tgoop.com/TheHabesha0/1726
Last Update:
#የካሌብ_ፅሁፎች
ሰላም ለእናንተ ይሁን! እንዴት አላችሁ ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች እስኪ በአሁኗ ሰዓት ላይብረሪ ውስጥ ተቀምጬ በሓሳብ ጭልጥ ብዬ የሞነጫጨርኳትን ግጥም አይሉት ብሶት ድርሰት አይሉት እልህ ብቻ ከዓቅሜ እና ጠባብ እውቀቴ በላይ ስለሆነችው ስለ....
እናት ሃገር ኢትዮጵያዬ 💚💛❤️አጠር ያለች ጽሁፌን ላካፍላችሁ መልካም ንባብ.....
ምን ተብሎ እንደሚጀመር እንኳን በቅጡ የማላውቅ ሰው ደፍሬ ስላንቺ ስለጻፍኩ በመጀመሪያ ይቅር በይኝ ....እናም ምን ልበልሽ እማ ???
የገነት ምሳሌ የአዳም አሻራ
የሆነሽ ሃገራችን ። እምዬ አንቺ እኮ ምሥራቅ ነሽ የፀሐዩ መውጫ! እባክሽ <<የሚያደርጉትን አያውቁም እና ይቅር በላቸው>> እያልሽ በተሰበረው ልብሽ ቃተሽ ለምኝልን። ከእሳቱ ጥፋት አሳልፊን እማ🙏
.....ግን እኮ ያወቅን መስሎን ነው!ብንዘልፍሽ ደግሞ ክብርም ስለሌለን እንጂ ልክሽን አውቀን አይምሰልሽ... የእውነት ያንቺን ክብር..... በጥቂቱ እንኳ የተረዱት እማ ከሕመምሽ መርጠው መርገፍን ወደዋል በፍቅርሽ
!! እኛ እኮ እውነት ስለሌለን አይደል ያጣነው እውነትሽን!? የያዝነው ሐይማኖት እንጂ የታለን እምነቱ ምንስ ነበረበት እሩቡን ቢያውሰን ከጥንቱ ???ለነገሩ እሱ መች ከልክሎን መርጠን እንጂ ባቢሎንን😭
...ቢሆንም የጥፋት ማሰናከያ ስላለ መሐላችን ስለታወረም ብርህ ህሊናችን ስለቀረበም ጥፋታችን ስለከፋ ሐጥያታችን ከበፊቱ ይልቅ ዛሬ አልቅሽልን!😭 ለምኝልን እጅሽን ዘርግተሽ ጸልይልን ለሚሰማሽ ፈጣሪያችን 🙏
ብቻ ይቅር ብለሽ ጥሪን/ኝ የእነ ኢትኤል የእነ ሄኖክ ሃገር....ቀና ብለሽ የተነሳሽ እና ያየሁ እለት ይውሰደኝ አምላክሽ እኔ ለአሑኑ በዚህ አበቃሁ 👐
📣ቻናሉን ለመቀላቀልና የተለያዩ ነገሮችን ለማግኘት👇
👉 @TheHabesha0 👈
👉 @TheHabesha0 👈
BY የካሌብ ጽሑፎች
Share with your friend now:
tgoop.com/TheHabesha0/1726