tgoop.com/YEMEREJAWECHSIBESEBCHANNEL/1777
Create:
Last Update:
Last Update:
"…በገዳሙ የሚኖር ማንኛውም መነኩሴ ከሊቅ እስከ ደቂቅ 150 መዝሙረ ዳዊት በቀን እንዲደግም። ከደገመ በኋላም መጸሐፉን መሬት ላይ ደፍቶ ያስቀምጥ። መቁጠሪያውንና መቋሚያውን ጸሎት ከጨረሰ በኋላ መሬት ላይ ይጣል። ምግብን በተመለከተ በቋርፍ ቤትም ሆነ ብእህል ቤቶችና በአትክልት ቦታዎች ጨው፣ በርበሬ፣ ያለበት ምግብ ከሰኞ ጀምሮ ለ3 ቀን እንዳይመገብ። በማንኛውም ቦታ የገዳማችን መነኮሳት ባእት እሳት እንዳይነድ። ከቤተ እግዚእብሔር የሚሰጠውን ብቻ እንዲመገብ። የተመገበበትን ፋጋ ከጨረሰ በኋላ ባፉደፍቶ እንዲያሳድር። ከምሽቱ 12 ሰዓት ውጭ የመቁንን ደውል እንዳይደውል። ውኃ ከአንድ ብርጭቆ በላይ እንዳይጠጣ። ሻይ እንዳይፈላ። ጭልቃ እንዳይጨለቅ ወስኗል።
"…ይህ ትእዛዝ በሁሉም የቋርፍ ቤት፣ የአትክልት ቦታ፣ የሞፈር ቤቶች፣ በየዋሻው እና በየፍርኩታው ላሉ ባህታውያን አባቶች መልክቱ ይተላለፍ። በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንና በሀገራችን የመጣው አደጋ ቀላል አይደለም በሚል ተወስኗል። ይህ ውሳኔ ከትናንት ሰኞ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ/ም ጀምሮ ተግባራዊ ተደርጓል።
"…በአባቶች በኩል ነገሩ በጥብቅ ተይዟል። ነገሩን ያከበዱት ይመስለኛል።
BY ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ለመናፍቃንና ለአህዛብ መልስ አላት!
Share with your friend now:
tgoop.com/YEMEREJAWECHSIBESEBCHANNEL/1777