Telegram Web
መልካም ወጣት ማለት ከኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሀይማኖት ወጥተህ በመ*ቅ አዳራሽ መክተም አይደለም።
መልካም ወጣት ማለት ክርስቶስ የተሰቀለበትን መስቀል ከአንገትህ ላይ በጥሶ መጣል አይደለም።
መልካም ወጣት ማለት ቅድስት ድንግል ማርያምን መካድ ማለት አይደለም።
መልካም ወጣት ማለት ለሰዎች ይታዩ ዘንድ በምድር ላይ ባለጠግነትንና ዝነኝነትን ማካበት አይደለም በምድር ላይ ሁሉ የከንቱ ከንቱ ነው።

ይልቁንስ መልካም ወጣት ማለት ወንጌል ነው
ወዳጄ ወንጌል ማለት በሽንገላ ከንፈር ኢየሱስ ያድናል ማለት አይደለም። ወንጌል ማለት ክርስቶስን አምኛለውኝ ብሎ በግላዊ ግብር ለክርስቶስ ያለመታመንም ማለት አይደለም። ወንጌል ማለት መከራ መስቀልን መሸከም ነው። ወንጌል ማለት ክርስቶስ የተጓዘበትን የኩርንችት መንገድ በደስታ መራመድ ነው ። ወንጌል ማለት ለማዕተብህ ትሞታለህ ሲባል ከስጋው ይልቅ ነፍስን አስበልጦ ቀድሞ መሰለፍ ነው። ወንጌል ማለት ስለክርስቶስ ፍቅር ስጋህን እና ምኞትህን ገድለህ ለሞተልህ አምላክ መሰጠት ነው። ወንጌል ማለት ነፍስን መግደል በማይችሉት ፈርዖኖች ፊት በክብር ማሸብሸብ ነው ።
ወንጌል የምታወራው ልብ ወለድ ሳይሆን የምትላላክለት መወደድ ትዕዛዝ እንጅ። ወንጌል ማለት ክርስቶስ በደሙ የዋጃት ቤተክርስቲያን ክብር ላይ ዕጣ ሲጣጣሉባት እንደ 44 ታቦት ብላቴናዎች ቀድሞ የመገኘት ጥሪ ነው። ወንጌል የምትታዘበው እና ከአውደምህረት ላይ የምትወረውረው የማትኖርበት ቃል አይደለም። የምታልፍበት የመከራ ኮረብታ እንጅ ።
ከእዚህ አማናዊ ወንጌል ከሆነው ህዝብ ተማር። በጣምም ተማር!
ልጆቻችሁን ወንድም እኅቶቻችሁን "መልካም ወጣት አዳራሽ" የምትልኩ ኦርቶዶክሳውያን ጊዜያዊ መላ ፍለጋ ልጆቻችሁን ለዘለዓለማዊ ሞት አሳልፋችሁ እየሰጣችሁ እንደሆነ ዕወቁ።
አዎ ልክ ነው ዘፋኙ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ነው አዎ ልክ ነው ሰካራሙ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ነው አዎ ልክ ነው ሱሰኛው ኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ነው አዎ ልክ ነው ተሳዳቢው ተራጋሚው ተደባዳቢው አመጸኛው የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ነው ነገር ግን ቤተ ክርስቲያኒቷ እና ሀይማኖቷ አጥብቀው ያወግዛሉ።
የአባ ዘጋስጫ ሀይማኖት የአባ ኤፍሬም ሀይማኖት የቅዱስ ያሬድ ሀይማኖት የቅድስት አፎሚያ ሀይማኖት የአቡነ ተክለ ሀይማኖት ገብረ መንፈስ ቅዱስ አቡነ አረጋዊ ሀይማኖት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ነው ትልቅ እምነት እና ከክርስቶስ ቀጥሎ በክርስቶስ መንገድ የሄዱ ቅዱሳን የተጠሩባት ሀይማኖት (1ቆሮ᎐11:1) እኔ ስጠራበት በመጥፎ ስራዬ ላፍር በሀይማኖታችን ግን ልኮራ ይገባል።
ይህ ሰበብ ሊሆነን አይገባም እኔ መልካም ወጣት እንድሆን መ*ቅ መሆን በፍጹም አይጠበቅብኝም!!
ኦርቶዶክሳውያን ሰባክያነ ወንጌል ማኅበረ ቅዱሳንና ሌሎች መንፈሳዊ ማኅበራት ሰንበት ትምህርት ቤቶች ኦርቶዶክሳዊውን ወጣት የመጠበቅ ኃላፊነትና አደራ ከጌታ የተሰጣችሁ ነውና ትውልዱን ከጥፋት ለመጠበቅ ድጋማችሁን ሁሉ የነፍስ ዋጋ ያድርግላችሁ።
ዳሩ ግን ባለ ጠጎች ሊሆኑ የሚፈልጉ በጥፋትና በመፍረስ ሰዎችን በሚያሰጥምና በሚያሰንፍ በሚጎዳም በብዙ ምኞትና በፈተና በወጥመድም ይወድቃሉ።

ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ሥር ነውና (፩ጢሞ ፮፣፲) አንዳንዶች ይህን ሲመኙ ከሃይማኖት ተሳስተው በብዙ ሥቃይ ራሳቸውን ወጉ።
አንተ ግን የእግዚአብሔር ሰው ሆይ ከዚህ ሽሽ ጽድቅንና እግዚአብሔርን መምሰል እምነትንም ፍቅርንም መጽናትንም የዋህነትንም ተከታተል።

መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደል የተጠራህለትንም በብዙም ምስክሮች ፊት በመልካም መታመን የታመንህለትን የዘላለምን ሕይወት ያዝ።
ደግሞ ሁለተኛ የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ ትወደኛለህን? አለው። አዎን ጌታ ሆይ፥ እንድወድህ አንተ ታውቃለህ አለው። ጠቦቶቼን ጠብቅ አለው።" (ዮሐ 21:16-17 )

#ኦርቶዶክሳዊ_ወጣት
👍2
ከመልካም ወጣትነት ወደ ለየለት ዕብደት ከተድላ ደስታ ወደ ልቅሶና ዋይታ
መልካም የነበረው ወጣት በዕብዶች፣ አጭበርባሪዎችና ዕውራን መሪዎች እየተጭበረበረና እያበደ ወደ ገደል እየገባ ነው።
በኦርቶዶክሳዊ እምነቱ ለዘመናት በሥነ ምግባር ታንጾ ደስተኛ የነበረው ትውልድ ወደ ለየለት ዋይታና ልቅሶ እየገባ ነው።

ዕውራን መሪዎቻቸው በዘረፉት ገንዘብ እየሳቁና እየተሳለቁ ትውልዱን ግን እየሳቁበትና እየተሳለቁበት፣ ብሎም እያሳቀቁት ነው።
ዛሬ ላይ ሃይማኖት-አልባ የሆነው የትናንቱ የአውሮፓውያኑ የፕሮቴስታንት እንቅስቃሴ መጀመሪያ ላይ እንደዚህ ነበር። አሁን ላይ በሥነ ምግባር ጉድለት በዓለም ላይ አንደኛ ሆኗል። የአምልኮ ቦታዎቻቸው እየተዘጉ ነው። ትውልዱ የዕለት ከዕለት ኑሮው ገደብ አልባ ኃጢአት መሥራት ላይ ያተኮረ ነው።

ምክንያቱ ደግሞ ዕውራን መሪዎች በባዶ ቅዠት ስለመሯቸው ነው። መጨረሻ ላይ እንደተጭበረበሩ ሲገባቸው የአምልኮ ቦታቸውን ሽጠው ለጭፈራና ለዳንኪራ መሰብሰቢያ አደረጉት።
የእኔ ትውልድ መልካም ወጣትም የነገ እጣ ፈንታው ይኼው ነው።
እጅግ በጣም ያሳዝናል።

“ ዕውሮችን የሚመሩ ዕውሮች ናቸው፤ ዕውርም ዕውርን ቢመራው ሁለቱም ወደ ጉድጓድ ይወድቃሉ።”
— ማቴዎስ 15፥14
👍3
ዲያቆን አለን ➻መመዘኛ መስፈርቱስ📒

#ዲያቆናዊት ማለት ለሴት ጾታ ሆኖ ኣገልጋይ ማለት ነው
🌹•••ዲያቆናዊት ለመሆን በክርስትያናዊ ሰነ ምግባር የተመሰከረላቸው እንግዳን በአግባቡ በመቀበል ፡ የቅዱሳን እግር በማጠብ ፡ የተቸገሩትን በመርዳት ፡ ለመልካም ስራዎች ንቁ በመሆን፡በመልካም ስራዎችዎ የታመነባቸው ፡ ከነገር የራቁ ፡ ልጆቻቸው በስርአት ያሳደጉ፡ ዕድሜያቸው ከስድሳ (60) ዓመት በላይ የሆኑ ፡ በአንድ ባል ፀንታ የኖረች፡ ሁለተኛ ያላገባች መሆን አለባት። ስለዚ በዚ ስነ ምግባር የተመሰከረላቸው ዲያቆናዊት ተብለው ይሾማሉ ። (ፍት.ክ.ኣን.8 ፡ 2ይ ዲዲስቅልያ 17 ፡ 1ይ ጢሞ 5፡9-11)

➻ስርዓተ ሲመት (የሹመት ስርዓት)

ሕገ ቤተክርስቲያን በሚፈቅደው መሰረት ይህን መመዘኛ አሟልታ የተገኘች ወደ ኤጲስ ቆጶስ ቀርባ የቡራኬ ጸሎት ከተፀለየላት በኋላ ኤጲስ ቆጶስ በኣንብሮት እድ ሳይሆን በቃል ብቻ ዲያቆናዊት ብዬሻለሁ ይላታል ።
➻የዲያቆናዊት ኣገልግሎት

በሴቶች መግቢያ በር ማስተባበርና መቆጣጠር ፡ከኤጲስ ቆጶስ፡ካህን አና ዲያቆን ወደ ሴት ምእመናን ትላላካለች። በንኡስ ክርስቲያን ጥምቀ አካላቸው ደግሞ ዲያቆናዊትዋ ትቀባቸዋለች።

በአጠቃላይ በስርዓተ ቤተክርስቲያን ሴቶችን የሚመለከት ለሴቶች ማስተማር መምከር እና ማገዝ ይገባታል።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን
👍2
እዚያው ጨርሱ... በውስጥ ተነጋገሩ...
+++
ለቅድስት ቤተክርስቲያን ሥርዓት ቀናዒ የሆኑ ሰዎች አንዳንድ "አገልጋዮች" በዐደባባይ ያበላሹትን ነገር ያርሙ ዘንድ በዐደባባይ ሐሳብ (ትችት፣ ነቀፋ) ሲሰነዝሩ "እባካችሁ በውስጥ ጨርሱ... እዚያው ጨርሱ" እያሉ አስተያየት የሚሰጡ ብዙዎች ናቸው። ለመሆኑ እዚው የት ነው? ውስጥስ የት ነው?

አውቃለሁ "እዚያው ጨርሱ" ማለት ጉዳዩን ዐደባባይ ሳታወጡት ተነጋግራችሁ ፍቱት ማለት ነው። ነገርግን ስለብዙ ምክንያቶች ጉዳዩን እዚያው መጨረስ የማይቻልበት ሁኔታ ይፈጠራልና አስተያይት ሰጪዎች ይህንን ታሳቢ ብታደርጉ።

አንዳንድ አገልጋዮች ስሕተታቸውን በግል ስትነግሯቸው የማይሰሙ፣ ሐሳብ የማይቀበሉ፣ በምእመኑ ዘንድ ያላቸውን ከልክ ያለፈ መወደድ ተማምነው ከእኔ በላይ ሊቅ የለም ብለው የሚያምኑና እንደውም ሐሳብ ያቀረበላቸውን ሰው የሚንቁና ሊሳለቁበት የሚፈልጉ ናቸው። እነዚህ አገልጋዮች አብዛኞቹ ያላቸውን እውቅና (ዝና) የሚያመልኩና ይህን ተማምነው ከስሕተታቸው እንዲታረሙ የሚነግሯቸውን ሰዎች ምንም አያመጡም እያሉ የሚደነፉ የዐደባባይ ቅዱሳን የጓዳ እርኩሳን ናቸው። ታዲያ ስትመክሯቸው ካልሰሙ ምን ታደርጋላችሁ? ከእንደዚህ ዓይነቶቹ ጋርስ እንዴት "እዚያው" መጨረስ ይቻላል?

አንዳንድ አገልጋዮች ደግሞ ስሕተታቸውን ስትነግሯቸው ለጊዜው ይቀበሉና ነገርግን ስሕተቱን ደጋግመው ይፈጽሙታል። አሁንም ስትነግሯቸው እየተቅለሰለሱ በይስሙላ ትሕትና ይቀበሏችሁና ዞረው የስሕተቱ መንገድ ላይ ይገኛሉ። እነዚህ ሰዎች አጭበርባሪዎች ናቸው። ከራሳቸውም አልፈው ሌሎችን የሚያሰናክሉም ናቸው። ከስሕተታቸው መመለስ የማይፈልጉ አስመሳዮችም ስለሆኑ ከእነርሱ ጋር ችግሮችን "እዚያው" መጨረስ አይቻልም።

አንዳንዶቹ ደግሞ ጭራሽ ስሕተትን በዐደባባይ የሚሠሩ ናቸው። ምናልባትም ባለማወቅ፣ ባለማስተዋልም ስሕተትን በዐደባባይ በሕዝብ ፊት የሚፈጽሙ ይኖራሉ። ታዲያ ስሕተቱ በብዙዎች ፊት ስለተፈጸመ ማስተካከያውም በብዙዎች ፊት መሆን አለበት። ለምሳሌ ዛሬ በሰማይ ኀሙስ ነው ብሎ በዐደባባይ መቀለድ ተገቢ አይደለምና ብዙዎችም ይህንን ሰምተው ሊሳሳቱ ይችላሉና እንደዚህ ዓይነቶችን ጉዳዮችም እዚያው መጨረስ አይቻልም።

ስለሆነም በየትችቶች ሥር እየገባችሁ "እዚያው ጨርሱ" የምትሉ ሰዎች እነዚህንና መሰል ምክንያቶችን ከግምት ውስጥ ብታስገቡ መልካም ነው። ከዚህ ባለፈ ግን የግል አጀንዳቸውን በዐደባባይ እያነሡ የሚናቆሩ፣ የሚሰዳደቡ ወዘተ አገልጋዮች ካሉ በእርግጥም እነርሱ እዚያው ቢጨርሱ የተሻለ ነው። ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን የሚጥሱ ሰዎችን በተመለከተ የሚሰነዘሩ የአካሄድ ትችቶችን ግን እዚያው ጨርሱ ማለት ተገቢ አይመስለኝም። እዚያው ጨርሱ ለማለት እንደምትጠቅሱት እዚህ መጨረስም ተገቢ የሚሆንበትን አግባብ በጥቅስ ማቅረብ ይቻላልና አንዳንዴ እዚያው ጨርሱ ከማለታችን በፊት ጉዳዩ ግላዊ ነው ወይስ ከሥርዓተ ቤተክርስቲያን ጋር ይገናኛል የሚለውን ብናስብበት መልካም ነው።
ልብ ይስጠን!
2
2025/07/08 21:58:27
Back to Top
HTML Embed Code: