ጥቂት ማስታወሻ!
☞በተለይ ለሙስሊም ወገኖቻችን አድርሱልኝ!
"በጩኸት ብዛት ሐሰትን እውነት ማድረግ አይቻልም!"
"#በኦርቶዶክሳውያን_እያሳበቡ_ግጭት_መቀስቀስ_ይቁም!"
➊ጎንደር በተፈጠረው ነገር ከማዘኔም በላይ፥ ምን እንደተፈጠረ ለማወቅ እንኳ በእጅጉ ተቸግሬ ነበር፡፡ (በዕለቱ) እኔ መደበኛ ሥራዬ ፈጣሪዬን ማገልገል ነውና የነበርኩትም እዚያው ነው፡፡
ነገሩን አስቀድመው ተዘጋጅተውበት የቆዩ ጽንፈኛ አካላት ግን፥ የእነርሱ ክፋትና ድርጊት እንዳይጋለጥ "የጦስ ዶሮ" ሊያደርጉን ሞክረዋል፡፡ አሁንም ቀጥለውበታል፡፡
እውነቱ ግን እኔ (ክርስቲያን ነኝና፥ ጠላትህን ውደድ የሚል ፈጣሪዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ነውና) ጽንፈኛ ግለሰቦች የሚሉትን አላደረግሁትም፥ ለወደፊቱም ጨርሶ ላደርገው አልችልም። (ምክንያቱም ከሃይማኖቴ ተቃራኒ ነውና)
➋የፋና ጋዜጠኛ ስለሚሉት፦
በመጀመሪያ የፋና Tv ጋዜጠኛ አልነበርኩምም፤ አይደለሁምም። የሬዲዮ ጋዜጠኝነቱን ካቆምኩም ከአንድ ዓመት በላይ አልፎኛል፡፡ (ሰዎቹ ግን ከምን እንዳመጡት አላውቅም ፥ አሁንም የፋና Tv ጋዜጠኛ እያሉ መለፈፋቸውን ቀጥለዋል)
በነገራችሁ ላይ ጽንፈኞቹ በሚከሱት ልክ አለመሆኔን የሚመሰክርልኝ እግዚአብሔር ቢሆንም፥ ለዘጠኝ ዓመታት በሠራሁበት የሬዲዮ ጋዜጠኝነት ሥራ ላይ፥ አንድም ቀን ሙስሊምም ሆነ የሌላ እምነት ተከታይ ወገኖቼን የሚያሳዝን ፕሮግራምም ሆነ ዜና ሠርቼ እንደማላውቅ ምስክሩ አድማጭ ነው፡፡
➌ስለሚዘዋወረው ድምጽ፦
በመጀመሪያ ደረጃ (ባለፈውም እንደተናገርኩት) አብዛኛው ጽንፈኞቹ የሚያዘዋውሩት ድምጽ፦
1፡ ተቆራርጦ ለፍላጎታቸው የዋለ ነው፤
2፡ ጽንፈኛ ግለሰቦች ለሚናገሩት የተሰጠ ምላሽ ነው፤ (እርሱም ቢሆን የአንዱን ቀን ትምህርት ከሌላኛው ቀን በመቀጠል መደበኛ መልእክቱን ለቋል)
3፡ አሁን እየቀሰቀሰ ነው ብለው የሚጠቀሙበት አምና የተነገረ ነው፤ (እሱም ከአውዱ ውጭ ተወስዷል)
4፡ በሚስጥር አገኘነው የሚሉት ሁሉ እኔው ራሴ በአደባባይ ያስተማርኩትና በyoutube የተለጠፈ ነው፡፡
➍ሙስሊሙን ይጠላል ስለሚሉት፦
እኔ ተወልጄ ያደግሁት ጎንደር ነው፤ ከልጅነት እስከ እውቀት የልብ ጓደኞቼ ሙስሊሞቹ ናቸው፡፡ የኢድ፥ የአረፋና የጳጉሜን ትዝታወቼ ዛሬም በልቤ ውስጥ አሉ፡፡ የቁርአን መግቢያ የአረብኛ ቋንቋ ያስጠኑኝ "ሻሒያችን" የምንላቸው አባትም ታላቅ ነበሩ፡፡ (ነፍሳቸውን ይማርና)
ዛሬም ድረስ ሙስሊም ወዳጆች አሉኝ፡፡ ጽንፈኞቹ ለክፋት ድምጽ እየቆራረጡ ከሚያጋጩ ይልቅስ ስለሙስሊም-ክርስቲያን ወንድማማችነት ያስተማርሁት ስንት ነበረ፡፡ በዚያውም ላይ (መናገሩ አስፈላጊ ባይሆንም) በማኅበራችን በየወሩ ከምናግዛቸው ወገኖቻችን መካከል ጥቂት የማይባሉት ሙስሊም ናቸው፡፡
ዋናው ነገር ግን ደጋግሜ እላለሁ፤ እኔ ክርስቲያን ነኝ። ሰዎችን ልቆጣ ልገስጽ እችላለሁ፡፡ ማንንም ግን መጥላት አልችልም፡፡ ይህ ከሃይማኖቴ ይጋጫል፡፡ ገሃነመ እሳትም ያስጥለኛል፡፡ ከሁሉ ይልቅ የምፈራው እግዚአብሔርን ነውና!
➎ወጣቶችን አደራጅቷል ስለሚባለው፦
የዚህ ወሬ መነሻው በ2013 ኅዳር ላይ ወጣቶችን ቅርሶቻቸውን ካስጎበኘሁ በኋላ የተናገርኩት ነው፡፡ ምንም እንኳ መደጀራት (በሕግም በሃይማኖትም) ስሕተትነት ባይኖረውም፥ እኔ ግን ተደራጁ ያልኳቸው ልጆች ሥራቸው ጓደኞቻቸውን (ቤተሰቦቻቸውን) ለንስሃ እንዲያበቁ ነበር፡፡ (እርሱም ወዲያው የቆመ ተግባር ነው)
ከዚህ ውጪ ግን በቤተክርስቲያን ዐውደ ምሕረት ወጥቼ ከማስተማሬ በቀር ያደራጀሁትም፥ ያስከተልሁትም ሰው የለም! (ምንስ ሊያረግልኝ)
➏እኔ ላይ እየተደረገ ያለው ዘመቻ በአጋጣሚ ትናንት በተፈጠረው ችግር አይደለም። የግድያ ዛቻ ሊደርሰኝ ከጀመረ ድፍን አንድ ዓመት አልፏል፡ ፡ ላለፉት 13 ወራት ተወልጄ ባደግሁባት ከተማ እንኳ በጎዳና ላይ እንደልብ መንቀሳቀስ ሳልችል ነው የቆየሁት። ጽንፈኞቹ መልካቸውን ቀይረው የመጡት ደግሞ በራሳቸው ያልተሳካላቸውን (በአጋጣሚው) መንግሥት ያሳካልናል ብለው ነው፡፡
➐እኛ (ኦርቶዶክሳውያን) እንደ ጽንፈኞቹ አይደለንም እንጂ፥ እግረ መንገዱንም እነዚህ ግለሰቦች መደበኛውን ሙስሊም አይወክሉም በሚል እሳቤ እንጂ ብዙ የምናውቀው ነገር ነበር። ከሃገር ውጪ እስከ ውስጥ ድረስ ኢትዮጵያን ለማፍረስና የሚጠሏት ሃገራት ሲሣይ ለማድረግ እነማን ምን እንደሚሠሩ ይታወቃል፡፡
እስኪ ተመልከቱት ፥ ፍልስጤም ውስጥ የተገደለችውን ጋዜጠኛ ፎቶ እንኳ እኛን ለመክሰስ ሲጠቀሙበት! (በነገራችሁ ላይ ጋዜጠኛዋ ክርስቲያን ናት!)
☞በዚያውስ ላይ ባለፉት 4 ዓመታት ብቻ በመቶዎች የሚቆጠሩ አብያተክርስቲያናት እንደ ችቦ ሲነዱ፥ በሺህ የሚቆጠሩ ክርስቲያኖች ሲገደሉ ዝም ያልነው ስለሃገርና ስለአብሮነታችን ነውኮ! (እንተዛዘን እንጂ) ለሚያልፍ ቀን ስለምን የግል ክፋታቸውን በእምነት በሚያላክኩ ሰዎች እንባላለን?
ሀገራችን አንድነታችን እንጂ መለያየታችን አይጠቅማትም፤ በግለሰቦች ትርክት መሳቡን ትተን በአንድነት (እንደ ቀድሞው) ብንኖር ደግ ነው፡፡
ሕያው እግዚአብሔር ምስክሬ ነው፤ ሙስሊም ወገኖቼ አብረን እንቁም! (ጥላቻ የለኝም፥ ለወደፊቱም እንዲኖረኝ አልሻም)
☞መንግሥትም በውጪ ሃገር ሆነው የግጭት ቅስቀሳ የሚያደርጉትን ባይደርስባቸው እንኳ፥ በሃገር ውስጥ ያሉትን አድቡ ይበልልን!
የእውነት አምላክ እውነቱን ለሁላችንም ይግለጥልን!
አሜን!
#ዲያቆን_ዮርዳኖስ_አበበ

👍1
"፯/7 ምክሮች!"
#ቁ፩.
☞ለንስሃ ተዘጋጅ!
☞ወደ ቤተክርስቲያን ና!
☞ወገብህን/ሱሪህን ታጠቅ!
(13/09/2012)
#ቁ.፪
☞ነገርን ሁሉ በ3ቱ መሥፈርት ሳትመዝን አትቀበል፡-
#መጽሐፍ_ቅዱስ #አዋልድ_መጻሕፍት #ቅዱስ_ትውፊት
#ቁ.፫.
☞ቁጥር ለማብዛትም ሆነ፡ ምን አለበት ብለህ መቼም ቢሆን ከመናፍቃን ጋር አትተባበር፡፡
እነርሱ ካሉ እግዚአብሔር ይለይሃልና!
#ቁ.፬
☞ምንም ነገርን ከመቀበልህ፡ ከመንቀፍህና ከመደገፍህ በፊት፡-
እንደ #ክርስቲያን ለፈጣሪህ ንገር!
እንደ #ሰው አገላብጠህ መርምር!
ቁ.፭
☞ከእግዚአብሔር እና የርሱ ከሆኑት በቀር ፈጽመህ ምስጢርህን አትግለጽ!
ኋላ ተወግተህ የምትሞተው ባወጣኸው ምስጢር፡ አመንኩትም ባልከው ሰው ነውና!
ቁ.፮
☞#የቤተክርስቲያንን ሥርዓት ትጠብቅ/ታስጠብቅም ዘንድ ቸል አትበል!
አጥሩ ከፈረሰ ቤቱም መፍረሱ፡ መዘረፉም አይቀርምና!
ቁ.፯
☞በሰማይ ካለው እግዚአብሔርና ወዳጆቹ በቀር በሥጋ ለባሽ አትታመን! አትከተለው!
አታድንቀው!
አታምልከው!
@Re (14/09/2012)
DnYordanos Abebe
Re post13/09/2014
https://www.tgoop.com/zikirekdusn

"ምክንያት ፈልገን መታረቅ ሲገባን፤ ምክንያት ፈልገን ነው አይደል ምንጣላው? ምክንያት ፈልገን እንጣላለን፤ የማያጣላ ነገር ቢኖር እንኳን የሚያጣላ እንፈልጋለን በደንብ አድርገን ማለት ነው፤ ሰው አንድ ሺህ መልካም ነገር ተደርጎለት አንድ ክፉ ነገር ሲያገኝ የምያስታርቀውን አንድ ሺህ ነገሮ ንቆ የሚያጣላ አንድ ነገር ካገኘ ፀብ ያነሳል። እግዚአብሔር ደግሞ ከሱ ጋር የሚያጣላን አንድ ሺህ ነገር እያለ፤ ከሱ ጋር የሚያስታርቀን አንድ ነገር ካገኘ በዚያን እግዚአብሔር ፊቱን ይመልሳል። 78 ነፍሳት በልቶ አይደል እንዴ ቀዝቃዛ ውሃ ሲያገኝ በዚያች የማረው፤...ብዙ በድሎ አንድ ሚያስታርቀው ካገኘ ሰው እግዚአብሔርን መሰለ ሚባለው በዚህ ጊዜ ነው። ብዙ በደል እያለ አንድ መታረቂያ ሲገኝ ፈልጎ መታረቅ እግዚአብሔርን መምሰል ነው"
መጋቢ ብሉይ ወሐዲስ አባ ገብረኪዳን!
መጋቢ ብሉይ ወሐዲስ አባ ገብረኪዳን!
❤3😢3🥰1
መልካም ጋብቻ መምህር እግዚአብሔር ከእናንተ ጋ ይሁን❤
❤13👍3
ብሔራዊ የሀዘን ቀን ይታወጅ!
ሰንደቅ አላማው ዝቅ ይበል!
"…ዛሬ በዐማራ ላይ እንዲህ በሚፈጸመው ጅምላ ጭፍጨፋ ዝም ያላችሁ ጳጳሳት፣ ሼኮችና ፓስተሮች ነገ የእናንተን መጨረሻ ማየት ብቻ ነው። ዛሬ ዝም ያላችሁ ኦሮሞዎች፣ ጉራጌ፣ አፋር፣ ሱማሌ፣ ደቡብ፣ ሲዳማ፣ ወላይታ ከንባታ ወዘተ ነገ የዐማራን ርዳታ የምትፈልጉበት ጊዜ ይመጣል።
"…ህዝቡ የዐማራን አስከሬን መቅበር ሰለቸው። ደከመውም።
"…ደግሜ እጠይቃለሁ…
፩ኛ፦ ሰንደቅ ዓላም ዝቅ ይበል
፪ኛ፦ ብሔራዊ የሀዘን ቀን ይታወጅ

❤1
"እንኳን ለእመቤታችን ሕንፀታ ቤተክርስቲያን አደረሰን"
ኢየሱስ ክርስቶስ ለድህነተ ዓለም የተገለጠባት ከተማ ድንግል ማርያም ናት
መዝ 47:2 የምድር ሁሉ ደስታ የፅዮን ተራራ ነው እርሱም የትልቁ ንጉስ ከተማ ነው ቅዱስ ያሬድም በሰማይ ስላለ አርያም ፈንታ በምድር ላይ ያለ አርያም የሆንሽ አንቺ ነሽ ቅዱስ ኤፍሬም በውዳሴ አምላክን ያለመለወጥ የወለድሽ ሆይ የምድር ሁለተኛ ሰማይ ሆንሽ እውነተኛ ፀሐይ ከአንቺ ወጥቶልና አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ጨለማን ያሳደደ የቅዱሳን ብርሃን የሚሆን እውነተኛ ፀሐይ የወለደችው ሁለተኞ ሰማይ ቅድስት ማርያም ናት።