tgoop.com/TheHabesha0/1702
Last Update:
መልካም ጥሩ ነው እውነት በጣም ጥቂት ከጥቂትም በጣት የምትቆጠሩ ቤተሰቦች የተሳተፋችሁበት ውይይት ነበር እናም አንዱ የእኔነት የያገባኛል ይመለከተኛል የመሰማት ስሜት ነው አንዱ የሐገር ፍቅር መገለጫ እውነት ነው ሁሉም ሰው እንዳላችሁት አመለካከቱ እንደየመልኩ ይለያይ ይሆናል ግን በየትኛውም ዘመን እና ሐገር ያሉ ሰዎች ከስልጣኔያቸው ጀርባ ሐገርራዊ #አንድነት አላቸው /ነበራቸው/ ይሄ የሚያስማማን ይመስለኛል እንደእኔ አስተሳሰብ...
እና ታድያ የቱ ጋር ነው የማንለያይበት ቦታ?? እኔ እንደዚህ እሱ እንደዛ የማንባባልበት ፅንፋችንስ ወዴት ነው ??? ይሄ ሁሉ ውድቀትና ውርደት እንደሐገር በዘመናት እየወረደ የመጣው ተቆጥሮ የማያልቀው እጢ እኮ የጀመረው አንድነታችንን ቀድሞ በመምታት ላንመለስ ወደምንለያይበት ፍጹም ሀገራዊ ልዩነት ውስጥ ኢትዮጵያዊነትን ከሁሉም ነገሮችና ምክንያቶች በታች ዝቅ አድርገው አውርደውና አዋርደው ከጢሻ ስር ጥለው ከጨረሱ በኋላ ያንን የዘቀጠ አመለካከትና ፍልስፍናቸውን ሲግቱን ነበር!
ታድያ በዚህ ሰዓት በሀሳብ በአመለካከታችን ውስጥ ባለው እይታ ሐገራዊ አንድነታችንን እያንዳንዳችን በግል ባለን ስብዕና ግንባታ ውስጥ ትኩረት ብናደርግና ብስለት በጎደለን ቦታ ላይ ቆም ብለን ብናስብ መልካም ይመስለኛል እውነት ግን ቤተሰብ ማውራትና መወያየት ምንም ፋይዳ የማይሰጥበት ሐገር ዘመንና ወቅት ላይ ስለተቀመጥን ብቻ ያ ትልቁ የኢትዮጵያዊነት መንፈሳችን በአቧራ አይጋረድ በፈተናዎቻችን አይጋረድ
ወንድም እህቶቼ ይህንን ፅሁፍ የምታነቡ ኢትዮጵያን የእናቴ ልጆች ሆይ ኑ እንስማማ ኑ እንታረቅ ኑ እንተማመን
ስለ አርማዋና ፩ ፈጣሪዋ እለምናችኋለው! እንንቃ ካንቀላፋንበት!
⚠️ከቻላችሁ ሰዎች በምክንያታዊነት ያመዘነ ከፍጹም አሉታዊ ስሜቶች የፀዳ የሰውን ልጅ ክብር ከሚነካና ከሚያዋርድ አስተሳሰብ የራቀ ቅንነትና ትህትና በሞላው የኢትዮጵያዊነት መንፈስ የፈለጋችሁትን ጥግ ይዛችሁ አሁንም ሐሳባችሁን አስቀምጡ! እውነት የሚማርበት ሰው አይጠፋም እኛ ከልባችን ከወጣ ሌላው ልብ ላይ የማይገባበት ምክንያት ያለ አይመስለኝም! / ካሌብ ነበርኩ/ @kalebo19King ከተሳሳትኩ ለመታረም ካላወቅኩ ለማወቅ ዝግጁ ነኝ !
የመወያያ ስብስባችን /Group/ ውስጥ ያልተቀላቀላችሁ በዚህ መስፈንጠሪያ( link) ውስጥ በመግባት ውይይታችንን መቀላቀል ለሌሎችም ማጋራት /Add,Share,forward ማድረግ ይቻላል! 👇👇👇 https://www.tgoop.com/ye_kaleb_tsehufoch
♥ ኢትዮጵያ ሁን
♥ አፍሪካሁን
♥ ሰው ሁን
🔊 ይህንን ድህረ-ገጽ ለመቀላቀል👇
@TheHabesha0 @TheHabesha0
@TheHabesha0 @TheHabesha0
BY የካሌብ ጽሑፎች
Share with your friend now:
tgoop.com/TheHabesha0/1702