tgoop.com/Tewahedo12/21531
Last Update:
✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
አሜን
✍"ችግር ለራሳችን እንድንጸልይ ያነቃቃናል፤ ፍቅር ደግሞ ለሌሎች ሰዎች እንድንጸልይ ያስገድደናል"
📚ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ቀናችንን በጸሎት እንጀምር
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
የዘመን መለወጫ
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
❓ #ዘመን መለወጫ ምንድ ነው
❓ #እንቁጣጣሽ ምንድነው
❓ #አዲስ አመት ለምን ቅዱስ ዮሐንስ ይባላል
❖ ኢትዮጵያ የወራት ሁሉ መጀመሪያ መስከረም ነው፤ ይህ ወር ዘመን መለወጫ፣ ዕንቁጣጣሽ፣ ቅዱስ ዮሐንስ እየተባለ ይጠራል፡፡
❖ ስለ አዲስ ዓመት በተለያየ ስም የመጠራቱ ታሪካዊ አመጣጥና ስያሜ መነሻ አሳቡ ምን እንደሆነ እንደሚከተለው እንመለከታለን፡፡
📌 #ዘመን_መለወጫ
❖ ዘመን መለወጫ መስከረም ወር የሆነበት ምክንያት “ብርሃናት /ፀሐይ፣ ጨረቃ፣ ከዋክብት/ የዓመት ዑደታቸውን በጳጉሜ ወር ጨርሰው በመስከረም ወር ስለሚጀምሩ ነው፡፡
❖ ሌሊቱ ከቀኑ ጋር ይተካከላል፤ ዓመቱን ጠንቅቀው ቢቆጥሩ 366 ቀናት ይሆናል፡፡
✍️ “ሌሊቱም ከቀኑ ጋራ ይተካከላል፤ ዓመቱም ጠንቅቆ ቢቆጥሩት ሦስት መቶ ስልሳ አራት ቀን ይሆናል፡፡
📖ሄኖክ 26፥44
✍️ “ዘመናችንን እንደ ቀድሞ አድሱ”
📖ሰ.ኤር 5፥21
❖ በዘመነ ኖኅ ዓለምን ንፍር ውኃ አጥለቅልቆት በኋላ ዳግመኛ ውኃው የጎደለበት በመሆኑ
✍️ “በመጀመሪያው ወር መባቻም ምድር ታየች” እንዲል፡፡
📖ኩፋሌ 7፥1
📌 #ዕንቁጣጣሽ
❖ ዕንቁጣጣሽ የተባለበት ምክንያት አንደኛ “ዕንቁ - ዕፅ አመጣሽ” ብሎ የአበባውንአህጉራትን መፈንዳት ያመለክታል፡፡
❖ ሁለተኛ ኖኅ ለሦስቱ ልጆቹ በእጣ ሲያካፍላቸው አፍሪካ ለካም ደረሰችው፤ በአፍሪካ ምድርም ሲገባ በመጀመሪያ ያረፈው በኢትዮጵያ ነበር፡፡
❖ ሀገሪቱም በአደይ አበባ አሸብርቃ ነበር፤ ወሩ ወርኀ መስከረም በመሆኑ ደስ ብሎት ዕንቁ ዕጣ ወጣሽልኝ ይህችን ወቅት እንቁጣጣሽ ብሏታል፡፡
❖ ሦስተኛው /1ነገ.10፥1-10/ ኢትዮጵያዊቷ ንግሥት ሣባ /መንሻ አዜብ የንጉሡን ጥበብ ከመስማት ማየትን መርጣ ወደ ንጉሥ ሰሎሞን ከብዙ ሠራዊቶቿ ጋር የእጅ በመያዝ ሄደች፡፡ ንጉሡም በደስታ ተቀብሎ እርሱም “እንቁ ለጣትሽወርኀ ጌጥ ይሁንሽ” በማለት አራት አይነት ቀለም የሚታይበት በቀንና በሌሊት የምታበራ ቀለበት ሰጥቷታል፡፡ ወሩም መስከረም ነበር፡፡ ከዚህ በመነሣት እንቁጣጣሽ የሚለው ስያሜ ወጥቷል፡፡
📌 #ቅዱስ_ዮሐንስ
❖ ሦስተኛው የአዲስ ዘመን ስያሜ ቅዱስ ዮሐንስ ነው፤ የመጥምቁ ዮሐንስ ተግባር ለዘመነ ወንጌል በር ወይም መነሻ እንዲሆን ለኢትዮጵያ ዐውደ ዓመት መስከረም አንድ ቀን እንዲከበር አባቶች ወስነዋል፡፡
📚ድርሳነ ዮሐንስ አፈወርቅ ገጽ 1-3
❖ መጽሐፈ ስንክሳር “የመስከረም ወር የተባረከ ነው፤ እርሱም የግብጽና የኢትዮጵያ ዓመቶች
መጀመሪያ ነው፤ የዚህ ወር ቀኑና ሌሊቱ እኩል 12 ሰዓት ነው፤ ከዚህ በኋላ ቀኑ እየጎደለ ይሄዳል” እንዲል፡፡
❖ በአጠቃላይ ዘመን መለወጫ ከላይ ባየናቸው የተለያየ ስያሜ ይጠራ እንጂ ዘመኑ አዲስ እየተባለ ቢጠራም አዲስ መሆን ያለበት ወርና ወቅቱ ብቻ ሳይሆን የእኛ የክርስቲያኖች ሥርዓት ነው፡፡
❖ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰውነታችሁን አታርክሱ የእግዚአብሔር ማደሪያ ነውና እያለ በመዋዕለ ሥጋዌው ያስተምር ነበር፡፡
❖ አዲስ ዓመት ሲመጣ በኃጢአት፣ በተንኮል፣ በክፋት የቆሸሸው ሰውነታችን በንስሓ፣ በቅዱስ ቊርባን፣ በመልካም ተግባር አዲስ ልናደርገው ይገባናል፡፡
መልካም አዲስ አመት!
📌 ምንጭ
✍️ ከተለያዩ መጽሐፍት
✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝
✍"ልብህን በእርጋታ አኑረው፤ የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር ዘገምተኛና ሰነፍ ሁን፤ ነገር ግን የቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድኅነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን"
📚ታላቁ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ይቆየን
Share
🇹 🇪 🇼 🇦 🇭 🇪 🇩 🇴
✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥
✝ @Tewahedo12 ✝
✝ @OrthodoxTewahedo12 ✝
✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥
BY ✞ ተዋሕዶ ✞ 🇹 🇪 🇼 🇦 🇭 🇪 🇩 🇴
Share with your friend now:
tgoop.com/Tewahedo12/21531