Telegram Web
በእስልምና ውስጥ እረፍት ማግኘት ይቻላልን..??🤔🤔

በእስልምና ትምህርት ውስጥ አላህ ለየትኛውም ሰው ገና በእናቱ ማሕጸን ሳለ ገነት ይግባ ወይስ በእሳት ይቃጣል የሚለውን የራሱን ውሳኔ በመልአክ እጅ ያስጽፋል.. ከዚያም ያ ሰው ማንም ሆነ ማን ከዚያ ከተጻፈለት ነገር ሊያልፍ አይችልም.. እድሜ ልኩን ጽድቅ ሲሰራ የኖረው ሰው የተጻፈበት በእሳት እንዲቃጠል ከሆነ በስተመጨረሻውም ቢሆን ጥፋትን ማድረግ ይጀምራል.. ይህንን ጥፋት የሚያደርገው አስቀድሞ "ፈጣሪ" እሳት እንዲገባ ስለወሰነበት ነው..

ምናልባት ማስረጃ አስፈላጊ ከሆነ ለዚህ ግልጽ ትምህርታቸው ለናሙና ያህል [ሳሂህ አል ቡኻሪ፡ ቅጽ 8. መጽ 77. ቁ 593] ይነበብ


ታድያ ግን አስቀድሞ ራሱ "ፈጣሪ" የሰውን መግቢያውን ከወሰነና የተጻፈ ነገር ከሆነ መልሶ ሰዎችን ወደ እኔ ተመለሱ በዚያ ውጡ በዚያ ግቡ ማለቱ ምንድን ነው..??

ሙስሊም ወንድም እህቶችስ ምናልባት በሚመጣው ዓለም ራሳችሁን ለገሃነም ከተጻፈባቸው ውስጥ ብታገኙት ምን ይሰማችኋል..?? ያው ስለ እናንተ ምን ተጽፎ ይሁን አይሁን ስለማታውቁት ማለት ነው አሁን ላይ.. "አላህ አንተ ጨካኝ ነህ ስለምን ይህንን ጻፍክብኝ" ትሉት ይሆን ወይስ..?? ምክኒያቱም እዛ ለመግባታችሁ ምክኒያቱ አስቀድሞ አላህ የወሰነባችሁ ስለሆነ ነውና ማለት ነው

@orthodoxAPOLOGETICS
ከፍ ያለ ሁሉ ዝቅ ማለቱ አይቀርም
=====================
በሰማይ መብረር ብትችልም የሆነ ጊዜ በምድር መንቀሳቀስ የማትችልበት ቀን ይመጣል። በሰማይ ራስህን ችለህ ብትበርም ቀን ሲጥልህ ግን በምድርም ላይ በሰው የምትደገፍበት ቀን ይመጣል። ከፍ ብለህ የምትበርበትን ጊዜ በልኩና በአግባቡ ተጠቀምበት።እግዚአብሔርን የያዘ ከፍታ፣የቅዱሳኑን ምልጃ የያዘ ከፍታ ዝቅ አይልም።በትዕቢት የተሞላ ከፍታ መሰረቱን እና እውነቱን የሳተ ከፍታ እንደ ሰይጣን መፈጥፈጡ፣ዳግም ላይነሳ ከፍም ላይል ዘላለማዊ መዋረድና ፍፁም የተናቀ ዝቅታ መጎናፀፉ ግድ ነው።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አስባችሀታል ፕሮቴስታንት ማለት ደቂቀ ሰይጣናት ተሰባስበው በአባታቸው ዲያብሎስ ምክንያት ወደ ገሃነም በፈቅዳቸው የሚንደረደሩበት የሙታን ስብስብ ነው።

በተለይ እንደ ከፍያለው ቱፍ አይነት ሃይማኖትንና ሰውነትን ለሚቀያይር ዋጋቸውን እንደ አስቆርቱ ይሁዳ በዲናር ለለወጡ በዘር ከረጢት ታጭቀው መንፈሳዊ መምሰል ቢሞክሩም ግብራቸው ግልፅ ነውና አስቀድመን አፈሩን ገለባ ያድርግላችሁ ከማለት የዘለለ መልዕክት የለንም።
📌 የተስፋ ሕይወት

❖ የተስፋ ሕይወት በእግዚአብሔር ቃል ኪዳን በስራው ለሰዎች ሁሉ ባለው ፍቅሩና በድንቅ አሰራሩ መታመንን ይፈልጋል፤ ልቦናዎቻችን በተስፋ ይሞሉ ዘንድ እኛ ራሳችንን ከምንወደው በላይ እርሱ እንደሚወደንና እኛ ለእኛ መልካም ነው ብለን ከምናስበው እጅግ የበለጠ እርሱ ለእኛ ያውቅልናል።

❖ እኛ ተቃራኒውን ልናስብ ብንችልም እግዚአብሔር ለአንተ የሚሰራው ድንቅ ስራ ከረቂቅ ጥበቡና ከመልካምነቱ የመነጨ መሆኑን ማወቅ ያስፈልጋል፤ አንተ በእግዚአብሔር እጅ ብቻ እንጂ በሌሎች ሰዎች እጆች ወይም በዲያብሎስ እጆች ውስጥ ወይም ደግሞ ለአጋጣሚና ለፈተና የተጋለጥክ አለመሆንህን ልታውቅ ይገባል።

❖ አንተ በእግዚአብሔር እጅ ያለህና በመዳፉ የተቀረጽክ ነህ፤
📖ኢሳ 49፥16
❖ እርሱ ከክንፎቹም በታች ተማምነህ እንድትጠለል አድርጎሀል
📖መዝ 91፥4
❖ እርሱ በቀንና በሌሊት ከአንተ ጋር ነው መውጣትና መግባትህንም ይጠብቃል
📖መዝ 121፥5

❖ እርሱ ስለሚወድህለም ልጄ ብሎ ጠርቶሀል
📖1ኛ ዮሐ 3፥1

❖ እርሱ እረኛህ ስለሆነም ምንም የሚያሳጣህ ነገር የለም
📖መዝ 22፥1

❖ እኛ ሁላችን የእግዚአብሔር ስለሆንን የጋጣው በጎች ነን፤ እርሱም መልካም እረኛ ስለሆነ በጎቹን አይዘነጋም፤ እንደ አባትነቱም ልጀቹን አይረሳም።
📖ዮሐ 10፥11

📌 ምንጭ
✍️አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ
📚የተስፋ ሕይወት ገፅ 14
👍1
።።። ። በሞት "ኦርቶዶክሳዊ እና ኢትዮጵያዊ" ሆነው አረፉ!

በመጨረሻም አቶ ገላሳ ዲልቦ በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን ከቅድስት ሥላሴ አፀድ "ኦርቶዶክሳዊ እና ኢትዮጵያዊ" ሆነው ፥ መለስ ዜናዊ በተቀበረበት እርሳቸውም ተቀበሩ።

ኦነግነትም እንደ ወያኔነት ፦ ፀረ ኦርቶዶክስ፣ ፀረ ሰው፣ ፀረ ኢትዮጵያ፣ ፀረ ሰንደቅ ዓላማ ፥ ያለ መኾንን አብነት በሞት አግኝተው፣ ከመኖር የተለየ ግብአተ መሬት ተፈጸመላቸው።

ባራመዱት የፖለቲካ ርዕዮተ ዓለም ምክንያት በዘራቸውና በሃይማኖታቸው የተነሳ የተገደሉ ነፍሳት በነፍስ ይማር ይቀበሏቸው።

ግን ግን ይህች ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን እንዲህ እጅግ ድንቅ ናት - የመለስና የገላሳ ፖለቲካ ልጆቿን በየቀኑ ይገድልባታል፤ ያሳድድባታል፤ መቅደሷን ይደፍርባታል፤ ያቃጥልባታል፤ ይዞታዋን ይነጥቅባታል፤ እርሷ ግን ከመቃብር በላይ ፥ ከተራራ ገዝፋ "ጌታ ሆይ ነፍሳቸውን ይቅር በል፣ ማርልን" እያለች ፤ እነ ገላሳን ከአፀደ መቅደሷ ከመቃብር በታች በክብር ታሳርፋለች።

ይህንንም የኦቦ ሽመልስ ዓይኖች ተመለከቱ። ቄስ በላይ ግን አቶ ገላሳ ከሞት ተነስተው መጥተው ቢያስተምሩት እንኳ "የዘር ፖለቲካ ቄስ" ከመኾን የማይመለስ መኾኑን አስመሰከረ።

አቶ ገላሳ በሞት "ኦርቶዶክሳዊ እና ኢትዮጵያዊ" ሆነው በቅድስት ቤተ ክርስቲያን አፀድ ውስጥ አረፉ! የግብር ልጆቻቸው የኾናችሁ ሁሉ ኑ ለነፍሳችሁ እረፍትን አግኙባት። ኑ! ቤተ ክርስቲያን እንዲህ ናት። የአምላኳን ፍጹም መሐሪነትና ይቅር ባይነት የተላበሰች የምሕረት ደጅ!! ኋላ ግን ፈራጅ!!
(ዓርብ ለእሑድ አጥቢያ፣ መጋቢት 24 ቀን 2014 ዓ.ም
👍2
ሙስሊሞች ቀደምት ነቢያትና ሐዋርያት ሙስሊሞች ነበሩ ብለው ያምናሉ። ይህን መረዳት ያመጡት ከሌላ ቦታ ሳይሆን ከራሱ ከቁርአን ነው (ሱራ 3:52 ሱራ 22:78) ሙስሊሞች እነዚህን እና መሰል የቁርአን አንቀጾችን በመጥቀስ እስልምና "የነቢያትና የሐዋርያት ሃይማኖት ነው" ብለው በኩራት ሲናገሩ ይሰማል

ነገር ግን ይህ ቁርአን እና እስልምናን እጅግ ትልቅ ጥያቄ ውስጥ ይጥላል። ለምን? ቀደምት ነቢያትና ሐዋሪያት ሙስሊሞች ነበሩ የሚለው ሀሳብ የእስልምና claim ነው። ይህ claim እውነት መሆኑን በምን ማረጋገጥ ይቻላል?

ስለሆነ አካል claim ከተደረገ፥ የዚያ claim እውነተኝነት መረጋገጥ ያለበት ከዚያው claim ከተደረገበት አካል ነው። ለምሳሌ፥ አቶ አማረ በሳይኮሎጂ የማስተርስ ዲግሪ አለው ከተባለ፥ ይህ claim መረጋገጥ ያለበት ከራሱ ከአቶ አማረ ነው። አቶ አማረ በዚህ የትምህርት ዘርፍ የማስተርስ ዲግሪ እንዳለው የሚያሳይ ማስረጃ መምጣት ያለበት ከራሱ ዘንድ ነው። እንጂ ይህን የተናገረው አካል "አለው" ስላለ ብቻ እውነት ነው ማለት አይደለም። ከባለቤቱ ማረጋገጫ መምጣት አለበት

በዚሁ አኳያ ቁርአን የቀደሙት ነቢያትና ሐዋርያት ሙስሊሞች ነበሩ ካለ፥ ሙስሊም መሆናቸው መረጋገጥ ያለበት ከራሳቸው ከነቢያቱና ከሐዋሪያቱ ነው። ማስረጃው ማምጣት ከራሳቸው ጽሑፎች ነው። ከራሳቸው ጽሑፎች ሙስሊም መሆናቸው እስካልተረጋገጠ ድረስ የቁርአኑን claim ተቀባይነት የለውም። ሙስሊሞችም በልበ ሙሉነት ሊጠቅሱት አይችሉም። ራሱ ማስረጃ የሚያስፈልገው claim ነውና

🚩 ቁርአን እየዋሸ ላለመሆኑ ማስረጃው ምንድነው? የቀደሙት ሐዋሪያትና ነቢያት ሙስሊሞች እንደነበሩ ከራሳቸው ጽሑፎች ማረጋገጥ ይችላልን?
👍1🥰1
ርዕሰ ባህታውያን እንኳን ተወለዱ ¡
=========================
እርስዎ ባይወለዱ ኖሮ ባህታዊያን ልደታቸውን በኬክ በጣፍጭ ብስኩትና መጠጦች ምግቦች ማክበርን ማንስ ያሳቸው ነበር¡?

ደግሞስ ባህታዊያን ከብህትና በዓት ወጥተው፣ከገዳም ርቀው በአዳራሽና በድንኳን “መልካም ልደት • • •”የሚለው የአለም ዘፈን ለቅድስናቸው ማንስ ይዘፍንላቸው ነበር¡

በእውነት እንኳን ተወለዱ ርዕሰ ባህታዊያን ቅዱስ አባ ዮሐንስ ተስፍ ማርያም ዘገዳመ ወንቅሸት ቅዱስ ገብርኤል ¡
😁2
🌴 ለዚህ ትህትና ሆሣዕና !🌴
🌿🌿🌿
"የአህያ ሥጋ አልጋ ሲሉት አመድ"
"ለአህያ ማር አይጥማትም" (በስንት ማንኪያ ማር ተሞከረች?) "የተናቀ ከተማ በአህያ ይወረራል" (በታሪክ ተዘግቦ ከሆነ ስሙ ይነገረን) …. ወዘተ በምድረ አበሻ የተነገሩ አህያን አመካኝቶ ለመዝለፍ የተፈለገን ሰውን ክብር ለመንካት ከተተረቱ በርካታ ሥነ ቃሎች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ ያገሬ ሰው "አህያ" ብሎ ሲሳደብ ጥቃት የማይገባው፣ ሲበደል ምላሽ የማይሰጥ፣ ክብረ በላ ደነዝ ….ለማለት ነው ፡፡

በጥንቶቹ የይሁዳ ግዛቶችም ለአህያ የነበረው አመለካከት ያው በንቀት ላይ የተመሰረተ ነበር ማለት ይቻላል። "የጽዮን ልጅ ሆይ! እነሆ ንጉሥሽ የዋህ ሆኖ በአህያ ላይና በአህያይቱ ግልገል በውርንጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወዳንቺ ይመጣል።" እንዲል ነቢዩ ኢሳይያስ፤ ትሁት የሆነው ንጉሥ በፈረስና ፈረሰኞች ታጅቦ በሰረገላ ሳይሆን በውርንጫይቱ ላይ ተቀምጦ ከደብረ ዘይት እስከ ኢየሩሳሌም በመምጣቱ ውስጥ አህያ በአካባቢው የነበራትን ሥፍራ ማየት ይቻላል።
በአህያ የተቀመጠ ሸሽቶ አያመልጥም፤ አሳድዶ አይይዝም፤ እርሱም ካልፈለጉኝ አልገኝም ከፈለጉኝም አልታጣም ሲል እንዲሁም የነቢያቱ ትንቢት ይፈፀም ዘንድ ነው፡፡ ጌታችን የማዳን ሥራውን ወደሚፈጽምባት ወደ ኢየሩሳሌም ገባ፡፡ ቤተ ፋጌ ሲደርስ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን ልኮ ‹‹ያስፈልጉኛልና የታሠሩትን አህያና ውርንጫዋን ይዛችሁልኝ ኑ፡፡›› ብሎ ላካቸው፡፡ እነርሱም እንደታዘዙት አመጡ፤ እስከ ቤተ መቅደስ 16 ምዕራፍ ሲሆን 14ቱን በእግሩ፣ 2ቱን ምዕራፍ (ከደብረ ዘይት ተራራ አካባቢ አንስቶ እስከ ኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ) በአህያ ሄዶ፣ ቤተ መቅደሱን 3 ጊዜ በውርንጫላዋ ከዞረ በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ ገባ፡፡

በሰውኛ ሲታሰብ ስትለፋ ውላ ምሷ ዱላና ገለባ፤ ፍዳዋን ስታይ ኖራ ስታረጅ ቀርቶ በቁሟ የአራዊት ሲሳይ የምትሆን ይህች ፍጥረት፤ በዓለም መንፈሳዊ ታሪክ ውስጥ ላንዲት አፍታ እንኳ ልታስበው ቀርቶ ከቶ ልትገምተው የማትችለው ነገር ተፈጸመባት፡፡ የደመና አክናፍ የ’ሳት ሰረገላ የሚያንስበት ፈጣሪ በእርሷ ጀርባ ላይ ተቀምጦ ከበረባት፡፡ የተዋረደች እንስሳ (አህያም) በኪሩቤል ላይ የሚቀመጠው ሰማያዊ ንጉሥ ክርስቶስ በትሕትናው ዙፋኑ መቀመጫ አደረጋት፤ ሸክም ያቆሰላት፥ ዱላ የሰለቻት፥ ዕረፍት የናፈቃት ‹‹ቀንበሬ ልዝብ፥ ሸክሜ ቀላል ነው›› ያለ ንጉሥ ተቀመጠባት፡፡

ዳውላና የነጋድራሶችን ሸቀጥ ተሸክማ አገር ‘ላገር የምትኳትን ይህች እንስሳ፤ ለቅጽበት እሳተ መለኰት ዙፋኑ ያደርገኛል ብላ ልታስብ ቀርቶ ልትቃዥ አትችልም ነበር ግን ሆነ። ክብሩን በእርሷ ሲገልጽ ይህ የመጀመሪያው አልነበረም፤ በብሉይ ዘመን የእግዚያብሔር ሰው በለዓም እግዚያብሔር ፈፅሞ የማይፈቅደውን ድርጊት ሊፈፅም ህዝቡን ያለጥፋቱ ሊረግም በእንስሳይቱ ጀርባ ላይ ሆኖ ጉዞ ጀመረ፡፡ ሲሔድባት ቆይቶ የእንስሳይቱ ጉዞ ድንገት ተገታ፡፡ ቆመች። በለዓም በሁኔታዋ ተበሳጭቶ ትሔድለት ዘንድ ቀጠቀጣት። ይሄኔ አህያይቱ በሰው አንደበት ተናገረችው፡፡ “ስለምን ያለጥፋቴ ትደበድበኛለህ፤ ሰይፈ ነበልባል ይዞ ከፊቴ የቆመው አይታይህም?” አለችው፤ ያ! የእግዚያብሔር መልዐክ ለእንስሳይቱ እንጂ ለበለዓም አልታየም ነበር።
ፈጣሪ በእንስሳቱ በኩል ለበለዓም ሊል የፈቀደው ነገር ነበርና እንስሳይቱን አከበራት፡፡

ጢባርዮስ ቄሳር የሕዝብና የንብረት ቆጠራ ሊያደርግ አገሩን በሙሉ ወደ ቤተልሔም ጠራ። እንግዳ መቀበያዎች በሙሉ ከየአገሩ በተሰበሰቡ ተቆጣሪዎች በመያዛቸው፣ ማርያምና ዮሴፍ ከቤተልሔም ነዋሪዎች በአንዱ ሰው ቤት ግርግም ገለባ ጐዝጉዘው ሰውነታቸውን ማሳረፍ ነበረባቸውና ጋደም አሉ። ብርዱ ቆዳን ሰርስሮ አንጀት ውስጥ የሚገባ ዓይነት ነው፡፡ ድንገት ማርያም በምጥ ተያዘች። የበኩር ልጇንም ወለደች። እረኞች ውዳሴ አቀረቡ፣ መላዕክት ዘመሩ። ስብሃት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ስምረቱ ለሰብ እያሉ። አህያይቱን ጨምሮ በግርግም የነበሩቱ እንስሳት ሙቅ ትንፋሻቸውን እያመነጩ ህፃኑን ሊንከባከቡት ሞከሩ። በዚህ ሰዓት የቤተልሔም በርካታ ቪላዎችና የእንግዳ ማረፊያዎች በግንዲላ ፍም ደምቀው፣ ነዋሪዎቻቸውንና እንግዶቻቸውን ለእንቅልፍ ያባብላሉ። ክርስቶስ ግን በእንስሳት ታጅቦ በእናቱ ማርያምና ዮሴፍ እቅፍ በመላዕክት መልካም ምኞት በእረኞች ዘፈን ውስጥ በግርግም ከበረ።

ክርስቶስ በተመላለሰባቸውና በኖረባቸው ጊዜያት ሁሉ ከምንም በላይ ትህትናን፣ ዝቅ በማለት ውስጥ ያለውን ክብርና በረከት ሲያስተምርና በተግባርም ሲያሳይ ኖሯል፡፡ ሆሣዕናም አንዱ ማስተማሪያው ነበር። ስመ ገናና ነው፡፡ ህዝቡም ሆነ ሮማውያኑ ቅኝ ገዢዎች ስለእርሱ ያላቸው ግንዛቤ የተምታታና ግልፅ ያለ ባይሆንም እጅግ ክብር ይሰጡት ነበር። ድውያንን ፈውሷል፤ አንካሶችን አዘልሏል፤ ከበረከቱ መና ብዙዎችን መግቧል። በድንቅ ትምህርቱ የሺዎችን አፍ አስከፍቷል። እንደሰው ቢታሰብ እንኳ ይህ ሰው በወርቅ የተንቆጠቆጡ ሰረገላዎች፣ በክብር ያጌጡ ጋሻ ጃግሬዎች ለንጉሥ የሚገባ የሠራዊት ሰልፍ ሲያንስበት ነው፤ ሊያውም የአባቱ የዳዊት ዙፋን ወደነበረበት ኢየሩሳሌም ሲገባ ግና ይህ ሁሉ ክብሩ በውርንጫ ጀርባ በህፃናት አጀብ ሆኖ እንዳይሔድ የሚከለክለው አልነበረም።

እርሱ በውርንጫዋ ጀርባ ላይ ተቀምጦ ኢየሩሳሌም የገባው የባለሰረገላዎችን ክብር ሊያዋርድ አልነበረም፡፡ ይልቁኑ በምድር ላይ በቆየባቸው ሰላሳ ሦስት ዓመታት ከሶስት ወር ውስጥ ማንንም አዋርዶ አያውቅም፡፡ ብዙዎችን ከትዕቢት ባርነት ነፃ ሊያወጣ ሲል ያደረገው ነው፡፡ በክብር ደመና የሚመላለስ ንጉሥ እኛ በምንንቃት ፍጡር ላይ ተቀምጦ መሔዱ፣ ቁሳዊ የሀብት ቁልል ብቻ ኖሮን ትህትና ለጐደለን ሁሉ መልዕክቱ ግልፅ ነው፡፡

ከምንም በላይ የልብን ውስጥ ክብርና ልዕልና እንድናስቀድም እጅግ ትሁት በሆነ መንገድ ተናገረ። "ከናንተ መካከል አንድ ስንኳ ንፁህ ቢኖር እርሱ የመጀመሪያውን ድንጋይ ይወርውባት!" ብሎ ፍትህ ከመስጠት በላይ ልዕልና የታል? የሰዎችን ልጆች ኃጢያት ሊመዘግብ ከተገባ እርሱ ፈጣሪ ነውና ከፈሪሳውያኑ ይልቅ ለህጉ ቀናዒ ነው፡፡ በአደባባይ እየተመፃደቁ ድንጋይ ያነሱባት ሁሉም እንደርሷ በድንጋይ ተወግረው ሊሞቱ ይገባቸው የነበሩ ናቸው ፡፡ ‘አንቺ ሴት ሒጂ ዳግመኛም ኃጢያት አትስሪ!’ አላት፡፡ ንጽህና ድንጋይ ካስነሳ ድንጋይ ሊያነሳባት ይገባ የነበረው እርሱ ብቻ ነበር ግን አላነሳባትም “ሒጂ!” አላት። ይህች ሴት ካላበደች ዳግም ያንን ኃጥያት ታደርገዋለች? ፈጽሞ! ድንጋይ ማንሳት ሲችል ድንጋይ ያላነሳ ትሁት! እርሱ ለድንጋይ አልመጣማ።

ይህ ሰንበት በጌትንት በክብር በውዳሴና በቅዳሴ ሆሣዕና በአርያም እየተባለ ሽማግሌዎችና ህጻናት አንደበት በድንጋዮችም ልሳን ሳይቀር እየተመስገነ ወደ ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም በክብር ሲገባ ለሰጠቸው ለተቀደስ ሰላምን ፍቅሩ መታሰቢያ ሆኖ የተሰጠ ነው።

ከደብረዘይት ወደ ኢየሩሳሌም በውርንጫ የሚያደርገውን ጉዞ ከመጀመሩ አስቀድሞ ኢያሪኮ ከተማ ውስጥ ነበር፡፡ ኢያሪኮ ቀራጩ ዘኪዮስ ቤት። ከነ ደቀ መዛሙርቱ ሲስተናገድ ውሎ ነበር አመሻሽ ላይ ጉዞ የጀመረው፡፡ ማንም የማይጠጋው፣ ፍቅር የተነሳው፣ ሕዝብ የጠላው፣ እርሱም ሕዝቡን የጠላው ቀራጩ ዘኪዎስን “ዛሬ ካንተ ጋር ነኝ!” አለው፡፡ ሕዝቡም ‘ይሄ ከሃጢያተኛ ጋር የሚውል ሃጥያተኛ ነው!’ አለና ተግተልትሎ ሊያየው እንዳልወጣ ትቶት በቤቱ ተከተተ፡፡ ፍቅርን አይቶ የማያውቀው ዘኪዎስ ባጋጠመው ነገር ተደነቀ፡፡ ጉድጓዱን
በፍቅር የሞላለት መሢህ ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታና ትዕዛዝ ከቤቱ ጣሪያ ሥር አርፏል፡፡

‘ከዚህ ፍቅር በኋላ በግፍ ያከማቸሁት ወርቅና ዲናር ለምኔ?’ አለ ዘኪዎስ፡፡ የህዝቡን ወርቅ ለህዝቡ አለና ጐዳና ላይ አውጥቶ በተነው፡፡ መሢሁ በትህትናና በፍቅሩ የዘኪዎስን ደዌ ፈወሰ፡፡ ከዘኪዎስ ቤት ጣሪያ ሥር ውሎ መባውን እየቆረሰ ወይኑን አብሮት እየጠጣ ልዑሉ ከበረ፡፡ ለእርሱ ክብር ማለት የተናቁትን ማክበር ነውና!

ክርስቶስ በሁሉም ትምህርቶቹና ድርጊቶቹ ትህትናን ከፍ ከፍ ያደረገ መምህር ነበር። ይህ ትህትናው እስከ መጨረሻዋ እራት ማለትም እስከ ጸሎት ሐሙስ አልፎም እስከ ጌቴ ሰማኔ ድረስ ዘልቋል። ዝቅ ብሎ የተማሪዎቹን እግር እስከማጠብ…የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው እስከማለት።

የሆሣዕናዋ ውርንጫ ነገር ሌላም የሚያሳስበን ነገር አለ። እጅግ የተናቀ የተዋረደና ለጉልበቱ ብቻ የሚፈለግ ፍጡር እንበል ሰው አንድ ቀን በአንዳች አጋጣሚ የመለኰቱ ክብር የሚገለጥበት ሊሆን እንደሚችል ማስተማሪያም ነው አጋጣሚው። ምክንያቱም መሢሁ ከአባቱ ከዳዊት ምድራዊ ዙፋን ይልቅ የመጣበትን የትህትና መንገድ ለማሳካት ስሙር ሆነው ካገኛቸው ፍጥረታትና ሰዎች መካከል የቤተ ፋጌዋ ውርንጫ አንዷ ናትና።

መለከት ባይነፋለትም በተንቀጠቀጠ የክብር ሰረገላ ላይ ባይቀመጥም፣ ልባቸው ውስጥ የነገሠባቸው በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎችና ህፃናት የዘንባባ ዝንጣፊ፤ መጐናጸፊያዎቻቸውንና የአርዛሊባኖስና ጥድ ቅርንጫፍ እያነጠፉ የታላቅ ንጉሥ አቀባበል ከማድረግ ወደ ኋላ አላሉም።

ወእንዘ ሰሙን በዓለ ፋሲካ ቀርቡ አርዳኢሁ ለአምላከ ጽድቅ ኀበ ደብረ ዘይት ሙራደ ዓቀብ ሀገረ እግዚአብሔር ወተቀበልዎ ሕዝብ ብዙኃን አዕሩግ ወሕፃናት ነሢኦሙ አዕፁቀ በቀልት እንዘ ይብሉ ሆሣዕና በአርያም ተፅዒኖ ዲበ ዕዋል ቦአ ሀገረ ኢየሩሳሌም በትፍሥሕት ወበሐሴት ይሁቦሙ ኃይለ ወሥልጣነ፡፡
“በፋሲካ በዓል ሰሞን የእውነት አምላክ ደቀ መዛሙርት ወደ ደብረ ዘይት ቀረቡ፤ በሀገረ እግዚአብሔር (ኢየሩሳሌም) አቀበቱ ላይ ብዙ አረጋውያንና ሕፃናት የዘንባባ ቅጠል ይዘው ሆሣዕና በአርያም እያሉ ተቀበሉት፣ በአህያ ውርንጫ ላይ ተጭኖ በፍጹም ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ገባ። ለእነዚህ ኃይልና ሥልጣንን ይሰጣቸዋል።
(ጾመ ድጓ ዘቅዱስ ያሬድ ኢትዮጵያዊ)

የሰሙነ ሕማማት መግቢያ በቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ ሆሳዕና ይባላል፤ ቀጥተኛ የቃሉ ትርጉም በብሉይ ኪዳን በዕብራይስጥ በተፃፈው በዳዊት መዝሙር 117፤25 “ נָּא הושִׁיָעה “/አሁን አድን የሚል/ ትርጉም ይኖረዋል፡፡
«ሆሣዕና» ቃሉ ከሁለት አረማይክ ቃላት የተሰራ ሲሆን ትርጉም «እባክህ እርዳ፣ አሁን አድን» ማለት ነው። እብራይስጡም ይህንኑ ቃል ወርሶ «הושענא » ሆሻአና ሲል ይገልፀዋል። አዎ «አሁን አድን፣ እባክህ እርዳን» ብሎ የአዳም ዘር ያጣውን ልጅነትና የደረሰበትን ሞት ለመላቀቅ የሚያሰማው የጩኸት ድምጽ ነው፣ «ሆሣዕና»!!!
ዳዊት ነቢይ በመንፈስ ቅዱስ ተመልክቶ ማዳኑን ሲጣራና አሁን ናልን ሲል ከዘመናት በፊት አድምጠነዋል። የውስጥ ዓይኖቹ ሩቅ አይተዋል። ማዳኑንም ሽተው እንዲህ ሲል ዘምሮለታል። «አቤቱ፥ እባክህ፥ አሁን አድን አቤቱ፥ እባክህ፥ አሁን አቅና» መዝ ፻፲፰፣፳፭

ሰሌን(ዘንባባ)-
እሾሓም ነው ፡-ትዕምርተ ኃይል፤ ትዕምርተ መዊዕ አለህ ሲሉ ዘንባባ ይዘው አመሰገኑት። እሳት አይበላውም ለብልቦ ይተወዋል፡-ባሕርይህ አይመረመርም ሲሉ
ፍሬው በእሾህ የተከበበ ነው፡-ዋህድ ባህርይ ነህ ሲሉ
ከዚህም ባሻገር በዘመነ ብሉይ ኤልሳዕ ኢዩን ቀርነ ቅብዑን ይዞ ሲያነግሰው፤ ዮዲት ሆሎፎርኒስን በገደለች ጊዜ፤ አብርሐም ይስሃቅን፤ ይስሃቅ ያዕቆብን በወለዱ ጊዜ ሰሌን(ዘንባባ) ቆርጠው ይዘው አመስግነዋልና፡፡
አህያይቱ የኦሪት ቀንበርም መሸከም የለመደች (የተለመደች ሕግ) እስራኤልም ህግን መጠበቅ የለመዱ ምሳሌ ስትሆን ዕዋል(ውርንጭላ) ወንጌል ያልተለመደችም ሕግ፤ ሕግን መጠበቅ ያልለመዱ የአሕዛብ ምሳሌ ናት። ከህፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አንደበት ለክብር ንጉሥ ምስጋና የቀረበበት ዕለት ነው ሆሣዕና! ሆሣዕና በአርያም !

“ለዚህ ታላቅ ትህትናህ ሆሳዕና በአርያም ምሥጋና በሠማይ!” ከማለት ያገዳቸው አንዳች የለም፡፡
ሆሣዕና በአርያም🌿
👍1
✥✥✥ ዕለት ሰኞ ✥✥✥

- ይህ ዕለት አንጽሖተ ቤተ መቅደስ እና መርገመ በለስ የተፈጸመበት ዕለተ ነው፡፡ በቅዱስ ማርቆስ ወንጌል እንደተገለጠልን ጌታችን ከቢታንያ ወጥቶ ወደ ኢየሩሳሌም ሲሄድ ተራበ፡፡ በለስም ከሩቅ ዓየ፣ በለስዋ ግን ከቅጠል ብቻ በቀር ፍሬ ምንም ኣላገኘባትም ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲህ ለዘለዓለም ፍሬ ኣይገኝብሽ ከአንቺ ፍሬ የሚበላ ኦይኑር አላት ያን ጊዜውንም በለሲቱ ደርቃለች (ማር.11፥12-19/ማቴ.21፥19/ሉቃ.1945-46)
በለስ የተባለች ኦሪት ናት፡- በለስ አገኘ ማለቱ ኦሪት በዚህ ዓለም ሰፍና አገኛት ሲል ነው፡፡ ወደ እርስዋም ሄደ ማለት ፈጻሜ ሕግ ተባለ (ሥርዓተ ኦሪትን ማለት በ8ኛው ቀን መገዘር በ40 ቀን መሥዋዕት ማቅረብን... እየፈጸመ አደገ) ማለት ነው፣ ፍሬ አላገኘባትም አለ ሕግ ከመባልዋ በቀር ድኅነትን አላደረገባትም፣ ፍሬ አይገኝብሽ አላት ሲል፡- ባንቺ ድኅንነት አይደረግ አላት፡፡ ይህም ቅዱ ዳዊት ‹‹መሥዋዕትን ቁርባንን አልወደድሁም ሥጋህን ኣንጻልኝ፣ የሚቃጠለውንና ስለኃጢኣት የሚቀርበውን መሥዋዕት አልወደድሁም ሲለ የኦሪትን ሕግ (ዐሠርቱ ትዕዛዛትን) አሳለፋቸው ማለት አይደለም፡፡ ቅዱስ ዳዊት እንደነገረን በመሥዋዕተ ኦሪት ፍፁም ድኅንነት ኣለመገኘቱን አውቆ ማሳለፉን እና ፍፁም ድኅንነት የምናገኝበትን ቅዱስ ሥጋውን እና ክቡር ደሙን መሥዋዕት አድርጎ ማቅረቡን ያሳያል፡፡››

አንድም፦ በለስ ያለው ኃጢኣትን ነው፡፡ የበለስ ቅጠል ሰፊ እንደሆነ ኃጢኣትን በዚህ ዓለም ሰፍና ኣገኛት፡፡ ወደ እርሷ ሄደ ፍሬም አላገኘባትም ማለት በአይሁድ አንደበት በሐሰት ኃጢኣተኛ ተባለ እንጂ (ስለ እኛ መተላለፍ እንደበደለኛ ተቆጠረ እንጂ) ኃጢኣትን አልሠራም ሲል ነው፡፡ ፍሬ አይገኝብሽ ሲል፡- ባንቺ በመጣ ፍዳ የሚያዝ አይኑር አላት ማለት ነው፡፡

ከዚህ በመቀጠል ጌታችን ወደ ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ ወደ ቤተ መቅደስ ገባ፡፡ ቤተ መቅደሱም ቤተ ጸሎት፣ ቤተ መሥዋዕት መሆኑ ቀርቶ ቤተ ምስያጥ (የንግድ ቤት) ሆኖ ቢያገኘው ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች እናንተ ግን የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችኋት ብሎ በዚያ ያሉትን ሁሉ ኣስወጣቸው፡፡ ይኸም በጠቅላላው ማደሪያው ቤቱ የነበርን የአዳም ለጆች ኃጢኣት ሰፍኖብን ስንኖር ቢያገኘን ኃጢኣታችንን ሁሉ እንዳራቀልን የሚገልጽ ነው፡፡ (ማቴ.21፥12-17/ማር.11፥15-24/ሉቃ.19፥4) ይቆየን
"The Arian dilemma"

መናፍቁ አርዮስ ያስተማረው የ "ወልድ ፍጡር" ኑፋቄ በዘመኑ ከተነሱ እንደ ቅዱስ አትናቴዎስ ካሉ አባቶች ጀምሮ እስከ ቅርብ ዘመን ሊቃውንት ድረስ ብዙ መልሶች የተሰጡበት ነው። አርዮሳውያን ይህንን ኑፋቄያቸውን አመክንዮአዊ መሰረት ለማስያዝ ከሚጠቀሟቸው ሙግቶች አንዱ የአርዮስ አጣብቂኝ (The Arian dilemma) ብለን ልንጠራው የምንችለው ጥያቄ አንዱ ነው።

ይህ ጥያቄ በአጭሩ "አብ ወልድን የወለደው በፍቃዱ ነው ወይስ ተገድዶ ነው?" የሚል ነው። ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች አብ ወልድን የወለደው በፍቃዱ ነው ካሉ አብ ባይፈቅድ ኖሮ ወልድ አይኖርም ነበር ስለምንል ይህ ደግሞ ወልድ ላይኖር ይችል ነበር ማለት ስለሚሆን የወልድን መለኮታዊነት (ከመለኮታዊ ባሕሪያት አንዱ 'የግድ መኖር' (Necessary existence) እንደመሆኑ) መካድ ነው። በአንጻሩ ክርስቲያኖች አብ ወልድን የወለደው ተገድዶ ነው ካሉ እግዚአብሔር ተገድዶ የሚያደርገው ነገር ሊኖር አይችልምና (ይህ ከእግዚአብሔር የበለጠ ሕግ አውጪ አለ ወይም እግዚአብሔርን የሚመራው ሌላ አካል አለ ማለት ስለሚሆን) የአብን አምላክነት መካድ ይሆንባቸዋል። በዚህም መሰረት ወይ ወልድ እግዚአብሔር አይደለም አልያም እግዚአብሔር አምላክ አይደለም ማለት ነው፡፡

ይህ በቀደሙ ሙስሊም ሊቃውንትም ጥቅም ላይ የዋለ አጣብቂኝ ለወልድ ብቻ ሳይሆን የመንፈስ ቅዱስን መለኮታዊነት ለመገዳደርም ጥቅም ላይ መዋል የሚችል ነው። ነገር ግን ሀሳቡ ሌላ ሶስተኛ ምርጫን ከግምት ያላስገባ ስለሆነ የውሸት አጣብቂኝ ነው፡፡ ቅዱስ አትናቴዎስ ዘእስክንድርያ ለአርዮሳውያን መልስ በሰጠበት መጽሐፉ እንደገለጸው "አብ ወልድን የወለደው በግዴታ ወይም በፍቃድ ሳይሆን በባሕሪይ ነው"[1] ሰዎች የተለያዩ ስሜቶች (ሐዘን ፣ ደስታ ፣ ቁጣ ወዘተ) የሚሰማቸው ተገድደው ወይም ፈልገው ሳይሆን በባሕሪያቸው ስሜት ያላቸው ፍጡራን ስለሆኑ ነው። እንስሳት የማያስቡት ተገድደው ወይም በፈቃዳቸው ላለማሰብ ወስነው ሳይሆን በባሕሪያቸው ማሰብ ስለማይችሉ ነው። አምላካችንም መሐሪ ፣ ቸር ፣ ፍትሃዊ የሆነው ተገድዶ ወይም በፈቃዱ ሳይሆን (እግዚአብሔር ፍትሃዊ የሆነው በፈቃዱ ነው ማለት ባይፈቅድ ኖሮ ኢፍትሃዊ ሊሆን ይችል ነበር ማለት ስለሚሆን ይህ የተሳሳተ አስተምህሮ ነው) በባሕሪው እነዚህ መገለጫዎች ዘለአለማዊ ገንዘቡ ስለሆኑ ነው። በተመሳሳይ አብ ወልድን የወለደው ወይም መንፈስ ቅዱስ ከአብ የሰረጸው በአንዱ ወይም በሶስቱ አካላት ፈቃድ ሳይሆን በባሕሪይ ነው።

ስንደመድመው ይህ ጥያቄ ለሥላሴ አካላት ብቻ ሳይሆን ለማንኛውም ከእግዚአብሔር ሕልውና ጋር ተለይተው ለማያውቁ ባሕሪያቱ በሙሉ (ነባቢነቱ ፣ ፍቅሩ ፣ ቁጣው ፣ ጌትነቱ ፣ ፈጣሪነቱ ወዘተ) ሊጠየቅ የሚችል ከመሆኑ ባለፈ ሶስተኛውን ምርጫ (የባሕሪይ ድርጊትን) ከግምት ስለማያስገባ የተሳሳተ ጥያቄ ነው።

[1] የልቡና ችሎት ፣ በረከት አዝመራው ገጽ 195-97

© @Jacobite_apologetics27
✞✞✞ እንኩዋን ለበዓለ ምሴተ ሐሙስ በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞

+*"+ ምሴተ ሐሙስ +"*+

=>ስም አጠራሩ ከፍ ከፍ ይበልና መድኃኒታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ ከ1978 ዓመታት በፊት "ምሴተ ሐሙስ"
በምትባለው በዚሕች ዕለት:-

1.በወዳጁ በዓልዓዛር ቤት የዓለማት ፈጣሪ ሲሆን
በትሕትና ዝቅ ብሎ የደቀ መዛሙርቱን እግር አጥቧል::

2.ለእኛ ድኅነት ይሆነን ዘንድ ቅዱስ ሥጋውን : ክቡር
ደሙን ለመጀመሪያ ጊዜ ሰጥቷል::

3.በጌቴሴማኒ ላበቱ እንደ ደም እየተንጠፈጠፈ ጸልዮ
"ወደ ፈተና እንዳትገቡ ጸልዩ" ሲል አስተምሯል::

4.ምሽት 3 ሰዓት አካባቢ ይሁዳ ሊቃነ ካህናቱን አስከትሎ
መጥቶ ለ30 ብር አሳልፎ ሰጥቶታል::
(ማቴ. 26:26 / ዮሐ. 13:1)

=>ይሕ ሁሉ ለእኛ ድኅነት ተፈጽሟልና ምስጋናና ክብር
ለፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይሁን::

=>+"+ ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘለዓለም
ሕይወት አለው:: እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሳዋለሁ::
ሥጋዬ እውነተኛ መብል: ደሜም እውነተኛ መጠጥ ነውና::
ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል:: እኔም
በርሱ እኖራለሁ:: +"+ (ዮሐ. 6:53-56)

=>+"+ እግራቸውን አጥቦ: ልብሱንም አንስቶ ዳግመኛ
ተቀመጠ:: እንዲሕም አላቸው:- 'ያደረግሁላችሁን
ታስተውላላችሁን? እናንተ መምሕርና ጌታ ትሉኛላችሁ::
እንዲሁ ነኝና መልካም ትላላችሁ:: እንግዲህ እኔ ጌታና
መምሕር ስሆን እግራችሁን ካጠብሁ እናንተ ደግሞ እርስ
በርሳችሁ እግራችሁን ትተጣጠቡ ዘንድ ይገባል::' +"+
(ዮሐ. 13:12-14)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

https://www.tgoop.com/zikirekdusn
👍2
ኢየሱስም ሆምጣጤውን ከተቀበለ ባኃላ ተፈፀሙ አለ።ራሱንም አዘንብሎ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ።
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ለመናፍቃንና ለአህዛብ መልስ አላት!
ኢየሱስም ሆምጣጤውን ከተቀበለ ባኃላ ተፈፀሙ አለ።ራሱንም አዘንብሎ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ።
ታመመ ሞትን ከተቀበለበት ከሥጋ ተዋሕዶ በመስቀል ላይ በፈቃዱ ለሥጋውያን ሞተ ባሕርየ መለኮት ሥጋን ተዋሕዶ በማኅፀን ካደረ ጀምሮ ሥጋ ገንዘቡ እንደመሆኑ በሥጋ ይኸንን ሥርዓት ፈጸመ፡፡
ለማይመረመር ለመለኮቱ ባሕርይ እንደሚገባ ደግሞ እርሱ ኅብስት አበርክቶ ዂሉን ያጠግባል፡፡ አይራብም አይጠማም አይደክምም አያንቀላፋም አይታመምም አይሞትም ሕይወትን ለዂሉ ይሰጣል፡፡ ዳግመኛ በዚያ በሲኦል ተገዝተው ያሉ ነፍሳትን ያድን ዘንድ በአካለ ነፍስ ወደ ሲኦል ወረደ በመለኮቱም ሲኦልን በዘበዘ፤››
(የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ ቄርሎስ)

እጆቹን እግሮቹን በተቸነከረባቸው ችንካሮች መወጋቱንም እናምናለን፡፡ ነቢዩ ኢሳይያስ ‹እርሱ ደዌያችንን ወሰደ ሕማማችንንም ተሸከመ እኛን ለማዳን ኃጢአታችንንም ለማስተስረይ መከራ ተቀበለ› እንዳለ
(ኢሳ 53;4)
በባሕርዩ ሕማም የሌለበት ሲኾን በሥጋ የታመመ ነው፡፡ በእርሱ ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ድነናል፡፡ በተገረፈና በተቸነከረም ጊዜ በመከራው ዂሉ መለኮትን ሕማም ተሰማው የሚል ሰው ቢኖር የተለየ የተወገዘ ይሁን››
(ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ጎርጎርዮስ)

እርሱ መቼም መች ከመለኮቱ ሳይለይ የሰውነትን ሥራ ዂሉ ገንዘቡ አደረገ፡፡ ይኸውም መራብ መጠማት መንገድ በመሔድ መድከም በመስቀል ላይ መሰቀል በብረት ችንካር መቸንከር ነው፡፡ በሰውነቱ መቸም መች ሰው ነው በአምላክነቱም ሰውን የፈጠረ ነው ነገር ግን መከፈል በሌለበት ተዋህዶ ሰው እንደ መኾኑ ስለ እኛ የታመመው የሞተው እርሱ ነው፡፡ በመለኮቱ ግን መቸም መች አይታመምም አይሞትም፡፡ ሕማምንና ሞትንም አይቀበልም፡፡ በሞቱ ሞትን ያጠፋው እርሱ ነው፡፡ ሲኦልንም የበዘበዘው እርሱ ነው፤›› (የአንጾኪያው ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ዲዮናስዮስ)፡፡

‹‹ነፍሱን ከሥጋው በለየ ጊዜ ያን ጊዜ በሲኦል ፈጥኖ ብርሃን ታየ፡፡ ጌታችን በአካለ ሥጋ ያይደለ በአካለ ነፍስ ወደ ሲኦል ሔደ፡፡ ሲኦል ተነዋወጠች፤ መሠረቶቿም እፈርስ እፈርስ አሉ፡፡ ምድርን ያለ ጊዜዋ እንዳታልፍ ክብርት ደሙን በምድር ላይ አፈሰሰ፡፡ ከኅልፈት ጠበቃት በእርሷ ያለውንም ዂሉ ጠበቀ፡፡ ስለ ፍጥረት ዂሉ ሥጋውን በመስቀል እንደ ተሰቀለ ተወው፡፡ ነፍሱ ግን ወደ ሲኦል ወረደች ከዚያ ተግዘው የነበሩ ነፍሳትን አዳነች፤ ሲኦልንም በዘበዘች፡፡ ፍጥረትንም ዂሉ ገንዘብ አደረገች፡፡ ሥጋውም በመቃብር ያሉ ሙታንን አስነሣ፤ ነፍሱም በሲኦል ተግዘው የነበሩ ነፍሳትን ፈታች፤›› (የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ ሐዋርያው ቅዱስ አትናቴዎስ)፡፡

‹‹ከብርሃን የተገኘ ብርሃን፣ ከባሕርይ አምላክ የተገኘ የባሕርይ አምላክ፣ የተወለደ እንጂ ያልተፈጠረ፣ በባሕርዩ ከአባቱ ጋር አንድ የሚኾን፡፡ ዂሉ የተፈጠረበት፤ ያለ እርሱ ግን ምንም ምን የተፈጠረ የሌለ፤ በሰማይ በምድር ያለውም ቢኾን፡፡ እኛን ስለ ማዳን ከሰማየ ሰማያት ወርዶ በግብረ መንፈስ ቅዱስ ከቅድስት ድንግል ማርያም ፍጹም ሰው ኾነ፡፡ የሠላሳ ዘመን ጐልማሳ ኾኖ በጲላጦስ የሹመት ዘመን ስለ እኛ ተሰቀለ፤ ስለ እኛም ታመመ፤ ሞተ፤ ተቀበረ፤›› (ሠለስቱ ምእት)፡፡

‹‹ምትሐት ያይደለ በእውነት ተራበ፤ ተጠማ፡፡ ዳግመኛም ከኃጥአን፣ ከመጸብሐን ጋር በላ፤ ጠጣ፡፡ ያቀረቡለትንም በላ፡፡ ራሱን አሳልፎ ለመስቀል ሰጠ፡፡ እጁን፣ እግሩን ተቸነከረ፤ ጐኑን በጦር ተወጋ፡፡ ከእርሱም ቅዱስ ምሥጢር የተገለጠበት ደምና ውኃ ፈሰሰ (ወጣ)›› (ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ)፡፡

‹‹የሚሠዋ በግ እርሱ ነው፤ የሚሠዋ ካህን እርሱ ነው፡፡ ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋርም መሥዋዕት የሚቀበል እርሱ ነው፡፡ በፈቃዱ መከራን በሥጋው የተቀበለ መከራንም ዂሉ የታገሠ እርሱ ነው፡፡ እንደ በግ ሊሠዋ መጣ፤ በግ በሚሸልተው ሰው ፊት እንደማይናገር አልተናገረም፡፡ በአንደበቱ ሐሰት አልተገኘበትም፤›› (ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ)፡፡

‹‹በሥጋ መወለድ፣ በመስቀል መከራ መቀበል፣ መሞት፣ መነሣት፣ ገንዘቡ የኾነ እርሱ እግዚአብሔር ቃል ነው፡፡ ስለዚህ በመስቀል ላይ ሳለ ከጥንት ጀምሮ በመቃብር ያሉ ሙታንን ዂሉ አስነሣ፤›› (ሰማዕቱ ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ፊልክስ)፡፡

‹‹ሙሴም ሞትን ያጠፋ ዘንድ አልቻለም፤ እርሱንም ይዞ ገዛው እንጂ፡፡ ከእርሱም በኋላ የተነሡ ነቢያትንም ዂሉ ሞት ገዛቸው እንጂ፡፡ ክርስቶስ ግን በቸርነቱ ለዂሉ ሕይወትን ሰጠ፤›› (የሮማ ኤጲስ ቆጶስ ቅዱስ አቡሊዲስ)፡፡

‹‹በመስቀል በሥጋ ተሰቅሎ ሳለ ለመለኮት ከሥጋ መለየት የለበትም፡፡ አንዲት ሰዓትም ቢሆን የዐይን ጥቅሻ ያህል ስንኳ ቢሆንም መለኮት ከትስብእት አልተለየም፣ በመቃብር ውስጥ በሰላም መለኮት ከትስብእት አልተለየም (የሮሜ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አዮክንድዮስ)፡፡

‹‹ከአብ ጋር አንድ እንደ መኾንህ ሞት የሌለብህ አንተ ነህ፡፡ ከእኛ ጋር አንድ እንደ መኾንህ በፈቃድህ የሞትህ አንተ ነህ፡፡ በመቃብር ያደርህ አንተ ነህ፡፡ በኪሩቤል ላይ ያለህ አንተ ነህ፡፡ ከሙታን ጋር በመቃብር የነበርህ አንተ ነህ፡፡ በአንተ ሕማምና ሞትም ድኅነት ተሰጠ፡፡ ከሙታን ጋር የተቈጠርህ አንተ ነህ፡፡ ለሙታንም ትንሣኤን የምትሰጥ አንተ ነህ፡፡ ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት በመቃብር ያደርህ አንተ ነህ፡፡ በዘመኑ ዂሉ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የምትኖር አንተ ነህ፡፡ በመለኮት ሕማም ሳይኖርብህ በሥጋ የታመምህ አካላዊ የእግዚአብሔር ቃል አንተ ነህ፤›› (የኪስኪስ ኤጲስ ቆጶስ ቅዱስ ኤራቅሊስ)፡፡

‹‹ኃጢአታችንን ለማሥተስረይ በሥጋ እንዲህ ታመመ፤ እንደ ሞተ ከነፍሱም በተለየ ጊዜ ሥጋውን እንደ ገነዙ እናምናለን፤›› (የኢየሩሳሌም ኤጲስ ቆጶስ ቅዱስ ዮሐንስ እንዲህ አለ)፡፡

‹‹ነቢይ ዳዊት ‹ነፍሴን በሲኦል አትተዋትም፤ የባሕርይ ልጅህንም ሙስና መቃብርን ያይ ዘንድ አሳልፈህ አትሰጠውም› አለ፡፡ ይህም ጌታ በተዋሐደው አካል ያለውን የነፍስና የሥጋ ተዋሕዶ ያስረዳል፡፡ የቀና ልቡና ዕውቀት በእርሱ ጸንቶ ይኖር ዘንድ፡፡ ዳዊት እንደ ተናገረው እውነት ኾነ፤ ነፍስ መለኮትን ተዋሕዳ ወደ ሲኦል ወርዳለችና፡፡ ሥጋም ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት በመቃብር ሳለ መለኮት ከሥጋ አልተለየም፤ አምላክ ሰው የመኾኑን እውነት ያስረዳ ዘንድ፡፡ መለኮት ነፍስን ተዋሕዶ በአካለ ነፍስ የሲኦል ምሥጢርን ገልጦ ፈጽሟልና በሲኦልም በቁራኝነት አልተያዘምና፤››
(የቆጵሮስ ደሴት ኤጲስ ቆጶስ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ)

ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን
የአባቶቻችን በረከት ይደርብን
👍1
"ቅዳሚት ሥዑር"
ዕለተ ቅዳሜ እግዚአብሔር አምላካችን የሚታዩትንና የማይታዩትን፣ በእግር የሚሔዱትን፣ በክንፍ የሚበሩትን እና በባሕር የሚዋኙትን እንስሳትን፣ በመጨረሻም ሰውን በአርአያውና በአምሳሉ ፈጥሮ ያረፈባት ዕለት ነች፡፡ የመጀመሪያዋ ቅዳሜ ለእግዚአብሔር የዕረፍት ዕለት ናት፡፡ እግዚአብሔርን ፍጥረታትን ፈጥሮ ከፈጸመ በኋላ ስላረፈባት ‹ሰንበት ዐባይ› (ታላቋ ሰንበት) ትባላለች፡፡ ይህቺን ዕለት እስራኤላውያን እንዲያከብሯት ታዟል፡፡ ዕለተ ቀዳሚት (ሰንበት ዐባይ) በዘመነ ሐዲስም የተለየ የደኅነት ሥራ ተከናውኖባታል፡፡ እግዚአብሔር ጥንት ሥነ ፈጥረትን በመፍጠር ዕረፍት እንዳደረገባት ዅሉ፣ የፍጥረት ርእስ የኾነውን አዳምን ለማዳን ሕማምና ሞት የተቀበለው አምላካችን ክርስቶስ በመቃብር አርፎባታል (ማቴ. ፳፯፥፷፩)፡፡

ቀዳሚት ሰንበት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በከርሠ መቃብር አርፎ የዋለባት ዕለት በመኾኗ ‹ቀዳሚት ሥዑር› ወይም ‹ቀዳም ሥዑር› ትሰኛለች፡፡ ‹ሥዑር› የተባለችበት ምክንያትም በዓመት አንድ ቀን ስለምትጾም (የጾም ቀን በመኾኗ) ነው፡፡ የጌታችን እናት ቅድስት ድንግል ማርያም፣ ወዳጆቹ ቅዱሳን ሐዋርያት ጌታችን ተላልፎ ከተሰጠበት ዕለት ጀምሮ ብርሃነ ትንሣኤውን እስኪያዩ ድረስ እኽል ውኃ በአፋቸው አልዞረም፡፡ ይመኩበትና ተስፋ ያደረጉት የነበረ አምላካቸው በመቃብር ስላረፈ ዕለቷን ሞቱን በማሰብና ትንሣኤውን በመናፈቅ በጾም አክብረዋታል፡፡

እመቤታችንና ቅዱሳን ሐዋርያት በማዘን፣ በመጾምና በመጸለይ ዕለቷን እንዳከበሯት ዅሉ የተዋሕዶ ልጆችም የተቻላቸው ከሐሙስ ጀምረው በማክፈል (በመጾም) እኽል ውኃ ሳይቀምሱ ለሁለት ቀናት ያድራሉ፡፡ ያልተቻላቸው ደግሞ ዓርብ ማታ በልተው ቅዳሜን በመጾም ትንሣኤን ያከብራሉ፡፡ በዚህ ዕለት ከሰኞ ከሆሣዕና ማግሥት ጀምረው እስከ ስቅለተ ዓርብ ድረስ በስግደት እና በጾም ያሳለፉ ምእመናን በዕለተ ቅዳሜ በቅጽረ ቤተ ክርስቲያን ይሰበሰባሉ፡፡ የጠዋቱ ጸሎት ሲፈጸምም ካህናቱ ‹‹ገብረ ሰላመ በመስቀሉ፤ በመስቀሉ ሰላምን መሠረተ» እያሉ በቤተ ክርስቲያን ለተሰበሰቡ ምእመናን የምሥራች ቄጠማ ያድላሉ፡፡

ቄጠማው የምሥራች ምልክት ነው፡፡ ቄጠማው የምሥራች ምልክት ተደርጐ የተወሰደው በኖኅ ዘመን ከተፈጸመው ታሪክ ጋር በማቆራኘት ነው፡፡ ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚነግረን በጻድቁ ኖኅ ዘመን የነበሩ ሕዝቦች ከሕገ እግዚአብሔር ውጪ ኾነው እጅግ የሚያሳዝን ኃጢአት በሠሩ ጊዜ በንፍር ውኃ ተጥለቅልቀዋል፡፡ በወቅቱ ጻድቁ ኖኅ ወደ መርከብ ይዞአቸው ከገባው እንስሳት መካከል የውኃውን መጉደል ለመረዳት ርግብን በመርከብ መስኮት አሾልኮ ይለቃታል፤ እርሷም ቄጠማ በአፍዋ ይዛ ትመልሳለች፡፡ ኖኅም በዚህ ቄጠማ የውኃውን መድረቅ ተረድቶ ተደስቷል (ዘፍ. ፱፥፩-፳፱)፡፡

ቄጠማ ለጥፋት ውኃ መድረቅ የምሥራች መንገሪያ እንደ ኾነ ዅሉ፣ አሁንም ‹‹በክርስቶስ ሞት ሞተ ነፍስ ከሰው ልጆች ተወገደ፤›› ስትል ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ለልጆቿ ቄጠማ ታድላለች፡፡ ምእመናንም የምሥራች ተምሳሌት የኾነውን ቄጠማ በግንባራቸው ያስሩታል፡፡ የክርስቶስ ተከታዮች ዅሉ ከጨለማ ወደ ብርሃን፤ ከዋዕየ ሲኦል (የሲኦል ቃጠሎ) ወደ ጥንተ ማኅደራቸው ገነት መመለሳቸውን በዚህ አኳኋን እየገለጡ በዓለ ትንሣኤን በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ያከብራሉ፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ይቆየን
2025/07/10 04:50:00
Back to Top
HTML Embed Code: