctbPqcOI70A.jpg)
Share with your friend now:
tgoop.com/Tewahedo12/21461