Forwarded from חֶסֶד
ዕለት ዕለት ስለምናደርጋቸው ከማወቅ እንጀምር።
ከትላንት ዘግይተናል ከነገ ግን አናረፍድም።
መልካም ፆም።
ከትላንት ዘግይተናል ከነገ ግን አናረፍድም።
መልካም ፆም።
††† እንኳን ለዓለም ሁሉ መምሕር ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ እና ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
††† ለቤተ ክርስቲያን የብርሃን ምሰሶ ስለሆነላት ስለ ታላቁ ሐዋርያዊ ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ምን እላለሁ? ምንስ እናገራለሁ? እንደ እኔ ያለ ኃጥእ: ለባሴ ሥጋና ገባሬ ንስሃ ስለሱ ሊናገር አይቻለውምና:: አባቶቻችን እንደ ነገሩን ስለ አፈ ወርቅ ለመናገር አፈ ወርቅ መሆን ያስፈልጋል:: እስኪ በቅዱሱ አባት ምልጃ ጥቂት ልሞክር::
††† ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ማን ነው?
††† ነገዱ ከሶርያ: የተወለደው በ347 ዓ/ም በእስክንድርያ ሲሆን አባቱ አስፋኒዶስ እናቱ ደግሞ አትናስያ ይባላሉ:: እነርሱ ደግ ቢሆኑ ይህንን እንቁ ልጅ እግዚአብሔር ሰጣቸው:: ዮሐንስ ለክርስቲያን እንደሚገባ በትምሕርትና በጥበብ አደገ:: ገና በሕጻንነቱ ወደ ግሪክ ሔዶ የዘመኑን ሳይንስ (ፍልስፍና) ከአፉ እስከ ገደፉ ተምሮ ተመልሷል::
ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅን ለየት ከሚያደርጉት ነገሮችም አንዱ ይሔው ነው:: በዘመናዊም ሆነ በመንፈሳዊ ትምሕርት ይህ ቀረህ የማይሉት ሊቅ የሆነው ገና በ15 ዓመቱ ነበር:: በ2 ወገን የተሳለ ሰይፍ በመሆኑ ስንኩዋን በሕይወተ ሥጋ እያለ ዛሬም ለንፉቃን ትልቅ የራስ ምታት ነው::
ቅዱሱ ገና በ16 ዓመቱ ሃብት: ንብረት: ውበት: ክብርና እውቀት የሞላለት ቢሆንም ያለውን ሁሉ ለነዳያን ሰጥቶ መጻሕፍትን ብቻ ሰብስቦ ከባልንጀራው ቅዱስ ባስልዮስ ጋር በርሃ ገባ:: ሰውነቱን በጾምና በጸሎት እየቀጣ በበርሃ ሲኖር ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስና ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ዼጥሮስ ወደ እርሱ መጡ:: ሊቀ ሐዋርያት የመንግስተ ሰማያትን መክፈቻ ስልጣን ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌሉን ሰጥተው ተሰወሩት::
ከዚህች እለት በሁዋላ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ባሕረ ምስጢራት ሆነ:: ብሉይ ከሐዲስ: ከኦሪት ዘፍጥረት እስከ ራዕየ ዮሐንስ ድረስ በአንድምታ ትርጉዋሜ ተነተናቸው:: በተለይ ሐዲስ ኪዳንን እየመላለሰ አመሰጠረው:: ቅዱስ ሕሊናው ሳይታክት: ንጹሕ እጆቹ ሳይዝሉ የጻፋቸው ድርሳናት: መልዕክታትና ትርጉዋሜያት ቢቆጠሩ አሥር ሺህ ሞሉ:: በእውነት ለዚህ አንክሮ ይገባል! የሚገርመው ይህን ሁሉ ሲሰራ እድሜው ገና ለጋ: ማዕርጉም ዲቁና ነበር::
ከዚህ በሁዋላ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ቅስና ተሹሞ በስብከተ ወንጌል ብዙ ቦታዎችን አዳረሰ:: በቅድስናው ወደውታልና የቁስጥንጥንያ ፓትርያርክ አድርገው ሾሙት:: አፈ ወርቅ ሲናገርም ሆነ ሲያስተምር እንኩዋን የሚያወራ ኮሽ የሚል የለም:: ከጣዕመ ትምሕርቱ የተነሳ ሕዝቡ በተደሞ ይሰሙት ነበር:: ሲያስተምር ምድራዊው ሰው ይቅርና ልዑላኑ መላእክት ተሰብስበው ያደንቁት ነበር:: አንዴም እመቤታችን በሕዝብ መካከል አፈ ወርቅ ብላ ጠርታዋለች:: ለዛም ነው አፈ ወርቅ የሚባለው:: ቅዱሱ በሥልጣነ ቃሉ መልዐከ ሞትን ገስፆ 10 ዓመት አቁሞታል::
ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ለሰው ፊት አያደላም:: በርሱ ዘንድ ንጉሥና ደሃ ነዳይ እኩል ነው:: ለሞት ያበቃውም ይሔው ነበር:: ምክንያቱም የወቅቱ ንግስት አውዶክስያ ያንዲት ድሃ መበለትን መሬት ቀምታ አልመልስም በማለቷ መክሮ አወገዛት:: እርሷ ግን ከኃጥአንና መናፍቃን ጋር መክራ 2 ጊዜ አጋዘችው:: በተሰደደበት ሃገር ፍሬ አፍርቶ: አስተምሮና አሳምኖ በ407 ዓ/ም አርፏል:: ቤተ ክርስቲያንና ምእመናን ሳይጠግቡት እንደናፈቁት በ60 ዓመቱ አጡት:: በወቅቱ ታላቅ ሐዘንና ለቅሶ ተደረገ::
አንድ ቀን የዘመኑ ደግ ንጉሥ አርቃድዮስ ግብር አገባ:: (ግብዣ አዘጋጀ) በዚያች ሌሊት ደግሞ ቅዱሱ ሊቅ ታጥቆ ሲጸልይ ሳለ: አባ ማርዳሪ የሚባል ጻድቅ ደግሞ 12ቱ ሊቃነ መላእክት (እነ ቅዱስ ሚካኤል) ከሰማይ በግርማ ሲወርዱ ተመለከተ::
ደንግጦ "ወዴት ናችሁ ጌቶቼ" ቢላቸው "ቁስጥንጥንያ: ወደ ዮሐንስ አፈ ወርቅ እንሔዳለን:: እርሱ እመቤታችንን እንደሚያመሰግናት ጌታ ነግሮናልና" አሉት:: "እባካችሁ እኔም የአፈ ወርቅ ምስጋናው እንዲገለጥልኝ መርቁኝ" አላቸው:: ሊቃነ መላእክቱም መርቀውት ጐዳናቸውን ቀጠሉ::
በማግስቱ በቤተ መንግስት ውስጥ ሊቃውንቱ: መሳፍንቱ: ዻዻሳቱ: ሕዝቡ ሁሉ ተሰብስበው ከድግሱ በሉ:: ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ግን በመንበሩ ተቀምጦ ነበር እንጂ አልበላም:: ድግሱ ሲጠናቀቅ ንጉሡ አርቃድዮስ ሊቁን "ጥያቄ አለኝ" ብሎ በጉባኤ መካከል ጠየቀው::
"ምነው ወንጌላዊ ማቴዎስ 'ኢያዕመራ ዮሴፍ እስከ አመ ወለደት ወለደ ዘበኩራ - የበኩር ልጇን እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም' ማለቱ (ማቴ. 1:25) ስለ ምን ነው?" ቢለው ቅዱሱ ተነስቶ: በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ ይተረጉምለት ጀመር::
"ድንግል ማርያም ንጹሕ ብርሌን ትመስላለች:: ብርሌ የተለያየ ቀለም ያለው ፈሳሽ ቢያስገቡበት ቀለሙ አብሮ ይቀያየራል:: እመቤታችንም ጌታን ጸንሳለችና ሕብረ መለኮቱ ሲለዋወጥ መልኩዋ አብሮ ሲለዋወጥ እያየ ዮሴፍ ይደነግጥ ነበር::
'እርሷ ማን ናት? በማሕጸኗ ያለውስ ማን ነው?' እያለ ይጨነቅ ነበር:: ጌታን ከወለደች በሁዋላ ግን አንድ ሕብረ መልክ ሆናለችና:: አስቀድሞ ማን እንደ ነበረች አላወቀም::
አሁን ግን እርሷም ወላዲተ አምላክ: ልጇም አምላክ ዘበአማን መሆኗን አወቀ ማለት ነው" እያለ ሲተረጉም ሰምተው ሁሉም ሲያደንቁ: በዚያ የነበረች ስዕለ አድኅኖ "አፈ ወርቅ! ልሳነ ወርቅ! አፈ በረከት!" ስትል ተናገረች::
ያን ጊዜ አርቃድዮስ የወርቅ ልሳን በሊቁና በስዕሏ ላይ አደረገ:: አፈ ወርቅ ግን ባጭር ታጥቆ "እሰግድ ለኪ! እሰግድ ለኪ! ወእዌድሰኪ . . ." ብሎ ዛሬ በተአምረ ማርያም የምናውቀውን ምስጋና ሰተት አድርጐ አደረሰላት:: ይህንን ምስጋናም ሊቃነ መላእክቱ ሰምተው እያደነቁ ወደ ሰማይ ወጥተዋል::
ሊቁ ባረፈ በ35 ዓመቱ በትንሹ ቴዎዶስዮስ ዘመን: በዚህ ቀን ሥጋው ፈልሷል:: ወደ ቁስጥንጥንያ ሲደርስም ከናፍቆት የተነሳ ታላቅ ዝማሬና እንባ ተደርጉዋል:: አፈ ወርቅም ቀና ብሎ ሕዝቡን ባርኩዋል::
††† ቅዱሱ ሲጠራ እንዲሕ ነው:-
*ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
*አፈ በረከት
*አፈ መዐር (ማር)
*አፈ ሶከር (ስኩዋር)
*አፈ አፈው (ሽቱ)
*ልሳነ ወርቅ
*የዓለም ሁሉ መምሕር
*ርዕሰ ሊቃውንት
*ዓምደ ብርሃን (የብርሃን ምሰሶ)
*ሐዲስ ዳንኤል
*ሊቀ ዻዻሳት ዘበርትዕ (እውነተኛው)
*መምሕር ወመገስጽ ዘኢያደሉ ለገጽ
*ጥዑመ ቃል - - -
††† ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ ኢትዮጵያዊት †††
††† ቆራጧ እናታችን ቅድስት ወለተ ዼጥሮስ ለእኛ ለኢትዮዽያውያን የተዋሕዶ አማኞች ሞገሳችን ናት:: እጅግ የሚደነቅ መንፈሳዊ አርበኝነትን በካቶሊኮች ላይ አሳይታለችና::
ቅድስት ወለተ ዼጥሮስ የተወለደችው በ16ኛው መቶ ክ/ዘመን በምሥራቅ ኢትዮዽያ ዳውሮ አካባቢ ነው:: ወላጆቿ ባሕር አሰግድና ክርስቶስ ዕበያ ይባላሉ:: ክርስትናን በሚገባ አጥንታ አድጋ: በወላጆቿ ፈቃድ በሥርዓቱ ባል አገባች:: ግን ወዲያው አፄ ያዕቆብ ገደሉባት::

ወላጆቿም ግድ ብለው ስዕለ ክርስቶስ የተባለ የሱስንዮስን የጦር መሪ አጋቧት:: እስከ 24 ዓመቷም ልጆችን ወለደች:: በዚህ ሁሉ ጊዜ የጾምና የጸሎት ሰው ነበረች:: አፄ ሱስንዮስ ተዋሕዶን ክዶ ካቶሊክ በሆነ ጊዜ ባሏ ወደ ንጉሡ እምነት ገባ::በዚህ ስታዝን ይባስ ብሎ ጠዳ ላይ የአቡነ ስምዓን (ዻዻሱን) ልብስ ግዳይ ይዞ ቀረበ:: እርሷም ልቧ ቆረጠ:: ፈጣሪ 3ቱን ልጆቿን አከታትሎ ወሰደ:: ደስ ብሏት ጠፍታ ሳጋ (ዛሬ ገዳሟ ያለበት) ገባች:: ቀጥላም መነኮሰች::
ከዚህ በሁዋላ እየዞረች መናፍቃን ስታሳፍር: ሕዝቡን ስታጸና ዓመታት አለፉ:: በሷ ስብከትም ብዙ መነኮሳትና ምዕመናን ሰማዕት ሆኑ:: እሷም በየገዳማቱ ተንከራተተች:: በደዌ ተሰቃየች:: በንጉሡ ተይዛ 2 ጊዜ ወደ በርሃ ተሰደደች::
ፋሲል ነግሶ: ሃይማኖት ተመልሶ ሃገር ሲረጋጋ ወደ ምጽሊ: ከዚያም ወደ መንዞ መጥታ ገዳም መሥርታ: መናንያንን ሰብስባ: ስታጽናና ኑራለች:: በተወለደች በ50 ዓመቷም በ1630ዎቹ መጨረሻ አካባቢ ዐርፋ ተቀብራለች:: የተጋድሎ ዘመኗም 26 ዓመታት ናቸው:: ቅድስት ወለተ ዼጥሮስ ሰማዕትም ጻድቅም ናት::
††† የጥቡዓን አምላክ የሊቁን ምሥጢር: የቅድስቷን መጨከን: ከበረከታቸውም ይክፈለን::
††† ኅዳር 17 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ (ፍልሠቱ)
2.ቅድስት ወለተ ዼጥሮስ ኢትዮዽያዊት
3.አባ ሲኖዳ (ዘደብረ ጽሙና - ጐጃም)
4.ጻድቃን እለ ወጺፍ
5.ቅዱሳን አብርሃምና ሐሪክ
6.ቅድስት ወለተ ዻውሎስና ወለተ ክርስቶስ
††† ወርኀዊ በዓላት
1.እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት
2.ያዕቆብ ሐዋርያ
3.መክሲሞስና ዱማቴዎስ
4.አባ ገሪማ
5.አባ ዸላሞን
6.አባ ለትጹን
7.ቅዱስ ኤዺፋንዮስ
††† "በድካምና በጥረት: ብዙ ጊዜም እንቅልፍ በማጣት: በራብና በጥም: ብዙ ጊዜም በመጦም: በብርድና በራቁትነት ነበርሁ . . . የቀረውን ነገር ሳልቆጥር ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው::" †††
(2ቆሮ. 11:23)
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

††† ❇️እንኳን ለ24ቱ ቅዱሳን ካህናተ ሰማይ እና ቅዱስ አዝቂር ሰማዕት ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††
†††✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††✝
††† ሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ †††
††† እግዚአብሔር ቅዱሳን መላእክትን ሲፈጥራቸው በነገድ መቶ (100): በክፍለ ነገድ አሥር (10) አድርጓቸዋል:: አቀማመጣቸውንም በሦስት ሰማያትና በ10 ከተሞች (ዓለማት) አድርጓል::
††† መላእክት ያሉባቸው ከተሞች ከታች ወደ ላይ "ኤረር: ራማና ኢዮር" ይባላሉ:: አሥሩ ክፍለ ነገድ ደግሞ ከነ አለቆቻቸው ይህንን ይመስላሉ:-
1."አጋእዝት" (የቀድሞ አለቃቸው ሳጥናኤል: አሁን የተረፉት በቅዱስ ሚካኤል ሥር ናቸው)
2."ኪሩቤል" (አለቃቸው ኪሩብ)
3."ሱራፌል" (አለቃቸው ሱራፊ)
4."ኃይላት" (አለቃቸው ሚካኤል)
5."አርባብ" (አለቃቸው ገብርኤል)
6."መናብርት" (አለቃቸው ሩፋኤል)
7."ስልጣናት" (አለቃቸው ሱርያል)
8."መኳንንት" (አለቃቸው ሰዳካኤል)
9."ሊቃናት" (አለቃቸው ሰላታኤል)
10."መላእክት" (አለቃቸው አናንኤል) ናቸው::
††† ከእነዚህም:-
*አጋእዝት: *ኪሩቤል *ሱራፌልና *ኃይላት መኖሪያቸው በኢዮር (በ3ኛው ሰማይ) ነው::
*አርባብ: *መናብርትና *ስልጣናት ቤታቸው ራማ (2ኛው ሰማይ) ነው::
*መኳንንት: *ሊቃናትና *መላእክት ደግሞ የሚኖሩት በኤረር (በ1ኛው) ሰማይ ነው::
መላእክት ተፈጥሯቸው እምኀበ አልቦ ኀበ ቦ ነው:: አይራቡም: አይጠሙም: አይዋለዱም: አይሞቱም:: ተፈጥሯቸውም ረቂቅ ነው:: ተግባራቸውም ዘወትር "ቅዱስ: ቅዱስ: ቅዱስ" እያሉ ፈጣሪያቸውን ማመስገን ነው:: ምግባቸውም ይሔው ነው::
ዕረፍት ብሎ ነገርን አያውቁም:: "አኮቴቶሙ ዕረፍቶሙ: ወዕረፍቶሙ አኮቴቶሙ" እንዲል:: በተጨማሪም መልአክ ማለት ተላላኪ (አገልጋይ) ነውና ከፈጣሪ ወደ ሰው ልጆች ለምሕረትም: ለመዓትም ይላካሉ::
ምሕረትን ያወርዳሉ:: ልመናን ያሳርጋሉ:: ቅጡ ሲባሉም ይቀጣሉ:: ስነ ፍጥረት (አራቱ ወቅቶች) እንዳይዛቡ ይጠብቃሉ::
*ዘወትርም ስለ ሰው ልጆች ያማልዳሉ:: (ዘካ. 1:12)
*ምሥጢርን ይገልጣሉ:: (ዳን. 9:21)
*ይረዳሉ:: (ኢያ. 5:13)
*እንዳንሰናከል ይጠብቃሉ:: (መዝ. 90:11)
*ያድናሉ:: (መዝ. 33:7)
*ስግደት ይገባቸዋል:: (መሳ. 13:20, ኢያ. 5:13, ራዕ. 22:8)
*በፍርድ ቀንም ኃጥአንን ከጻድቃን ይለያሉ:: (ማቴ. 25:31)
*በአጠቃላይ ለሰው ልጆች ሕይወትና ድኅነት ሲባል ከፈጣሪያቸው የተሰጣቸውን ትዕዛዝ ሲጠብቁና ፈቃዱን ሲፈጽሙ ይኖራሉ::
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በዚህች ዕለት የሃያ አራቱን ቅዱሳን ካህናተ ሰማይን መታሰቢያ ታደርጋለች:: እኒህ ቅዱሳን መላእክት በነገድ 10 ሲሆኑ መጠሪያቸው "ሱራፌል" : መኖሪያቸውም በኢዮር ነው:: ነገር ግን ሃያ አራቱ አለቆቻቸው ተመርጠው በመሪያቸው በቅዱስ ሱራፊ አለቅነት በጽርሐ አርያም ያገለግላሉ::
በቀናች ሃይማኖት ትምሕርት ሁሉም ቅዱሳን መላእክት ለእግዚአብሔር ቅርብ ቢሆኑም: በነጠላ የቅዱስ ሚካኤልን ያህል: በነገድ ደግሞ የኪሩቤል (አራቱ እንስሳ) እና የሱራፌልን (ሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ) ያህል ቅርብ የለም::
††† ሃያ አራቱ ቅዱሳን ካህናት ሥራቸው:-
1.እንደ ሞገድ ከአንደበታቸው ምስጋና እየወጣ: ጧት ማታ ፈጣሪያቸውን ይቀድሱታል:: (ኢሳ. 6:1, ራዕይ 4:11, 5:11)
2.የሥላሴን መንበር ያለ ማቋረጥ ያጥናሉ:: (ራዕይ 5:8)
3.የሰው ልጆችን: በተለይም የቅዱሳንን ጸሎት በማዕጠንታቸው ያሳርጋሉ:: (ራዕይ 8:3)
4.የረከሱትን ይቀድሳሉ:: (ኢሳ. 6:6)
5.ዘወትርም ለሰው ልጆች ምሕረትን ሲለምኑ ይኖራሉ:: (ዘካ. 1:12)
ስለ እነዚህ ቅዱሳን ካህናት (ሱራፌል) ታላቁ ቅዱስ መጽሐፍ ብዙ ይላል:: ለምሳሌ:- ዐቢይ ነቢይ ወልዑለ ቃል ኢሳይያስ ፈጣሪው ተቀይሞት በነበረበትና ዖዝያን በሞተበት ወራት: ግሩማን ሆነው ሥላሴን "ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ" እያሉ ዙሪያውን ከበው ሲያመሰግኑ ሰምቷል::
ከእነርሱም አንዱ (ሱራፊ) መጥቶ በጉጠት እሳት ከንፈሩን ዳስሶ ከለምጹ አንጽቶታል:: (ኢሳ. 6:1) አቡቀለምሲስ የተባለ ቅዱስ ዮሐንስም በራዕዩ በግርማ: በአምሳለ አረጋዊ ተመልክቷቸዋል:: (ራዕይ 4:4)
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫን የመሰሉ ቅዱሳን ሊቃውንት ደግሞ በጣዕመ ምስጋናቸው ሲገልጿቸው:-
"ካህናተ ሰማይ ቅውማን በዐውዱ::
አክሊላቲሆሙ ያወርዱ::
ቅድመ መንበሩ እንዘ ይሰግዱ::
ይርዕዱ::
ከመ ኢይዝብጦሙ ሶበ ይበርቅ ነዱ::" ብለዋል:: (መጽሐፈ ሰዓታት)
ትርጉሙም "በፈጣሪ መንበር ዙሪያ የሚቆሙ የሰማይ ካህናት አክሊለ ክብራቸውን አውርደው በመንበሩ ፊት ይሰግዳሉ:: መብረቀ መለኮቱ በተገለጠ ጊዜም በፍርሃት ይንቀጠቀጣሉ::" ነው:: ግሩም ባሕርየ ሥላሴን ሊቋቋመው የሚችል ፍጡር የለምና::
ቅዱሳን ካህናተ ሰማይ በምስጋናቸው: በማዕጠንታቸውና በምልጃቸው ክቡራን ናቸውና ዘወትር ልናከብራቸው ይገባናል:: የረከሰ ማንነታችንን ይቀድሱ ዘንድ: በምልጃቸውም ዘንድ እንድንታሰብ: ጸሎታችንንም ያሳርጉልን ዘንድ እንለምናቸው::
††† ኅዳር 24 ቀን ዓመታዊ በዓላቸው ነው ማለት በየወሩ በ24 ወርኀዊ በዓላቸው መሆኑን ያሳያልና ዘወትር ልናስባቸው ይገባል::
በተለይ ያዘነን ልብ ደስ ያሰኛሉና እንደ ሊቃውንት እንዲህ ብለን እንጠራቸዋለን::
"ሰላም ለክሙ ካህናተ ሕጉ ወትዕዛዙ::
ለእግዚአብሔር ቃል ዘጶዴሬ ሥጋ አራዙ::
እምነቅዐ አፉክሙ ሐሴት ዘኢይነጽፍ ዉሒዙ::
ኪያየ ኅዙነ ወትኩዘ ልብ ናዝዙ::
ወበክንፍክሙ ብርሃናዊ ዐውድየ ሐውዙ::" (አርኬ ዘኅዳር 24)
††† ቅዱስ አዝቂር ካህን †††
††† ከዜና ካህናት ወደ ዜና ካህናት እንለፍ:: ቅዱስ አዝቂርን የመሰሉ ካህናት ምንም ሥጋ ለባሽ ቢሆኑም ሥልጣናቸውና ግብራቸው ሰማያዊ ነውና መላእክትን ይመስላሉ:: አንድም በስልጣናቸው ከመላእክት ይበልጣሉ::
"ካህናትየ ይቤሎሙ::
ወእምኩሉ ፈድፋደ አክበሮሙ::
ዘኢተገብረ ለመላእክት ተገብረ ለካህናት::"
ትርጉም "አገልጋዮቼ አላቸው::
ከሁሉ በላይ አከበራቸው::
ለመላእክት ያልተደረገ ለካህናት ተደረገ::" እንዳለ ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ:: (መጽሐፈ ቅዳሴ)
ቅዱስ አዝቂርም የናግራን (አሁን የመን) ክርስቲያን ሲሆን በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን በንጹሕ የክህነት አገልግሎቱ ሰውንም: ክርስቶስንም ደስ ያሰኘ አባት ነው:: አሕዛብን: አረማውያንን ሁሉ ድል ነስቶ መንጋውን ጠብቋል:: በቁጥርም አብዝቷል::
ገርፈው ቢያስሩት በቃሉ ስልጣን የብረት በሮችን ከፍቶ አሕዛብን ሲያጠምቅ ተገኝቷል:: ሊገድሉት ሲወስዱት በየመንገዱ ይሰብክ ነበር:: ገዳዮቹ በርሃ ላይ ውኃ ጥም እንዳይገድላቸውም በአንዲት ገበታ ላይ ዝናም አዝንሞ 700 ወታደሮች ከነ ፈረሶቻቸው አጥግቧል::
በመጨረሻም አይሁድ በድንጋይ ሲወግሩት ድንጋዮቹ እየተመለሱ አናት አናታቸውን ብሏቸዋል:: ያን ጊዜ በብስጭት አንገቱን ቆርጠውታል:: አብረውም ቅዱስ ኪርያቅ ወዳጁንና 48 ተከታዮቹን ሰይፈዋል::
††† አምላከ ቅዱሳን ካህናተ ሰማይ ከምስጋናቸው ሐሴትን: ከማዕጠንታቸው በጐ መዓዛን ያውርድልን:: በረከታቸውንም ያብዛልን::

††† ኅዳር 24 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1."24ቱ" ቅዱሳን ካህናተ ሰማይ (ሱራፌል)
2.ቅዱስ አዝቂር ሰማዕት
3."48" ሰማዕታት (ማሕበሩ)
4.አባ ዮሴፍ ዘሃገረ ጻን
5.ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ጥዑመ ዜና
6.ቅዱስ ኪርያቅ ሰማዕት††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት (መምሕረ ትሩፋት)
2.ቅዱስ ቶማስ ዘመርዐስ
3.አቡነ ዘዮሐንስ ጻድቅ ዘክብራን
4.ቅዱስ አጋቢጦስ (ጻድቅ ኤጲስቆጶስ)
5.ቅዱስ አብላርዮስ ታላቁ
6.ቅዱስ አባ ሙሴ ጸሊም (ኢትዮጵያዊ)
7.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
††† "በዙፋኑ ዙሪያም ሃያ አራት ዙፋኖች ነበሩ:: በዙፋኖቹም ላይ ነጭ ልብስ ለብሰው: በራሳቸውም የወርቅ አክሊል ደፍተው ሃያ አራት ሽማግሌዎች ተቀምጠው ነበር:: ከዙፋኑም መብረቅና ድምጽ: ነጐድጓድም ይወጣል:: በዙፋኑም ፊት ሰባት የእሳት መብራቶች ይበሩ ነበር:: እነርሱም ሰባቱ የእግዚአብሔር መናፍስት ናቸው::" †††
(ራዕይ ፬፥፬)
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
https://www.tgoop.com/zikirekdusn

Telegram
ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት - ዘብሔረ ጎንደር (ዲ/ዮርዳኖስ አበበ)
በዚህ ቻናል ዲ/ዮርዳኖስ የሚያስተምራቸው ወቅታዊ እና የነገረ ቅዱሳን (ዝክረ ቅዱሳን ትምህርቶችን ከእርሱ በመቀበል እናስተላልፋለን):: "ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
በዚህም ጊዜ መልአኩ ፋኑኤል ወደ እርሷ ቀርቦ አንድ ክንፉን አንጥፎ አንድ ክንፉን ጋርዶ መገባት፤ ከዚያም በክብር ዐረገ፤ ሊቀ ካህናቱና ሕዝቡም ‹‹የምግቧ ነገር ከተያዘልን በቤት እግዚአብሔር ትኑር›› ብለው ወደ ቤተ መቅደስ አስገቧት፡፡
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ሰማያዊ ኅብስትና መጠጥ እየተመገበች በቤተ መቅደስ ለ፲፪ ዓመታትም ኖራለች፡፡
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነትና ተራዳኢነት አይለየን፤ በረከቷ ይደርብን፤አሜን!
ምንጭ፡- ነገረ ማርያም

በዓታ ለማርያም
ታኅሣሥ በባተ በሦስተኛው ቀን የሚታሰበውና የሚከበረው በዓል ‹‹በዓታ ለማርያም›› በመባል ይታወቃል፡፡ ከእናቷ ከቅድስት ሐና እና ከአባቷ ቅዱስ ኢያቄም በስዕለት የተወለደችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት ዕለት የከበረ እንደመሆኑ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በድምቀት ታከብረዋለች፡፡
በዓት ቃሉ የግእዝ ሲሆን ቤት ማለት ነው፡፡ ደጋጎቹ የእግዚአብሔር ሰዎች ቅዱስ ኢያቄምና ቅድስት ሐና ልጅ አጥተው ለብዙ ዘመናት ከመኖራቸው የተነሣ በኀዘን ፈጣሪያቸውን ሲማጸኑ ቃል በመግባት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሦስት ዓመት ሲሆናት በእግዚአብሔር ቤት ትኖርና ታገለገል ዘንድ በቤተ ክርስቲያን እንድትኖር ስለሰጧት በዓሉም ስያሜውን በዚያ መሠረት አግቷል፡፡
በዚያን ጊዜም በቤተ ክርስቲያን ያገለግል የነበረው ካህኑ ዘካርያስ ስዕለታቸውን አስተውሶ ቅድስት ድንግል ማርያምን ሊቀበላት ሲቀርብ እንደ ፀሐይ የምታበራ ሕፃን ሆና አገኛት፤ በመገረምና በመጨነቅም ከወላጆቿ ጋር ምን ሊመግቧት እንደሚችሉ በመጨነቅ ላይ ሳሉ ሕዝቡ በተሰበሰበበት መካከል መልአኩ ፋኑኤል ኅብስት ሰማያዊ ጽዋዕ ይዞ ከሰማይ ወረደ፡፡ ካህኑ ዘካርያስም ለእርሱ የመጣ መና መስሎት ሲቀረብ ወደ ላይ ተመለሰበት፡፡ በዚያ የተሰበሰቡት ሰዎችም እያንዳንዳቸው ቢሞክሩ በተመሳሳይ መልኩ ተመልሶ ወደ ላይ ራቀባቸው፡፡ ‹‹ምን አልባት ለእንግዶች የመጣ ሀብት እንደሆነ›› ብለው ቅድስት ሐና እና ቅዱስ ኢያቄም እንዲቀርቡ ቢደረግም ለእነርሱም ራቀባቸው፡፡ ካህኑ ዘካርያስም ቅድስት ሐናን ‹‹እግዚአብሔር የሚያደርገውን የሚያውቅ የለምና ልጅቷን ትተሸ ወደዚህ ነይ›› አላት፤ ሆኖም ግን ቅድስት ማርያም እናቷ ትታት ስትሄድ መከተል ጀመረች፤ ምርርም ብላ አለቀሰች፡፡

Forwarded from ማኅበረ ቅዱሳን ( Mahibere Kidusan)
✍️✍️ሐመር መጽሔት በታኅሣሥ ወር እትሟ!
✍️".. ጉዳዩን ከአንዱ ወደ ሌላው መግፋት ሳይሆን ሁሉም የየድርሻውን ወስዶ፣ ሁሉም የሚጠበቅበትን ተግባር በአግባቡ አከናውኖ ሁሉም ሰላምን ተከትሏት..) #ሐመር #መጽሔት ታኀሣሥ በ፳፻፲፯ ዓ.ም መልእክት ዐምድ ✍️
༺ ༻
#የኅትመት ዘመን ፦# # ታኀሣሥ ፳፻፲፯ ዓ.ም
#አዘጋጅ ፦በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማኀበረ ቅዱሳን በልማት ተቋማት አስተዳደር በመጽሔት ዝግጅት ክፍል የሚዘጋጅ ትምህርታዊ መጽሔት
• ገጽ ብዛት፦፳፰
ዋጋ ፦፵ ብር

• ሐመር መጽሔት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ሃይማኖት ሥርዓትና ትወፊት ጠብቃ በልማት ተቋማት አስተዳደር በመጽሔት ዝግጅት ክፍል በየወሩ የምትወጣ መንፈሳዊ መጽሔት ናት፡፡
• ሐመር መጽሔት ፴፩ ኛ ዓመት ቁጥር ፲፪ # ታኀሣሥ ፳፻፲፯ ዓ.ም መልእክት ዘማኅበረ ቅዱሳን " #ይእዜኒ ለሰላም ንትልዋ መድኃኒነ ተወልደ ነዋ” (ቅዱስ.ያሬድ) "በሚል ዐቢይ መልእክት ያለንበት ዘመን ግን “የዓባይን ልጅ ውኃ ጠማው” እንደሚባለው የሰላም አምላክ ደሙን ያፈሰሰላት፣ሥጋውን የቆረሰላት፣ የሕይወት ዋጋ የከፈለላት፣ሁል ጊዜ “ጸልዩ በእንተ ሰላም፤ ስለ ሰላም ጸልዩ”እያለች የምትጽልይ፣ስለ ሀገር፣ ስለ ሠራዊት፣ ስለ ሕዝብ የምትለምን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በውስጥም በውጭም ሰላም አጥታ እየታወከች ፤ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከአባቶች በኩል “መምህር ወመገሥጽ ዘኢያደሉ ለገጽ” በመሆን ለማንም ሳይወግኑ ማንንም ሳይፈሩና ሳያፍሩ የሚመከረውን መምከር የሚገሠጸውን መገሠጽ የውስጥ መለያየትንም በመፍታት በአንድነት ለሰላም እንዲቆሙላት እንደምትጠበቅ ፣በዓለ ልደት የተጣሉት የታረቁበት፣ የተለያዩት አንድ የሆኑበት፣ ሰላም የተሰበከበት እንደሆነ ሐመር በመልእክት ዐምድ ታስነብባለች።
.#ዐውደ ስብከት ሥር” # “ናሁ ድንግል ትፀንስ ወትወልድ ወልደ” በሚል ርእስ ይህ ትንቢት በብሉይ ኪዳን ስለ እመቤታችንና ስለክርስቶስ በአንድነት
ከተነገሩ ደረቅ (ቀጥተኛ) ትንቢቶች መካከል አንዱ መሆኑን ፣የእመቤታችን ሕይወት ሰለእኛ ምን እንደሚያስተምረን ታስነብባለች።
#በትምህርተ ሃይማኖት ዐምድ ሥር “# “ቃል ሥጋ ሆነ” (ዮሐ.፩፥፲፬) ክፍል አንድ " በሚል ዐቢይ ርእስ በመልአከ ሰላም ቀሲስ ደጀኔ ሺፈራው ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ "በመጀመሪያ ቃል ነበረ "በማለት ወንጌሉን የመጻፉን ምክንያት በጥልቀት ቀርቦበታል።ቃል ሥጋ የሆነው እንደሆነ በዝርዝር ተዳሶበታል፤ድንግል ማርያም እንዴት ኢየሱስን ክርስቶስን እንደወለደችው የሊቃውንት መጽሐፍ በማጣቀስ ትምህርት ይሰጣል ።
#ዐቢይ ጉዳይ ዐምድ ሥር ደግሞ “# የቅዳሴ አገልግሎትና ምሥጢሩ" በሚል ርእስ በቤተ ክርስቲያን ዙሪያ የተሠራ ጥናታዊ ጽሑፍ (Investigative Reporting) ላይ ትኩረት ያደረገ ስለ ቅዳሴ በዝርዝር ያሳያል
• #ክርስትና በማኀበራዊ ዐምድ ሥር ደግሞ "#ኦርቶዶክሳዊ የልጆች አስተዳደግ "በሚል ርእስ አንድ ነገር መፍትሔ መነሻው በተከሰተው ችግር ላይ ያለን ግንዛቤ እና ከዚያ ችግር ለመውጣት የሚነሣ የልቡና ቁጭት እንደሆነ ያሳያል ።የልጆች ማንነት ፤የልጆች እና የወላጅ /አሳዳጊ/ ግንኙነት ምን መምሰል እንዳለበት ፤ ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብን በመገንባት አርአያ መሆን እንደሚገባ በአጠቃላይ ልጅን በመንፈሳዊ ዕውቀት፣በሥነ ምግባርና በኢትዮጵያዊ ባሕል ቀርጾ ማሳደግን የመሰለ ወላጅ ለልጁ የሚመኘው ተግባር ያለ አይመስለኝም።"በማለት ትኩረት ለልጆች መስጠት እንደሚገባ በአጽንዖት ታሰተምራለች።
• #በእናስተዋውቃችሁ ዐምድ ሥር “#የስደተኞች መጠጊያ ጁባ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን " በሚል ርእስ የአመሠራረት ሁኔታውን ፣ ያሉን መልካም ዕድሎችና ተሞክሮዎች ታስቃኛለች ።
• #በነገዋ ቤተ ክርስቲያን #ዐምድ ሥር “ መንፈሳውያን ማኅበራት ለነገዋ ቤተ ክርስቲያን" በመ/ር ዳንኤል ሰይፈ ሚካኤል ክፍል አንድ በሚል ርእስ ስለ መንፈሳዊ ማኅበራት ምንነትና አመሠራረት ጥናት ተኮር ጹሑፍ ይዛለች ።ስፍር ቁጥር የሌላቸው፣ ህልውናቸው በምንና እንዴት እንደሆነ ለመረዳት አሰቸጋሪ የሆነ፣ የሚሠሩት ሥራም ሆነ የሚፈጽሙት
ተልእኮ ተለይቶ የማይታወቅ በርካታ ማኅበራት ያሳያል ።
#በኪነ ጥበብ ዐምድ "# በፍላጻ የተወጋ ልብ ክፍል _፪ "በሚል ታስነብባለች ።ዲያቆን ጴጥሮስ በሚል የአንድ ቅን ወንድማችን ታሪክ ታስነብባለች። የሚገርም እጅግ የሚመስጥ ታሪክ ይዛለች።በተለይም የሐረማያ ግቢ ጉባኤ ተማሪዎች እና ደቡብ ኢትዮጵያ ያላችሁ ከገጸ ባሕርይው ተነስታችሁ ዲ/ን ጴጥሮስ ማን እንደሆነ ትረዳለች ።በእርግጠኝነት በዕንባ ይኽን ኪነ ጥበብ ታነቡታላችሁ ።(ገጽ_፳፫)
• #የጥያቄዎቻችሁ መልስ ዐምድ “በዐልና አከባበሩ- # ክፍል ፩ " በሚል ርእስ #“በዓልንና የበዓል አከባበርን” በተመለከተ የሚነሡ ጥያቄዎችን መሠረት በማድረግ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የትምህርትና ማሠልጠኛ መምሪያ ዋና ኃላፊ የሆኑትን መጋቤ ሐዲስ ኀይለ እግዚእ አሰፋ ጋር የተደረገ ጥያቄና መልስ ይዛለች ።
ሐመር መጽሔት #፴፩ ኛ ዓመት ቁጥር ፲፪ በማሰራጨት ፡በማንበብና በማስነበብ የድርሻችን እንወጣ !
magazine @eotcmk.org #ሐመር #መጽሔት ዝግጅት ክፍል

ከአሥርቱ መዓርጋተ መላእክት ውስጥ አንደኞቹ አርባብ ይሰኛሉ። ረበበ ማለት ጋረደ፣ ሸፈነ ማለት ሲሆን አርባብ ማለት የሚጋርዱ፣ የሚሸፍኑ የሚል ትርጉምን ይሰጣል፡፡ እነዚህም መላእክት የእግዚአብሔርን መንበር በክንፎቻቸው ስለሚሸፍኑ እና ስለሚጋርዱ ይህን ስያሜ አግኝተዋል። ዳግመኛም ዘወትር ከሚወረወረው የሰይጣን ፍላጻ (ጦር) ያመልጡ ዘንድ ለሰው ልጆች ሁሉ ሽፋን ከለላ ስለሚሆኑ ስለዚህ አገልግሎታቸው አርባብ/"የሚጋርዱ" ተብለው ይጠራሉ። የእነዚህም የመላእክት ሠራዊት አለቃቸው ሠለስቱ ደቂቅን ሰይጣን በናቡከደነጾር ልብ አድሮ ካነደደው እሳት ጋርዶ፣ ሸፍኖ ያዳናቸው ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡
ቅዱስ ገብርኤል በተለይ ልጅ ወደሚወልዱ ደጋግ ቅዱሳን አበው እና ቅዱሳት እማት ‹አብሣሬ ጽንስ›/‹ጽንስን የሚያበሥር› ሆኖ በመላክ በተደጋጋሚ በመጽሐፍ ስሙ የተጠቀሰ መልአክ ነው፡፡ ለማኑሄ እና ለሚስቱ ሶምሶን የተባለ ኃያል ሰው እንደሚወልዱ፣ ለሊቀ ካህናቱ ዘካርያስ ዮሐንስ መጥምቅን የመሰለ ደገኛ ልጅ እንደሚወልድ፣ ክብር ይግባትና እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ በማኅጸኗ እንደሚቀረጽ ያበሠረ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ነውና ‹መልአከ መበሥር› በመባል ይጠራል፡፡(መሳ 13፥4 ፣ሉቃ 1፥13 ፣ሉቃ 1፥26)
በተጨማሪም አዲስ እና ደስ የሚያሰኘውን የአምላክን መወለድ ዜና ብሥራትም በመናገሩ እና በሐዲስ ኪዳንም ስሙ ተደጋግሞ በመነሣቱ ምክንያት ‹መጋቤ ሐዲስ› በመባል ይታወቃል፡፡ ለብፁዕ ዳንኤልም ዕውቀት እና ማስተዋል የሰጠው ጥበብንም ያስተማረው መልአክ ቅዱስ ገብርኤል መሆኑን ይኸው ነቢይ በመጽሐፉ ምስክርነትን ይሰጣል፡፡(ዳን 8፥15)
የአምላክን ሰው ሆኖ ወደዚህች ምድር መምጣት ያበሰረው ቅዱስ ገብርኤል እንደሆነ ሁሉ ፤ ‹ልደት እና ዕርገት በአንድ መልአክ ተበሠሩ› በሚለው በቅዱስ አትናቴዎስ ዘእስክንድርያ ትምህርት ደግሞ የአምላክን ወደ ሰማይ ማረግም ለሰማያውያን መላእክት ‹መኳንንት ደጆቻችሁን ክፈቱ› ሲል ዳግመኛ ያበሠረው ይኸው መልአክ መሆኑ ተጠቅሶ እናገኛለን፡፡
እንኳን አደረሳችሁ!!!
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
[email protected]

የዕለቱን ወንጌል እናንብብ!
ታኅሣሥ 19 ቀን 2017 ዓ.ም
የሉቃስ ወንጌል ም 1 ቁ 11 - 21
መልካም ዕለተ ቀዳሚት ሰንበት !
#ethiopianorthodoxtewahedochurch #የዕለቱ_ወንጌል
#tewahedomediacenter#saturday

ከግርግሙ ማን ይቀራል?
የምድር ነገሥታት ሰማያዊውን ንጉሥ ለማምለክ ሊመጡ ይገባል። ወታደሮችም ሠራዊትን ሁሉ በአፉ እስትንፋስ ያጸናውን ጌታ ለማገልገል ሊቀርቡ ያስፈልጋል። ሴቶችም ኀዘናቸውን ወደ ደስታ ይለውጥ ዘንድ ከሴት የተወለደውን ያዩ ዘንድ ሊመጡ ይገባል። ሕፃናትም ከሚጠቡ እና ከሕፃናት አፍ ምስጋናን ያዘጋጅ ዘንድ ሕፃን የሆነውን ይመለከቱ ዘንድ ሊመጡ ያስፈልጋል። እረኞችም ነፍሱን ስለ በጎቹ የሚያኖር መልካሙን እረኛ ለማየት ይመጡ ዘንድ ይገባል። ባሮችም የባርነት ቀንበራቸውን ሰብሮ በነጻነት ያከብራቸው ዘንድ የባሪያውን መልክ የነሣውን ሕፃን ያዩ ዘንድ መምጣት ይገባቸዋል። ዓሣ አጥማጆቹም የቃሉን መረብ አስይዞ ሰው አጥማጅ የሚያደርጋቸውን ወንድ ልጅ ለማየት ይቀርቡ ዘንድ ይገባቸዋል። ቀረጥ ሰብሳቢዎችም ከቀራጮች መካከል ወንጌላዊ አድርጎ የሚመርጠውን ጌታ ለማየት ሊመጡ ይገባቸዋል። ዘማውያን ቅዱሳት እግሮቹን በዘማውያን እንባ እንዲታጠብ የሚሰጠውን የፍቅር አምላክ ለማየት ይቀርቡ ዘንድ ይገባል። ኃጥአን ሁሉ የዓለምን ኃጢአት የሚሸከመውን የእግዚአብሔር በግ ለማየት ሊመጡ ይገባል።
#ዛሬ ከቀኑ 10፡00 ሰዓት በአእላፋት ዝማሬ እንገናኝ!
https://www.tgoop.com/Dnabel