Telegram Web
‹‹ጀነት እገባለሁ ብለህ ታስባለህ?›› ብለው ገጠሬውን ጠየቁት።
የበስራን መስጅድ ለመጎብኘት የመጣው የገጠር ሰውም፦‹‹ወላሂ በፍፁም አልገባም ብዬ ተጠራጥሬ እንኳ አላውቅም። አዎን እገባለሁ! በእልፍኞቿም እየተዟዟርኩ እዝናናለሁ፣ መጠጦቿንም እያማረጥኩ እጎነጫለሁ፣ በጥላዎቿም ተጠልዬ ፍሬዎቿንም እበላለሁ፣ በዛፎቿ የንፋስ ዜማ እየተመሰጥኩ በህንፃዎቿ እደመማለሁ፣ በህንፃዎቿ ከትሜ በቅንጡ ክፍሎቿ እኖራለሁ ›› አላቸው።

ሰዎቹም፦‹‹ጀነት እገባለሁ ብለህ ምትፎክረው እምትተማመንበት ፅድቅ አለህን?›› ሲሉ ጠየቁት።

ገጠሬውም፦‹‹በአላህ ከማመን እና ከሱ ሌላ የሆነን አማልክት በሙሉ ከመካድ የበለጠ ምን ፅድቅ አለ?›› አላቸው።

‹‹ታድያ እምነት ላይ ሁነህ የምትፈፅማቸውን ሀፅያቶች አትፈራምን?›› ሲሉ ጠየቁት።

እሱም፦‹‹አላህ ለሀፅያት ምህረትን አዘገጅቷል፣ ለስህተትም ይቅርታን መድቧል፣ ለአመፅም እዝነትን ወስኖልናል። አላህም ወዳጆቹን በእሳት ከመማገድ የተጥራራ ነው›› አላቸው።

ያ አላህ ከአመፃችን በላይ ያካበበውን እዝነትህን ትለግሰን ዘንድ እንለምንሀለን!!
~ ልብ ሰላሞን የምታገኘው የሰላሙን ባለቤት አብዛታ ባወሳች ቁጥር ነው።

~ ልብ የምትረጋጋው አብዝቶ አላህን በማውሳት ነው።

~ የሰው ልጅ እርጋታ ስክነት የሚያገኘው ፈጣሪውን ይበልጥ በቀረበው ቁጥር ነው።
«ያ ዳዉድ! እኔን ውደደኝ፣ የሚወደኝንም ሰው ውደድ፣ ሰዎችም እኔን እንዲወዱኝ አድርግ» የሚል ትዕዛዝ ለዳዉድ ዐሰ መጣለት።

«ያ ረብ! እኔስ እወድሀለሁ፤ ግና እንዴት ሰዎች እንዲወዱህ ማድረግ እችላለሁ?» ሲል ጠየቀ።

«በመካከላቸው ስሜን በመልካም አንሳ፣ ፀጋዎቼን ዘርዝር፣ ከእኔ መልካምን እንጂ ሌላን አያውቁም'ና»

-------------------

«ያ ሐናን፣ ያ መናን!» እያለ ይጣራል ሰውዬው ከጀሀነም መሀል ቁሞ ለ1 ሺህ አመታት ያህል እየተማገደ።

«ጂብሪል! ሂድ'ና ይህን ባርያዬን አምጣልኝ።» ይላል የዙፋኑ ባለቤት።
ጂብሪልም ሂዶ ባርያውን ከጀሀነም አውጥቶ እጌታው ፊት ያቁመዋል።

«የጀሀነም ክፍልህን እንዴት አገኘኻት?» ብሎ አላህ ይጠይቀዋል።
«መጥፎ ክፍል ናት» ይላል ባርያ እጌታው ፊት ቁሞ።
«በሉ ወደ ክፍሉ መልሱት» ይልና ወደጀሀነም በሚወስደው መንገድ ይሸኘዋል።

ባርያም ወደመጣበት ጀሀነም እየተመለስ በሚያሳዝን ዘዬ ወደ ኋላ እየዞረ ያየል።
«ምንድነው እሱ ኋላ ኋላ ምትዞረው? » ብሎ አላህ ይጠይቀዋል።

«ከጀሀነም አስጠርተህ ካስወጣኸኝ በኋላ እኮ ዳግም ትመልሰኛለህ ብዬ አልገመትኩም ነበር» ይላል ባርያ የአላህን እዝነት እያንኳኳ።

«በሉ እንድያ ከሆነ፤ ወደ ጀነት ውሰዱት» ብሎ ተስፋ የቆረጠ ባርያን የማይታመን ተስፋ ይለግሰዋል።

--------------------

የሆነ ግዜ ውዴ ሰዐወ የኛን የቀዥቃዣነት ጉዳይ ሲያብሰለስሉ ቆይተው፦ «ያ ረብ! ኡመቴን ሂሳባቸውን እኔው ላድርግ፤ ገመናቸውን ማንም እንዲያይብኝ አልሻም» አሉት።

«ሙሀመድ! እነሱ ላንተ ህዝቦችህ ናቸው፤ለኔ እኮ ባሮቼ ናቸው። የባሮቼን ገመና እንኳን አንተም ሆንክ ሌላው እንዲያይባቸው አልሻም» አላቸው። ጉዳችን ድሮም ተነቅቶብናል።
---------------------

ነብይህ ነጋ፣ ጠባ «ኡመቲ...ኡመቲ» እያሉ አላህን በእንባ በሲቃ ሲወተውቱት... «በቃ የኡመትህን ጉዳይ የቅያም ቀን ባንተ እጅ አደርግልሀለሁ፤ እራስህ ሂሳብ ታደርጋቸዋለህ» ብሎ ሊያባብላቸው ሞከረ።

«አይ አንተ ከኔ በላይ ለነሱ ታዝንላቸዋለህ» ይሉታል።
«እንግድያውስ አደራውን ለኛ ከሰጠኸን በኡመትህ ጉዳይ አያሳስብህ እናስደስትሀለን» ብሎ ተስፋ ሰጣቸው።
----------------------

ለ40 አመታት በሽፍታነት ህዝቡን ሲያምስ የከረመ ወጠምሻ ከጫካው ቁሟል። ዒሳ ዐሰ ከአንድ ሀዋሪያው ጋ ያን ጫካ እያቋረጠ ነው።

ሽፍታው አያቸው ከነሱ ጋርም ትንሽ ለመራመድም ከጀለ፤ ግና ሀያእ ያዘው።
እንደምንም በሀፍረት ይከተላቸው ጀመር። ባሳለፈው ህይወት አንገቱን ደፍቶ ከሀዋሪያው ጎን ጠጋ ጠጋ እያለ ይራመድ ጀመር።

«የኔ አይነቱ ወራዳ ነውንዴ ከዚህ አይነት መልካም ሀዋርያ ጎን ሚራመደው!» እያለ ራሱንም ይወቅስ ጀመር።

ከዒሳ ዐሰ ኋላ የሚራመደው ሀዋሪያ ለሽፍታው የንቀት ስሜት ፊቱ ይጨፈገጉ ጀመር።
«የዚህ አይነቱ ወራዳ ከኔ ጎን ይሄዳል እንዴ!» ብሎ ወደ ፊት ቀደም አለ።

ሽፍታው ከሁለቱ ኋላ ኋላ ይከተላቸዋል። ሁለቱ ዒሳ እና ሀዋሪያው መንገዳቸውን ቀጥለዋል።

ዋሕይ መጣ።
«ለሁለቱም ንገራቸው፤ ከዚህ በፊት የሰሩትን ደምስሼዋለሁ።

ሀዋርያህ ባሳየው ንቀት ምክንያት ከዚህ በፊት የሰራው መልካም ተደምስሷል።

ሽፍታውም ባሳየው የመተናነስ ተግባር ያሳለፈውን ወንጀሎች አስደምስሷል» ብሎ በአንድ ጀምበር የአመታትን ታሪክ ቀየረ።



በዚህ መልኩ ተስፋ በቆረጡ ልቦች ውስጥ የሚነፍሰውን የእዝነት መአዛ አናፍሰህ፤ በአጉል ተስፋ የሚታለሉትን እንዲህ አደብ ታስይዛለህ። ተከተል!
👍
ተስፋ የመጭው ህይወትህ ህልውና ሲሆን፤ ፍራቻ ደግሞ ተስፋህን ቅርፅ የሚያስይዝልህ ማስመርያህ ነው።

ስገዛህ አድጌ፣ ስገዛህ ባረጅም
እዝነትህን እንጂ ስራዬን አላምንም።

ፀጉሬ እስኪነፃ ረቢ ባመልክህም
በካቲማው ጉዳይ አልተማመንም

ጅምሩን እንዳሻህ ባሰኘህ አኑረኝ
ግና ስንገናኝ ለከትም አሳምረኝ።

ኢብሊስ ትዕቢቱ ከእዝነት ክልል አስወጥቶት ቁጣው የተወሰነለት ለት ጂብሪል እና ሚካኢል ያለቅሱ ጀመር።

«ይህን ያህል ለቅሶ ምን ሁናችሁ ነው ምታለቅሱት?» ብሎ ጌታህ ጠየቃቸው።
«ያ ረብ! ለኛስ ምን እንዳዘጋጀህልን አላወቅንም።ፈርተናል» አሉት።
«እንዲሁ እንደፈራችሁ ቆዩ። ተጠንቀቁ» ብሎ ድንበሯን እንዳይስቱ አስጠነቀቃቸው።
👇
ዳዉድ ዐሰ ስህተቷን ከፈፀመ በኋላ ለዘመናት ቢያለቅስም ምንም ምላሽ ባለማግኘቱ ግራ ቢገባው፦ «ጌታዬ! ለቅሶዬን እንኳ እያየህ አታዝንልኝም?» ብሎ ተንሰቀሰቀ።

«ዳዉድ ሆይ! ሀፅያትህን ረስተሃት፤ ለቅሶህን ታወሳልኛለህን!?» ብሎ ወቀሰው።

ዳዉድም ዐሰ፦«አመጼን እንዴት እረሳታለሁ! እኔ አንተ በሰጠኸኝ ዘቡር ሳዜም እኮ ወራጅ ጅረቶች ይቆማሉ፣ የንፋስ ንፍሰቶች ይሰክናሉ፣ አዕዋፍ ከበላይ ያስጠልሉኛል፣ አራዊቲ ከምኩራቤ ይመሰጣሉ።

ኢላሂ! ሰዪዲ! ምን አይነት ባይተዋርነትን ነው በኔ እና ባንተ መካከል የጋረድከው!?» ብሎ ተዋደቀ።

አላህም፦ «ያ የመታዘዝህ ውጤት ነበር፤ ይህ ደግሞ የአመፅህ ባይተዋርነት ውጤት ነው።
ዳዉድ ሆይ! አደምን ተመልከት ከፍጥረቶቼ አንዱ ነው። በእጄ ፈጥሬ መንፈሴን ነፋሁበት።

መላዕክቶቼን ለክብሩ አስጎብድጄ፣ የልቅናን ልብስ አጎናፅፌው፣ የክብርን ዘውድ ከራሱ ብደፋለት ብቻዬን ቦዘንኩ ብሎ ሀዋን ድሬለት ከጀነት አነገስኩት።

ብዙም ሳይቆይ ቢያምፀኝ እርቃኑን የተዋረደ አድርጌ ከጉርብትናዬ አባረርኩት።

ዳዉድ ሆይ! አድምጥ፤ እውነት ነው የምነግርህ።
ታዘዝከን፤ ታዘዝንህ።
ጠየቅከን ሰጠንህ
አመፅከን አዘገየንህ
ከነ አመፅህ ብትመጣም ተቀባዮችህ ነን»

👇
ሀጃጅ ቢን ዩሱፍ ከሰዒድ ኢብኑ ጁበይር ዘንድ መጥቶ፦«ጭራሽ ስቀህ እንደማታውቅ ሰማሁ፤ ምን ነው አልክ?» ብሎ ጠየቀው።

«እንዴታ! ጀሀንም ተለኩሳለች፣ ሰንሰለቶቹ ተዘርግተዋል፣ የጀሀነም ወታደሮች በተጠንቀቅ ቁመዋል። እንዴት እስቃለሁ።»

«ሀሰን! እንዴት ነህ?» ብሎ ጠየቀው አንዱ ሀሰንን።
«ደህና ነኝ» መለሰለት።
«ኑሮ እንዴት ይዞሀል?» ሌላ ጥያቄ ደገመለት።
ሀሰን ረዐ ፈገግ አለ፦ «ስለ ኑሮ እየጠየቅከኝ ነው?
የሆኑ ሰዎች መርከብ ላይ ተሳፍረው፣ ባህሩ መሀል ሲደርሱ መርከቢቱ ተሰብራ እያንዳንዱ ሰው አንዳንድ ጣውላ ላይ ቢንሳፈፍ፤ ኑሮ እንዴት ያዘው ነው ሚባለው?»
«በመጥፎ ሁኔታ» አለው።
«የኔ የካቲማ ሁኔታ ከነሱ ስጋት የባሰ ነው»
ኢነ ጀሀነመ ለመውዒዱሁም አጅመዒን የምትለዋ የካፊሮች የማስጠንቀቅያ አንቀፅ በነቢ ሰለላሑ አለይሒ ወሰለም ላይ የወረደች ለት ሰልማን አል ፋሪሲይ ጭንቅላቱን በእጁ ይዞ እየጮኸ ጠፋ፣ ፈረጠጠ፣ 3 ቀን ሙሉ የደረሰበት አልታወቀም።

«ልጄ! በልጅነት እድሜህም በጉርምስና እድሜህም መልካምነትህን እንጂ ሌላ አላስተዋልኩም። ምን ተፈጥሮ ነው ሌት ተቀን እጌታህ ፊት ምታነባው?» ብላ እናት ልጇን ጠየቀች።

«እማ! ምናልባት የሆነ ወንጀል ስፈፅም አላህ አይቶኝ በልዕልናዬ እምላለሁ ይቅር አልልህም ብሎኝ ይሆናል ብዬ እኮ ነው» ሲል መለሰላት።

የሲራጥን ድልድይ ከጀርባህ ትተኸው እስክትሻገር ድረስ በትራስህ ረግተህ ልትተኛ አይገባም።
አስ - ሰሚዕ
ከአላህ ውብ ስሞች መካከል ሲሆን ትርጉሙም:- "የትኛውም ቋንቋ እና ጥሪ ሳይገድበው ድምፆችን(ድብቁንም ግልፁንም) ባጠቃላይ የሚሰማ ማለት ነው::"
👇👇👇👇👇👇
https://www.tgoop.com/tewihd
አላህ ብቻ የሚያውቃቸው የሩቅ ቁልፎች አምስት ናቸው

1ኛ.ነገ ምን እንደሚከሰት አላህ እንጅ ማንም አያውቅም

2ኛ.በማህጸን (በሽል)ውስጥ የተረገዘን አላህ እንጅ ማንም አያውቅም

3ኛ.ዝናብ መቼ እንደሚመጣ አላህ እንጅ አንድም አያውቅም

4ኛ. ማንኛዋም ነፍስ የት ቦታ ላይ እንደምትሞት አታውቅም

5ኛ.የቂያም ቀን መቼ እንደሆነ አላህ እንጅ ማንም አያውቅም …

እነዚህን እውቀቶች አላህ ብቻ የሚያውቃቸው መሆኑ ነብያችን ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም አስተምረውናል…

ምንጭ፦ [ሶሒሑል ቡኻሪ ፤ 4697 ]

https://www.tgoop.com/tewihd
⭕️ በሰዎች ዘንድ ያለህ እውቅና ምንም ያህል ቢልቅ በሚወዱህ ሰዎች መቀበርህ አይቀርም

⭕️ በሰዎች ዘንድ ደረጃህ ምንም ያህል ከፍ ያለ ቢሆን በሚያደንቁህና በሚወዱህ ሰዎች ዘንድ መረሳትህ አይቀርም።
ስለዚህም በህይዎትህ ውስጥ በየእለቱ «መልካም ፋናን በመልካም ስራህ አስቀምጥ»!!!!
💚
https://www.tgoop.com/tewihd
ማብራሪያ፡‐

⒈ተማኢም “ሂርዝ” ከዓይነ ጥላ ለመጠበቅ ከልጆች አንገት ላይ የሚንጠለጠል ነው። “የቁርአን አንቀጾች የተጻፉበት ከሆነ ይፈቀዳል፡፡” ይላሉ ከሠለፎች ከፊሎቹ። ሌሎቹ ደግሞ ኢብን መስዑድን ጨምሮ  መንገድ መክፈቱን አልወደዱትም። ሐራም እንደሆነ ይገልጻሉ፡፡

⒉“አዛኢም” በመባልም ይታወቃል ሩቃ። ሽርክ ያልሆነ እንዳለው የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ)፡- “ለአይነ ጥላና ለህመም (ትኩሳት/ንዳድ) ይፈቀዳል” ሲሉ ገልፀዋል፡፡

⒊“ቲወላህ” መስተፋቅር ነው። የባልና ሚስትን ፍቅር ይጨምራል ተብሎ ይታመናል በአድራጊዎች ዘንድ::

ምንጭ፡‐ ኪታቡ ተውሒድ ሸይኽ ሙሀመድ አብዱልወሃብ ረሒመሁላህ

ጆይን፡‐ https://www.tgoop.com/tewihd
⭐️ዙ ኑረይን ኦንላይን የቁርአን ማዕከል★ የብርሃን ጉዞ!

ባሉበት ቦታ ሆነው በተመቾት ሰዓት ለግሎ ኡስታዝ ተመድቦሎት ቁርዓንን የሚማሩበት


በቴሌግራም ለመመዝገብ📌
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@zunureynmedrsa
@Zunurey
🌐በዋትስ አፕ
👇👇👇👇👇👇📌
🎴+251987235671 +251995008580 ወይም +https://wa.me/qr/C7AYA66LHJPDJ1
«መንሃጅ» ማለት ምን ማለት ነው⁉️


✍️በቋንቋ ደረጃ:

«መንሃጅ» ማለት (ግልጽ የሆነ) «መንገድ» እንደ ማለት ነው።



አላህ በቁርአን ላይ እንዲህ ይላል፦
{لِكُلٍّ جَعَلْنا مِنْكُمْ شِرْعَةً وَمِنْهاجاً}"
"ከናንተ ለሁሉም ሕግንና መንገድን አደረግን:.."
((አል ማኢዳህ፡ 48))
*
ኢማሙ ጦበሪይ በተፍሲራቸው ላይ እንዲህ ይላሉ፥

"وأما"المنهاج"، فإنّ أصله: الطريقُ البيِّنُ الواضح، ... ثم يُستعمل في كل شيءٍ كان بيِّنًا واضحًا سهلاً"
"ሚንሃጅ የሚለውማ፦ መሰረቱ ግልጽና የተብራራ የሆነው መንገድ ነው።
ከዚያም በሁሉም ነገር ላይ ይተገበራል፤
ግልጽ፣ የተብራራና ቀላል ሆነ።"

((ተፍሲሩ ጥጦበሪይ፡ 10/384))
*
ገጣሚውም እንዲህ ይላል፤
مَــنْ يـكُ فِـي شَـكٍّ فَهـذَا فَلْـجُ
مَـــاءٌ رَوَاءٌ وَطَـــرِيقٌ نَهْــجُ
*
በእንግሊዝኛው "Methodology", "Syllabus", "Curriculum" የሚሉት ቃላት ይተኩታል።
በአጠቃላይ <<መንሃጅ>> የሚለውን ቃል መንገድ፣ ፈለግ፣ ፋና፣ ትውፊት፣ አካሄድ የሚሉት ቃላቶች እንደየ አገባቡ ይተኩታል።
*
✍️በሸሪዓዊ ደረጃ ደግሞ፤
````
እውቀታዊና ተግባራዊ በሆኑ የአምልኮ ተግባራቶች እንዲሁም
በሰዎች መካከል ስላለ መስተጋብር ሁሉ የአላህ ህግ (ሸሪዓዊ ብይን) የሚገለጽበት መንገድ ማለት ነው።
الطريق الذي يبين به أحكام الله في العبادات العلمية والعملية وفي المعاملة بين الناس .

*
👉ታዲያ በቃላዊ ደረጃ የተለያዩ መንሃጆች (መንገዶች) አሉ።

ለምሳሌ፦
የፈላስፎች መንገድ (መንሃጁል ፈላስፋ)፣
የሰለፎች መንገድ (መንሃጀ ስሰለፍ)፣
የሙስሊሞች መንገድ (ሚንሃጁል ሙስሊም) ወዘተ ይባላል።
*
✍️ነገር ግን እንደ አጠቃላይ እንደ ሙስሊም እኛ መከተል ያለብንና አርአያ አድርገን መያዝ ያለብን የመልካም ቀደምቶችን የሰለፎችን መንገድ ነው።
እርሱም "መንሃጁ ስ-ሰለፍነ ሷሊሕ" ይባላል።

ይህ መንሃጅ (መንገድ)፡
ነብያችንን ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም በመልካም የተከተሉ ሶሐቦች፣
ሶሐቦችን በመልካም የተከተሉ ታቢዒዮች፣
ታቢዒዮችን በመልካም የተከተሉ አትባዑ ታቢዒዮችንና ከዚያም በኋላ ያሉትን መልካም ቀደምቶች ያቀፈ ነው።

✍️ለምሳሌ፦
ሶሐቦች እንዳሉ ሆነው እነ ኢማም አቡ ሐኒፋ፣ ኢማሙ ማሊክ፣ ኢማሙ ሻፊዒይ፣ ኢማሙ አሕመድ፣ ቡኻሪ፣ ሙስሊም፣ ነሳኢይ፣ ኢብኑ ማጃህ፣ አቡ ዳውድ፣ ቲርሚዚይ፣ ሸይኹል ኢስላም ኢቡ ተይሚይያህ፣ ኢብኑ ቁዳማህ፣ ኢብኑ ዓብዱልበር፣ ኢብኑ አቢ ዱኒያ፣ ኢብኑል ቀይዩም፣ ኢብኑል ጀውዚይ፣ ሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ዓብዱል ወሃብ እና ሌሎችም።

✍️ከዘመናችን ታላላቅ እንቁዎች ውስጥ ደግሞ፥
ኢማም ኢብኑ ባዝ፣ ኢብኑ ዑሠይሚን፣ ኢማም አልባኒ፣ ሸይኽ ሙቅቢል፣ ሸይኽ ሙሐመድ አማን አልጃሚ፣ ሸይኽ ሰዕዲይ እና ሌሎችም።

✍️አሁን ላይ በህይወት ካሉት ውስጥ ደግሞ፥
ሸይኽ ዶ/ር ሷሊሕ ፈውዛን፣ ሸይኽ ረቢዕ አል መድኸሊይ፣ ሸይኽ ዶ/ር ሙሐመድ ሰዒድ ረስላን፣ ሸይኽ ዶር ፕሮፌሰር ሱለይማን አር-ሩሐይሊ፣ ሸይኽ ዶ/ር ፕሮፌሰር ዓብዱረዛቅ አልዐባድ፣ ሸይኽ ሱሐይሚይ፣ ሸይኽ አሊ አደም፣ አል-ሸይኽ እና ሌሎችም።



*
✍️እነዚህ ከዋክብቶች በመንሃጀ ስሰለፍ (በቀደምቶች ትውፊት፣ ፋና) ላይ ያሉ ናቸው።
ቁርአንና ሐዲሥንም እነዚያ ቀደምቶች በተረዱትና ተግብረውት በነበረው ነገር ይረዳሉ፣ ይተገብራሉ።
አስተምህሯቸውም ከነርሱ ያፈነገጠ አይደለም።
በዚህም የተነሳ አህሉ ሱንና ወልጀመዓ ይሰኛሉ።
ሱንናን አጥብቀው በመያዝ በሐቅ ላይ የተሰባሰቡ ናቸውና።



*
👉ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ በእስልምና ሽፋን የተለያዩ የጥመት አንጃወች እንደ አሸን ፈልተዋል።
ከቀደምት ሰለፎች መንሃጅ ውስጥ የሌለን አካሄድ በመሄድ፣
የራሳቸውን መንገድ ቀይሰው እየሄዱ ነው።
ከነዚህ ከተፈለፈሉ መንሃጆች ውስጥ

ለምሳሌ:
~~~~~~~
የሺዓ መንሃጅ፣ የአሕባሽ መንሀጅ፣ የሱፍያ መንሃጅ፣ የኢኽዋን መንሃጅ፣ የተብሊግ መንሃጅ፣ የሐዳድያ መንሃጅ፣ የጀህምያ መንሃጅ፣ የአሻዒራ መንሃጅ፣ የሙዕተዚላ መንሃጅ፣ የኸዋሪጅ መንሃጅ፣ የተክፊር መንሃጅ ወዘተ የመሳሰሉት፣
ሁሉም ከአህለ ሱንና ወል ጀመዓ ያፈነገጡና ከሰባ ሁለቱ ጠፊ ቡድኖች ውስጥ የሚካተቱ ናቸው።

እነዚህ በውጭ ሃገር ብቻ የሚገኙ አይደሉም።
በሃገራችንም ውስጥ አሉ።

✍️ለምሳሌ፦
ኢኽዋን የሚባሉት ቡድኖች
አንድን ህዝብ በመሪህ ላይ አምጸህ ውጣ ብለው ለከፋ ችግር ሲዳርጉት በየሃገሩ ይስተዋላል።
በሰላማዊ ሰልፍ፣ ከዲን ይልቅ በስልጣን ጥማት የተነሳ የፖለቲካ ፍትጊያ መገለጫቸው ነው።
አብዛኛውን ጊዜ ሚዲያ ያገነናቸውና በሰፊው የዋህ ህዝብ ዘንድ ታዋቂነት ያላቸው ሰዎች በብዛት ይገኙበታል።


*
✍️አህለ ሱንና ወል ጀመዓዎች የተለያዩ መጠሪያዎች አሏቸው።
ለምሳሌ፥
በቀደምቶች ትውፊት ላይ የሚጓዙ ስለሆነ ሰለፍዮች ይባላሉ።
ከእሳት የምትድነዋ አንዷ ብቻ ስለሆኑ <<ፊርቀቱ ናጂያህ>> ይባላሉ።
"ጧኢፈቱ መንሱራም" ይባላሉ።
ሁሉም መልካም ገለጻዎች ስለሚገልጿቸው ነው።



*
*
✍️ስለዚህ ከእኛ የሚጠበቀው፣
ሁሉንም ከሱንና ያፈነገጡ፣ የሰለፎችን መንሃጅ (መንገድ፣ ትውፊት) የሳቱ ቡድኖችንና ግለሰቦችን በመራቅ፤
በትክክለኛው የቀደምቶች (የሰለፎች) መንሃጅ ላይ ጸንቶ መጓዝ ነው።
ቁርአንና ሐዲሥንም እነርሱ ተረድተው በኖሩበት መንገድ መኖር ነው።

መርሃችን «ቁርአንና ሐዲሥን በመልካም ሰለፎች አረዳድ መረዳት መሆን አለበት።»
መንሃጃችንም የሰለፎች መንሃጅ ይሰኛል።
ለነርሱ የበቃው ይበቃናል።

ወደ ሰለፎች በተግባሩና በንግግሩ የተጠጋም "ሰለፍይ" ይባላል።
አንድ ሰው "ሰለፍይ ነኝ!" ሲል "ሙስሊም አይደለሁም!" ማለቱ አይደለም።
እንዳውም ለሙስሊምነቱ ምንም ጥርጥር የለውም።

"እያንዳንዱ ሰለፍይ ሙስሊም ነው።
እያንዳንዱ ሙስሊም ነኝ ባይ ግን "ሰለፍይ" ሊሆን አይችልም።"
አንዳንዶች <ሰለፍያ> ሲባሉ ይደነግጣሉ።
ሰለፍያ ማለት ግን የሰለፎች (ማለትም የሶሐቦችና የታቢዒዮች) መንገድ ነው።
👇⤵️👇⤵️👇⤵️👇
@tewihd
🫵አንተ የሰራከውን ወንጀል ብቻ ሳይሆን የሰዎችንም ወንጀል ትሸከማለክ።
መቼ

ለዚህ ቁርኣን መልስ ይሰጥካል አላህ እንዲህ አለ ፦
وَلَيَحْمِلُنَّ أَثْقَالَهُمْ وَأَثْقَالًا مَّعَ أَثْقَالِهِمْ وَلَيُسْـَٔلُنَّ يَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ عَمَّا كَانُوا۟ يَفْتَرُونَ

ሸክሞቻቸውንና ከሸክሞቻቸው ጋር (ሌሎች) ሸክሞችንም በእርግጥ ይሸከማሉ፡፡ በትንሣኤም ቀን ይቀጥፉት ከነበሩት በእርግጥ ይጠየቃሉ፡፡

ይህ ማለት በተለያዩ ሶሻል ሚዲያዎች ላይ የምታሰራጨው:  ዘፈን ፣ቪዲዮ ብቻ ምናለፋክ አንተ የላካቸውን መጥፎ ነገሮች  ሰዎች ከፈፀሙት የነዚህን ሰዎች ወንጀል ትሸከማለክ።
    አላህ ባንተ ምክንያት ዘፈን በሰሙ ሰዎች ይተሳሰብካል።
            ባንተ ምክንያት መጥፎ ነገር ባዩ ሰዎች ወንጀል አንተን ይተሳሰብካል።
  
   👉ወንጀሌ ይብቃኝ አትልም🤚

  ስለዚህ ተጠንቀቅ  ወንድሜ ❗️


https://www.tgoop.com/tewihd
2025/07/09 14:41:51
Back to Top
HTML Embed Code: