Telegram Web
እያነበባችሁ ሼር በሀይለኛው ሼር አድርጉት

የተሰማኝ ደስታ እጥፍ ድርብ ነው “ለምን?” ካላችሁ ኦርቶዶክሳዊነት ረቀቅ ነው።ፍቅሩ ሲገባህ የቅዱሳኑ ተጋድሎ ሲማርክ የእመ አምላክ እናትነት፣ደግነት፣ምልጃና በረከት ሲፀናብህ የቅድስት ሥላሴ አምላክነት ምስጢሩ ሲሰርፅብህ የቅድስት ቤክ እውነተኛነት ቀጥተኝነት ሲገባህ በፈቃድህ ትማረካለህ ወደህ እጅ ትሰጣለህ።

ውድ ወዳጆቼ ይህንን ስራ ማለት አልፈልግም ይህንን ታላቅ ሱታፌ በእኛ ደካማ እና ሀጥያተኞቹ ላይ አድሮ የስራው እግዚአብሔር ብቻ ነው።ወንድሞቼን እና እህቶቼን አባቶቼን እና እናቶቼን ከጠፉበት ሰብስቦ ወደ በረቱ ያስገባቸው መንፈስ ቅዱስ ነው።የልባቸው ጥያቄ እርሱ በሀይሉ ስላወቀ ነው።ከእኔም ከጓደኞቼም የሆነው እንደ አንድ ታናሽ መታዘዝ ብቻ ነው።ምስክርነታቸውን የሰጡ ብዙ ናቸው።እኔም ከፈቃዳቸው ነውና እንድንማርበት እነዚህን ለአብነት እንሆ • • •

ኑሐሜን ግዛው(መአዛ ማርያም)ከፕሮቴስታንት(ካናዳ)
ነፃነት ሻፊ(ወለተ መድህን)ከፕሮቴስታንት(ኖርዌይ)
ኤፍሬም አዱኛ (ወልደ ጊዮርጊስ)ከፕሮቴስታንት
ዮናስ ደሞዝ(ገብረ ሥላሴ)ከፕሮቴስታንት
ዳናዊት ዮሴፍ(እህተ ማርያም)ክፕሮቴስታንት(አውስትራሊያ)
ዳዊት ዳባ(ገብረ ሥላሴ)ከፕሮቴስታን
አቶ ጊድዮን ኤባ(ወልደ አብ)ከፕሮቴስታንት
ወ/ሮ መርከብ ሞሲሳ(ሥርጉተ ማርያም)ከፕሮቴስታንት
(ያልተጠቀሱ 4 ሴት እና 9 ወንድ)

ናኦድ ኢሳያስ(ገብረ ማርያም) ከኢቫንጀሊካን
ብሌን ዋለልኝ(ወለተ ገብርኤል)ከሞርሞን(ይህ ሀይማኖት እኔ አላውቀውም)

አሚን ዳውድ(ክንፈ ገብርኤል)እስልምና
ሙራድ ሲራጅ(ወልደ ማርያም)ከእስልምና
ቶፊቅ ኑሩ(አክሊለ ገብርኤል)ከእስልምና
ሒክመት ኑርሴን(ሥርጉተ ሥላሴ)ከእስልምና
ሙና ሙሐመድ(አስራተ ማርያም) ከእስልምና
ሙሐመድ ሷሊህ ሙሐመድ( ወልደ ሩፍኤል)ከእስልምና
(ያልተጠቀሱ 3 ሴት 3 ወንድ)

ጉቱ ገላና (ወልደ መስቀል)ከሀገር ባህል እምነት

እነዚህ የክርስቶስ ቤተሰቦች የቅድስት ቤተክርስትያን ልጆች ሆነዋል እግዚአብሔር የወደደውን ከወደደው ቦታ በፍቅሩ ይጠራል።ገና እርሱ በፈቀደው ግዜና ሰዓት ሌሎችንም ይጠራል።

እናንተ የክርስቶስ ሙሽሮች እንግዲህ የጠራችሁ በቤቱ ያፅናችሁ ለክብር እና ለፅድቅ ያድርግላችሁ።

ምስጋና ለክንቱ ውዳሴ ቢጥልም እኔ ግን ወንድምቼን እና እናቶቼን ከልቤ በእግዚአብሔር ሥም አመሰግናለሁ።
ቢኒ(ኃይለ ገብርኤል)
ትንሹ(ወልደ ኢየሰስ)
ወ/ሮ ንግስቲ(ሒሩተ ሥላሴ)
አይመን ጆርጅ(ገብረ ፃድቅ)
እግዚአብሔር ይስጣችሁ።ባደረጋችሀት ልክ ሳይሆን አብዝቶ ይስጣችሁ!
ለቅዱስ ፓትርያሪክ አቡነ ማትያስ
ለቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ መርቆሪዎስ
ለብፁአን ሊቃነ ጳጳሳት!

እነሆ ልጆቻችሁ የአማራና የትግሬ ወጣቶች ለመተራረድ ሰይፍ እየሳሉ ነው። ሰይጣን የደገሰው የክርስቲያኖች ሞት እንዳይቀርበት ከዘር ዘር፣ ከክልል ክልል እየሮጠ ሁሉን ግራ አጋብቶ ዝም አሰኝቷል። የደም ጎርፉን ማንም፣ ምንም የሚያስቀረው፣ ለማስቀረትም ፍላጎት ያለው አይመስልም። እባካችሁ እናንተ ዝምታውን ስበሩ።

አባቶቼ!!! የምታለቅስ እናትን ማስተዛዘን ትርጉም የሚኖረው፣ በልጁ ሞት አስክሬን የታቀፈን አባት ነፍስ ይማር ማለት ፅናት የሚሆነው፣ ነገ ቤተክርስቲያንን እናቴ የሚለው ይህን ጥፋት ልጆችዋ ለማጥፋት ሲንደረደሩ ቤተክርስቲያን ዛሬ ተው ማለት ከቻለች፣ ከለመነች ብቻ ነው።

ይህንን መተራረድ ፣ ብልጽግና፣ ሕውሃት ፣ ራሽያ፣ ቻይና፣ አሜሪካ፣ ትግሬነት፣ አማራነት ... አያስቆሙትም። የኢትዮጲያ ሰላም ከእግዚአብሔር ብቻ ነው። ለዚህ ደግሞ ለእርቅ ዝግጁ የሆኑ ልቦችን መፈለግ፣ መገሰፅ እና ማወያየት ያስፈልጋል።
አሉ! አንዲት ኢትዮጲያን፣ ሰላም፣ ፍቅርን ተስፋ አድርገው ህይወታቸውን ለመስጠት ፈቃደኛ የሆኑ።
አሉ! ከዘራቸው በላይ ኃይማኖታቸው ይዟቸው ዝም ያሉ "አማሮች" እና ዝም ያሉ "ትግሬዎች" ትክክለኛ ክርስቲያኖች አሉ! እነርሱን መፈለግና ተስፋ መስጠት ፣ ተደናግሮ ከሚያደናግረው በላይ ድምፃቸው እንዲሰማ ማድረግ ያስፈልጋል።

ብጹአን ሊቃነ ጳጳሳት ይህን ጦርነት ለማስቀረት መጣር መሰደብ፣ መዋረድ፣ መጠላት...ሊያመጣ ይችላል። ክብራችን ከክርስቶስ እንጂ ከሰው አይደለምና እባካችሁ በርቱ።
እግዚአብሔር አንድ ግዜ ይቅር ብሎ ይህንን ተጨማሪ መገዳደል በእናንተ ዘመን እንዳናይ ይርዳን። እኛን ለይቶ ከኮሮና ሞት የታደገን አምላክ ፊቱን ከፈለግን ዛሬም ከእኛ ጋር ሊሆን የታመነ ነው። ምዕመናንን መቀስቀስ ወደ እርሱ መጮህ የቤተክርስቲያን የዚህ ወቅት ብቸኛ ስራዋ ነው!!!

እግዚአብሔር ይርዳችሁ!!!
እግዚአብሔር ይርዳን!
መ/ር ቴዎድሮስ አሰፋ (ኃይለ ሚካኤል)

ግልባጭ፡-
ለማህበረ ቅዱሳን
ለሰንበት ት/ቤቶች ሕብረት
ለተለያዩ መንፈሳዊ ማህበራት።
የሚስጢረ ቁርባን መመሪያ ልቆርቡ በፈለጋችሁ ወይም በተጠየቃችሁ ጊዜም አካፍሏቸው።

ስጋየን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ህይወት አለው፡፡ ስጋየ እውነተኛ መብል ደሜም እውነተኛ መጠጥ ነውና ዮሐ 6÷54-55

ምሥጢረ ቁርባንና ሥርዓቱ

- ከመቁረባችን በፊት ሊደረጉ የሚገባቸው ቅድመ ዝግጅቶች?
- ከቆረብን በኋላ ሊደረጉ የማይገቡ/ የተከለከሉ ነገሮች?
- ሊቆርብ የሚገባው ማነው?

ከ ሰባቱ ምስጢራተ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ አንዱ ምስጢረ ቁርባን
ሲሆን ቁርባን የሚለው ቃል የሱርስት ቃል ሲሆን በቁሙ ለእግዚአብሔር
የሚቀርብ መንፈሳዊ አምኃ፣ መስዋዕት ፤ መባዕ ለአምላክ የሚቀርብ የሚሰጥ
መንፈሳዊ ነገር ሁሉ ማለት ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን ዘመን ይቀርብ የነበረው
የመስዋዕት ቁርባን ፤ ከበግ ፤ ከላምና ፤ ከተለያዩ እንስሳት ነበር ። በሐዲስ ኪዳን
ግን እንስሳት በቤተ መቅደስ ውስጥ መስዋዕት (ቁርባን) ሆነው አይቀርብም፤
መስዋዕት ሁሉ በክርስቶስ ሥጋና ደም ተጠቃሏልና ።

ይህንም የአዲስ ኪዳን መስዋዕት የመሠረተው ራሱ ጌታችን ሲሆን ፤ በጸሎተ
ሐሙስ ማታ አስራ ሁለቱ ሐዋርያት እንዳሉ በመጀመሪያ መስዋዕተ ኦሪትን ሰርቶ
ካሳለፈ በኋላ ኅብስቱና ወይኑን ባርኮ “ነገ በመስቀል ላይ የሚቆረሰው ሥጋዬና
የሚፈሰው ደሜ ይህ ነው ብሉ ጠጡ ብሎ ሰጣቸው” ። ማቴ 26 ፥ 26 ።

በመሆኑም ማንኛውም በክርስቶስ ክርስቲያን በወልድ ውሉደ እግዚአብሔር፣
በመንፈስ ቅዱስ መንፈሳዊ የተባለ/የተሰኘ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን
ተከታይ/አማኝ ዘላለማዊ ህይወትን ለማግኘት የጌታችን የፈጣሪያችን
የአምላካችን የኢየሱስ ክርስቶስን ስጋና ደም የመቀበል ሐይማኖታዊ ግዴታ
አለበት ‹‹በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም ሥጋዬን የበላ ደሜንም የጠጣ
የዘለዓለም ሕይወት አለው›› እንዲል ክርስቶስ፡፡(ዮሐ 6:53-58)

ምስጢረ ቁርባን ካህኑ ኅብስቱን በጻህል ወይኑን በጽዋ አድርጎ በጸሎተ ቅዳሴ
እየጸለየ በባረከው ጊዜ ኅብስቱ ተለውጦ ሥጋ መለኮት ወይኑም ተለውጦ ደመ
መለኮት ይሆናል ። እኛም ይህን ቅዱስ ሥጋና ክቡር ደም በምንቀበልበት ጊዜ
የዘላለም ሕይወት ለማግኘት ይህንን የክርስቶስ ስጋና ደም የምንቀበልበት ታላቅ
ምስጢር ሲሆን ለእኛ ሲል የተቀበለውን መከራና ስቃይ እያሰብን ራሳችንን
በንስሓ ከኃጢአት ንጹህ አድርገን ከንስሓ የቀረውን በደላችንን እንደሚደመስስልን
፤ ከበደል እንደሚያነጻንና የዘለዓለም ሕይወት እንደሚሰጠን አምነን መሆን
አለበት ።

በብሉይ ኪዳን ዘመን እስራኤላውያን ስለ ኃጢአታቸው ለእግዚአብሔር
የሚያቀርቡት ሁሉ ቁርባን (ከእህልና ከአትክልት የሚዘጋጅ) እና መስዋዕት
(ከእንሰሳት ወገን የሚዘጋጅ) ሲባል ለመጀመሪያ ጊዜ ለእግዚአብሔር መስዋዕት
ያቀረበው አዳም ነው፡፡ በአዲስ ኪዳን ግን ቁርባን ወይም መስዋዕት የሚባለው
እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ያቀረበው ሲሆን ሰዎች ወደ እግዚአብሔር
የሚቀርቡበት መንገድ መሆኑንም ቃሉ ያመላክታል፡፡

በአዲስ ኪዳን ቁርባን የሚባለው የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ
እውነተኛ ስጋና ደም ነው፡፡ 1ኛቆሮ 11 ፥ 23-27፤ ገላ 3፡1 በተጨማሪም
መስዋዕት ይባላል 1ኛ ቆሮ 5፡7 ፤ ዕብ. 10፡14፡፡ ጌታችን ይህን ምሥጢር
ከማሳየቱ (ከመመስረቱ) በፊት በዮሐ 6 ፥ 53-58 ። “ሥጋዬን ካልበላችሁ
ደሜንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም ሥጋዬን የበላ ደሜንም
የጠጣ የዘለዓለም ሕይወት አለው ። ሥጋዬ እውነተኛ መብል ደሜም እውነተኛ
መጠጥ (ሕይወትን የሚሰጥ) ነው ” በማለት ስለምሥጢረ ቁርባን በስፋት
አስተምሯል ።

የቅዱስ ቁርባን ጥቅም/ በቅዱስ ቁርባን የሚታይ ጸጋ:-

- ህብስቱና ወይኑ ተለውጦ እውነተኛ ስጋ ወልደ እግዚአብሔር እና እውነተኛ
ደመ ወልደ እግዚአብሔር ሲሆን ማየት 1ኛ ቆሮ. 10፡16
- ከዚህ ዓለም በሞት ስንለይ በሰማያዊ መንግስት የዘለዓለም ሕይወት
እናገኛለን ። ዮሐ 6 ፥ 53 ።
- ፍጹም የሆነ የኃጢአት ስርየት (ድኅነት) እናገኛለን ። 1ኛ ዮሐ. 1፡7 ፤ ዕብ
9፡14 ፤ ማቴ 26 ፥ 26-28 ።
- ከጌታችን ከአምላካችን ከፈጣሪያችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር እና ከቅዱሳኑ
ጋር ህብረት ይኖረናል። 6፡56 ፤ ዮሐ. 1ቆሮ 10 ፥ 17
- መንፈሳዊ ብርታትና ሃይልን እናገኛለን
- ምስጢር ይገለጻል፤ ጋብቻ ይጸናል

ሊቆርብ የሚገባው ማነው?

በክርስቶስ የባህርይ አምላክነት ያመነ፣ ሐይማኖታዊ ምስጢር የገባው፣ ንስሃ
የገባና የተሰጠውንም ቀኖና በሚገባ የፈጸመ ሰው እድሜና ጾታ ሳይለይ
ከምስጢረ ቁርባን መካፈል ይችላል፡፡

ከመቁረባችን በፊት ሊደረጉ የሚገባቸው ቅድመ ዝግጅቶች/ነገሮች:-

- ስጋዊ ንጽህና /ሰውነትን መታጠብ፣ ንጹህ ልብስ መልበስ፣ ነጠላ
ማጣፋት…/
- ከመቁረባችን ከሶስት ቀን በፊት ከግብረ ስጋ ግንኙነት መታቀብ/መከልከል
- አፋችንን እሬት እሬት እስኪለን ድረስ መጾም /ለአስራ ስምንት ሰዓታት/
የክርስቶስን መከራ፣ ሕማማተ መስቀል አሰብን የሚያሰኘንም ከበረከቱ
የሚያሳትፈንም ይህ ነውና/
- ንስሐ መግባት፣ እራስን ለካህን ማሳየት/ ማስመርመር፣ ቀኖና ተቀብሎ
በሚገባ መፈጸም ይገባናል፡፡ ንስሐ ሳይገባ በድፍረት መቀበል ግን እንደ በደል
ይሆንብናልና፡፡ 1ኛ ቆሮ. 11፡27
- በሚቆረብበት ቀን እንቅፋት/ መሰናክል ቢያጋጥመን ለምሳሌ. ነስር፣
እንቅፋት፣ ትውከት፣ ወደ አፍ የሚገባ ትንኝ፣ ዝንብ… ቢያጋጥመን፤ በዚያን ቀን
ሊቆረብ አይገባም፤
- ለወንዶች ዝንየት/ ህልመ ለሊት ፤ ለሴቶች የወር አበባ ከታየን በዚያን ቀን
ስጋ ወደሙን መቀበል ክልክል ነው፡፡

ከቆረብን በኋላ ሊደረጉ የማይደረጉ/ የተከለከሉ ነገሮች:-

- ልክ እንደቆረቡ አፍን በነጠላ/ጋቢ መያዝ ያስፈልጋል፤ ቀጥሎ የቅዳሴ ጸበል
መጠጣት (የቅዳሴ ጸበል አገልግሎት ስጋ ወደሙን ለተቀበሉ (ፍትሐ ነገሥት
አንቀጽ 13) እና ለድውያን/ለሕሙማን/ (ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 14) ፤ ሲሆን ስጋ
ወደሙን ለተቀበሉት ሰዎች የሚሰጠው ግልጋሎት የተቀበሉት ስጋና ደም
አፋቸውና በጥርሳቸው ላይ ቀርቶ ወደ ውጪ እንዳይነጥብ ለቃልቆ/
ተጉመጥሙጦ ለማውረድ ብቻ ነው፡፡ ይህም በቅዳሴ ጸበል ብቻ እንጂ በሌላ
ሊፈጽሙት አይገባም (ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 13፡52)
- አብዝቶ መብላት፣ መጠጣት፣ መብጣት፣ መነቀስ፣ ደም ቀድቶ ማውጣት
አይገባም፡፡
- ከቆረብን በኋላ ለሁለት ቀን ከግብረ ስጋ ግንኙነት መታቀብ/መከልከል/
መራቅ አለብን
- ከተቆረበ በኋላ በተለይም ከጥንቃቄ ጉድለት የተነሳ እንቅፋት/ መሰናክል/
እክል ቢያጋጥመን ለምሳሌ. ነስር፣ እንቅፋት፣ ትውከት፣ ወደ አፍ የሚገባ ትንኝ፣
ዝንብ… ቢያጋጥመን፤ ንስሃ ልንገባና ያጋጠሙንን እክሎች በሙሉ ለካህን/
ለንስሃ አባታችን/ ልንናገርይገባል፡፡የተሰጠንን ንስሃም ሳንፈጽም ዳግም መቁረብ አይፈቀድም/ አይገባም፡፡
- ሩቅ መንገድ መሔድ፣ መስገድ፣ አይገባም፡፡ ይህም ምስጢሩ፡- በስጋ ወደሙ
ድካም የለበትምና፡፡ አንድም በመንግስተ ሰማይ ከገቡ በኋላ ድካም የለምና
አንድም ድኀነት በስጋና በደሙ ሳይሆን በትሩፋት ነው እንዳያሰኝ ነው፡፡
- ተላምጠው የሚተፉ ነገሮች እንደ ማስቲካ፣ የሸንኮራ አገዳ፣ የተለያዩ
ፈራፍሬና አትክልቶች መብላት አይገባም፡፡
- ጥፍር መቁረጥ፣ ጸጉር መላጨት፣ ከልብስ መራቆት አይገባም፡፡ ምክንያቱም
መለኮት የተለየው ነው ያሰኛልና፡፡

“ሥጋዬን ካልበላችሁ ደሜንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም ሥጋዬን የበላ ደሜንም የጠጣ የዘለዓለም ሕይወት አለው "ዮሐ 6:54
👍1
ከነገ ሀምሌ ፲፬ ጀምሮ በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ምሕላና ጸሎት እንዲደረግ መመሪያ ተሰጥቷል።

“ኀቤከ እግዚኦ አንቃእዶነ አዕይንተነ ዘትነብር ውስተ ሰማይ።
ናሁ ከመ አዕይንተ አግብርት ውስተ እደ አጋእዝቲሆሙ።
ወከመ ዓይነ አመት ውስተ እደ እግዝእታ።
ከማሁ አዕይንቲነ ኀበ እግዚአብሔር አምላክነ።
እስከ አመ ይሣሃለነ።
በሰማይ የምትኖር ሆይ፥ ዓይኖቻችንን ወደ አንተ አነሣን እነሆ፥ የባሪያዎች ዓይኖች ወደ ጌታቸው እጅ እንደ ሆኑ፥ የባሪያይቱም ዓይን ወደ እመቤትዋ እጅ እንደ ሆነ፥ እንዲሁ እስኪምረን ድረስ ዓይናችን ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ነው።” (መዝሙር ፻፳፪/፻፳፫፥፩)

ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎ፣ የደቡብ ወሎና በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን (ከሚሴ) አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በወልድያ ከተማ ከሚገኙ የአድባራት አስተዳዳሪዎችና የሰበካ ጉባኤ አባላት ጋር ተወያይተው ከነገ ሐምሌ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት የሚገኙ ገዳማት፥ አድባራትና አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ምሕላና ጸሎት እንዲያድርጉ መመሪያ ሰጥተዋል፡፡

ምሕላና ጸሎቱ የታወጀው ሀገራችን ኢትዮጵያ በገጠማት ወቅታዊ ፈተና ምክንያት መሆኑን ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ አውስተዋል፡፡

ብፁዕነታቸው አክለውም የሚያጋድሉን ናቸው እንጂ ባዕዶቹ የምንገድል እኛው የምንሞተውም እኛው ነንና እግዚአብሔር ይህን የመጠላለፍ መንፈስ አስወግዶ የመተሳሰብ መንፈስን እስኪያሰፍንልንና ይቅር እስኪለን ድረስ ዘወትር ጠዋት 12፡00 (አስራ ሁለት ሰዓት) በየአብያተ ክርስቲያናቱ ካህናትና ምእመናን በመገኘት ወደ ፈጣሪ እንዲማጸኑ ብፁዕነታቸው አባታዊ መልዕክትና መመሪያ አስተላልፈዋል፡፡
ለአርበኞች መሞትን ያስተማራቸው
ታላቁ ጴጥሮስ ነው ባርኮ የሰጣቸው።

ጴጥሮሳዊነት ያሸንፋል።
የባንዶች መንፈስ አሸንፎ አያውቅም። የኢትዮጵያ ጠላቶችም አዲሶች አይደሉም ደጋግመው ሞክረው አፈር በልተዋል። የሰሜን ባንዶች አቡነ ጴጥሮስን ገረፉት። አላንበረከኩትም!! ሁሌም ማባበያ አለ አቡነ ጴጥሮስ ጋር ማባበያው አልሰራም!!!

ኢትዮጵያን ከጥፋት የሚታደገው ጴጥሮሳዊነት ነው። ስለ ሀገር መሞት ክብር ነው ሀገር ሻጭ ባንዳ ላይመለስ ይጠፋብ ጴጥሮሳዊነት ለክብር መሞት ነው ለሀገር መውደቅ ነው ለእውነት መስዕዋት መሆን ነው ጴጥሮሳዊነት አርበኝነት ነው።
ጴጥሮሳዊነት ይለምልም
መድኃኒዓለም ሆይ ፦በደረቅ ግንባር ዓይንን ይፈጥሩ ዘንድ በተቀደሰው የአፍህ ምራቅ ጭቃን ለለወሱ እጆችህ ሰላምታ ይገባል በጵርስፎራ በስጋ ወደሙ የምት ነገር ትምህርተ ኅቡአት ነኅ ስለ አንተ ነገስታት ክብራቸውን ያወርዳሉ ሠራዊቶቻቸውም ትጥቃቸውን ይፈታሉ ።

እግዚኦ ተዘከረነ በውስተ መንግስትከ!
2025/07/13 18:06:56
Back to Top
HTML Embed Code: