tgoop.com/TheHabesha0/1701
Last Update:
.... እማ ምን ብናደርግልሽ ትደሰቻለሸ?የቀድሞውን ብንመልስ እማ እስቲ ንገሪኝ የቀድሞዎቹ ጀግኖችሽ ዛሬን ቢያዩ ምን ይላሉ? ምን የሚሉ ይመስልሻል? እኔስ ትዝታ በሚሉት ልጓም በሌለው ፈረስ የኃሊት አሻግሬ ትላንትን ሳያት ብኖራት ናፈኩ እነዛን ጀግኖች ማየት ናፈኩ እማ እውነት ነው ለካ ፈረስ ያደርሳል እንጂ አይዋጋም የሚባለው እኔንም ልክ እንደዛ በትዝታ ፈረስ ወደ ኃላ ቢመልሰኝም ከማለም በቀር መኖርን ግን አልቻልኩም። እማ ካልሰማሽ አንድ ነገር ልንገርሽ አንዱ በዓለም የታወቀ ሄሮዶተስ የተባለ የታሪክ አባት በአንድ ወቅት ምን አለ መሰለሽ
<<...በኢትዮጵያ እጅግ ያማሩ ደመ-ግቡ ቆንጆዎችና ውብ ሰዎች አሉባት። ርህራሄያቸውም እንደ እግዚአብሔር ነው። በመንገድ ለሚያልፍ ሰው የሚሆን ድግሥ ያሰናዳሉ። ምንም ቢሆን መንገደኛ የሚበላውን አያጣም። በእድሜያቸውም ከመቶ እስከ መቶ ሀያ፣ እስከ መቶ ሰላሳም ይኖራሉ። ነውርና ክፉ ነገር በአገራቸው የተጠላ ነው። የጤና ምንጮች የሆኑ ውሀዎች (ወንዞች) ስላሏቸው በጠጣጧቸው ጊዜ ሰውነታቸው ይታደሳሉ። በሀብትም እጅግ የበለፀጉ ናቸው።...>>
ሰማሽ እናቴ ደስ አይልም ግን ዛሬ ቁጭ ብዬ ስላንቺ እያሰብኩኝ ከዘመኑ ትውልድ እንደድሮው የሚጋደልልሽ ብፈልግ ብፈልግ በላይ ዘለቀን፣ አብዲሳ አጋን የመሰሉ ጀግኖችን አጣሁ የኢትኤል ሀገር ሆይ አንድ ጀግና ሲሞት እንደዚ ብሎ ነበር መፅሀፎችን ሳገላብጥ ነው ያየሁት
"ሀገሬ አጥፍቼ እንደሆነ ፈጣሪ ነፍሴን አይቀበላት ያላጠፋሁ እንደሆነ ግን ወንድ አይብቀልብሽ "ብሎሻል አሉ
እና እርግማን ነው ትውልዱን ያሰረው የድሮ ታሪክሽን ፍቆ በአዲስ መጥፎ ታሪክ የቀየረው ማነው? ከአባቶቻችን ጋር የሚያገናኘውን ድልድይ የሰበረው ማነው? ታሪካችንን እንዳናውቅ የጋረደን ማነው? ለዚ ሁሉ ተጠያቂ ማነው? እማ እባክሽን ንገሪኝ?🙏😭😭😭😭 እማ ስላንቺ ባወራ እኮ አልጠግብም የትኛውን አውርቼ የትኛውን ልተው "ሁሉን ቢያወሩት ሆድ ባዶ ይቀራል" ይላል አንድ ወዳጄ ታውቂያለሽ አንድ ነገር እርግጠኛ ነኝ እነዛን ጀግኖቾ የወለደች ማህፀን ዛሬም አልነጠፈችም ለሁሉም ጊዜ አለው አይደል ያለው ጠቢቡ ሰለሞን ያንቺም ቀን ይመጣል። እንዳትጠራጠሪ ተስፋን እኮ ካንቺ ነው የተማርኩት ለዛሬ ይብቃኝ አይደል? ሌላ ጊዜም እንደዚሁ እፅፍልሻለሁ። ያንቺው ትላንትን ናፋቂ ፤ ዛሬን ኗሪ፤ ነገን ደግሞ አላሚዋ ልጅሽ ኢትኤል ነበርኩ።
"አንገትሽ ራስሽን ችሎ ልየውና ማግስቱን ይውሰደኝ አስር ሞት ይምጣና"
💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️
ቻናሉን ለመቀላቀልና የተለያዩ ነገሮችን ለማግኘት
👉@TheHabesha0👈
👉@TheHabesha0👈
BY የካሌብ ጽሑፎች
Share with your friend now:
tgoop.com/TheHabesha0/1701