tgoop.com/ThinkBig1/1386
Last Update:
የጊዜ ፈተና!
ሰዎችን ጊዜ እንዲፈትናቸው ፍቀዱ!
አንድ የስነ-ልቦና አዋቂ እንዲህ ሲል ተናገረ፡- “ማንኛውም ሰው ያልሆነውን መስሎ በመኖር ወይም በአስመሳይነት ከሶስትና ከአራት ወራት በላይ የመቆየት አቅም የለውም፡፡ ሰዎች በዚህ ጊዜ ውስጥ እውነተኛ ቀለማቸውንና እናንተን የቀረቡበትን እውነተኛ የመነሻ ሃሳብ አውቀውትም ሆነ ሳያውቁት መግለጣቸው አይቀርም”፡፡
ሰዎችን ጊዜ እንዲፈትናቸውና እውነተኛ ቀለማቸውን እንዲያወጣው የመፍቀዳችን እውነታ እንደተጠበቀ ሆኖ የእኛ የቤት ስራ ግን መዘንጋት የለብንም፡፡ አንዳንድ ሰዎች እኮ “ጊዜ” የተሰኘው እውነተኛ ፈታኝ የቤት ስራውን በመስራት ሰዎችን ማንነት ቀስ በቀስ ቢገልጥላቸውም እነሱ ግን ያንን ለማየት የሚያስችል ንቃቱም የላቸወም፡፡ ጊዜ እውነቱን ሲያወጣልን ያንን ለማየት የተከፈተና የነቃ አይን ከሌለን ምንም ትርጉም የለውም፡፡
ከሰዎች ጋር ያገናኛችሁ ሁኔታ የፍቅር፣ የንግድም ሆነ ሌላ የአጋርነት ሂደት፣ ምንም ነገር ውስጥ በፍጹም ብችኮላ አትግቡ፡፡ ሰዎቹ ላይ ላዩን የተቀቡት አርቴፊሻል ቀለም እየፈዘዘ ሄዶ እውነተኛው ቀለማቸው እስከሚወጣ ድረስ ልባችሁን ጠብቁ፡፡
የጊዜን እውነተኛ ፈታኝነት ለመጠቀም የሚከተሉትን መርሆች አትዘንጉ . . .
1. የሰዎቹን ንግግርና ተግባር በሚገባ ተከታተሉ፡፡
ለሰዎች ጊዜን ስትሰጡ ንግግራቸውና ተግባራቸው በሚገባ አጢኑ፡፡ ዛሬ የተናገሩትን ነገ ያለመድገማቸውን፣ ታሪካቸው የመለዋወጡንና ተግባራቸው አንድ ወጥ የመሆኑንና ያለመሆኑን በሚገባ ብትመለከቱ ምልክቶችን ማየታችሁ አይቀርም፡፡
2. ካለማቋረጥ ውስጣችሁን አድምጡ፡፡
ከሰዎች ጋር ባላችሁ ግንኙነት ውስጣችሁ የሚከለከላችሁንና የሆነ የተዛባ ነገር እንዳለ የሚሰማችሁን ነገር በፍጹም አልፋችሁ አትሂዱ፤ በሚገባ እስቡበት፡፡
3. ወጥመድን ለዩ፡፡
በዚህ አውድ መሰረት “ወጥመድ” ማለት አንድ ነገር ትክክል እንዳልሆነ እያወቃችሁት ነገር ግን ሰውየው ከሚያሳያችሁ የሚጠቅም የሚመስል ሁኔታ የተነሳ አልፋችሁ ስትሄዱና በጓጓችሁለት ነገር ምክንያት ስህተቱን ከማየት ስትጋረዱ ነው፡፡
4. የውሳኔ ሰዎች ሁኑ፡፡
አንድ ግንኙነት ወይም መንገድ እንዳማያዛልቃችሁ አውቃችሁ ሳለ ነገር ግን ከተለያዩ ጥቅሞች ወይም ዋጋ የሚያስከፍል ሁኔታ የተነሳ ከውሳ እንዳትገቱ መጠንከር አስፈላጊ ነው፡፡ ምን ያህል ብልሆች ብንሆንም የውሳኔ ሰዎች ካልሆንን ከመሳት አናመልጥም፡፡
Dr Eyob Mamo
❀꧁@ThinkBig1 Channel꧂❀
❀꧁@ThinkBig1 Channel꧂❀
#ሀ_ሲ_ኔ
BY በትልቁ ማሰብ ᴛʜɪɴᴋ ʙɪɢ1
Share with your friend now:
tgoop.com/ThinkBig1/1386