ሀገርን በሆድ ለሚለውጡ የእነዚህ ብላቴኖች ንግግር ምን ይዋብ ምንስ ረቂቅ ንግግር ይሆን!!
እንሸኝሀለን!!!
ቤተክርስቲያንን እንዳተነፍስ ሰቅዘህ የያዝካት የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ አቡነ ዮሴፍ ሆይ፣ መኳንንቱን ተማምነህ የደለብክባት እናት ቤተክርስቲያን የ80 ሚሊዮን ምዕመኖቿን ለቅሶ አፍነህ ይዘህ እግዚአብሔር ዋጋህን ባይሰጥህ እንኳ እመነኝ እኛ ዋጋህን እዛው እንዲሰጥህ ወደ ፈራጁ እንሸኝሀለን! ፓትርያርኩ የፈረሙበት ከንቲባዋ አርብ እንድትመጣ የተላከላት ደብዳቤ «አልሰማሁም፣ አልተጠራሁም» ብላ እንድትቀር በለመደው ሴራ በማመቻቸት እስከዚች ሰዓት እንዳይወጣ፣ እንዳይላክ ይህ ሰው አግዶ አፍኖ ይዞታል! ትግሉ ውስጣዊም መሆኑ ደግሞ መራር ያደርገዋል!

#በጸሎት_ጊዜ_ምን_እናድርግ?
#በጸሎት_ጊዜ_ምን_እያልን_እንጸልይ?
👉ዓምድ ሳይደገፉ መቋሚያ ሳይዙ በሁለት እግር ቀጥ ብሎ መቆም። (መዝ. 5:3)
👉ወገብን መታጠቅ ልብስን ዝቅ አድርጎ ማደግደግ ነው። (ሉቃ. 12:35 ፍት. መን አንቀጽ 14)
👉በጸሎት ጊዜ ፊትን ወደ ምስራቅ መልሶ መቆም ወዲያና ወዲህ ወደ ግራና ወደ ቀኝ ወደ ሌላም አለማለት በሰፊሐ እድ በሰቂለ ሕሊና ሁኖ መጸለይ ይገባል። (መዝ. 133:2፤ ዮሐ. 11:41)
👉ጸሎት ሲጀመርና ሲፈጸም አመልካች ጣትን ከሌሎች ጣቶች ጋር አመሳቅሎ በትእምርተ መስቀል አምሳል በጣት ማማተብ ነው። በዚህም የመድኃኔዓለምን መከራውን ማሰብ።
🙏የሚጸልይ ሰው በትህትናና በጸጥታ ሁኖ ለሌላ ሰው እንዳይሰማ ለራሱ ጆሮ ብቻ እንዲሰማ አድርጎ ኃጢአቱን እያሰበ መጸለይ ይገባዋል። ይህም የሚያደርገው ስለ አለፈው ኃጢአቱና በደሉ ነው። (1ኛ ሳሙ. 1:3)
🙏የሚጸልይ ሰው በጥቡዕ ልብ በጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር ይነጋገራል። አሳቡን በእግዚአብሔር ላይ ይጥላል። የዓለምን አሳብ ሁሉ ይተዋል።
🙏የሚጸልይ ሰው ሲያማትብ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አዐትብ ገጽየ ወኵለንታየ በትእምርተ መስቀል" እያለ ነው። ሁለተኛም "እግዚኦ መሐረነ እግዚኦ መሐከነ እግዚኦ ተሣሃለነ ወባርከነ አሜን" እያለ ያማትባል። ሦስተኛም "ስብሐት ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለም ዓለም አሜን እግዚኦ ረስየነ ድልዋነ ከመንበል በአኮቴት አቡነ ዘበሰማያት" የሚለውን ጸሎት 3 ጊዜ እየደገመና እየሰገደ በማማተብ በጸሎት መጀመርያና መጨረሻ ጊዜ ማድረግ አለበት። #እንዲሁም_መስቀልን_ከሚያነሳ_ቃል_ሲደርስ_ማማተብ_ስግደትንም_ከሚያነሳ_ቃል_ሲደርስ_መስገድ_ይገባዋል።
#የጸሎቱ_ቅደም_ተከተል_መጀመርያ_አቡነ_ዘበሰማያት_ሁለተኛ_መዝሙረ_ዳዊት_ውዳሴ_ማርያምና_ሌሎችም_ቀጥሎ_አቡነ_ዘበሰማያት_ጸሎተ_እግዚእትነ_ማርያም_ጸሎተ_ሃይማኖት_በመጨረሻም_አቡነ_ዘበሰማያት_ኬርያላይሶን_41_ጊዜ ይባላል።
-ሲጸልይ ማዘን ማልቀስ ይገባዋል። ሲያለቅስም በደሉንና ኃጢአቱን እያሰበ ለያንዳንዱ በደል ዕንባን ማፍሰስ ነው።
-የሚጸልይ ሰው በጸሎት ላይ አቋርጦ ከማንም ሰው ጋር ፈጽሞ መነጋገር የለበትም። ጸሎቱን ለማቋረጥ ችግር ቢገጥመው ግን በአቡነ ዘበሰማያት አሥሮ ንግግሩን ሲፈጽም ከአቋረጠበት ተነስቶ ጸሎቱን ሊጸልይ ይገባል። (የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ስርዓተ አምልኮና የውጪ ግንኙነት ገጽ 81፤ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ገጽ. 28-29: ሊቀ ካሕናት ክንፈ ገብርኤል አልታየ)
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
🍀🍀💐🍀💐🍀🍀💐🍀💐🍀🍀

በዮናስ ይውህና የእግዚአብሔር ፍቅር ምህረት ሲገለጽ
የነነዌ ሰዎች በኃጢአታቸው እንዳይጠፉ እግዚአብሔር
ከብዙ ምሁራን አዋቂዎች መካከል የመረጠው የዋሁ ዮናስ ነው ዮናስ የተመረጠበት አዋቂ ጥበበኛ ስለሆነ አይደለም በየዋህነቱ ነው
ዮናስ በየዋህነቱ የነነዌ የንስሐ አባት እንዲሆን በእግዚአብሔር ተመርጠዋል
እግዚአብሔር ለቅድስና ለሰማያዊ አገልግሎት ሰዎችን ሲመርጥ መስፈርት አለው መስፈርቶቹ የዋህነት ቅንነት መልካምነት ቸርነት በጎነት ርህሩህነት ወዘተ ናቸው
ከእያንዳንዳችን እግዚአብሔር የሚጠይቀው መስፈርቶች
እነዚህን ነው
እንዲያውም ሐዋርያው እንዲህ ብሎ ይዘረዝራቸዋል
ገላትያ 5 (22፤ የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው።ይልና የሚቀጥለውን ስታነቡት
እነዚህ መስፈርቶች በህይወታቸው የያዙ ሰዎች ስጋን እስከ ክፉ ምኞቱ ሰቀሉት ይላል እንዴት ደስ ይላል
በእግዚአብሔር ለመመረጥ ቅኔ አቋቋም ድጓ ትርጓሜ የነገረ መለኮት ተመራማሪ ወይም ዶክተር ፕሮፌሰር ወዘተ መሆን አያስፈልግም የሚያስፈልገው አንድ ዮናስን መሆን ነው
የነነዌ የንስሐ አባት ዮናስ ብዙ ውጣውረድ አልፎ ነነዌ ከደረሰ በኋላ አገልግሎቱን ጀመረ እናንተ የነነዌ ሰዎች እስከ ሶስት ቀን ንስሐ ባትገቡ ከሰማይ እሳት ወርዶ ያቃጥላችኋል አላቸው
የነነዌ ሰዎች ጆሮአቸውን ለንስሐ አባታቸው ሰጥተው መልክቱን በደንብ ከዳማጡ በኋላ ነገ ከነገ በኋላ ይደርሳል አላሉም ሳይውሉ ሳያድሩ ወዲያውኑ ንስሐ ገብተው አድረዋል ለእነሱ የታዘዘው እሳት በሶስተኛው ቀን ታይቶ ተመልሷል እግዚአብሔር በእያንዳንዳችን ህይወት ውስጥ የሚነደውን የኀጢአት እሳት በቸርነቱ ይመልስልን
ለእሳቱ መጥፋት ምክንያት የዮናስ ትምህርት ፍሬ አፍርቶ የነነዌ ሰዎች ንስሐ በመግባታቸው እና እግዚአብሔር ተወካፌ ንስሐ መሆኑን ለመግለጽ ነው
ይህ የንስሐ ውጤቱ ነው ንስሐ ምን ያደርጋል ተብላችሁ ስትጠየቁ ከእሳት ያድናል ብላችሁ ትመልሳላችሁ
የተወደዳችሁ ክርስቲያኖች እዝነ ልቡናችንን ለዮናስ ንስሐ አባታችን በመስጠት የእግዚአብሔርን መልክት ልንሰማ ይገባል
አንዳንድ ሞኞች ንስሐ አባት እንደግለሰብ አይተው ገለል ብለው ያልፋሉ ወገኖቼ ንስሐ አባት ይማርም አይማርም ንስሐ አባት ዮናስ ነው የሚያስተላልፈው የእግዚአብሔርን መልክት ነው ያለ ንስሐ አባት እግዚአብሔርን ማግኘት አይቻልም ንስሐ አባት መገናኛ መስመር ነው።

አንድ ላይ ለተሰራ ኃጢአት በሀገር ደረጃ አንድ ላይ የተገባ አስደናቂ ንስሐና እግዚአብሔርም የተቀበለው ጾምና ጸሎት–ጾመ ሰብአ ነነዌ
ጾመ ሰብአ ነነዌ (የነነዌ ሰዎች ጾም)የተባለችውን የሦስት ቀን ጾም የጾሙት በነነዌ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ናቸው፡፡ ነነዌ (Nineveh ) በጤግሮስ ወንዝ ዳርቻ የምትገኝ ስትኾን መሥራቿም ናምሩድ ነው (ዘፍ.፲፥፲፩-፲፪)፡፡ ጥንታዊቷ የነነዌ ከተማ ለአሦር መነሻ የሆነች፤ እጅግ ሰፊና ያማረች፤ የቅጥሯ ርዝመትም ፲፪ ኪሎ ሜትር የሚሸፈን ነበር፡፡ በከተማዋ ንጉሡ ሰናክሬም ብዙ ሕንጻዎችን ገንብቶ ነበር (ዮናስ ፬፥፲፩)፡፡
ነነዌ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ታሪካቸው በስፋት ከተጻፈላቸው የሜሶፖታምያ ከተሞች አንዷ ናት፡፡ ብዙ የሥነ መለኲት ምሁራን ከዛሬዋ የሞሱል ከተማ በተቃራኒ ከባግዳድ ሰሜን ምዕራብ 350 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ እንደ ነበረች ይስማማሉ፡፡ ምንም እንኳን በ4000 ቅ.ል.ክ. ገደማ በናምሩድ በኩል ብትቆረቆርም /ዘፍ.10፡11-12/ የአሦራውያን ዋና ከተማ የሆነችው ግን በ1400 ቅ.ል.ክ. ነው /2ነገ.19፡36/፡፡ በከተማዋ በጣም ታዋቂ የነበረው የጣዖት ቤተ መቅደስ የአስታሮት ቤተ መቅደስ ይባላል፡፡
በዚያ ዘመን የነበሩ የነነዌ ሰዎች ኃጢአታቸው በዝቶ እግዚአብሔር ሊያጠፋቸው ሲል ዮናስ የስሙ ትርጓሜ ‹ርግብ› የሆነ በዳግማዊ ኢዮርብዓም ዘመነ መንግሥት የነበረ ነቢይን ቸርነትና ምሕረቱ የማያልቅበት እግዚአብሔር መክሮ፣ ዘክሮ እንዲመልሳቸውና ንስሐ እንዲገቡ ነቢዩ ዮናስን ወደ ነነዌ ሕዝብ ላከው (ሉቃ.፲፩፥፴)፡፡ ይህ ነቢይ መኖሪያው በገሊላ በጋትሔፌር ድንበር ከተማ ነበረ፤ አባቱም አማቴ ይባላል፡፡ በዚያን ጊዜ ኢዮርብዓም ሶርያውያንን አባሮ የእስራኤልን ድንበር እንዲመልስ ነቢዩ ዮናስ ትንቢትን ተናገረ (፪ኛነገ.፲፬፥፳፭፤ ዮናስ ፩፥፩)፡፡ ነቢዩ ኤልያስ ያስነሣው የሰራጵታዋ መበለት ሕፃን ነቢዩ ዮናስ እንደ ሆነ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ያስረዳል (፩ኛነገ.፲፯፥፲፱)፡፡ መድኃኒታችን ክርስቶስም የዮናስን ከዓሣ ሆድ መውጣት የራሱ ትንሣኤ ምሳሌ አድርጎ ነግሮናል (ማቴ.፲፪፥፲፱-፵፪፤ ሉቃ.፲፩፥፴-፴፪)፡፡
እግዚአብሔር አምላክም ‹‹ሔደህ በነነዌ ላይ ስበክ›› ባለው ጊዜ ነቢዩ ዮናስ ‹‹አንተ መሐሪ ነህ፤ ልትጠፉ ነው ብዬ ተናግሬ ብትምራቸው ሐሰተኛ ነቢይ እባላለሁ›› ብሎ ላለመታዘዝ እስራኤልን ለቆ በመርከብ ወደ ተርሴስ ሸሸ፡፡ እግዚአብሔርም ታላቅ ነፋስን አስነሥቶ መርከቧ በማዕበል እንድትመታ አደረገ፡፡ ከዮናስ ጋር በመርከቧ ተሳፍረው የነበሩ ነጋድያንም ያላቸውን ሀብት ወደ ባሕሩ መጣል ሲጀምሩ ነቢዩ ዮናስ ጥፋቱን ተገንዝቦ ‹‹ማዕበሉ በእኔ ምክንያት የመጣ ስለሆነ ንብረታችሁን ሳይሆን እኔን ወደ ባሕር ጣሉኝ›› ብሎ ተማጸናቸው፡፡ እነርሱም ‹‹ስለዚህ ሰው ነፍስ እንዳንጠፋ፣ ንጹሕም ደም በእኛ ላይ እንዳይደረግብን አይሆንም›› አሉ፡፡ ወደ ባሕሩ ለመጣል ዕጣ በተጣጣሉ ጊዜም ዕጣው በዮናስ ላይ ስለ ወጣ ነጋድያኑ ዮናስን ወደ ባሕሩ ጣሉት፡፡ ወዲያውኑ ከእግዚአብሔር ዘንድ የታዘዘ ታላቅ ዓሣ አንበሪ ዮናስን በአፉ ተቀብሎ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት አሳድሮ ወደ ነነዌ አደረሰው፡፡ እግዚአብሔር የቅል ተክልን ምሳሌ በማድረግ ቅጠሉ በመድረቁ ዮናስ ባዘነ ጊዜ ‹‹አንተ ላልደከምክበት እና በአንድ ቀን በቅሎ ላደገ ቅል ስታዝን እነሆ በታላቂቱ ነነዌ ከተማ ያሉ ከአንድ መቶ ሃያ ሺሕ በላይ ሕዝብና እንስሳቱ የእጄ ፍጥረቶች ስለ ሆኑ ያሳዝኑኛል›› በማለት ነቢዩ ዮናስም ውሸታም ላለመባል መኮብለሉ ስሕተት መሆኑን አስረድቶታል፡፡
ዮናስም ነነዌ መሬት ላይ መድረሱን ባወቀ ጊዜ ከእግዚአብሔር መሸሽ አለመቻሉን ተረዳ፤ የነነዌ ሰዎችንም ‹‹ንስሐ ግቡ›› እያለ መስበክ ጀመረ፡፡ የነነዌ ሰዎችም ንስሐ በገቡ ጊዜ እግዚአብሔር ይቅር ብሎ ከጥፋት አድኗቸዋል፡፡ ሐሰት እንዳይባልም እሳቱ እንደ ደመና ሆኖ ከላይ ታይቶአል፡፡ የታላላቁ ዛፍ ቅጠል እስኪጠወልግ ድረስ አድርቆ ለሕዝቡ አሳይቷቸዋል፡፡ ንስሐቸው በከንቱ እንዳልቀረ አስረድቷቸዋል (ትንቢተ ዮናስ)፡፡ ታኅሣሥ ፭ ቀን የሚነበበው የመጽሐፈ ስንክሳር ክፍል ‹‹ወበልዐ አሐደ ኀምለ›› በማለት ንስሐ ያልገቡ አንድ አገር ያህል ሰዎች በእሳቱ እንደ ጠፉ ይነግረናል፡፡
ጾመ ነነዌ የሦስት ቀን ሱባኤ ነው፤ በሦስት ቀናት ጾምና ጸሎት ንስሐ የገቡ የነነዌ ሰዎች ከጥፋት እንደ ዳኑ ሁሉ፣ በብሉይ ኪዳን አስቴር ሦስት ቀን ጾማ፣ ጸልያ በእስራኤል ላይ የመጣውን መቅሠፍት እንዲመለስ አድርጋለች (አስ.፬፥፲፭-፲፮)፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ከበዓል ስትመለስ ሕፃኑ ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ መንገድ ላይ ጠፍቶአት ከሦስት ቀን ፍለጋ በኋላ በቤተ መቅደስ አግኝታዋለች (ሉቃ.፪፥፵፮)፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ለሄሮድስ በሰጠው ምላሽ መልስ ሦስት ቀን የሱባኤ ፍጻሜ መሆኑን ገልጿል (ሉቃ.፲፫፥፴፪)፡፡
ጾመ ነነዌ የእግዚአብሔርን ቸርነትና መሐሪነት የምናስታውስበት ጾም ነው፡፡ ይኸውም እኛ ፍጡራኑ በበደልን ጊዜ ፈጽሞ ከማጥፋት ይልቅ ምክንያት ፈልጎ እንድንድን ያደርገናል፡፡ ዮናስ ለስብከት ፈቃደኛ ባይሆን እንኳን እግዚአብሔር በተለየ ጥበቡ እንዲሔድ አድርጎታል፡፡ በእርግጥ እግዚአብሔር ሌላ የሚልከው ነቢይ አጥቶም አይደለም፤ እርሱንም ጭምር ሊያስተምረው ስለ ፈለገ እንጂ፡፡ የነነዌ ሰዎች የተነሳሕያን ምሳሌ ናቸው፡፡ ይህም ማለት ሰው ጥፋቱን አምኖ ንስሐ ከገባ እግዚአብሔር ይቅር ማለቱን አይተውም፡፡ ለዚህም ነው ዮናስን ‹‹አንተ ላልደከምክበት እና በአንድ ቀን በቅሎ ላደገ ቅል ስታዝን እነሆ በታላቂቱ ነነዌ ከተማ ያሉ ከአንድ መቶ ሃያ ሺሕ በላይ ሕዝብና እንስሳቱ የእጄ ፍጥረቶች ስለ ሆኑ ያሳዝኑኛል›› ያለው፡፡
ቀደምት የቤተ ክርስቲያን አባቶቻችን ይህን እና ሌሎች አጽዋማትን እንድንጾም የወሰኑልን ያለ ምክንያት አይደለም፡፡ ሕጉ የተዘጋጀልን እንደ ነነዌ ሰዎች እኛም ጾመን፣ ጸልየን ከኃጢአታችን እንነጻ ዘንድ ነው፡፡ ዛሬ ዓለማችን በኃጢአት ማዕበል እየተናወጠች ባለችበት ወቅት እኛም እንደ ነነዌ ሰዎች ከበደላችን ብንመለስ እና ንስሐ ብንገባ ቸሩ ፈጣሪያችን እግዚአብሔር ይቅርታና ምሕረት የባሕርይ ገንዘቡ ስለ ሆነ ‹‹ወደ እኔ ተመለሱ፤ እኔም ይቅር እላችኋለሁ፤›› ይለናል፡፡
ስለሆነም በነቢዩ ዮናስ ላይ የተደረጉ ተአምራትንና ካለመታዘዝ የሚመጣ ቅጣት ቀላል አለመሆኑን በማስተዋል፣ ለነነዌ ሰዎች የወረደውን ምሕረት በመገንዘብ ለእግዚአብሔርም ሆነ ለሃይማኖት አባቶች እና ለወላጆቻችን መታዘዝ ይገባናል፡፡ ስንጾምም እግዚአብሔር አምላካችን መዓቱን በምሕረት፣ ቍጣውን በትዕግሥት መልሶ በኃጢአት ለጠፋው ዓለም ይቅርታውን ይልካል፡፡ በመጾማችን ራሳችን ከመዓትና ከመቅሠፍት ከመዳናችን ባሻገር በእኛ በደል ምክንያት አገራችን፣ ዕፀዋቱና እንስሳቱም ሳይቀር ከድርቅና ከቸነፈር ይተርፋሉና፡፡
እኛ ክርስቲያኖችም ይህን በማዘከር “ንስሐ ብንገባ እንደ ነነዌ ሰዎች ከተቃጣው ማንኛውም መቅሰፍት እንድናለን” በማለት በየዓመቱ ከዓብይ ጾም መግቢያ ሁለት ሳምንት አስቀድማ ካለችው ሰኞ ጀምሮ እስከ ረቡዕ ድረስ “ጾመ ነነዌ” በማለት እንጾማታለን፡፡ ዘንድሮም ዓብይ ጾም የካቲት 21 ስለሚገባ ከዛ ሰኞ የካቲት 7 እስከ ረቡዕ የካቲት 9 እንጾማታለን፡፡
እግዚአብሔር የመረጠውን ዓይነት ጾም እንድንጾም ከተቃጣው ማንኛውም ዓይነት ፈተናም እንድናመልጥ ሰውን በመውደድ ሰው የሆነው ክርስቶስ ይርዳን አሜን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

👍1
Forwarded from ሐዋርያዊ መልሶች
-----------------
#ኤርሚያስ_አበበ
እኔ ለተወሰኑ ጊዜያት ክርክሮችን ማድረጉን አልፈልግም ግን ይሄንን ሰው ፈቃደኛ ከሆነ ላይቭ ባወያየው ምን ይመስላቹሃል..?? ማንም መምህር እኔን ለማወያየት ፈቃደኛ ሊሆን አልቻለም እያለ ነው አሉ.. ከዚህ በፊት ስለ ታቦት ካልሆነ አልወያይም ብሎ ሳይወያይ ቀርቷል.. ያው ውይይት ዶግማቲክ የሆኑ ጉዳዮች ላይ ሲሆን ፍሬያማ ይሆናል.. ለምሳሌ የጌታ ሥጋና ደም ላይ መወያየት ቢችል በጣም ሃሪፍ ነው.. ካልሆነም ግን ምክንያትም ላለመስጠት "ታቦት በሐዲስ ኪዳን" በሚል ርእስ መወያየትም እንችላለን ያው ፍላጎቱ አሁንም እርሱ ከሆነ.. ያው ወሳኙ ነገር ውይይቱ የሚሆነው በገለልተኛ ቦታ እና በሞደሬተር ይሆናል..
ሼር አድርጉለት እስቲ እባካችሁን.. ብዙ ፕሮቴስታንት ወንድም እህቶቻችን የሆነ ቦታ ነው ያስቀመጡት..
@orthodoxAPOLOGETICS

ድል የነሳው እንዲሁ ነጭ ልብስ ይጎናፀፍል፣ ስሙንም ከህይውት መፅሐፍ አልደመስስም፣በአባቴና በመላእክቱም ፊት ለስሙ እመሰክርለታለሁ። ራዕይ 3÷5
በረከታቸው በእኛ ላይ ትሁንና ለረጅም አመታት በአርምሞ እና በትህርምት የኖሩት ዝምተኛ አባት በዕለተ ቅዱስ መርቆርዮስ ነበር ከስደት አፈሯን እና በረከቷን ወደ ሚናፍቋት ቅድስት ሃገር ኢትዮጵያ የተመለሱት ይሔው ዛሬም በእለተ ቅዱስ መርቆርዮስ ከዚህ አለም ድካም አረፉ።
በረከታቸው ትደርብን!

❤1
"ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ባሉኝ ግዜ ደስ አለኝ። መዝ 121÷1
ቅድስት ( የዐቢይ ጾም ሁለተኛ ሳምንት )
«ቅድስት» ማለት የዘይቤ ፍችው « የተቀደሰች የተለየች » ማለት ነው፡፡ ምስጢራዊ መልእክቱ ግን የምስጢረ አድኅኖት ታላላቅ ሥራውን ለመጀመር መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶሰ በገዳመ ቆሮንቶስ ገብቶ ከቆመ ሳያርፍ፣ ከዘረጋ ሳያጥፍ የጾማት የአርብዓው ቀንና ሌሊት ልዩ የሆነችና ክብርት ጾም የምትጀመርበትን ሁለተኛ ሳምንት ከልብ ያሳስበናል፡፡ ማቴ. 4-2
ቅድሰት የዐቢይ ጾም ሁለተኛ ሰንበት ስያሜ ነው፡፡ ስያሜውም ከኢትዮያዊው የዜማ ሊቅ ከቅዱስ ያሬድ የተገኘ ነው፡፡ ከዚህ ሰንበት ዋዜማ ጀምሮ ስለ ዕለተ ሰንበት ቅድስና ይዘመራል፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም ሰንበቱን ስለ ቅድስና ልጆቿን ታስተምርበታለች ፡፡ በቅዳሴ ጊዜ የሚሰበከው ምስባክ ፤ የሚነበቡ መልዕክታት ፤የሐዋርያት ሥራ ና ወንጌል ስለ ቅድስት የሚያስተምሩ ናቸው፡፡
‹‹ቅዱስ›› ማለት ልዩ፤ክቡር ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔር አምላካችን በባሕርዩ ቅዱስ ነው፡፡ ይህም ቅድስና ከማንም ያላገኘው የባሕርይ ገንዘቡ ነው፡፡ መጻሕፍትም የባሕርይ ቅድስናውን ተባብረው መስክረዋል፡፡ ባባሕርዩ ቅዱስ ስለሆነ ‹‹ቅዱስ፡ቅዱስ፡ቅዱስ›› እየተባለ ይመሰገናል፡፡( ኢሳ 6፡1-3፤40፡25 ራዕ 15፡4 ፤ 1ሳሙ2፡2-3፡፡) እኛም ቅዱስ ልጁ በሥጋ ተገልጦ እንዳስተማረን በየዕለት ጸሎታችን ‹‹ስምህ ይቀደስ›› እንለዋለን፡፡ የቅድስና ምንጭ ፡ ቅድስናን የሚሰጥ እርሱ ብቻ ነው፡፡ ‹‹ ቅዱስ›› የሚለው ቃል ለሰዎች ፡ለመላእክት ፡ ለቦታ ፡ለዕቃ፡ ለዕለታት … ቢቀጸልም ቅድስናቸው በባሕርይው ቅዱስ ከሆነው ከእግዚአብሔር የተገኘ ነው፡፡ይህም የጸጋ ቅድስና ይባላል፡፡
እግዚአብሔር ቅዱስ ስለሆነ በመልኩና በምሳሌው አክብሮ የፈጠረንን እኛም ቅዱሳን እንድንሆን ይፈለጋል፡፡ቅዱስ ጴጥሮስ ‹‹ዳሩ ግን እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁን›› ተብሎ ስለተጻፈ የጠራቸው ቅዱስ እንደሆነ እናንተ ደግሞ በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ ›› ያለንም ይህንን ሲያስተምረን ነው፡፡ ከመፈጠራችን አስቀድሞ መጠን በሌለው ፍቅር የወደደን እግዚአብሔር ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣን ፤ለውርደት ሳይሆን ለክብር፤ለርኩሰት ሳይሆን ለቅድስና፤ለሞት ሳይሆን ለሕይወት ነው፡፡የመፈጠራችንም ዓላማ በፊቱ በፍጹም ምግባርና ሃማኖት በመመላለስ ከእርሱ ጋር እንድንኖር ነው፡፡ ብርሃን ከጨለማ፡ ጽድቅ ከኃጢአት፡ጋር ኅብረት የለውምና ከእርሱ ጋር ለዘላለም ነግሰን ለመኖር በቅድስና መኖር ይጠበቅብናል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም ‹‹ እግዚአብሔር ለቅድስና እንጂ ለርኩሰት አልጠራንምና ›› ያለንም ለዚህ ነው፡፡/1ተሰ 4*7/ እግዚአብሔር እኛን የፈጠረበትን አላማ ለኤፌሶን ክርስቲያኖች እንዲህ ገልጾላቸዋል ‹‹ በክርስቶስ ኢየሱስ ሰማያዊ ሥፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ይመስገን፡፡ ብሎ ካመሰገነ በኋላ ‹‹ ዓለም ሳይፈጠር በፊቱ ቅዱሳን ፡ንጹሐንና ያለነውር በፍቅር ያደርገን ዘንድ ለእርሱ መረጠን›› ኤፌ 1፡3-4 አስቀድሞ ስለወደደንና ስላከበረንም ከሌሎች ፍጥረታት በተለየ መልኩ የሚያስፈልገንን ሁሉ አዘጋጅቶ በእጆቹ ካበጀን በኋላ የሥነ ፍጥረት ዘውድ አድርጎ በገነት አኖረን ፡፡( ዘፍ 1፡26 ፤መዝ 8፡1)
የቀደመው አዳም አታድርግ የተባለውን በማድረጉ በንዝህላልነትና በስንፍና በከይሲ ዲያብሎስም ምክር ተዋረደ፡፡ በሞተ ሥጋ ላይም ሞተ ነፍስ ፤በርዕደተ መቃብር ላይ ርዕደተ ሲኦል ተፈረደበት፡ በባሕርዩ ሞት ገባበት፡ተዳደፈ፡፡ ክፉ ፍትወታት የሚያጠቁትና የሚያሸንፉት የዲያብሎስና የኃጢአት ባርያ ሆነ፡፡ በማይለወጥ ፍቅር የወደደን እግዚአብሔር ግን ጠፍተን እንድንቀር አልተወንም፡፡ በሰጠን ተስፋ፡በተቆጠረው ሱባኤና በተነገረው ትንቢት መሰረት ዘመኑ ሲደርስ በተዋህዶ ሰው ሆነ፤ የተዋረደ ሥጋችንን አከበረ፡፡ በከበረ ደሙ ዋጀን፤ከኃጢአታችን አጠበን፡፡ በእርሱ ምክንያት የእግዚአብሔር ልጆች ተባልን ፡፡ጌታችንና መድኃኒታችን ሰው የሆነውና ለመዳናችን የሆነውን ዋጋ ሁሉ የከፈለው ለእኛ ያለውን ፍቅርና ለኃጢአት ያለውን ጥላቻ ለእኛ ለማሳየት ነው፡፡ ‹‹ ነገር ግን የኃጢአትን ሥራ ይሽር ዘንድ ከእርሱ ጋር የተሰቀለውን አሮጌውን ሰውነታችን እንደሆነ ይህን እናውቃለን ›› የተባለውም ለዚህ ነው፡፡
(ሮሜ 6፡6) እኛን ወደ ቀደመ ክብራችን ለመመለስ የተከፈለውም ዋጋ ታላቅ ከሆነው የጋብቻ ምስጢር ጋር በማያያዝ እንዲህ ገልፆታል ‹‹ ክርስቶስ አካሉ ለሆነችው ቤተ ክርሰቲያን ራስዋ አዳኝዋም እንደሆነ ወንድ ለሴት ራስዋ ነውና … ወንዶችም ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንን እንደወደዳት ራሱንም ስለእርስዋ ቤዛ አድርጎ እንደሰጠላት ሚስቶቻቸውን ይውደዱ፡፡ በውኃ ጥምቀትና በቃሉ ይቀድሳትና ያነጻት ዘንድ የነጻችና የተቀደሰች ትሆን ዘንድ እንጂ በላይዋ እድፈት ወይም ርኩሰት እንዳይገኝባት ቤተ ክስቲያኑን ለእርሱ የከበረች ያደርጋት ዘንድ…›› ኤፌ 5፡23-28
ስለዚህ ጌታችን በደሙ ኃጢአታችንን እንደ ቸርነቱ ይቅር ብሎናል፡፡ኤፌ 1፡7 ከእንግዲህ የራሳችን አይደለንም ፡፡ በሰውነታችንም ኃጢአትና ዐመፃን ልናደርግበት አይገባም ፡፡‹‹በዚህ በሚሞት ሥጋችሁ ኃጢአት አታንግሷት፤ለምኞቱ እሺ አትበሉት፡፡ ከሙታን ተለይቶ እንደተነሳ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አድርጉ እንጂ ሰውነታችሁን ለኃጢአት የዐመፅ የጦር መሣሪያ አታድርጉት፤ ሰውነታችሁንም ለእግዚአብሔር የጽድቅ የጦር መሣሪያ አድርጉ››ተብለናል፡፡ (ሮሜ6፡12-13)
የተወደዳችሁ ምዕመናን እግዚአብሔር ደስ ብሎት የሚቀበለውን ህይወት ለመኖር አንፈልጋለን ፡፡ ለመሆኑ ይህ ሊሆን የሚችለው እንዴት ብንመላለስ ነው? መልሱን ሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብ ‹‹አንደበቱን ሳይገታ ልቡን እያሳተ እግዚአብሔርን የሚያመልክ የሚመስለው ማንም ቢኖር የእርሱ አምልኮቱ ከንቱ ነው፡፡ ንጹሕ የሆነ ነውርም የሌለበት አምልኮ በእግዚአብሔር አብ ዘንድ ይህ ነው፤ወላጆች የሌሉአቸውን ልጆች ባልቴቶችንም በችግራቸው መጠየቅ በዓለምም ከሚገኝ ርኩሰት ሰውነትን መጠበቅ ነው፡፡››በማለት ይመልስልናል( ያዕ 1፡26-27)፡፡ በክርስቶስ ደም የተቀደሰና የእግዚአብሔር ማደሪያ የሆነውን ሰውነታችንን በዓለም ከሚገኝ ርኩሰት መጠበቅ የሰማያዊ ርስት ወራሾች ያደርገናል፡፡ በዓለም የሚገኘውን ርኩሰትም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹የሥጋ ሥራ ›› በማለት ገልጾታል፡፡‹‹እርሱም ዝሙት ፣ርኩሰት፣መዳራት፣ጣዖት ማምለክ፣ሥራይ ማድረግ፣መጣላት፣ ኩራት፣የምንዝር ጌጥ ፣ቅናት፣ቁጣ ፣ጥርጥር፣ፉክክር፣ ምቀኝነት፣ መጋደል፣ ስካር ፣ይህንም የመሰለ ሁሉ ነው፡፡››እነዚህን የሚያደርጉ ሰዎችም ከመንግስተ እግዚአብሔር በአፍአ ወይም በውጭ እንደሚቀሩ ሲያስረዳ‹‹አስቀድሜ እንደነገርኋችሁ ይህን የሚያደርግ የእግዚአብሔርን መንግስት አያይም›› ብሏል ( ገላ5፡19)።
በሕይወታችን ሁሉ የምግባርና የሃይማኖት ፍሬ አፍርተን መገኘት ለቅድስና የጠራንን እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት ነው፡፡እነዚህንም ነገሮች ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹የመንፈስ ፍሬዎች ›› ብሏቸዋል፡፡ እነርሱም ‹‹ፍቅር፣ደስታ ፣ሰላም፣ትዕግስት፣ምጽዋት፣ቸርነት ፣እምነት ፣ገርነት ንጽሕና ››ናቸው፡፡ገላ 5፡22 እግዚአብሔር ማደርያው ይሆን ዘንድ የመረጠውን ሰውነታችንን እርሱ የሚከብርበትን ሥራ ልናደርግበት ያስፈልጋል፡፡

"ፆም፣ጸሎት እና ስግደት"
ጾም ለተወሰኑ ሰዓታት ከምግብ መከልከል ለተወሰኑ እለታት ከጥሉላት ምግቦች መከልከል እና ለዘላለሙ ማለትም እስከ እለተ ሞት ደግሞ ከክፉ ነገር መከልከል ነው። ቅዱስ ያሬድ ዓይን ይጹም እዝንኒ ይጹም እምሰሚዐ ኅሡም ዓይን ይጹም ያለው እስከ እለተ ሞት ድረስ ክፉ ነገርን ከማየት፣ ከመስማት፣ ከመዳሰስ፣ ከመቅመስ መከልከልን ነው። ሰባቱ የአዋጅ አጽዋማት የሚባሉት፦
1) ረቡዕና አርብ (ጾመ ድኅነት)
2) የነነዌ ጾም
3) የገሐድ ጾም
4) የነቢያት ጾም
5) ጾመ ኢየሱስ (ዐቢይ ጾም)
6) ጾመ ማርያም (ፍልሰታ)
7) ጾመ ሐዋርያት
ናቸው።በጾም ጊዜ ከዘጠ ኝ ሰዓት በፊት አይበላም። በስድስት ሰዓት በሰባት ሰዓት የሚበላው ስህተት ነው። ረቡዕ እና አርብ በበ ዓለ ሃምሳ አይጾሙም። የብሉይ ኪዳን ጾም ከእለት መቅሰፍት ከሥጋ መከራ ያድናል እንጂ ነፍሳዊ ድኅነት አያሰጥም ነበር። በሐዲስ ኪዳን የምንጾመው ጾም ግን ነፍሳዊ ድኅነትንም ያሰጣል።የነነዌ ጾም ሁልጊዜም ሰኞ ጀምሮ እስከ ረቡዕ በዓመት ውስጥ ሦስት ቀን የሚጾም ጾም ነው።የገሐድ ጾም የልደት(የገና ዋዜማ) እና የጥምቀት ዋዜማ የምንጾመው ጾም ነው። የልደት ዋዜማን የምንጾመው ገሐድ ብለን ነው። የጥምቀትን ዋዜማ (ጥር 10) ቀንንም የምንጾመው ገሐድ ብለን ነው። ጥምቀት ሰኞ ቢውል የገሐድ ጾም እሑድ ብቻ ከጥሉላት ተከልክሎ ይጾማል። እንጂ ጥር 9 ቀንንም ጨምሮ መጾም አግባብ አይደለም። የጥምቀት ዋዜማን ገሐድ አለ እንጂ የጥምቀትን የዋዜማ ዋዜማ ገሐድ አይልም። የነቢያት ጾም በአራቱም ዘመናት ማለትም በዘመነ ዮሐንስ፣ ማርቆስ፣ ሉቃስ፣ ማቴዎስ ሁልጊዜም ህዳር 15 ይጀመራል እንጂ በአራት ዓመት አንድ ጊዜ ህዳር 14 ይሆናል የሚባል ትምህርት የለም። የሥርዓት መጽሐፋችን ፍትሐ ነገሥት ነው። እርሱ ደግሞ ህዳር 15 ይጀመር ይላል እንጂ ከአራት ዓመት አንድ ጊዜ ህዳር 14 ይሁን አይልም። የፍልሰታ ጾም ነሐሴ 1 ጀምሮ እስከ ነሐሴ 16 ያለው ጾም ነው። የሐዋርያት ጾም ደግሞ ከጰራቅሊጦስ ማግሥት ጀምሮ እስከ ሐምሌ 5 የሚጾመው ጾም ነው። የጽጌ ጾም የፈቃድ ጾም ነው።
ጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር የምንነጋገርበት አደባባይ ነው። ፍትሐ ነገሥታችን ጸሎት ብሂል ተናግሮ ምስለ እግዚአብሔር ብሎ ያመጣዋል። አንድ ክርስቲያን በቀን ቢያንስ ሰባት ጊዜ መጸለይ ይገባዋል። እነዚህም፦
1) ጠዋት 12 ሰዓት
2) ከጠዋቱ 3 ሰዓት
3) ቀትር 6 ሰዓት
4) ከቀኑ 9 ሰዓት
5) ሠርክ 11 ሰዓት
6) ከምሽቱ 3 ሰዓት
7) ከሌሊቱ 6 ሰዓት
ናቸው። የጠዋቱ ጸሎተ ነግህ ይባላል። እነዚህ መደበኛ ይሁኑ እንጂ ማንኛውም ክርስቲያን ከእነዚህ በተጨማሪ በፈለገው ሰዓት እና ቦታ መጸለይ ይችላል። ቤተክርስቲያን ውስጥ ሴቶች ጸጉራቸውን ተሸፍነው ይጸልዩ። በሰባቱም ሰዓታት ኢየሱስ ክርስቶስ አዳምን ለማዳን የተቀበላቸውን መከራ እያሰቡ መጸለይ ይገባል። ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት ምጽአትን እያሰብን ልንጸልይ ይገባል። ጠዋት በሰላም ላሳደረን አምላክ ምስጋና አቅርበን ውሏችንን የሠመረ ያደርግልን ዘንድ የምንለምንበት ሊሆን ይገባል። ጌታችን ሐዋርያትን በጾም እና በጸሎት የሚሸነፉ አጋንንት እንዳሉ ነግሯቸዋል። ስለዚህ አጋንንትን ለማራቅ ሕይወታችን መልካም እንዲሆን እንጹም እንጸልይ።
በዓበይት በዓላትና በሰንበት አይሰገድም። ነገር ግን በሰሙነ ሕምማት ማንኛውም በዓል ቢውል ይሰገዳል። ለምሳሌ የስቅለት ቀን የማርያም በዓል ወይም በዓለ እግዚአብሔር ቢውል ይሰገዳል። ስቅለት ራሱ ከዓበይት በዓላት አንዱ ሲሆን የሚከበረው በስግደት ነውና። በስግደት ለፈጣሪ መገዛታችንን እንገልጣለን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር አሜን ይቆየን