Telegram Web
"…እንደተናገረ ተነሥቶአል ! ማቴ 28፣6
           መቃብሩም ባዶ ነው እልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልል

ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን
አሰሮ ለሰይጣን
አግአዞ ለአዳም
ሰላም
እምይእዜሰ
ኮነ
ፍስሐ ወሰላም፡፡





👉" መጽሐፍ እንደሚል ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፥ ተቀበረም፥ መጽሐፍም እንደሚል በሦስተኛው ቀን ተነሣ" 1ኛ ቆሮ15 ፣ 3-4

👉" ሕያውን ከሙታን መካከል ስለ ምን ትፈልጋላችሁ? ተነሥቶአል እንጂ በዚህ የለም።" ሉቃ 24፣5
👍3
የሞዓ ተዋህዶ ወቅታዊ መግልጫ
በየ አቅጣጫው ካላጠፋንሽ እሚሏትን ቤተክርስቲያን ጽንፈኛው ፕሮቴስታንት ብድግ ብሎ መስቀል ዐደባባይን እንውረስ አለ። በዝምታ ታለፈ።

ጽንፈኛው ሙስሊምም ትምህርቱን በመቅሰም ደሴ ላይ የቅዱስ ገብርኤልን ቤተ ክርስቲያን መስጊድ እናደርገዋለን አለ። ይኽም ዝም ተባለ።

ሕዝቡ ግን ምን ሲደረግ? አለ። ይኽ በደሴ ደብረ ገሊላ ቅዱስ ገብርኤል ለጉባኤ የታደመ ምእመን ነው።

ጽንፈኞች ዐይኖቻችሁ እስኪቀሉ እንደተቅበዘበዙ ይቀራሉ እንጅ የአባቶቹን ርስት የማያስነካ ትውልድ ተነሥቷል።
ውሉደ ያሬድ ሊቃውንት እንኳን ለቀለም አባታችሁ በዓለ ስዋሬ አደረሳችሁ!!! በቤተክርስቲያን ታሪክም ሆነ በኢትዮጵያ ባለውለተኝነት እግራችን እስኪነቃ ብንዞር የቅዱስ ያሬድን ያህል ባለውለታ የምናገኝ አይመስለኝም ሊቅነትን ከብህትውና ጋር ዜማን ከስብከት ጋር ሀገር ወዳድነትን ከትህትና ጋር አስተባብሮ የያዘ ቅዱስ!!!

ሌሎች ስለእርሱ ሲሰሙ መግቢያ ይጠፋቸዋል ዜማው አቅላቸውን ያስታቸዋል ተመራምረው ተመራምረው ፅፈው ፅፈው አይበቃቸውም እኛ ቤተሰቦቹ ደግሞ ጥሎልን የሄደውን እንቁ ዜማ ትተን አንዴ ቅዱሱን ሙዚቀኛ እናደርገዋለን ሌላ ጊዜ ደግሞ ዜማውን ሬጌና ብሉዝ ከተባሉ ኳኳታዎች ጋር ልናግባባውና ልናነፃፅረው እንነሳለን ሲገርምኮ!!

##################################

ሰላም ለአጽፋረ እግርከ ከዋክብተ ጽባሕ ጽዱላት
እስከ ምዕራበ እግር አብርሃ መልዕልተ አጻብዕ ሰማያት
ከመ ተሰወርከ ያሬድ እምገፀ ዐይኑ ለሞት
ሰውረኒ በጸሎትከ እምዕለት እኪት
ወባልሓኒ እምኩሉ መንሱት

ሃገሩን በዜማው ጣዕም ያረሰረሰ አእላፍ መናንያንንና ሊቃውንትን ወልዶ ለሀገር ያበረከተ ጥዑመ ልሳን ወሊቀ ካህናት ቅዱስ ያሬድ ለበአለ ስዋሬው በሰላም አደረሳችሁ

የታላቁ ሊቅ የቅዱስ ያሬድ በረከት ይደርብን

ኦርቶዶክሳውያን እንኳን ለብርሀናችን ለካህኑ ያሬድ በዓለ ስዋሬ አደረሳችሁ

ኢትዮጵያውያን በሙሉ የራሳችንን ወርቆች ጥለን የሰው ብረት አድናቂዎች ሆነን ብንዘነጋውም እንኳን ለስም መጠሪያችን ለቅዱስ ያሬድ በዓለ ሥዋሬ አደረሰን

Berhanu Tekleyared
2025/07/09 22:19:27
Back to Top
HTML Embed Code: