ይሔው ማህሌተ ፅጌ
“ ተቀኙም፣አዚሙም፣ውዳሴና ምስጋና ለእግዚአብሔር እናት አልቅሱም፣አንቡም፣ መጋቤ አለማትን ይዛ መርቧን አስቡ፣አለምን በመዳፉ ይዞ ስደት ላደከመው ቅዱስ ጌታ፣አሳዳጆችን የሚመልስ ጌታ እርሱን አሳዳጆች ሲያስጨንቁት።ይህንን እያየች ፍፁም ሀዘን ፍፁም መከራ ላየች ቅድስት ድንግል ስደቷን አስቡ።

በtik tok ላይ ለጠየቃችሁኝ እና ሰሞኑን በface book እና በtik tok ለምትበጫበጩ አዛኝ ቅቤ አንጓች ሁሉ ልብ በሉ።
ይህ ልጅ(ዘማሪ ዲ/ን ሰለሞን አቡበከር) ከእስልምና ወደ ኦርቶዶክስ እምነት ሲገባ ቤክ ደስ ብሏት ተቀበለችው።ያከበረችውን ስም የሰጠችውን እውቅና ያለበሰችውን ይህችን ቤ/ክ ከመሰሎቹ ከነበጋሻው፣ትዝታው፣ዘርፌ፣ አሸናፊ ገብረ ማርያም፣ሀዋዝ እና ሌሎችም “ይህች አሮጊቷ ሳራ መታደስ አለባት!” ብለው በቁም ዘበቱባት ቅዱሳንን እንበልጣለን ብለው ከቅዱሳን ጋር እኩል ተገዳድረው የስድብ አፍቸውን ከፈቱ።ሌሎቹ በግልፅ ፕሮቴስታንት መሆንን ሲመርጡ እርሱ ተሃድሶ ላይ ተንጠልጥሎ ቀረ።አሁን ደግሞ ድጋሜ ኦርቶዶክስ መሆንን መረጠ።መብቱ ነው።
በዚህ ልጅ መመለስ ከሰው ይልቅ መልዓክት በሰማይ ደስ ይላቸዋል።እኛም እንደ አማኝ መመለሱ ፍስሐን እናደርግ ዘንድ ግድ ይለናል።የጠፍ ሞቶ የነበረ ወንድማችን ነውና ዳግም ህይወት መዝራቱን አንጠላም።
እውነታው ግን እንዲህ ነው። ሰሞኑን እንደ ወጀብ እያመላለሳችሁ በface book እና በtik tok ሰላም የምትነሱን ቅቤ አንጓች የሆናችሁ ሁሉ። ይህ ልጅ ሀይማኖት እንደ ቲሸርቱ የቀያየረ ነው። ያመነዘረው የዘሞተው እኮ እግዚአብሔር አብዝቶ በሚፀየፈው (ቀላጭ)በሚያስብል ሃይማኖት ነው። ሃይማኖት ማለት በተስፍ መፅናት እንጅ ባልተመቸ እና በከፍ ግዜ ጎረበጠኝ ሰለቸኝ እያሉ እየቀመሱ የሚያረጋግጡት በእጅ የሚያማስሉት ወጥ አይደለም።
ይህ ልጅ በግልፅ ፀያፍ የሆነ ንግግርን ቤ/ክ ላይ ተናግሯል፣ቅዱሳንን እንደ ቆሎ ጓደኛው በስድብ አጥረግርጓቸዋል።ለብዙ አማኞች መሰናከል ምክንያት ሆኗል።እንዲህ ሆኖ ሳለ “በቃ ተውት ተፀፅቷል አትግፉት”ማለት ምን ማለት ነው?ማነው የገፍው?መፀፀትስ እንዴት ነው?
በሶሻል ሚድያ ተፀፀቻለው ማለት ንስሐ አይደለም።በካህናትና በጳጳሳት እግር ስር መስቀል እየተሳለሙ post በማድረግ ምንም ማረጋገጫ አይደለም።ማንም አመነ አላመነ ካደ አልካደ ካህናትንና ጳጳሳትን ባርኩኝ ብሎ የሚጠጋ ግለሰብ እስቲ መስቀልህ እየተባለ አይጠየቅም።መሳለም የፈለገ ቀርቦ መሳለም ይችላል።እነርሱም ማሳለም አባታዊም ሀይማኖታዊም ግዴታቸው ነው።ቤ/ክ በጭንቅ እና በመከራ ላይ ባለችበት ወሳኝ ግዜ ላይ በቤ/ክ ሙድ መያዝ ደስ አይልም።ፍፁም ድጋሜ የከፍው ሐጢያት ነውና።
ከተፀፀተ ከልብ ከተሰበረ በቀደመው ግዜ እንደሱ ክደው ብፁዓን አባቶች ማረጋገጫ ሰጠዋቸው።ቤ/ክ ድምጿን ሰጣቸው ዛሬ በአውደ ምህረት በአገልግሎት የምናያቸው ብዙ አሉ።እንደ እነሱ የቤተ ክርስትያኒቱን መዋቅር ጠብቆ መሔድ ነው።ከዚያ ባለፈ ግን በsocial Media ላይ ያዙኝ ልቀቁኝ ማለት ምንም ፍይዳ የለውም።በከንቱ መጮህና ምዕመናንን አወዛግቦ አጉል ርህራሔንና ድጋፍ ስጡኝ ከሚል ማስተዛዘኛነት ልቆ አይታይም።
ወንድሜ ከተፀፀትክ ቀኖና የምትሰጥህ ቤ/ክ እንጂ በface book እና በtik tok የሚያጅብህ መንጋ አይደለም። እባክህ ብዙ ማውራት አይደለም ጥቂት መስራት ነው።የምስራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ብቻ አይደሉም ይቅርታህን የሚቀበሉት።እርሳቸው የቤ/ክ አንድ አካል እንጅ ምልዓተ ቤ/ክንን ወክለው መናገር እንደማይችሉ አንተም ታውቀዋለህ።በበር እንደወጣህ በጓሮ ለመግባት አትድከም።ስታደርገው ያላፈርክበትን ስትመለስ አትፈርበት ስታሰናክል ያልፀፀተህ ስትመለስ ደብቁኝ አትዩኝ አትበል።
መቼም እንዴት መመለስ እንዳለብህ ከጭምቷ ዘማሪት ምርትነሽ መማር ትችላለህ። የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ምልዓተ ጉባዔው አይቷት መርምሯት ለረጅም ግዜ አገልግሎት አቁማ እራሷን በንስሐና በቀኖና አፅንታ መፀፀቷን መመለሷን ቤክ ተናግራላት ተመልሳ አገልግሎቷን እያየን ነው።እናም ወንድማችን አንተም ይህንኑ አድርግ የሚሻልህ ሳይረፍድ መመለስ ነው ። እንዲያ እስካልሆነ ድረስ ግን አሁንም ተሃድሶ አሁንም መናፍቅ ነህ ብለን ከማመን አንድንም።በግልፅ ፊለፊት ውጣ በአደባባይ በቤተ ክርስቲያን ድምፅ በአባቶች ምልዓል ተገስፀህ ቀኖናህን ወስደህ ማገልገል መብትህ ነው።የface book እና የtik tok ደንገጡርና ጋሻ አጃግሬ አይጠቅምህም።ይቅርብህ በሩን እንጅ መስኮቱን አትምረጥ።እውነታው ይህ ነው።
የface book እና የtik tok ንስሐ እና ቀኖና ሰጭዎች ብዙ አትጩኹ።ሰለሞን ቢሔድ ብዙ ሰለሞን ታስነሳለች።እርሱ በመሔዱ እርሱ ተጎዳ እንጅ ነገም ቤክ ትኖራለች።ያለ ህፀፅ ታበራለች ታደምቃለች ትደምቃለች።ከዚያ ባለፈ ግን ቤ/ክ የአሸሸ ገዳሜ እና የጩኸት ሜዳ አይደለችም።ጩኸቱን በልክ አድርጉት የስርዓተ ቤተ ክርስትያን ጉዳይ እንጅ የቲፎዞ ጉዳይ አይደለም ነገሩ።
★https://www.facebook.com/groups/3378965202135639/?ref=share
★https://www.instagram.com/p/CVLFw1-sFi0/?utm_medium=copy_link

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
❤1
"የንስሐ መንገዶች"
የራስ ኃጢአትን ማመን፣ መጥላትንና ማዉገዝ ነው፡፡
“እንድትጸድቅ መጀመሪያ ኃጢአትህን ተናገር” እንዳለው ኢሳ 43፥26
#ክቡር_ዳዊትም
“በደሌን አልሸፈንኩም፤ ለእግዚአብሔር መተላለፌን እነግራለሁ አልሁ፤ አንተም የልቤን ኃጢአት ተውህልኝ” ብሎ እንደ ተናገረው ነው
መዝ 31፡5
ስለዚህ አንተም ስለ ሠራኸው ኃጢአት ራስህን ውቀሰው፤ በዚህ እግዚአብሔር ይቅር እንዲልህ ታደርገዋለህና፡፡
ይህ ብቻ ሳይሆን ስለ ኃጢአቱ ራሱን የሚወቅስና ኃጢአቱን የሚኰንን ሰው በተመሳሳይ ኃጢአት በቀላሉ አይወድቅምና፡፡
ስለዚህ በጌታ የፍርድ ዙፋን ፊት የሚወቅስህ እንዳይኖር ዛሬ እውነተኛ ወቃሽ የኾነውን ሕሊናህን አንቅተህ በራስህ ላይ ወቃሽና ከሳሽ አድርገህ ሹመው፡፡ ይህ አንዱና ደገኛው የንስሐ መንገድ ነው፡፡
የወገኖቻችንን በደል ይቅር ማለትና በበደሉህ ላይ ቅሬታና ቂም አለመያዝ ነው፡፡
#እንዲህ_ስናደርግ
“ለሰዎች ኃጢአታቸውን ይቅር ብትሉ፥ የሰማዩ አባታችሁ እናንተንም ደግሞ ይቅር ይላችኋል” እንዲል እኛ በጌታችን ላይ ያደረግነውን በደል ይቅር እንባላለንና
ማቴ 6፥14
#ከልብ_የመነጨ_ጸሎት
ጨካኙ ዳኛ እንዲፈርድላት ያደረገችው ያቺ መበለት እንዴት እንዲፈረድላት እንዳደረገችው አታያትምን?
ሉቃ 18፥3
አንተ ግን ርኅሩኅና መሐሪ የኾነ ጌታ ነው ያለህ፤ እርሷ በጠላቶቿ ላይ እንዲፈርድላት ነው የጠየቀችው፤ አንተ ግን የምትለምነው ስለ ራስህ ድኅነት ነው፡፡
#ምጽዋት
ይህም እጅግ በጣም ታላቅ የኾነ ኃጢአትን የማስተሥረይ ኃይል አለውና፡፡
ናቡከደነፆር ኃጢአትን ንቅስ ጥቅስ አድርጎ ወደ ክሕደት ዓይነት ሁሉ በገባ ጊዜ እንዲህ ብሎታልና
“ንጉሥ ሆይ! ምክሬ ደስ ያሰኝህ፤ ኃጢአትህንም በጽድቅ በደልህን ለድሆች በመመጽወት አስቀር”
ዳን 4፥27
ይህን ቸርነትና ሰውን መውደድስ ምን ይተካከለዋል?
ስፍር ቁጥር የሌለውን ኃጢአት ከሠራ በኋላ፣ ከዚያ ሁሉ በደል በኋላ እንደ እርሱ ለሆኑ ሰዎች ርኅራኄን ቢያደርግ ከተገዳደረውና ከተጣላው አምላክ ጋር መታረቅ እንደሚችል ቃል ተገብቶለታልና፡፡
ትሕትናና ራስን ማዋረድ ኃጢአትን ያደክማል
ይህንንም ቀራጩ ያረጋግጥልናል፤ ዓይኖቹን ወደ ሰማይ ማንሣት እንኳን እስኪፈራ ደርሶ በታላቅ ትሕትና ራሱን ባዋረደ ጊዜ
“ጻድቅ ኾኖ ኼደ” ተብሏልና ሉቃ 18፥13
ስለዚህ ምንም ምግባር ቢኖርህም እንኳን በደልህን ከመናገር በቀር በጎ ምግባርህን አታስበው፤ ያን ጊዜ እግዚአብሔር የበደል ሸክምህን ያራግፍልሃል፡፡
ስለዚህ እነዚህን መንገዶች ተመላለስባቸው እንጂ ሰነፍ አትሁን፡፡
በአጠቃለይ የተለያዩ ቢሆኑም ቅሉ ሁሉም የሚያደርሱት ግን ርስት መንግሥተ ሰማያት ነው
እነዚህን ለመፈጸም አምላከ ቅዱሳን ይርዳን አሜን

ጌታዬ ሆይ ከራሴ አድነኝ!!
አምላኬ ሆይ በቃልህ እኔ እውነትም፣ ሕይወትም መንገድም ነኝ ብለህ ተናግረሃል ፤ ይህንንም በሙሉ ልቤ አምናለሁ። ይህን የማምነውን እውነታ ግን መኖር አቅቶኛል። እንግዲህ አምናለሁ ማለቴ ውሸታም ነኝ፤ በምልዓት ባለማመኔ በውስጤ ባንተ ሁለት ማንነቶች ሁሌም ይፋለማሉ። መንፈሴ አንተ በእውነት የተጠሙትን የምታረካ የሕይወት ውኃ እንደሆንክ ታውቃለች፤ ተጠምታ አርክተኻታል፤ ግን ጥሟን ባረካኸው ልክ ያው በይበልጥ አንተን ትጠማለች። የተጠሙትን እያረካህ በይበልጥ ይጠሙህ ዘንድ ትጋብዛለህና። የድሮው ማንነቴ ግን በዚህ አንተን ያለማቋረጥ የመፈለግ ሂደት ውስጥ ሊተባበር አልቻለም። ብርሃንን በጥብቅ ቢሻም፣ ያየውን ብርሃን ለመከተል ግን ትጋት ያጥረዋል። አንተን መከተል ባለብኝ መጠን አልተከተልኩህምና ፣ በውስጤ የሚካሄደው አምባጓሮ አድክሞኛል። ስለዚህም አምላኬ አድነኝ እላለሁ፣ አኗኗሬን ካመረሩብኝ ካንተ ከራቁ ሰዎችም፣ በየሄድኩበት ወጥመድን ከሚሸምቅ ሰይጣንም ሳይሆን፣ ከሁሉም በፊት ጌታዬ ከራሴ አድነኝ። አንተ ያለመሰልቸት ከበሩ ቆመህ ስትጣራ እየሰማ፣ ግን የልቡን በር ከፍቶ ማስተናገድ ከተሳነው ካረጀው ክፉ ማንነቴ፣ አምላኬ ሆይ አድነኝ!!
O Lord, save me from myself!!
Lord you have said I am The Truth, The Way and The Life, and I believe that with my whole heart. Sadly, I can't live fully to what I believe. Then I am lying, I don't believe fully, as there are two wills in me fighting over you. My spirit has grasped how You are indeed the Living water Who would quench my thrist once and for all. I thirst and I am satisfied, the more You quench my thirst, the more I thrist after You. You satisfy and endow one with the need for more all at once. But my person, who I am is not cooperating in this salvific process. It longs after the Light but is too lazy to run after it. I have made myself weary for not following you to the measure I should. Thus I say save me Lord, save me, not from wicked men who have made my existence tedious, not from the devil who sets traps on my every step, But first from myself. From the old man within me who has made it impossible for me to accept you in my heart's chamber by replying for your uninterrupted calling. O lord, save me!!
★ አያት ቅድስት ኪዳነ ምህረት እና ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ ፍ/ሎ/ሰ/ት/ቤት።

ለመድኃኔዓለም
----------------------
★ ሁሉን የያዘውን ያዙት፤ሁሉን የሚገዛውን አሰሩት፣ህያው የአምላክን ልጅ አሰሩት፤በቁጣ ጎተቱት በፍቅር ተከተላቸው፤በሚሸልተው ፊት እንደ ማይናገር እንደ የዋህ በግ ከኋላቸው እየተከተለ ወሰዱት።
★ ሊቃነ መላዕክት በመፍራትና በመንቀጥቀጥ ከፊቱ የሚቆሙለትን በአደባባይ አቆሙት፤ኃጢያትን ይቅር የሚለውን ኃጥእ አሉት፤በመኳንት በሚፈርደውን በእርሱ ፈረዱበት።
★ ለሱራፌል ዘውድ የሚያቀዳጃቸውን የእሼክ ዘውድ አቀዳጁት፤ለኪሩቤል የግርማ ልብስ የሚያለብሳቸውን ለመዘበት ቀይ ግምጃ አለበሱት።
★ ኪሩቤል በእሳት ክንፍ ተሸፍነው ከፊቱ የሚሰውሩለትን እርሱን ክፉ ባሪያ እጁን አፅንቶ ፊቱን ፀፍው።
★ የመላእክት ሰራዊት በፍፁም መደንገጥ ለሚሰግዱለት እየዘበቱበት በፊቱ ተንበረከኩ።
★ ይህን ያህል ትህትና እንደምን ያለ ትህትና ነው?ይህን ያህል ትዕግስት እንደምን ያለ ትዕግስት ነው?ይህን ያህል ዝምታ እንደምን ያለ ዝምታ ነው?
★ ይህን ያህል ቸርነት እንደምን ያለ ቸርነት ነው? ይህን ያህል ሰውን ማፍቀር እንደምን ያለ ፍቅር ነው?
★ ፍቅር የአምላክን ልጅ ከዙፍኑ ሳባው እስከ ሞትም አደረሰው፤ በደል የሌለበትን እንደበደለኛ ሰቀሉት፤ሕይወትን የሰራውን ከበደለኞች ጋር ቆጠሩት።
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ (ቅዳሴ) ከቁጥር 46-53

ተማሪዎች ፈተና ከመፈተናቸው በፊት ይህን ይጸልዩ
ቅዱስ ቄርሎስ ሣድሳዊ ዘእስክንድርያ የደረሱት
#ጸሎት
‹‹ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ
‹‹በችግርህ ቀን ጥራኝ ፤ አድንሃለሁ አንተም ታከብረኛለህ›› ብለህ የአንተን መጠጊያነት መፈለግን ስላስተማርከኝ አመሰግንሃለሁ!
አሁንም ጌታ ሆይ! በዚህ የፈተና ሰዓት ጥበብና ማስተዋልን ትሰጠኝ ዘንድ እማጸንሃለሁ፡፡
ይህን ፈተና በሰላም አልፍ ዘንድ ጸጋን (ሞገስን) ስጠኝ፡፡ ፈተናውን በምሠራ ጊዜ ጥልቅ የሆነ ሰላምህንና በረከትህን ስጠኝ፡፡
ጌታዬ ኢየሱስ ውጤት በሚሰጡኝ ጊዜ በመምህራኖቼ ዓይን መወደድን ትሰጠኝና ልባቸውን ታለሰልስልኝ ዘንድ እለምንሃለሁ፡፡ የከበርከው ጌታእኔ ኃጢአተኛ ነኝ ፤ ዓመቱን ሙሉ አንተን ደስ አላሰኘሁህም ፤ ውስጤንም ጭምር ፤ ነገር ግን ከልቤ ደንዳናነትና ከኃጢአቶቼ የተነሣ ሳይሆን ከምሕረትህ እና ከርኅርኄህ የተነሣ እንደትረዳኝ እለምንሃለሁ፡
ጌታ ሆይ ‹‹ለምኑ ይሰጣችኋል፣ እሹ ታገኛላችሁ፤ አንኳኩ ይከፈትላችኋል›› ብለሃል፡፡ እናም እነሆኝ እየለመንኩ ነው፤ የምሕረትህንም ደጅ እያንኳኳሁ ነው፡፡ ‹‹ወደ እኔ የሚመጣውን ከቶ ከእኔ አላወጣውም›› ብለሃልና ጸሎቴን አትናቅ፡፡በቅድስት ድንግልና በመላእክትህ ሁሉ አማላጅነት መልስልኝ!! አሜን!"
ለዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪዎች እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን!
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

ተፈጸመ ናሁ ማኅሌተ ጽጌ ሥሙር ተፈጸመ ናሁ አስምኪ ቦቱ አስምኪ ቦቱ ንግሥተ ሰማያት እነሆ ልጄን ከገብፅ ጠራሁት ተብሎ በቅዱስ መጽሐፍ እንደተነገረ የእመቤታችን የስደት ዘመን በተፈፀመ ጊዜ ልጇን ክርስቶስን ይዛ ከግብፅ ተመለሰች።
እለ ትነብሩ ተንስኡ ወእለ ታረምሙ አውስኡ ማርያምሃ በቃለ ስብሐት ጸውኡ
የተቀመጣችሁ ተነሱ ዝም ያላችሁ ተናገሩ ድንግል ማርያምን በምስጋና ቃል ጥሩ አመስግኑ
#ማኀሌተ_ጽጌ

"እስከ ማዕዜኑ ትነብሪ ከመ ፈላሲ ወነግድ ውስተ ርስትኪ ግብኢ እምብሔረ ባዕድ ብሥራትኪ ድንግል ክብርተ ዘመድ
እስመ ጠፍአ ናሁ ቀታሌ ሕፃናት ብድብድ በቤተልሔም አልቦ አመፃ ወሐይድ፡፡"
"በምሥራችሽ ዘመዶችሽን ደስ የምታሰኚ እና የምታኮሪ እመቤቴ ድንግል ማርያም ሆይ እንደ እንግዳና እንደ ስደተኛ ሆነሽ እስከመቼ ትኖሪያለሽ። ከባዕድ ሀገር ወደ አባትሽ ሀገር ወደ ርስትሽ ተመለሽ እንጂ፤ ሕፃናትን የሚፈጅ የሚገድል ተስፋ በሽታ የሆነው ሄሮድስ እነሆ ዛሬ ጠፍቷልና ዛሬ በቤተልሔምም ልጅ መቀማት መበደል ቀርቷልና፤ ወደ ሀገርሽ ተመለሽ።"
(ሰቆቃወ ድንግል)
ደብረ ቁስቋም በደቡብ ግብፅ የሚገኝ ተራራ ነው፡፡ ደብረ ቁስቋም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲሁም ቅዱስ ዮሴፍንና ቅድስት ሰሎሜን ይዛ ከስደት ሲመለሱ ያረፉበት ቦታ ነው፡፡
ይህም በቅዱስ ወንጌል እንደተጻፈ ሄሮድስ ክርስቶስን ለመግደል በፈለገ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ለአረጋዊው ዮሴፍ በሕልሙ ‹‹ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ›› ባለው መሠረት የተፈጸመ ነው፡፡ (ማቴ. ፪፥፲፫-፲፭)
የክርስቶስ ስደቱ ቀድሞ በነቢዩ ኢሳይያስ ‹‹እነሆ እግዚአብሔር በፈጣን ደመና ተቀምጦ ወደ ግብፅ ይመጣል፡፡ የግብፅም ጣዖታት በፊቱ ይዋረዳሉ›› ተብሎ በተነገረው መሠረት የተፈጸመ ነው፡፡ ነቢዩ ፈጣን ደመና ያለው ጌታችን በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ጀርባ ላይ ሆኖ ወደ ግብፅ መውረዱን ለመግለጽ ነው፡፡ (ኢሳ. ፲፱፥፩) በስደቱም ጣዖታተ ግብፅ እየተሰባበሩ ሲወድቁ፤ በእነርሱም አድረው ሰውን ሲያስቱ የነበሩ አጋንንትም ሲሸሹ ታይተዋል፡፡
ደግሞም ጌታችን ዳግማዊ አዳም ነውና በምክረ ከይሲ (ዲያብሎስ) ምክንያት ተሰዶ የነበረው ቀዳማዊ አዳምን ለመካስ ተሰደደ በዚህም አጋንንትን ከሰው ልቦና አውጥቶ አሳደደ፡፡
እመቤታችንም ልጇን ይዛ ከስደት ስትመለስ ያረፈችበትን ተራራ ደብረ ቁስቋምን ባረከችው ቀደሰችውም ይህ ተራራ የተቀደሰ ተራራ ስለመሆኑ የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ታኦፊሎጎስ በድርሳነ ማርያም እንዲህ አለ፤ ‹‹ይህም ከሀገሮቹ ሁሉ ተራሮች የሚበልጥ (የተለየ) ከፍ ያለ ተራራ ነው፡፡ በውስጡ ቅዱስ አግዚአብሔር ያድራል፡፡ ይህንን ተራራ የእግዚአብሔር ልጅ ወዶታል አክብሮታልምና ከዓለም ሀገሮች ሁሉ ከተቀደሰች እናቱ ጋር አድሮባታልና፡፡ ከመላእክት ቤት ያድር ዘንድ አልወደደም ቢታንያንም አልመረጠም፡፡ ከተራራው ላይ ባለች ገዳም ቤት ውስጥ አደረ እንጂ ነቢዩ ዳዊት የጽዮንን ተራራ ወደደ በአርያምም መቅደሱን ሠራ እንዳለ፡፡››
‹‹አንተ ተራራ ሆይ የእግዚአብሔር ማደሪያ በሆንህ ጊዜ በኪሩቤልና በሱራፌል መካከል ፍጹም ደስታ ተደረገ፡፡ የመላእክት ሠራዊት ቅዱስ የሆነ ፈጣሪያቸውንና ጌታቸውን ይታዘዙ (ያገለግሉ) ነበር፡፡
አንተ ተራራ ሆይ ያደረብህ ጌታችን ስለሆነ ከተራሮች ሁሉ ከደብረ ሲናም ይልቅ ከፍ ከፍ አልህ ጌታችን በደብረ ሲና ባረፈ ጊዜ ፍጹም ደስታ ታላቅ ብርሃንም በሆነ ጊዜ መቅረብና መመልከት ከሙሴ በቀር የቻለ የለም፡፡ እርሱም ቢሆን ፊቱን ማየት አልቻለም፡፡ ሥጋ ለባሽ ሁሉ እርሱን ዐይቶ በሕይወት መኖር የሚቻለው የለምና፡፡ እኛ ግን አየን፤ ከዚህ ማደሩንም ተረዳን፤ ዳግመኛም ንጽሕት በሆነች በማርያም ዘንድ አየነው፡፡ ቅድስት ከሆነች ከእመቤታችን ማርያም ዘንድ በቤተልሔም ስለ እኛ በተዋሐደው ሥጋ በጨለማና በሞት ጥላ ሥር ያለን እኛን ከቸርነቱና ሰውን ከመውደዱ የተነሣ መጥቶ አዳነን፤ ከዓለም ሁሉ ይልቅ ጣዖትን በማምለክ ሲበድሉም ወደ ግብፅ ሀገር ወርዶ በእነርሱ ላይ የመለኮትነት ብርሃኑን በማብራት ታላቅ የሆነ ክብሩን ገለጠ››፡፡
(ድርሳነ ማርያም)
ኅዳር ፮ ቀንን የሚነበበው የመጽሐፈ ስንክሳር ክፍል ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግመኛም በኋላ ዘመን ሐዋርያትን በደብረ ቁስቋም ሰብስቦ፤ ታቦትንና ቤተ ክርስቲያኑን አክብሮ የቊርባን መሥዋዕትንም ሠርቶ ቅዱስ ሥጋው ክቡር ደሙን እንደ ሰጣቸው፤ እኛንም ለዚህ ክብር የበቃን እንሆን ዘንድ የእግዚአብሔር አምላክ ቅዱስ ፈቃድ ይሁንልን አሜን፡፡
ምንጭ ድርሳነ ማርያም መጽሐፍ ትርጉም!