Telegram Web
☞እንዴት ዋሉ የኔታ!

ቸሩ መድኃኔዓለም ይመስገን የኔ ልጅ!

☞እባክዎን አባቴ (እንድድን፡ እንዳልጠፋም) የማደርገውን ይንገሩኝ፤ አሁን ለመስማት ዝግጁ ነኝ፡፡

አይ የኔ ልጅ! እስካሁን ስጮህ፡ ስጣራ ወዴት ኖረሃል? ሰዓቱ መሽቷልኮ! አይታይህም?

☞አባቴ ይቅር ይበሉኝ! የነገሩኝ ሁሉ እውነት አልመስልህ ቢለኝ ነበርኮ ጩኸትዎን ቸል ማለቴ!
አሁን ግን የትኛውንም ምክርዎን ለመስማት ዝግጁ ነኝ፤ ብቻ ይዘዙኝ።

ልጄ፦ ሁሉም የሚያምረው በጊዜውና በቦታው ነው። የጠዋቱ ምክር ለማታ አይሆንህም። በዚያውም ላይ ላንተም መሽቶብሃል፤ እኔንም ደክሞኛል።

☞እባክዎን ይቅር ይበሉኝ አባቴ? ከፈጣሪዎም ያስታርቁኝ።

አይ የኔ ልጅ! የኔን ተወው፤ ቂምም አልያዝኩብህ። እግዚአብሔር ግን የበቀል ሰይፉን መዝዞብሃል። ይልቅ የሥጋው ቢቀር በነፍስህ ተስፋ ብታገኝ በቀሩት ጥቂት ደቂቃዎች ለንስሃና ለፍቅር ተፋጠን! ሌላ የምልህም የለኝ!

☞የንታ እዘኑልኝ እባክዎን?

ይልቅስ አንተው ለነፍስህ እዘንላት!

☞ . . .
. . .
ዲን ዮርዳኖስ
🚫🚫 ትውስታ እያረፍችሁ አንብቡት 🚫🚫

የ2012 ዓም የበረኸኞቹ መልእክት
ትውስታ፣ ትዝታ፣ ማስታወሻ
~★★~
በበረኸኞቹ አባቶች አማካኝነት በ2013 ዓም ለህዝቡ ሁሉ እነግር ዘንድ የታዘዝኩትን መልእክት ለእናንተ ከመናገሬ በፊት ባለፈው ዓመት በወርሃ ህዳር የጻፍኩላችሁን ማስታወሻ ታነቡት ዘንድ ጋበዝኳችሁ።

• የዘንድሮው ደግሞ ጫን ያለ ነው። ይኸው ለመጻፍ እንኳ ጨንቆኛል። ከምር ምጥ ላይ ነኝ። ጽፌዋለሁ፣ አዘጋጅቼዋለሁም። ታነቡና ራሳችሁንም ታዘጋጁ ዘንድ ለእናንተም ማስተላለፌ የግድ ነው። ደግሞም አይቀርም። የዩቲዩብ አገልግሎት እረፍቴንም ጨርሻለሁ። እመጣለሁ። ነጭነጯንም እነግራችኋል። ነገ ወይ ተነገ ወዲያ ግን ቁርጥ ነው። ለማንኛውም እንደመግቢያ ይህቺን ያለፈች ማስታወሻ ተረጋግታችሁ፣ ደጋግማችሁ አንብቧት።
**
የበረኸኞቹን ትንቢት አስታውሱ !!
ልብ ብላችሁም አድምጡ
*★★★*
• ጦማሩ #BLOCK አለው። የተጻፈው ለተዋሕዶ ልጆች ብቻ ነው። ያስቀስፋችኋል፣ ወገብ ዛላችሁንም ያስቆርጣልና መልእክቱ የማይመለከታችሁ ኦጎኖቼ ከዚህ ጦማር ስር ምንም ዓይነት አስተያየት እንዳትሰጡ ይመከራል።

#ETHIOPIA | ~ እናንተም በጥሞናና በጥንቃቄ ተረጋግታችሁም አንብቡት። ሁሉ ሰው እንዲደርሰውም አድርጉ። በማኅበር፣ በግሩፖችም ላይ ልቀቁት። አንብባችሁ ብቻ ማለፍ ሳይሆን ተጠቀሙበት።
•••
ባለፈው ዓመት በወርሀ ነሐሴና እንደገናም በዘንድሮው ዓመት በወርሀ መስከረም መግቢያ ላይ በረኸኞቹ በትግራይ ኢሮብ የሚገኘው የአሲምባ መስቀለ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን እንደተመረቀ ደገኛው የ610 ዓመት የዕድሜ ባለፀጋው አባት አባ ዘወንጌል ይሰወራሉ፣ ከዚያ በኋላ በኢትዮጵያ እስከ 2015 ዓም ምህረት መግቢያ ድረስ የሚቆይ የኢትዮጵያ ፅኑ መከራ ይጀምራል ብለህ ለህዝብ ሁሉ ንገር ተብሎ የተነገረኝን የበረኸኞቹን ቃል አስቀድሜ ጽፌላችሁ እንደነበር ታስታውሳላችሁ።
•••
በረኸኞቹ እንደ ቃላቸውም የመስቀለ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ባለፈው ወር በወርሀ መስከረም ተመርቋል። ከቤተ ክርስቲያኑ ምረቃ በኋላም እንደተነገረውም ደገኛው አረጋዊ አባት አባ ዘድንግል ወደ አምላካቸው ተጠርተው ሄደዋል። አባ ዘወንጌል ባረፉ ማግስትም የኢትዮጵያ መከራ እንዳይበርድ ሆኖ በኦሮሚያ ተጀምሯል። የተዋሕዶ ልጆችና ጥቂት የሌላ እምነት ተከታዮች ላይ ዘግናኝ የእርድ ጭካኔ ተፈጽሞባቸዋል። በረኸኞቹ ከነገሩኝ ሁሉ አንዲቷም ሳትፈጸም የቀረች የለችም።
•••
እኔ ደግሞ ፈርዶብኝ አንዳንዴ ከበረኸኞቹ መልእክተኞች ጋር እሟገታለሁ። ለዚህ አገልግሎት ተመርጠሃልና ባሰኘህ ሰዓት ለህዝቡ መልእክቶቹን ልቀቅ ያሉኝን በመያዝ ይኸንኑ ፈቃድ በማግኘቴም መልእክቶቹን ከመልቀቅ እታቀባለሁ። ነገር ግን በግርድፉም ቢሆን መናገሬን አልተውኩም። መልእክቱ እኔ ያላየሁት፣ ለእኔም በግሌ ያልደረሰኝ መልእክት ስለሆነ ምንም እንኳ በረኸኞቹ የሚናገሩት እውነትና በቃላቸው ሐሰት የማይገኝባቸው እንደሆኑ ባምንም ደግሞ እኔም ሰው አይደለሁ እሳሳለሁ፣ እፈራለሁ፣ እንደሰውም እጠራጠራለሁ። በፈለከው ጊዜ ለህዝቡ ንገር የሚለውን ቃላቸውንም ይዤም ትንቢቱ የሚቀየር እየመሰለኝም በተሰፋ እቁነጠነጣለሁ። እጓጓለሁም። አሁን ሳየው ግን የተናገሩት ሁሉ ሳይፈጸም የሚቀር አይመስልም።
•••
እኔማ እላቸዋለሁ ይኸው በጎንደር እኮ ሱባኤ ተይዟል። በአክሱም ምህላ ተይዟል። በወልዲያ እየተጸለየ ነው። በመላዋ ኢትዮጵያ ሲኖዶሱ ጸሎተ ምህላ አዟል። እናም ህዝቡ እንዲህ በንስሐ ከተመለሰ የኢትዮጵያ መከራ ያበቃል፣ ወይም ደግሞ ቀኑ ያጥራል እላቸውና ከበረኸኞቹ መልእክተኞች ጋር ትንቢቱ የሚቀየር እየመሰለኝ እሟገታለሁ። እከራከራቸዋለሁ። እነሱም ይሉኛል አይ አንተው እሱን ተወው። ሰማይ ዝቅ፣ ምድር ከፍ ቢል የኢትዮጵያ ትንሣኤ እንዲሁ በብላሽ አይገኝም። በውድ ዋጋ ነው የኢትዮጵያ ትንሣኤ የሚመጣው። አዲስ ኢትዮጵያ ናት የምትፈጠረው። ይሄ አሮጌ ሁሉ ይወገዳል። ኢትዮጵያ ከትንሣኤዋ በፊት አጨዳው የግድ ነው፣ ያለልክ ቀና ቀና ስላልን አጨዳው የግድ ነው ብለው ይሞግቱኛል።
•••
ደግሞም ይሉኛል አንተው ሞኝ ነህ እንዴ ይሄ ሁሉ ነጭ ነጠላ ለብሶ እግዚኦ የሚለው ምእመን መች ንስሐ ገባና ነው? ህዝቡ ንስሐ ገብቷል ወይ? ፍርሃት ከቤቱ አውጥቶ የሰበሰበው እንጂ በእውነት ከልቡ ንስሐ ገብቶ፣ በደሉን አምኖ በፈጣሪው ፊት ተንበርክኮ የቆመ መሰለህ ወይ? ህዝቡ ይሄ የሚጸልየው በጎንደርም፣ በአክሱምም ሌሊት ተነስቶ እግዚኦ ሲል የምታየው ሥጋ ወደሙ ቅዱስ ቁርባንስ ይቀበላል ወይ? ከተጣላው ወንድም እህቱ፣ እናት አባቱ፣ ጎረቤት ጓደኛው፣ ዘመድ ወገኑ ጋር ታርቋል ወይ? ንገረን ታርቋል ወይ? ግፍ መሥራቱንስ አቁሟል ወይ? የበደለውን ክሶ፣ በግፍ የሰረቀውን፣ የቀማውን መልሷል ወይ? ቅዳሴ ሲያስቀድስ፣ ኪዳን ሲያደርስ አይተኸዋል ወይ? ተኝቶ አሸሼ ገዳሜ ሲልም አይደልወይ የሚያረፍደው። የስም ክርስቲያን እንጂ ክርስትናን በህይወት የሚኖርባት አለወይ? ቀበቶን የሚተካ ማዕተብ አንገቱ ላይ ከማንጠልጠል የዘለለ ምን የረባ የክርስትና ህይወት አለው። በዓለ ጥምቀትን ቲሸርት ለብሶ ሲዘምር የሚውለው ወጣት አስቀድሶ፣ ቆርቦ አይተኸው ታውቃለህ?
•••
ከጳጳሳቱ አንስቶ እስከ ዲያቆኑ ቤተ መቅደሱን አላቆሸሹትም ወይ? የወለደ ጳጳስ በፍርድ ቤት አጽሙ በወራሽ ልጁ ይመርመርልኝ እስከማለት አልተደረሰም ወይ? ወታደሮች ጳጳስ፣ ካድሬዎች ጳጳስ ሆነው መቅደሱን አላቆሸሹትም ወይ? የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች ውሎአቸውና አዳራቸው የት ነው? ንገረን እስቲ? የእግዚአብሔርን ገንዘብ ውስኪ መጠጫ፣ መዳረያ፣ የዝሙት መፈጸሚያ፣ መነገጃ፣ ህንፃና ቪላ መሥሪያ አላደረጉትም ወይ? በጧፍ፣ በንዋያተ ቅዱሳት እጦት ገዳማት አልተዘጉም ወይ? የቤተ መቅዱሱን አገልግሎት የሚመሩት ክህነት ያላቸው በሙሉ መቅደሱን አቆሽሸውታልና ጽዳቱ የግድ ነው። እናም ዘመዳችን አክሊለ ገብርኤል አጨዳው አይቀርም። የግድ ነው። የኢትዮጵያ ትንሣኤ እንዲሁ በብላሽ አይገኝም። የኢትዮጵያ ትንሣኤ በውድ ዋጋ ነው የሚመጣው።
•••
አሁን ዘመኑ ልክ እንደ ጌታ ዘመን ያለ ነው። መጀመሪያ በጭለማ ያለው ህዝብ የብርሃን ጭላንጭል ይታየዋል። የማይደርስበትን የብርሃን ጭላንጭል ያያል። ብርሃኑ ላይ ለመድረስ ግን ስንቅ መያዝ ያስፈልጋል። በባዶ ሆድ አይደረስበትም። ሥጋወደሙ የተቀበሉ፣ ንስሐ የገቡ ሰዎች ብቻ ጨለማውን ይሻገሩታል። ንጉሡ ከመምጣቱ በፊት አባጣ፣ ጎርባጣው የግድ መስተካከል አለበት። ተራራው ዝቅ ማለት አለበት። ጉድባው ጉድጓዱ መሙላት አለበት። በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር እስከ 2014 መጨረሻ ድረስ መከራው እንዲሁ ይቀጥላል። ዘመኑ የምንጣሮ ዘመን ነው። ከኢትዮጵያ መከራ ፍጻሜ በኋላ የመላዋ ዓለም መከራ ደግሞ ከዚያ በኋላ ይጀምራል።
•••
አሁን የሚቀረው የእርስ በእርስ ጦርነቱ ነው። ለእሱ ደግሞ መንግሥት በሰፊው እየሠራበት ነው። ያውም በሬድዮና በቴሌቭዥን ሳይቀር እየሠራበት ነው። መንግሥት ስም እንጂ የመንግሥትነት ቁመናው ካጠረ ቆየ። ለዚህ ነው ዜጎች ቀን በቀን የሚታረዱት። አለቃው ይበዛል። አዛዥ እንጂ ታዛዥ አይኖርም። ሁሉ አለቃ፣ ሁሉ አዛዥ ይሆናል። ፍትሕና ሕግ ስፍራቸውን ለቀው ይሰደዳሉ። ትርምስምሱ ይወጣል። የሚያዝ የሚጨበጠው ይጠፋል። ክስ አድማጭ አይኖረውም። ወታደር ግራ ይጋባል። ዜጎች አማራጭ ያጣሉ። የውስጥም የውጪም ጠላቶች መግቢያ ቀዳዳው ይሰፋላቸዋል።
1👍1
•••
በአራቱም አቅጣጫ ኢትዮጵያ ትወረራለች። ሰላም በማስከበር በሚል ሰበብም በ2 ሃያላን ሀገራት የሚመሩ ሰባት የሙስሊም ሀገራት በኢትዮጵያ ምድር ላይ እሳት ያዘንባሉ። በአሰብ ወደብ ላይ በልዩ ሁኔታ የተከማቸው የጦር መሣሪያ በኢትዮጵያ ምድር ላይ እንደበረዶ ይዘንባል። ብዙ ፍጅትም ይሆናል። ኦርቶዶክሳውያን በያሉበት፣ በየተገኙበት እንደከብት ይታረዳሉ። የኢትዮጵያ ምድር በደም ትጨቀያለች። የደም ጎርፍ፣ የደም አበላ በምድሪቱ ላይ ይፈሳል ነው የሚሉት በረኸኞቹ። [ በጦርነቱ የሬሳ ክምር የሚታይባቸው ሥፍራዎችም ተጠቅሰዋል ]
•••
የእርስ በርስ ጦርነቱን ተከትሎም ክፉ ረሃብ በኢትዮጵያ ይመጣል። የሚበላ የሚጠጣ ከምድሪቱ ይጠፋል። ከጦርነቱ የተረፈውን ህዝብ ረሃብ ይፈጀዋል። በስደት ምክንያት የዐቢይ ጾም የማይጾምበት ጊዜም ይመጣል። በረሃቡ ጊዜ ግን ጥቂቶችን የመትረፊያ ገዳማት ግን አሉ። ሰው የሚተርፍባቸው ገዳማትና አድባራት አሉ። ታቦተ ኢየሱስ ያለባቸው ገዳማትና አድባራት በሙሉ ሰው ይተርፍባቸዋል። በጊዜው እስከ አሁን ዝግ የሆኑ ዋሻዎች ይከፈታሉ። የሚተርፉ ኢትዮጵያውያንም በዚያ ይጠለላሉ። ከአሁኑ ጨውና የማይነቅዙ እህሎች ቢከማቹባቸው ብለውም ይመከራሉ። የአፋር መንገድ የወራሪው ኃይል መግቢያ መንገድ ስለሆነና ቀድሞ ስለሚዘጋም ከወዲሁ በየገዳማቱ ጨው ተገዝቶ ቢላክ ይመረጣልም ይላሉ በረኸኞቹ። የማይነቅዙ እህሎችና ጨው በየገዳማቱ ቢከማቹ መልካም ነውም ይላሉ።
•••
የዋልድባ ገዳም አባቶች በስፋት ሰማዕትነትን ይቀበላሉ። ታቦታቸውን ይዘው ጥቂቶች ቀደም ብሎ ወደተዘጋጀው የራስ ደጀን ተራራ ላይ ባለ ልዩ ዋሻ ይቆያሉ። አሁን ከምናውቃቸው ሰባት ያህሉ ገዳማት ሙሉ በሙሉ ይወድማሉ። ኋለኛ በሚመጣው ደገኛ ንጉሥ ዘመን ግን በወርቅ ጉልላት በአዲስ መልክ ይሠራሉ። ከአሁኑም ታቦታቱን በየመሰወሪያ ሥፍራቸው ያስቀመጡ ገዳማትም አሉ። አብያተ ክርስቲያናት እንደ ችቦ ይነዳሉ።
•••
አሁን ስማቸው በዝርዝር ቀድሞ የተያዙ በዳር ሀገር ያሉ ክርስቲያኖች በቅድሚያ እየተለዩ ይታረዳሉ። አሰቃቂ ሞትም ይሞታሉ። ሥራው የሚሠራው በመንግሥት ሰዎች ይሁንታ ነው። መልካም ስም ያላቸው። ጥሪት ሀብት ያላቸው። በማኅበረሰቡ ዘንድ የሚፈሩ፣ የሚከበሩና የሚወደዱ ክርስቲያኖች እየተለቀሙ ይገደላሉ። አሰቃቂ ሞትንም እንዲሞቱ ይደረጋሉ። በኦሮሚያ የተጀመረው በሁሉም ክልሎች ይቀጥላል። ብዙዎችም በሰማዕትነት ያርፋሉ።
•••
ከዚያ ከረሃብና ጦርነት ጋር ተያይዞ የሚመጣውና የታዘዘው ደግሞ በሽታ ነው። ክፉ በሽታ ይመጣል። ክፉ ወረርሽኝ ይከሰታል። ወረርሽኙ የ12 ሁለት ሰዓት ዕድሜ ብቻ የሚሰጥ ክፉ በሽታ ሲሆን ይኼም ጦርነቱንና ረሃቡን ተከትሎ ይመጣል። ለእሱም ምን ምን ቢዘጋጅ እንደሚተርፉበት በበረኸኞቹ በዝርዝር ተነግሯል። እሱንም ዝርዝሩን ከነ አዘገጃጀቱ እንዲሁ በሚቀጥለው አንዱን ቀን እነግራችኋለሁ።
•••
የአንበጣው መንጋ በመጪው ጊዜ ረሃብ ስለመከሰቱ ጠቋሚ ነው። ምን አልባትም ከደረስን በሚቀጥለው ጥር ወር ገበሬው በጎተራው የሚያስገባው እህል ላይኖረው ይችላል። ያ ደግሞ ጫና የሚያመጣው በከተሜው ህዝብ ላይ ነው። የገበሬ መራብ የሚጎዳው ከተሜውን ጭምር ነው። የፈለገ ገንዘብ በባንክ ቢጠራቀም ገንዘብ ብቻውን አያኖርም። ምግብ አይሆንም። የገበሬ መራብ ከተሜውን እቤትህ እንዳለህ ቋንጣ አድርጎ ሊያስቀርህ እንደሚችል ይህን እወቅ።
•••
ከአንበጣው ቀጥሎ አሁን ደግሞ ጽኑ ህማም የሚያመጡ፣ ልክ እንደ ቻይናው በርድ ፍሉ ዓይነት ገዳይ ህማም የሚያመጡ የወፍ መንጋ ግሪሳዎች ይከሰታሉ። አሁንም በአፋር በረሃ ውስጥ እየተራቡ መሆናቸው እየተሰማ ነው። የሀገር ውስጥ ስደት ተጀምሯል። የዋግ ህምራ ገበሬዎች ከብቶቻቸውን ይዘው እየተሰደዱ ነው የሚል ዜናም እየወጣ ነው። በወንጭፍ የማይሸሽ እህል የሚያወድም የግሪሳ ወፍ ደግሞ ሌላ ስጋት አምጥቷል። ፈጥሯልም። እናም መጪው ጊዜ ከባድ ነው።
•••
መፍትሄው ንስሐ መግባት፣ ሥጋወደሙ መቀበል። እናም የሚሆነውን ሁሉ ተዘጋጅቶ መጠበቅ ብቻ ነው። ለዚህ ነው በቀላል የሰፈር ሽማግሌ መብረድ የሚችል ፀብ ሀገር የሚያተራምሰው። ምክንያቱም ትንቢቱ የግድ መፈጸም ስላለበት ነው።
•••
አሁን በየትኛውም ዩኒቨርሲቲ የምትማሩ ኦርቶዶክሳውያን ተማሪዎች ብዙም ግራ አትጋቡ። በውድ ዋጋ የምትገለጠው የኢትዮጵያ ትንሣኤ ይገለጥ ዘንድ አቧራው፣ ትቢያው፣ ቆሻሻው ሁሉ ከላይዋ ላይ መወገድ አለበት። ምዕራባውያኑም አረቦቹም፣ ሩቅ ምሥራቃውያኑም አዲሲቷ ኢትዮጵያ እንደምትገለጥ ያምናሉ። ዋካንዳ፣ ጃካራንዳ እያሉ በገደምዳሜው በፊልምም በመጽሐፍም የሚነግሩን ምስጢሩ ስለገባቸው ነው። እስራኤልም ታቦተ ጽዮንን አሁን የምትፈልግበት ዘመን ላይ ደርሳለች። ለዚሁ ሲባል ታቦት የማያከብር፣ ቤተ ክርስቲያን የሚያቃጥል ትውልድ እንደ አሸን በኢንኪዩቤተር እንዲፈለፈል አድርገዋል። የራሱን አናንቆ ታቦት አያስፈልገንም የሚል ትውልድ ፈልፍለዋል።
•••
ምዕራባውያኑ ይሄ ሁሉ ግፍ እየተፈጸመ ፀጥ፣ ዝም፣ ጭጭ ያሉት ወደው እንዳይመስልህ። የሁለቱ መንፈስ ትግል ላይ ስለሆኑ ነው። የምስጢራዊቷ ኢትዮጵያ፣ የመንፈሳዊቷ ኢትዮጵያ መንፈስና የአውሬው መንፈስ ትግል ላይ ናቸው። በየገዳማቱ በላያቸው ላይ ሳር እስኪበቅልባቸው ድረስ በጸሎት የተጉ፣ ከመንፈሱ ጋር ጉረሮለጉረሮ እየተናነቁ የመጨረሻ ጦርነት ላይ ያሉ አባቶችም አሉ። እንዲያውም ምዕራባውያኑ ከሩዋንዳ የከፋ የእልቂት ዜና ለመስማት ቢቋምጡም አጋንንቱ በጸሎት እየታሰረ፣ ወዲያ ወዲህ ከማለት በቀር እስከአሁን የከፋ ጉዳት ባለመታየቱም ይደነቃሉ። የእልቂቱ ብቅ ጥልቅ፣ ብልጭ ድርግም ማለትም ይደንቃቸዋል። አሁን ግን የግድ ነው። አጨዳው ይመጣል። የኢትዮጵያ ትንሣኤም ከዚያ በኋላ ይሆናል።
•••
ከሚተርፉትና የአዲሲቷን ኢትዮጵያ ትንሣኤ ከሚያዩት ከጥቂቶቹ ይደምረን። ይቁጠረንም። አሜን !! ጌታሆይ ቶሎ ና !!
•••

#ማስታወሻ | ~ ነገ ንስሐህን የሚቀበል ካህንም ላታገኝ ትችላለህና ይሄን መልእክት የማንበብ ዕድል የገጠማችሁ ወገኖች በሙሉ ጨርቄን፣ ማቄን፣ ሳንል፣ ወገቤን ደረቴን ሳትል፣ ምክንያት ሳትደረድር፣ ዕለቱኑ ዛሬውኑ ንስሐ እንግባ። ተናግሬያለሁ።

• ሰማይ ስሚ ፥ ምድርም አድምጪ፥ ቤተ ክርስትያንም መስክሪ። አበቃ። ውርድ ከራሴ

ሻሎም ! ሰላም
ዘመድኩን በቀለ
ለእግዚአብሔር ለአገልግሎት እንደ ማርጀት ምን ፅድቅ አለ ጉልበቴ ለሰንበት ት/ቤቴ
"ንኢ ኅቤየ ኦ ድንግል ምስለ ወልድኪ ፍቁርኪ ኢየሱስ ክርስቶስ ከመ ትባርኪ ላዕሌነ።"

                           መጽሐፈ ሰዓታት

እመቤቴ ማርያም ሆይ እንቺን በሙሉ ልብና በሙሉ እምነት ነይ የማለት አቅም ማነንቴ ውስጥ አለ ለማለት አልደፍርም። ግን መጥተሽ የልቤን ትርምስምስ ጓዳ ታሰናጅው ዘንድ ናፍቄያለውና እመቤቴ ሆይ ወደኔ ነይ እልሻለሁ፤ ብትመጪም አንኳን ምንም አንቺን ከልጅሽ ጋር ለማስተናገድ የሚችል ልብ ባይኖረኝም ግን ነይ የማለት ጩኸቴን አላቆምም፤ ከካህናቱ ጋር ያለመታከት እመቤቴ ሆይ ነይልኝ እልሻለሁ፤ ሁሌም እምነት በጎደለውና በአፉ እየተናገረ በልቡ የማያምነው ማንነቴ ውሸታም መሆኑን ባውቅም ግን ከጥሪዬና ከእሮሮዬ ብዛት አይተሽ አንድ ቀን በሙሉ እምነት ነይልኝ እንደምታስብይኝ ስለማውቅ አልታክትም፤ ነይ እመቤቴ እልሻለሁ፤ ስለዚህ እንዳትቀሪብኝ መጥተሽ በትእቢትና በራስ ወዳድነት የደከመችውን ነፍሴን በፍቅርና በትህትና እረፍት ስጭልኝ፤ እመቤቴ ሆይ እባክሽ ለነፍሴ እረፍት ትሰጭልኝ ዘንድ ነይ....

"ድንግል ሆይ እኛን ትባርኪ ዘንድ ከልጅሽ ከወዳጅሽ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ወደኔ ነይ።"
እንኳን አደረሳችሁ ቤተሰቦቻችን !
ማቴዎስ 6
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁵ ስለዚህ እላችኋለሁ፥ ስለ ነፍሳችሁ በምትበሉትና በምትጠጡት፥ ወይም ስለ ሰውነታችሁ በምትለብሱት አትጨነቁ፤ ነፍስ ከመብል ሰውነትም ከልብስ አይበልጥምን?
²⁶ ወደ ሰማይ ወፎች ተመልከቱ፤ አይዘሩም አያጭዱምም በጎተራም አይከቱም፥ የሰማዩ አባታችሁም ይመግባቸዋል፤ እናንተ ከእነርሱ እጅግ አትበልጡምን?
²⁷ ከእናንተ ተጨንቆ በቁመቱ ላይ አንድ ክንድ መጨመር የሚችል ማን ነው?
²⁸ ስለ ልብስስ ስለ ምን ትጨነቃላችሁ? የሜዳ አበቦች እንዴት እንዲያድጉ ልብ አድርጋችሁ ተመልከቱ፤
²⁹ አይደክሙም አይፈትሉምም፤ ነገር ግን እላችኋለሁ፥ ሰሎሞንስ እንኳ በክብሩ ሁሉ ከነዚህ እንደ አንዱ አልለበሰም።
³⁰ እግዚአብሔር ግን ዛሬ ያለውን ነገም ወደ እቶን የሚጣለውን የሜዳን ሣር እንዲህ የሚያለብሰው ከሆነ፥ እናንተ እምነት የጎደላችሁ፥ እናንተንማ ይልቁን እንዴት?
³¹ እንግዲህ፦ ምን እንበላለን? ምንስ እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን? ብላችሁ አትጨነቁ፤
³² ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ፤ ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና።
³³ ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል።
³⁴ ነገ ለራሱ ይጨነቃልና ለነገ አትጨነቁ፤ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል።
ሙሉ ቤተሰብ ተመልሶ በከመ ፈቀደ ይገብር ወበከመ ሐለየ ይፌጽም አልቦ ዘይክል ተዋስኦቶ ወአልቦ ዘይብሎ ምንተ ገበርከ ዘንተ አሕሰምከ ወዘንተ አሰነይከ ("እንደ ወደደው ያደርጋል እንዳሰበው ይጨርሳል ሊመልስለት የሚቻለው የለም…ምን አድርገሀል? ይህን አጥፍተሀል ፣ይህን አሳምረሃል የሚለው የለም)
በዘመኔ ይህን ተዓምር ያሳየኸኝ የኔን የምስጊኑን ጸሎትም ያልናቅህ ጌታዬ መድኃኒቴ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ በውኑ ላደረክልኝ ነገር ምን እከፍልሀለሁ፤
ፍልሰታሽን ትጉህ ከሆኑ አባቶቼና ወንድሞቼ ጎን ቆሜ ንዒ እያልኩ የተማጸንኩሽ እመቤቴ
በኮልታፋ አንደበቴ ስምህን የምጠራው አባቴ ቅዱስ ማርቆስ ሆይ
በውኑ እውነት ሆነ፤ልመን እኔም እንደሰዎቹ ለመመስከር በቃሁ


ከህጻኑ በስተቀኝ የምትገኘዋ እህቴ/የአገልግሎት ጓደኛዬ/ ጎበዝ ደራሲ እንደደረሰው ድርሰት ብትነበብ የማትሰለች ልጅ ናት እኔ ሰሙ እላታለሁ ሙሉ ስሟ ሰሚራ ሚፍታህ ነው፡፡
ሰሙን በጣም ልቀርባት ሞከርኩ እናም ከጊዜያት በኋላ ጠለቅ ብለን ስናወራ ከእስልምና እንደተመለሰች (ታሪኩ ረጅም ስለሆነ ይጠር ብዬ ነው) እና ገና የሚቀሩ እህት ወንድሟ እንዳሉ አወራችኝ፤ ያላትን ትጋት ልገልጸው አልችልም በማ/ቅዱሳን አ/አበባ ማዕከል መዝሙር ክፍል እና ልደታ ወረዳ ማዕከል ላይ አብረን ስናገለግል ሁሌም ስንገኛኝ የምታወራኝ ቤተሰቦቼ በሙሉ ወደ ቀናችው ሃይማኖት ሳይመለሱ ልጅነት ሳያገኙ አላርፍም ትለኝ ነበር ለንስሀ አባቷ ሳይቀር ቤት እየመጡ ኮርስ እንዲያስተምሯቸው እያደረገች፤ብቻ ያልጣረችው፤ያልገባችበት ጉድጓድ የለም፡፡
እኔ በምንም ላግዛት ባለመቻሌ ሁሌም እበሳጫለሁ ብቻ ግን በስመ ክርስትናዋ እርዳት እያልኩ እማጸን ነበር፡፡ አምና በፍለሰታ ጾም ላይ አሁን ዲያቆን የሆነው ወንድሟ እና 2ቱ እህቶቿ ነኢማ እና ሙኒራ ሚፍታህ አምነው ተጠምቀው አስፈላጊውን ትምህርትም ወስደው በዚህ ዓመት በነበሩ አገልግሎቶች ላይ አብረውን በዝማሬ ሲያገለግሉ ሰነበቱ፡፡

በዚህኛው ፍልሰታ ታዲያ ማርቆስ መጥቼ በቆምኩኝ ቁጥር፤ምስካዬ ኅዙናን በማስቀድስ ቁጥር 2 ነገሮች ሁሌ በሀሳቤ እየመጡ ይረብሹኛል 1ኛው በቅርቡ ሁላችንም ሳንጠብቀው አብሮን ሲያገለግል ቆይጦ ሳይታሰብ በሞት ከመሐላችን የተለየው ወንድሜ መኮንን /ሞኬ/ ን ሳስብ እየዘመርኩ/ቆሜም እያስጠናሁ እሱ ፊቴ እየመጣ እስከሚታወቀኝ ድረስ እለዋወጥ ነበር፤ ከዚህ ስሜት ለመውጣት ብርታቱን ስጠኝ እያልኩ ፤
2ኛው እህቴ ሰሚራን ትጋቷን አስብና አምላኬ ሆይ ምናለ የዚችን ልች ብርታት ለኔ ብታድለኝ ፤ ደግሞም የቀሩት እናትና አባቷ የሥላሴን ልጅነት ቢያገኙ እያልኩ እጸለይ ነበር
በተለይ የደብረታቦር ቀን ከማርቆስ በስተጀርባ ባለው የወንዶች መግቢያ ተደፍቼ ይህንኑ ብዬ ወደ አገልግሎት ወጣሁ አምለከ ማርቆስ የሰሙንም የኔን የምስጊኑን ልመናዬን ሰምቶ የሰሙ እናትና አባቷም ሙሉ ቤተሰቡ እንደምታዩት አምረው ደምቀው እናትና አባታቸውን አስቆርበው ልጅነት አግኝተዋል፡፡ ዛሬ ደስታ እምባ አሶጥቶ በስራ ቦታዬ አስነብቶኛል ፡፡
.

ክፍል አንድ
*********
#የፓስተሩና_የቄሱ_ወግ

ፓስተር... ኦርቶዶክሶች ማርያም አረገች የሚሉትን ተረት ሰምተሃል? አለው ለቄሱ

ቄሱ... "አዎ"
ፓስተር...."ይገርማል ግን እኮ ማርያም አላረገችም"

ቄሱ.... አለማረጓን እንደት አወቅህ?
.
ፓስተር....."መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ማርያም አርጋለች" ስለማይል ነዋ።

ቄሱ...ትክክል ነህ ኦርቶዶክሶቹ ተሳስተዋል። ምክንያቱም ማርያም እንኳን ወደ ሰማይ ልታርግ ጭራሹንም እኮ አልሞተችም።

ፓስተር••• በኢየሱስ ስም!...ያምሃል እንዴ?እንደት አልሞተችም ትላለህ? መሞትማ ሙታለች።

ቄሱ... እሺ ከሞተች ከመጽሐፍ ቅዱስ "ማርያም ሙታለች" የሚል አሳየኝ?

ፓስተር.... መጽሐፍ ቅዱስ ላይስ የለም።

ቄሱ እና መሞቷን በምን አረጋገጥክ?

ፓስተር •••"ሞታለችማ እሚለን ተአምረ ማርያም ነው" ብሎ እርፍ 😂😂😂

ቄሱ..ክክክ😂 አይ ፓስተር መሞቷን ከተአምረ ማርያም አንብበህ ስታምን ስለ እርገቷ የሚናገረውን ግን ማመን ለምን አቃተህ? ልጄ!

ፓስተር----ዝምምምምምምምምምምምምምምም!
===============================
ቆይ ግን እነዚህ ሰዎች አዋልድ መጻሕፍትን እኛ ስንጠቅስ ተረት ተረት..... እነርሱ ሲጠቅሱ ደግሞ እውነት የሚሆነው በየትኛው ሕግ ነው???

እና ተሐድሶ ፕሮቴስታንቶች ሁሉ ጌታን እንዲቀበሉ እጸልያለሁ።
👍1
2025/07/13 11:12:46
Back to Top
HTML Embed Code: