Telegram Web
TIKVAH-MAGAZINE
ኢትዮጵያ አሁን ላይ ከ1ሚሊዮን በላይ ፍልሰተኞችን እያስተናገደች ትገኛለች። ኢትዮጵያ አሁን ላይ ከ1ሚሊዮን ሰባ አንድ ሺ በላይ ፍልሰተኞችንና ጥገኝነት ጠያቂዎችን እያስተናገደች ያለች መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛው የሥደተኞች ኮሚሽን (UNHCR) ቁጥራዊ መረጃዎች ያሳያሉ። ከዚህ ውስጥ 80 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች እና ህጻናት መሆናቸው ሲገለጽ 54 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ እድሜያቸው 0-…
#Update

° "ኤርትራውያን ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች ለእስርና እንግልት እየተዳረጉ ነው በሚል የሚሰራጨው መረጃ ትክክል አይደለም" - የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛው የሥደተኞች ኮሚሽን (UNHCR) በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ትግራይና አፋር ክልል በኩል ከኤርትራ የሚገቡ ስደተኞች ጥበቃ እና ከለላ ያስፈልጋቸዋል ሲል በሪፖርቱ ጠቅሶ እንደነበር ይታወሳል።

ቢቢሲ በሰራው ዘገባም በአዲስ አበባ የሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞች መጠነ ሰፊ እስራት እየተፈጸመባቸው ፖሊስ የሚወስደው ርምጃ እየተጠናከረ መምጣቱን ዘግቦ ነበር።

ይህን ተከትሎም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት በጉዳዩ ላይ ከደቂቃዎች በፊት መግለጫ አውጥቷል።

አገልግሎቱ በመግለጫው፥ የሚዲያዎቹን ዘገባ ተከትሎ አደረኩት ባለው ማጣራት፣ ሕጋዊ የስደተኝነት ዕውቅና ኖሯቸው ለእስርና እንግልት የተዳረጉ ስደተኞች በሀገሪቱ አለመኖራቸውን አረጋግጫለሁ ብሏል።

በዚህም በሀገሪቱ የሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች ላይ ያነጣጠረ የዘፈቀደ እስርና እንግልት እየተከናወነ ነው በሚል በሀገር ውስጥና በውጭ ሚዲያ አውታሮች የተሰሩ ዘገባዎችን ተቋሙ "መሠረተ ቢስ" ሲል አጣጥሎታል።

አክሎም፥ ስደተኞች የሀገሪቱን ሕግና ሥርዓት ጥሰው ለእስር የተዳረጉበት ሁኔታ የሚኖር ከሆነ፣ አገልግሎት መሥሪያ ቤቱ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት የሚከታተለው ይሆናል ሲል አክሎ ገልጿል፡፡

በተጨማሪም የስደተኞች ምዝገባ ቆሟል በሚል ሚዲያው የሚያሰራጨው መረጃም ከእውነት የራቀ ነው ያለው አገልግሎቱ፥ "የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት የስደተኝነት መስፈርትን ለሚያሟሉ አካላት ምንም ልዩነት ሳያደርግ የምዝገባ አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል፤ እየሰጠም ይገኛል" ብሏል፡፡

የወሳኝ ኩነት ምዝገባና የምስክር ወረቀት አገልግሎትን ጨምሮ የስደተኝነት መታወቂያ የመስጠት ተግባር ከበፊቱ በተጠናከረና በተደራጀ መልኩ እየተከናወነ መሆኑንም ተቋሙ ገልጿል።

ኢትዮጵያ ከ26 ሀገራት ከለላና ጥበቃ ፈልገው ለመጡ ከ1.1 ሚሊዮን በላይ ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች ከለላና ጥበቃ እየሰጠች ትገኛለች፡፡ ከነዚህ ውስጥ አብዛኛውን ቁጥር የሚይዙት ከጎረቤት ደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያ፣ ሱዳንና ኤርትራ የሚመጡ ስደተኞች ናቸው፡፡

#Ethiopia
#Eritrea
#Refugees

@TikvahethMagazine
#የሥራ_ማስታወቂያ

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በ81 የሥራ መደቦች በዜሮ ዓመት የሥራ ልምድ ከ800 በላይ እንዲሁም የሥራ ልምድ በሚጠይቁ 41 የሥራ መደቦች ሰራተኞችን አወዳድሮ መቅጠር እንደሚፈልግ አስታውቋል።

አመልካቾች ከታህሳስ 9 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ቅዳሜን ጨምሮ ባሉት 15(አስራ አምስት) ተከታታይ የሥራ ቀናት አስፈላጊ የትምህርትና የሥራ ልምድ ማስረጃችሁን ዋናውንና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ በመያዝ፦

📍 በአዲስ አበባ ከተማ ፒያሳ እናት ህንፃ አጠገብ በሚገኘው የተቋሙ ቢሮ፣

📍 በድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት፣

እንዲሁም በሁሉም ክልሎች የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት በአካል ቀርባችሁ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን ተቋሙ ገልጿል።

ስራ ልምድ ለሚጠይቁ የሥራ መደቦች አመልካቾች አግባብነት ያለው የሥራ ልምድ ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ሲሆን ዜሮ ዓመት ዲግሪ የትምህርት ደረጃ ለሚጠይቁ ስራ መደቦች ላይ ደግሞ የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና (Exit Exam) ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

እንዲሁም የዩኒቨርስቲ መመረቂያ ውጤት ለወንድ 2.5 እና ለሴት 2.00 መሆን አለበት። የትምህርት ደረጃ /Level/ ለሚጠይቁ ስራ መደቦች የCOC ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባችኋልም ተብሏል።

ዜሮ ዓመት ለሚጠይቁ ስራ መደቦች ላይ የሚያመለክቱ ተወዳደሪዎች ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ የተመረቁ መሆን አለባቸው የተባለ ሲሆን መስፈርቱን አሟልተው ለሚመረጡ ተወዳዳሪዎች ተቋሙ የሚሰጠውን ስልጠና ለመውሰድ ፍቃደኛ መሆንና ተቋሙ በሚመድብበት ቦታ ለመስራት ፈቃደኛ መሆን ይጠበቅባቸዋል።

የተለያዩ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር ቋንቋ ክህሎት ያላቸው እንዲሁም መሠረታዊ የኮምፒዩተር ክህሎት (Basic computer skill) ያላቸው ተወዳዳሪዎች ይበረታታሉ ተብሏል።

❗️ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ማስታወቂያውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ሊሰርዝው እንደሚችል ጠቁሟል።

ዝርዝሩን ይመልከቱ https://ics.gov.et/job/national-job-opening

#Share

@TikvahethMagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
መኖሪያዎን በፍጥነት እና በጥራት እየገነባን እንገኛለን!

እርሶም በካሬ 99,000 ብር በ15% ቅድመ ክፍያ

📌ቦሌ ደንበል (ከ71 ካሬ ጀምሮ)

📌 ገርጂ መብራት ሀይል
(ከ 169 ካሬ ጀምሮ)

📌ብስራተ ገብርዔል ከሚገኙ አፓርትመንቶች መኖሪያዎን ይምረጡ !

📌 የንግድ ሱቆች ከ 20 ካሬ ጀምሮ በገርጂ ሳይት

📞 0931333432 ወይም 0909340800

ማን እንደ ቤት🏘
ፓልም ሪል እስቴት 🌴
𝐍𝐞𝐰 𝐓𝐫𝐚𝐢𝐧𝐢𝐧𝐠 𝐏𝐫𝐨𝐠𝐫𝐚𝐦 𝐀𝐧𝐧𝐨𝐮𝐧𝐜𝐞𝐦𝐞𝐧𝐭 📣📣📣

"National Customs Procedure" Second Round Training

For More Information join our channel @EFFSAAtrainingcenter
and Registration,

📱 +251 903 182525
📞 +251 115 589045
📍 Kazanchis, Nigist Towers Hotel and Apartments, 4th floor (In front of Elilly Hotel)
TIKVAH-MAGAZINE
#Update ° "ኤርትራውያን ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች ለእስርና እንግልት እየተዳረጉ ነው በሚል የሚሰራጨው መረጃ ትክክል አይደለም" - የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛው የሥደተኞች ኮሚሽን (UNHCR) በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ትግራይና አፋር ክልል በኩል ከኤርትራ የሚገቡ ስደተኞች ጥበቃ እና ከለላ ያስፈልጋቸዋል ሲል በሪፖርቱ ጠቅሶ እንደነበር ይታወሳል። ቢቢሲ…
#Update

° "ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የውጭ አገር ሰዎች ባልተፈቀደላቸው የሥራ መስክ ተሰማርተው ይገኛሉ"

° "ማንኛውም የውጭ አገር ዜጋ የአገራችንን ህግ ተላልፎ ከተገኘ በህግ ተጠያቂ ይሆናል" -
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

ኤርትራውያን ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች ለእስርና እንግልት እየተዳረጉ ነው በሚል የተሰሩ ዘገባዎችን አስመልክቶ በትላንትናው ዕለት የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት "ሕጋዊ የስደተኝነት ዕውቅና ኖሯቸው ለእስርና እንግልት የተዳረጉ ስደተኞች በሀገሪቱ የሉም" የሚል መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በበኩሉ በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ የህግ ጥሰት የፈፀሙ የውጭ ዜጎችን የተመለከተ ማብራሪያ ሰጥቷል።

በመግለጫውም ከጎረቤት አገራት ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ዜጎች ለ9ዐ ቀናት ያለ ቪዛ ክፍያ በቀን ማህተም ገብተው እንዲቆዩ መፈቀዱን አስታውሷል።

ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የውጭ አገር ሰዎች የስራ ፈቃድና መኖሪያ ፈቃድ ሳይኖራቸው ባልተፈቀደላቸው የሥራ መስክና ህገወጥ የማዕድን፣ የገንዘብ፣ አደገኛ እፅ፣ የሰዎች ዝውውርና መሰል ህገወጥ ተግባራት ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ ብሏል።

በተለይ በርካታ ኤርትራዊያን ወደ ሀገር የሚገቡት በህገወጥ መንገድ ነው ያለው መግለጫው ከተፈቀደላቸው የጊዜ ገደብ በላይ በመቆየት በህገ-ወጥ መንገድ እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ ሲል ከሷል።

በዚህም

- ለውጭ አገር ዜጎች ባልተፈቀዱ የስራ መስኮች በመሰማራት በህገወጥ መንገድ ከትንሸ ሱቅ ችርቻሮ እስከ ያልተፈቀዱ ትላልቅ ስራዎች ተሰማርተው ሳለ፤

- በርካታ የኤርትራዊ ዜግነት ያላቸው ዘመድ ለመጠየቅ በማስመስል ከዱባይ፣ ከኤርትራ፣ ከኡጋንዳ በመመላለስ የኮንትሮባንድ እና ሌሎች ህገወጥ ተግባራት ሲያከናውኑ፤

- በተለያዩ አገራት ከሚገኙ ሌሎች ህገ-ወጥ ደላሎች ጋር በመተሳሰር ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ሲሳተፉ፤

- ለተለያዩ ሕገወጥ ተግባራት የሚያገለገሉ ሐሰተኛና የተጭበረበሩ የጉዞና የይለፍ ሰነዶች፣ ማህተሞች፣ የባንክ ቡኮች በማዘጋጀትና በመጠቀም ህገ-ወጥ ተግባራት ሲፈጽሙ ተገኝተዋል ብሏል።

መግለጫው አክሎም ማንኛውም የውጭ አገር ዜጋ የአገራችንን ህግ ተላልፎ ከተገኘ በህግ ተጠያቂ ይሆናል። ይህ ግን በአንድ ሀገር ዜጋ ብቻ ተፈጻሚ የሚደርግ አሰራር ተደርጎ በአንድ አንድ ሚድያዎች መዘገቡ ስህተት ነው ብሏል።

በተጨማሪም በስደተኝነት የተመዘገበ ማንኛውም የኤርትራዊ ዜግነት ያለው ሰው ያለ ፈቃዱ ከአገር እንዲወጣ እና ተገቢነት የሌለው ክፍያ እንዲክፍል የተደርግ ሰው የለም ብሏል።

ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

@TikvahethMagazine
ከደቡብ ሱዳን ተነስተዉ በሱርማ ወረዳ ከብት ለመዝረፍ የሞከሩ አርብቶአደሮች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

ከደቡብ ሱዳን መነሻቸዉን አድርገዉ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በሚገኘዉ ምዕራብ ኦሞ ዞን ሱሪ ወረዳ የአርብቶ አደሮችን ከብቶችን ዘርፈዉ ለመሄድ የሞከሩ 46 የደቡብ ሱዳን አርብቶ አደሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸዉን የሠላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ

የኢፌዲሪ የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ የፌዴራል ፖሊስ እና የክልልና የአካባቢዉ ፖሊስ በመቀናጀት በቁጥጥር ስር ማዋላቸዉን የክልሉ ሠላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አንድነት አሸናፊው ገልጸዋል።

የተዘረፉ 250 ከብቶች እና 21 የተለያዩ ጦር መሳሪያዎች መያዛቸዉንና የተመለሱ ከብቶችም ለባለቤቶች የተሰጡ መሆኑን ተናግረዋል።

ዘራፊዎቹ አሁን ላይ በፌደራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር እንደሚገኙ  አቶ አንድነት አሸናፊ ገልጸዋል።

መረጃው የክልሉ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ነው።

@TikvahethMagazine
ቀጣዩ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የሊቀ-መንበር ማን ይሆናል ?

አፍሪካ ህብረት የሊቀ-መንበርነት ምርጫ በወርሀ የካቲት በ አዲስ አበባ ይካሄዳል። ይህ ምርጫ በየአራት አመቱ የሚካሄድ ሲሆን፣ ተመራጩም የአፍሪካ ህብረት ህጋዊ ተወካይና ዋና የአፍሪካ ህብረት ዋና ሥራ አስፈፃሚ እንዲሁም ኮሚሽኑ የገንዘብ ነክ ጉዳይ የበላይ ሀላፊ ይሆናል።

በ2025 አ.ም በአዲስ አበባ በሚካሄደው 38ተኛው ጉባኤ አዲስ ሊቀ-መንበር ይመረጣል ተመራጩም ሊቀመንበር የአሁኑን የአፍሪካ ህብረት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሙሳ ፋኪ ማህማትን የሚተካ ይሆናል።

በዚህ የምርጫ ፉክክር የቀድሞው የኬንያ ጠቅላይ ሚንስትር ራይላ ኦዲንጋ ለዘንድሮም ምርጫ ከፍተኛ ግምት አግኝተዋል።

ራይላ የአፍሪካ ህብረት የመሰረተ- ልማት ልዩ መልክተኛ ( special Envoy) ሆነው ከ 2018 እስከ 2024 አገልግለዋል።

ራይላ ለአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበነት ቦታ ከሌሎች ተወዳዳሪዎች ከፍተኛ ፉክክር ይገጥማቸዋል ተብሎ ይታሰባል።

ከዚህም መካከለሰ የ59 ዓመቱ የጅቡቲው የውጪ ጉዳይ ሚንስትር መሀሙድ አሊ የሱፍ ሌላው ለምርጫው ከፍተኛ ግምት የተሰጣቸው ናቸው።

የ55 ዓመቱ የ ቀድሞው  የማዳጋስካር ሪቻርድ ራንድሪያ ማናድራቶ የኢኮኖሚና የፋይናንስ ሚኒስቴር ለዋና ሥራ አስፈፃሚነት በምርጫው ይወዳደራሉ።

እነዚህ ተወዳዳሪዎች ዛሬ በአፍሪካ ዋና መቀመጫ በአዲስ አበባ አፍሪካን በሚመለከት ያላቸውን እቅድ የፖሊሲ ጉዳዎች እና ቅድሚያ የሚሰጡዋቸው ሀሳቦች ላይ ክርክር ያካሂዳሉ።

የምርጫ ክርክሩ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴሌቪዥን እንዲሁም በሌሎች የኦላይን እና የቀጥታ ስርጭት አማራጮች ከምሽት 1 ሰዓት እስከ 3 ሰዓት ድረስ የሚተላለፍ ይሆናል።

#Mjadala
#TheAfricaWeWant
#AddisAbaba

@TikvahethMagazine
TIKVAH-MAGAZINE
Photo
#Update

በሊባኖስ በተከሰተው ጦርነት ምክንያት የተፈናቀሉ እንዲሁም ከዚያ በፊት ወደ አገር ለመመለስ ጠይቀው የመውጫ ቪዛ ሲጠባበቁ የነበሩ 316 ዜጎች ወደ አገራቸው መመለሳቸውን በቤይሩት-ሊባኖስ የኢትዮጵያ ቆንጽላ ጀነራል ጽ/ቤት አስታውቋል።

ከተመለሱት ዜጎች ውስጥ 167 ዜጎች  በሊባኖስ በተከሰተው ጦርነት ምክንያት የተፈናቀሉና በሊባኖስ ከአለም አቀፉ የስደተኞች  ድርጅት(IOM) ጋር በመተባበር ረቡዕ ታህሳስ 2 ቀን ወደ አገር እንዲመለሱ የተደረጉ ሲሆኑ 17 እናቶችና 22 ህፃናት ይገኙበታል ተብሏል፡፡

በተለያዩ ምክንያቶች የመኖሪያና የሥራ ፈቃድ ሳይኖራቸው በሊባኖስ ረዥም ዓመታት ሲኖሩ የነበሩ ሰነድ አልባ ዜጎቻችን ወደ አገራቸው ለመመለስ ባቀረቡት በጥያቄያቸው መሠረትት ደግሞ 149 የሚሆኑት ወደ ሀገር ቤት ተመልሰዋል።

@TikvahethMagazine
Forwarded from Concept Hub Ethiopia
#ሐሳብአለኝ

ሐሳብ አለኝ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 1 በነገው ዕለት ለአንባቢያን ይደርሳል፤ ይጠብቁን!

#አዳዲስድምጾች: የሐሳብ መሪነትና ሙያዊ ብቃት የሚንጸባረቅበት መድረክ

#EmergingVoice : A hub for thought leadership and professionalism

#TikvahFamily 🩵

@Concepthubeth
ኮንሰፕት ሀብ (Concept Hub) የሐሳብ መድረክ ነው።

ዛሬ በይፋ እንድታነቡት የምንጋብዛችሁ "ሐሳብ አለኝ" የተሰኘው ዲጂታል መጽሔት እና በብሎግ አማራጭ የቀረቡት የጹሑፍ ሥራዎች ወጣቶች እድሉ ቢኖራቸው ለሚሰሩት ሥራ ጥቂቱ ማሳያ ነው።

ወጣቶች ተቀባይ ብቻ አይደሉም። ከሌሎች የሚማሩት ብዙ ነገር እንዳለ ሁሉ ሐሳባቸውን የሚገልጹበት፤ የሚሞክሩበትና ፈጠራቸውን የሚያጎለብቱበት መድረክም ያስፈልጋል።

ይህ መድረክም ወጣቶች ሐሳባቸውን እንዲያካፍሉ፤ ለማኅበረሰባቸው ጠቃሚ የሚሉትን ሐሳብ እንዲያዋጡ፤ አዲስ እይታና የፈጠራ ክህሎታቸውን የሚያዳብሩበት ነው።

በተጨማሪም፥ ወጣቶችን እንዲጽፉ፤ ጥናትና ምርምር እንዲያደርጉ፤ የመፍትሔ ሐሳቦችን እንዲያፈላልጉና ለማኅበረሰብ ለውጥ እንዲሰሩ እድሉን መስጠትና ያስፈልጋል ይህ መድረክም ለዚህ የታሰበ ነው።

የተለያዩ ክህሎት ያላቸው ወጣቶች፤ ወጣት ባለሞያዎች፤ ወጣት መምህራንና ጸሐፊያን፤ ጋዜጠኞች፣ የጤና እና የኢኮኖሚ ባለሞያዎች፤ የሰብዓዊ መብትና የአከባቢ ጥበቃ ተሟጋቾች ሌሎች ብዙ ወጣት ሞያተኞችን አሉን ይህ መድረክ ማኅበረሰብ የሚጠቅም ሐሳባቸውን የሚያካፍሉበትም መድረክ ጭምር ነው።

ኮንሰፕት ሀብ ኢትዮጵያ (Concept Hub Ethiopia ) በቲክቫህ ኢትዮጵያ የተጀመረ ተነሳሽነት ሲሆን በዲጂታል መጽሔት ብቻም ሳይሆን በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በወጣቶች የሚደረጉ ውይይቶች፤ ዶክመንተሪዎች፤ የዲጂታል አጫጭር ሥልጠናዎች ወደፊት ይዞ ይመጣል።

🖥 www.concepthub.net

#TikvahFamily 🩵

@Concepthubeth
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ተለቀቀ

"ሐሳብ አለኝ" ቅጽ 1 መጽሔት በዚህ Telegram Mini App ላይ ያገኙታል 👉 @ConceptHubeth_bot

ይጎብኙን www.concepthub.net

#TikvahFamily 🩵

@TikvahethMagazine
መኖሪያዎን በፍጥነት እና በጥራት እየገነባን እንገኛለን!

እርሶም በካሬ 99,000 ብር በ15% ቅድመ ክፍያ

📌ቦሌ ደንበል (ከ71 ካሬ ጀምሮ)

📌 ገርጂ መብራት ሀይል
(ከ 169 ካሬ ጀምሮ)

📌ብስራተ ገብርዔል ከሚገኙ አፓርትመንቶች መኖሪያዎን ይምረጡ !

📌 የንግድ ሱቆች ከ 20 ካሬ ጀምሮ በገርጂ ሳይት

📞 0931333432 ወይም 0909340800

ማን እንደ ቤት🏘
ፓልም ሪል እስቴት 🌴
𝐍𝐞𝐰 𝐓𝐫𝐚𝐢𝐧𝐢𝐧𝐠 𝐏𝐫𝐨𝐠𝐫𝐚𝐦 𝐀𝐧𝐧𝐨𝐮𝐧𝐜𝐞𝐦𝐞𝐧𝐭 📣📣📣

"National Customs Procedure" Second Round Training

For More Information join our channel @EFFSAAtrainingcenter
and Registration,

📱 +251 903 182525
📞 +251 115 589045
📍 Kazanchis, Nigist Towers Hotel and Apartments, 4th floor (In front of Elilly Hotel)
ኢትዮጵያዊን ሥራ ፈጣሪዎች በየግሬት ሪፍት ቫሊ ኢኖቬሽን ሰሚት ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ ቀረበ።

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ የፈጠራ ሥራዎችን ለማጎልበት የግሬት ሪፍት ቫሊ ኢኖቬሽን ሰሚት ማዘጋጀቱን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መግለጫ አስታውቋል።

ከጥር 23- 24 በስካይላይት ሆቴል በሚዘጋጀው በዚህ ዝግጅት በግብርና፣ በጤና እና በትምሕርት ዘርፍ የማኅበረሰብ ልማትን ለሚያፋጥኑ የላቁ የፈጠራ ውጤቶች  $750,000 የአሜሪካ ዶላር በሽልማት መልክ ይበረከታል ተብሏል።

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ ሊቀ-መንበርሉሊት እጅጉ "ይህ የፈጠራ ውድድር አሸናፊዎች በተዘጋጀላቸው በመቶ ሺዎች የአሜሪካ ዶላር የሚገመት ሽልማት ለሀገር ምሰሶ በሆኑ ዘርፎች ያሉ ተግዳሮቶችን ለመፍታት መላ እንዲፈጥሩና ችግር እንዲፈቱ ያስችላቸዋል" ብለዋል።

ሉሊት እጅጉ ግሬት ሪፍት ቫሊ ኢኖቬሽን ሰሚት/ጉባዔ ለፈጠራ ባለሙያዎች አስቸኳይ ጥሪ ያቀርባል ያሉ ሲሆን "ተስፋ ሰጪ የፈጠራ ሐሳብ ባለቤቶች ለውድድር እንድታመለክቱ፤ አጋሮች ድጋፍ እንድታደርጉ ጥሪ እናስተላልፋልን" ብለዋል።

አመልካቾቶ የተጀመሩ ምርቶች ወይም አገልግሎቶች፣ ወይም በትንሹ አዋጭነታቸው የታየ ደረጃ ላይ ቢሆን ይበረታታሉ ተብሏል። በተጨማሪም የሽያጭ ዝርዝር ስትራቴጂክ እቅድ ሊኖራቸው ይገባል ተብሏል።

ለማመልከት ስለ ቢዝነሱ 5-10 ስላይድ፤ ከ 10 ገጽ ያልበለጠ ዝርዝር የቢዝነስ እቅድ፣ የፋይናንሺያል ሞዴል እና ትክክለኛ የንግድ ፍቃድ ማዘጋጀት አለባቸው ተብሏል።

በግብር፣ በጤና እና በትምሕርት ዘርፎች ልዩ ፈጠራ ያላችሁ ኢንተርፕርነሮችና ሥራ ፈጣሪዎች፣ የስታርትአፕ አንቀሳቃሾች ይህን ዌብሊን https://www.grvsummit.com በመጠቀም የመወዳደሪያ ሐሳባችሁን እስከ እሁድ, ታኅሣሥ 9 2017 ዓ.ም. ድረስ እንድታስገቡ ይሁን።

በተጨማሪም ጉባዔው የፓነል ውይይቶች፣ ወርክሾፖች፣ ኤግዚቢሽን እና ከኢንዱስትሪ ባለድርሻዎች ጋር የትውውቅ መድረክ የተዘጋጁበት በመኾኑ ተሳታፊዎች ልምድ እንደሚቀስሙበትና ተጠቃሚ እንደሚኾኑበት ይሆናል ተብሏል።

ለበለጠ መረጃ [email protected] መልዕክት መላክ ይቻላል ተብሏል።

@TikvahethMagazine
2025/01/08 07:45:26
Back to Top
HTML Embed Code: