Telegram Web
የዲ/ን አቤል ካሳሁን ትምህርቶች እና ሌሎችም ግሩም ትምህርቶች ተካተውበታል። እኔ ምርጫየ ነው።
በዚች ሊንክ እየገባችሁ አንቡቧት!
ሥጋን ማክበር፡ ፈቃደ ሥጋን ማግረር
--
ትናንት የተዋናዩን (ተስፉ ብርሃኔ) ወደ ክብሩ የመመለስ ጉዞ ትረካ በኃዘን ጀምሬ በኩራት ጨረስኩት፡፡ ፍጹም ንስሐ! ፍጹም መመለስ! እሰይ የኔ ወንድም! መጨረሻህን ያሳምርልን! የቤታችንን አመሻሽ አሳመርክልን፡፡ የአንድ ሰው መመለስ ለሰማውያኑም ደስታ ነው እንኳንስ ለእኛ ለድኩማኑ! ተስፉን ምክንያት አድርጌ የተራ ተመልካች ያህል ስለ አርቲስቶቻችን፣ ጋዜጠኞቻችን፣ ስለሚዲያችን መናገር እመኛለሁ፡፡ ስለ እነርሱ ያለኝ እይታ ርኅራኄና የባለቤትነት ስሜት ያለበት ነው፡፡ በእነ መሠረት መብራቴ ላይ የሚወርደውን ገደብ የተላለፈ እምነታቸውን ሳይቀር የሚጋፋ ጸያፍ አስተያየት እንዳላየ ያለፍኩባቸው ቀናት ሁሉ ይቆጩኛል፡፡ ደጋፊ ተቋም በሌለበት ራሳቸውን ከትቢያ ያነሡ ወንድም እኅቶቼ ላይ የሚሰነዘር ኃላፊነት የጎደለው አነጋገር ያበሳጨኛል፡፡ እመለስበታለሁ! ለዛሬው ሽው ያለኝን - ማታ የተስፉ ብርሃኔን የሚጠት የመመለስ ታሪክ ስሰማ የተሰማኝን - ጥበበኞቻችን ቢያስተውሉት የምለውን ሐሳብ ላንሳ፡፡
--
ሥጋችን በእግዚአብሔር እጅ የተበጀ ነው፡፡ ሥጋችን ከሥላሴ አንዱ አካላዊ ቃል (እግዚአብሔር ወልድ) ገንዘብ ያደረገው ነው፡፡ ሥጋችን በተዋሕዶ ከብሮ አምላክነትን ገንዘብ አድርጎ በአብ ቀኝ በዕሪና (በባሕርይ አምላክነት) ተቀምጡዋል፡፡ ክርስቶስ በመዋዕለ ሥጋዌው የሥጋ ደዌያትን ፈውሷል፡፡ በጸሎተ ሐሙስ ሥጋና ደሙን ለድኅነት ሰጥቶናል፡፡ የሞተው ለነፍሳችንም ለሥጋችንም መዳን ነው፡፡ ሲመጣም በግዘፈ ሥጋ በግርማ መለኮት ነው፡፡ ሥጋችን ለመንፈስ ቅዱስ ማኅደር እንዲሆን የተፈጠረ ተንቀሳቃሽ መቅደስ ነው፡፡ ሥጋ በተፈጥሮው ንጹሕና በእግዚአብሔር የተበጀ ክቡር ቅዱስ ፍጥረት ነው፡፡ ሥጋ ከነፍስ ተለይቶ የሚሠራው ጽድቅም ሆነ ኃጢአት የለም፡፡ ጽድቁም ርኩሰቱም በሥጋና ነፍስ ተዋሕዶ ነው፡፡ ሥጋን ለርኩሰት ነፍስን ለጽድቅ ሥራዎች ሰጥቶ መናገር ዘይቤአዊ አነጋገር ነው፡፡ ሥጋ ርኵስ አይደለም፡፡ ለርኵሰት አልተፈጠረም፡፡ የፈቃዳችን ማደፍ ለሚያመጣው አበሳ ተሸካሚ እንዲሆን፣ የነፍስን ሐሳብ በገቢር ስለሚተረጕም አበሳውን ሁሉ ተግባሪው ተላላኪው ላይ ጭነነው ነው - ሥጋ ላይ፡፡
--
ሥጋችን የተሰጠን እንጂ የፈጠርነው አይደለም፡፡ የተሰጠንን ተጠቅሞ የምናደረገውን መምረጥ ነው የእኛ ጉልበት፡፡ ስንመርጥ ደግሞ ሥጋን በሚያከብር አምላካዊ የእጅ ሥራ መሆኑን ባገናዘበ መልኩ ቢሆን በደለኛ (ረሲዕ)ም ኃጢአተኛም ከመሆን እንድናለን፡፡ ረሲዕ ማለትን አበው ራሱን የሚበድል ይሉታል፡፡ ኃጥእንም ደግሞ አምላኩን የሚበድል፡፡ ሁለቱም ተላላፊዎች ናቸው፡፡ ሥጋችንን እናክብር፤ ፈቃደ ሥጋችንን እናግርር (እንግራ)! አንተ ያንተ ብቻ አይደለህምና ራስህን መበደልን እንደ መብት አትየው! ያውም የአደባባይ ሰው ሆነህማ …!
--
ጠቢባን እኅት ወንድሞች፡- በከበረው ሥጋችሁ የከበረችዋን ጥበብ አክብሯት! ብዙ እንሳሳላችኋለንና ስለ እናንተ ይገደናልና የፈቃደ ሥጋ ምርኮኞች አትሁኑብን!

በአማን ነጸረ

💭 ከሞት ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ💀
ክፍል ፩

🎤ስለትውልድህና ዕድገትህ ብታጫውተኝ?

💀ሞት : አያቴ ምኞት ፣ አባቴ ቃየል ፣ እናቴ ደግሞ ኃጢአት ይባላሉ። የተወለድኩት 5500 ዓመታት ከክርስቶስ ልደት በፊት ነው። ከዚያ ወዲህ በመላው ዓለም እየተዘዋወርኩ የሰውን ልጅ ከዚህ ዓለም ወድያኛው ዓለም ሳጓጉዘው እኖራለሁ።

🎤 ለመሆኑ ሞት የሚለው ስምህ ትርጉም ምንድነው?

💀ሞት : ትርጉሙ አንድ ብቻ አይደለም ፡ እንደየሰው ማንነት ይለያያል። ለግንዛቤ ግን 3 ዓይነት ትርጉሞቼን ልንገርህ።

የመጀመርያው በቅዱሳን ትርጓሜ "መንገድ" ማለት ነው መቼም መጽሐፍ ቅዱስን በሚገባ እንደተማርከው አልጠራጠርም። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ "ልሔድ ከክርስቶስ ጋር ልኖር እናፍቃለሁ" በማለት ተናግሯል። መንገድ ያለኝ እኔን ነው። ምን ያህል እንዳቀለለኝ ተመልከት ።፣(ኩራት እየተሰማው) ለቅዱሳን ከዚህ የመከራ ዓለም ወደሚወዱትና ወደ ሚወዳቸው አምላካቸው የሚጓዙብኝ መንገድ ነኝ በቃ!

በሁለተኛው ትርጓሜ ደግሞ "መገላገያ" እባላለሁ። ኑሮ የመረረው አልሳካ ያለው የደዌ ዳኛ የአልጋ ቁራኛ ያሰቃየው "በገላገልከኝ" ይላል። ይሁን እንጂ ብዙዎቹ ከተናገሩኝ በኋላ ስመጣ ይፈሩኛል።(የፌዝ ሳቅ)

በሦስተኛ ደረጃ ደግሞ "መቅጫ" የሚያደርጉኝ አይጠፉም ፡ የዚህ ዓለም ደስታ ፈንጠዝያ ፣ ጭፈራ ፣ ሥጋዊ እርካታ ወዘተ የማይጠገባቸው አለሌ መለሌ እንደሆኑ መኖር ሚፈልጉ ሰዎች ቀጨኸን ልትቀጨን ነው ሲሉ እሰማቸዋለሁ። ሌላም ብዙ ትርጉም አለኝ።

🎤ከሰው ልጅ ተፈጥሮ የሚገርምህን ብትነግረኝ?

💀ሞት : ከሰው ልጅ ተፈጥሮ "ሞኝነቱ" ነው የሚገርመኝ ። ተመራመርኩ ፣ አወቅሁ ፣ መጠቅኩ ፣ ጨረቃ ደረስኩ እንዲያውም አሁን አሁንማ ነፍስ ልሠራ ነው እያለ ሚፎክረው ሰው ራሱን ሳያውቅ ቀርቶ መሞኘቱ ይገርማል። ከአጠገቡ ጓደኛውን ስወስደው እኔ መኖሬ ትዝ አይለውም። በአጥቢያው የጌታው ሥጋና ደም ሲፈተት ልቀበል ብሎ የማያስብ አምላክ እንዳለ የሚረሳ። በዓለም ወንጌል እየተሰበከ ሲያልፍ የማይነካው ፣ እንዲህ ያለ ፍጡር ሞኝ አይደለም ትላለህ?(በምፀት እያሾፈ)

እናንተስ በዚህ ምድር ምትኖሩት አርባ ፣ ሃምሳ ቢበዛ ስድሳ ነው እስቲ ከዛ በኋላ የት እንደምትሄዱ ንገረኝ? በዚህ ዓለም ምትኖሩት ጥቂት በወዲያኛው ዓለም የምትኖሩት ግን ለዘለዓለም ነው ። ምኑ ተቆጥሮ? ታድያ እንዴት ሰውን የሚያህል ዐዋቂ ፍጡር ዘመን የማይቆጠርለትን ደስታ ዘመን በሚቆጠርለት ጊዜያዊ ነገር ይለውጣል!? እግዚአብሔር የለም እያለ ሲያሾፍ የነበረውን ስንት ትእቢተኛ እያጣደፍኩ ወስጄ ለሰማያዊ ፍርድ ለሲዖል ኋላም ለገሃነም እሳት ሳቀርበው የነበረው ጭንቀትና ውጥረት ፣ የነበረው ልቅሶ .....ኤዲያ ሰው ማለት ማሽላ ነው። ይስቃል-ያራል። ለምን ትሞኛላችሁ? የፈለጋችሁትን ያህል ተደሰቱ ፣ ብሉ ጠጡ አጊጡ ፣ ሥልጣን ያዙ ግዙ ንዱ እንጂ ከእኔ እጅ ፍፁም አታመልጡ ፣ ጭብጥ ጭብጥብጥ ኩምትር ኩምትርትር አድርጌ ስወስዳችሁ በኋላ ቀጭውን እንዳየ ሕጻን ልጅ ልትቁለጨለጩ ምንድው ኩራቱ ትእቢቱ?የፈጠራችሁን እግዚአብሔርን ሳትታዙ ድንገት ስመጣባችሁ ሞኝነታችሁ ያስገርመኛል።

አሁን ያ አጋግ(፩ሳሙ ፲፭፣፴፪) ታሪኩን አንብበው እንዲያ ሕዝቡን ሁሉ መከራ ሲያሳይ በእግዚአብሔር ላይ ሲቀልድ ኖረና በእጄ የገባ ጊዜ "በውኑ ሞት እንደዚህ መራራ ነውን?" ብሎ ዐረፈው ፈሪ ሁላ ቀድማችሁ አትዘጋጁም። ብዙ አስለፈለፍከኝ።

🎤 መልካም እሺ ውድ ታዳሚዎቻችን ከሞት ጋር ያደረግነው ክፍል ፩ ቆይታ በዚሁ ተጠናቀቀ ተከታዩን ክፍል በቅርቡ ይዘን የምንቀርብ ይሆናል። ሰላም ግዜ!

ምንጭ - ሐመር መጽሔት
1👍1

💭ከሞት ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ💀
ክፍል 2

🎤 ለመሆኑ መኖሪያህ የት ነው?

💀 ሞት : የት ይመስልሃል? እንደ እናንተ እንደ እናንተማ ሩቅ ነኝ።ሞኝ ሁሉ ፡ ከጎናችሁ ነኝ ፡ ካጠገባችሁ ነኝ።ከደም ስራችሁ ሁሉ ቅርብ ነኝ። አንዳንዱማ ሬሳ ላይ ወይም መቃብር ሥፍራ ብቻ ያለሁ ይመስለዋል። ስትበሉ ስትጠጡ ስትጸልዩ ስትጾሙ እታዘባለሁ። እኔ ከሰው ርቄ አላውቅም።እናንተ ግን ትረሱኛላችሁ። መኖሬም ትዝ ስለማይላችሁ ዘላለም በዚህች ምድር ትኖሩ ይመስል ከሥጋ ፍቃድ ሌላ አይታያችሁም ። አንድ አንድ ጊዜ ታሳዝኑኝና በበሽታ፣ በጓደኛ ሞት ወዘተ አስደነግጣችኋለሁ ምን ይደረጋል? "ታሞ የተነሳ እግዚአብሔን ረሳ" ነው ወዲያው ትረሱኛላችሁ ። ሰው ሞትን ይረሳል እንጂ ሞት ሰውን አይረሳም።(በኩራት ይንጠራራል)

🎤በጣም የተደሰትክበት ቀን ካለ ብትገልጽልኝ

💀 ሞት :(በፈገግታ) አሉ! እጅግ በጣም ፡ ቃየል አቤልን ሲገል ፣ የሰው ልጅ በኃጢአቱ በንፍር ውሃና በእሳት ተቃጥሎ ሲጠፋ ፣ ከእስራኤል በአንድ ቀን 24,000 ሰው ሲረግፍ በፓለቲከኞች ሴራ ሰው ሲረግፍ፣ በግዴለሾች ነፍስ ሲጠፍ፣እራሱን ሰው ሲያጠፍ • • • ምኑን ልዘርዝርልህ ያን ቀን እየፈነደኩ ሳግዝ ነው የዋልኩት።

🎤 ዛሬ ዛሬስ በምን ትደሰታለህ?

💀 ሞት : አሁን አሁንማ ከማዝንበት የምደሰትበት ይበዛል ።(በትዕቢት) በኑፋቄና በክህደት ስትያዙ በዝሙት በአሸሼ ገዳሜ በስርቆት ወዘተ ስትዋጡ ፌሽታየ ነው ደስታየ። ብቻ ይችን ምስጢር ለማንም ትንፍሽ አትበል።

🎤 ወገን አለህ ወይስ አንድ ብቻ ነህ?

💀 ሞት : አለኝ

🎤 እስቲ በዝርዝር ንገረኝ

💀 ሞት : ሁለት ዓይነት ዘር አለኝ ፡ የመጀመርያው ሞተ ሥጋ ይባላል ሁለተኛው ደግሞ ሞተ ነፍስ !

ሞተ ሥጋ ለማንም የማይቀር ቅዱሳን እንኳን የሞቱት ሞት ነው። የነፍስ ከሥጋ መለየት ነው። ሞተ ነፍስ ግን በራሱ ሁለት ወገን አለው አንደኛው በዚህ ዓለም በኃጢአት የምትሞቱት ሞት ነው። ሰው ኃጢአት ከሠራ ሞተ ማለት ነው። ለምሳሌ - የጠፋው ልጅ ወደ አባቱ ሲመለስ "ይሄ ልጄ ሞቶ ነበር ደግሞም ሕያው ሆነ" ሲል አባቱ ተናግሯል (ሉቃ ፲፭፣፳፬) ነገር ግን በአካለ ሥጋ አልሞተም ነበር።

ኃጢአት ስለሠራ ከአባቱ ቤት ስለኮበለለ ግን እንደሞተ ተቆጠረ ። ከንስሐ ከሥጋ ወደሙ በጠቅላላው ከነገረ ቤተክርስቲያን መራቅ የቁም ሞት ይባላል። ሞኝ ሁላ! እናንተ ሙታን ሙት ልትቀብሩ ጥሩንባ ነፍታችሁ ደረት እየደቃችሁ "ዋይ ዋይ የት ትሄዳለህ?" ትላላችሁ በእናንተ ቤት ማትሞቱ ይመስል ሙት ትላላችሁ። መቅበራችሁም ነው? እናንተ እራሳችሁ ከሞታችሁ ስንት ዘመን አለፈ። ይልቅ ጎበዝ ከሆናችሁ ጥሩንባ ንፉና ዘመድ አዝማድ ሰብስባችሁ ለራሳችሁ አልቅሱ። ዝንጀሮ የራሷ መላጣ አይታያት በሰው መላጣ ትስቃለች አሉ።

እኔ እኮ የእገሌ ሀገር ሕዝብ ሠላሳ ሚሊዮን ፣ አርባ ሚሊዮን ፣ አሥር ሚሊዮን ስትሉ ይገርመኛል። እንኳን ሠላሳ እና አርባ አንድ ሚሊዮን ሰው ይገኛል? ዕድር ያላወቀው ሠፈር ያልቀበረው አሁንም ያልተሰረዘ ስንት ሟች አለ መሰለህ!

ይ ቀ ጥ ላ ል
"ቡና ርኩስ ነውን ?

ብዙዎች ቡናን በአፈ ታሪክ እና በዘልማድ አባባል ርኩሰነው ቡናን መጠጣትም ኃጥያት ነው በማለት በራሳቸው መላምት ሲተቹ ይታያሉ ግን ?

(1) በመጽሐፍ ተከልክሉል ?

አንድ አንድ ሰዎች ቡና በድርሳነ ፅዮን እና በዜና ስላሴ ተከልክሉል ይላሉ ።እስካሁን ግን ምዕራፍ እና ቁጥር አንቀፅ እና ገፅ ጠቅሶ ይህንን ይላል የሚል የለም በእርግጥ መፀሐፍቱ ለምዕመኑ በቅርብ ባለመገኘታቸው ለማሳመኛ ተጠቅመውባቸው ካልሆነ በቀር በሁለቱም መፀሐፍት ቡና አትጠጡ የሚል እንደሌለ ሊቃውንትም መፀሐፉቱም ይናገራሉ።

(2) የዲያብሎስ ደም (መሥዋት ) ነው የሚሉም አሉ

ለዲያብሎስ ተብሎ የተፈጠረ ወይም የተለየ የመሥዋዕት እህል ተክል ወይም እንሰሳ የለም ። አንድ አንድ ሰዎች ያልተማሩትን ወይም ከመጸሐፍ ከሊቃውት ያላገኙትን እየተረጎሙ "ቡናው የዲያብሎስ ደም የቡና ቁርሱ የዲያብሎስ ስጋ " በማለት ከሥጋ ወደሙ ጋር አመሳስለው ለመተርጎም እና ለዲያብሎስ ለመስጠት ያስባሉ ትልቁ ኃጢያትስ የእግዚአብሔርን ፍጥረት ለዲያብሎስ መስጠት ነው።
አንድ ሰው ለዲያብሎስ ነው የምሰዋው ብሎ እስካመነ ድረስ ቡናም ሻይም በግም ዶሮም ቢሰዋ እንደ እምነቱ ለዲያብሎስ ባርነቱን ይገልጥበታል ። ያሰው ግን ዲያብሎስን በምግባር በሐይማኖት መቃወም ከቻለ ደግሞ ዲያንሎስ ከርሱ ይሸሻል ። ሲጅመር ዲያብሎስ መንፈሰ ርኩስ እንጂ መች እንደሰው ስጋ ደም አጥንት አለው ና ።ኤፌ 6፦12 ቡና ግን በዕለተ ሰሉስ ከውኃና ከነፍስ የተፈጠረ ተክል ነው እግዚአብሔር የፈጠራቸው ፍጥረታት ደግሞ መልካም እንደሆኑ ታላቁ መጽሐፍ ይነግረናል ዘፍ 1፦12 ይህንን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምስክርነት ትተን የቡና ተክል ርኩስ ነው ብንል ተቃውሞችን ከእግዚአብሔር ጋር መሆኑን አንዘንጋ።

(3) የተወገዘ ነው ?

አንድ አንዶች ቡና በቤተ ክርስቲያን የተወገዘ ነው ብለው ያምናሉ ፡ይናገራሉ ያወገዘው አካል ማን እንደሆነ ግን አይገልጡም ለመሆኑ የማውገዝ ስልጣን ያለው ማነው ? አንድ አንዶች ባህታዊ እገሌ አውግዘውታል ሲሉ ይሰማሉ አንድ ውግዘት የሚጸናው የሚያወግዘው ሰው ትክክለኛ ስልጣነ ክህነት ካለው ያውገዘበትም ምክኒያት ቤተ ክርስቲያን በደነገገችው ሥርዓት እና ህግ መሰረት ከሆነ ብቻ ነው
ከዚህ ውጭ የሚደረግ ውግዘት ግን "ግዝት ዘበከንቱ "ተብሎ ይጠራል በመሆኑም ቤተ ክርስቲያን ቡና አትጠጡ ብላ ስረዓት ሳትሰራ አትጠጡ ብሎ ማውገዝ "ግዝት ዘበከንቱ " ከመሆን አያልፍም

(4) ክርስቶስ ሲሰቀል ለምልሞ ስለተገኘ ?

ስለቡና ከሚነገሩ አፈታሪኮች አስገራሚው ይሄ ነው ጌታችን ሲሰቀል ቡና ጫት ጥንባሆ ለምልመዋል እየተባለ የሚነገረው ነው ።ጌታችን ሲሰቀል ሶስት አመፀኛ ዛፎች ሌላው ሁሉ ሲደርቅ እነሱ አልደርቅም ማለታቸው በቤተክርስቲያን የትኛውም መፀሐፍ ላይ ያልተመዘገበ እና አፈታሪክ መሆኑን አንባቢያን እንድትገነዘቡልኝ እፈልጋለው
አመፁ እዳይባሉ እጨቶች ናቸው
ሌላው ጌታ ሲሰቀል የታዪት ሰባት ተዓምራት ምንምን እንደሆኑ በመፀሐፍ ተመዝግቦ አለ ።
ፀሐይ ጨለመች ጨረቃ ደም ለበሰች
መቃብራት ተከፈቱ ከዋክብት ረገፉ
ሙታን ተነሱ አለቶች ተሰነጣጠቁ
የቤተመቅደስ መጋረጃ ከሁለት ተከፈለ
ከነዚህ ውጭ ሶስት ዛፎች ለመለሙ የሚል ትምህርት ግን የለም።

(5) .በአርዩስ ፈርስ ላይ የበቀለ ነው ?

አርዩስ በክህደቱ ጸንቶ አፅመሆዱ ተዘርግፎ ሲሞት በፈርሱ ልስይ አስቀድመን የጠቀስናቸው ሶስት እፀዋት በቅለዋል ይባላል ። ይህ ደግሞ ከእውነት የራቀ ሐሰት ነው የኒቂያ ጉባኤ ታሪክ የአርዩስን ህልፈተሞት የፃፉ የውጭ ሐገር የሆኑ የሐገር ውስጥ የታሪክ ሊቃውንት ይህንን ጉዳይ መቼም ቢሆን አንስተውት አያውቁም ነገርግን ውሸት ሲቆይ እውነት ይባላል እንደሚባለው እየሆነ እንጂ ይህንን ትምህርት የሚያስፋፉትም ቢሆኑ ከቤተክርስቲያን መጽሐፍት ልብ የሚሞላ መረጃ አያቀርቡም ። በቤተ ክርስቲያን ትምህርት ቅዱሳን አፅማቸው ባረፈበት ተዓምራት በሰሩበት ለምሳሌ ገድለ ቅዱስ ጊዩርጊስ የደርቀውን ዛፍ አለምልሞ ፍሬ እንደሰጠ ታሪኩ ይናገራል
አመጸኛውና ከሐዲው አርዩስ ዕፅ አለመለመ ካልን እማ የበቃ ፃድቅ ነው ማለታችን ነው። መፈጠራቸውም ሌላው እፀዋት ተፈጥረው ያለቁት በዕለት ሰሉስ መሆኑን መጸሐፍ ቅዱስ ይነግረናል ፈጥረታት መፈጠራቸውም በዕለተ አርብ መጥጠናቀቃቸውንም መጸሐፍ ይነግረናል "እግዚአብሔርም ከሰራው ስራ ሁሉ አረፈ" ፍጥረት መፍጠሩን ጨረሰ። ታዲያ እነዚህ ዕፀዋት በአርዩስ ፈርስ ላይ በቅለዋል ካልን አዲስ ፍጥረት ሆነው ከብዙ ሺህ አመታት በሁላ ተገኙ ልንል ነው ።ይህ አባባል ከሥነ ፍጥረት ትምህርት ጋር የሚቃረን የሐሰት ትምህርት ነው

(6) ባዕድ አምልኮ ነው ?

ማንኛውም ነገር ባዕድ አምልኮ የሚሆነው ለእግዚአብሔር ሊፈፀም የሚገባው ነገር ለዚያነገር ሲደረግለት ነው። እንደ አምላክ ሲቆጠር ፣ተስፍ ስንጥልበት መሰዋዕት ሲሰዋለት የአምልኮ ስግደት ሲሰገድለት እና እጣ ፋንታችንን በእርሱ ብቻ ስንወስን እና ወዘተ ከዚህ ውጭ ግን ቡና እስከሶስተኛ ስለተጠጣ የቡና ቁርስ ስለተደረገለት አምልኮ ባዕድ አይባልም

በእርግጥ አንድ አንድ ሰዎች ከትምህርት ማነስ የተነሳ ቆሎ የ.ሚበትኑ ሲኒ እያዩ የሚጠነቁሉ እና ቡና ካልተወቀጠና ካክተፈላ በቤቱ እንዳች ክፉ ነገር እንደሚመጣ የሚያስቡ አሉ። ይህ ግን የሰዎች በእምነት ያለመብሰል እና ስለቡና ያላቸው የተዛባ አመለካከት የመነጨ እንጂ ቡና አምልኮ ባዕድ ሆኖ አይደለም ።

ቡና ፋሬው በጥንተ ተፈጥሮ ንፁህ ሆኖ ሳለ ተጠቃሚው የሰው ልጅ ግን ለእርኩስ መንፈስ መሥዋዕት አድርጎ ሲያቀርበው "ርኩስ" "ይሆናል ለባዕድ አምልኮ ተብሎ ከተፈላ ጠጭውንም ያረክሰዋል በዚህም መልኩ መምህራን አትጠጡ ብለው ቢሰብኩ እውነታቸውን ነው ያሰኛል ምክኒያቱም ለጣዑትም ሆነ ለዲያብሎስ የተሥዋውን መብላት የተከለከለ ነው

"ማንም ግን ይህ ለጣዑት የተሰዋ ነው ቢላችሁ ከዚያ ካሳወቃችሁ እና ከህሊና የተነሳ አትብሉ "1ቆሮ 10፥28 በአጠቃላይ ቡና መጠጣት የለበትም የሚል አጉአጉል ትምህርት የቤተክርስቲያን አይደለም ግን ከቡናጋር ተያይዘው የሚመጡትን የባዕድ አምልኮ እንዳያመልክ ህዝቡን ማስተማሩ አይከፋም ቡናም መጠጣት አለበት ከተባለ በቡናነቱ ብቻ መጠጣት አለበት

የአድባር የቆሌ መለመኛ የጠንቆላ መለማመኛ የሐሜት መነሐሪያ ሰውን መቦጨቂያ ካደረግ ነው አምልኮ ባዕድ አድርገነዋል ማለት ነው ። ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ አታምልክ ዘጸ 20፥3 የሚለውን ህግ እንዳንረሳ ይገባናል

ለሁሉም ግን ከመብላት መፃም ከመጠጣት መከልከል ይጠቅምናል እና በመብልና በመጠጥ የጸደቀ የለምና

ሁሉ ተፈቅዶልኛል ሁሉ ግን የሚጠቅም አይደለም ሁሉ ተፈቅዶልኛል ነገር ግን ሁሉ የሚያንፅ እርይደለም 1ቆሮ 10፦23
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ ቃለ ተዋሥኦ መጽሐፍ ከገፅ 1- 7።
(በዲ/ን ኅሩይ ባዬ)
እንኳን #ለወርኀ_ጽጌ (ለዘመነ ጽጌ) በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!!!
በሀገራችን ኢትዮጵያ እንዲሁም በቤተክርስቲያናችን አስተምህሮ ከመስከረም ፳፮ ጀምሮ ጸአተ-ክረምት ይባላል። ዘመነ-ክረምት አልፎ ዘመነ-ጽጌ (ዘመነ-መጸው) የአበባና የፍሬ ወቅት ይባላል። በዚህ ወርኅ (በዘመነ ጽጌ) የጌታችን ፣ የእመቤታችን ፣ የአረጋዊው ጻድቅ ዮሴፍ፣ የቅድስት ሰሎሜ #ስደት ይታሰባል በጾም ይዘከራል።
ቀደምት ቅዱሳን ነቢያት ስለ ስለሠራዊት ጌታ ስለእግዚአብሔር ወልድ ስለኢየሱስ ክርስቶስ #ስደት አስቀድመው እንደተነበዩ
ቅዱሳት መጻሕፍት ይነግሩናል።
"ናሁ ይወርድ እግዚአብሔር ውስተ ምድረ ግብፅ ተጽዒኖ ዲበ ደመና ቀሊል። ኢሳ ፲፱፥፩
"እነሆ ልዑል እግዚአብሔር በቀላል #ደመና ተጭኖ ወደ ግብፅ በረሀ ይወርዳል። ኢሳ 19፥1

"እምግብፅ ጸዋዕክዎ ለወልድየ ለክብረ ቅዱሳን። "ሕያው እግዚአብሔር አብ እንዲህ አለ! "ሕያው እግዚአብሔር ወልድ ልጄን ከግብፅ ጠራሁት። ትንቢተ ሆሴዕ 11፥1
" ወናሁ መልአከ እግዚአብሔር አስተርአዮ በሕልም ለዮሴፍ እንዘ ይብል ተንሥእ ወንሳእ ሐፃነ ወእሞ ወጉይ ውስተ ብሔረ ግብፅ። ወሀሉ ህየ እስከ አመ እነግረከ። ማቴ ፪፥፲፫

"እነሆ የእግዚአብሔር መልአክ ለዮሴፍ በሕልም ታይቶ እንዲህ አለው "ሄሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ይሻልና ተነሳ ፣ ሐፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብፅ ውረድ (ወደ ግብፅ በረሀ ሺሽ።) እስክነግርህም ድረስ በዚያው ቆይ አለው። ማቴ 2፥13
የቸሪቱ አማላጅ የእመቤታችን #አማላጅነት ፣ የቸሩ አምላክ የልጇ የመድኃኔዓለም ክርስቶስ #ቸርነት አብረው የተሰደዱት የአረጋዊው ጻድቅ የዮሴፍና የቅድስት ሰሎሜ #በረከት ከሁላችንም ጋር ይሁን። አሜን!!!
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ለመናፍቃንና ለአህዛብ መልስ አላት!
Photo
ምንድነው? ለምን ሼር አደረከው?
ይህ ታሪካዊ ጉባዔ ነው!
2025/07/12 20:35:11
Back to Top
HTML Embed Code: