tgoop.com/Yahiwenesei/2461
Last Update:
#የተዓምረኛው የጪጩ ደ/ኃ/ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ታሪክ በአጭር በአጭሩ
#ክፍል _፩
+++ #ጽንሰተ_ሀሳብ - #የሀሳብ_መጸነስ +++
#ታሪኩ የሚጀምረው በ1886 ዓ/ም ነው። ከዚያ በፊት በጪጩ ፣ ዲላና አካባቢው ላይ ቤተክርስቲያን ስላልነበር በጪጩ አካባቢ ይኖሩ የነበሩ ኦርቶዶክሳዊያን ክርስቲያኖች ከምስጢራተ ቤተ ክርስቲያን ለመሳተፍ ይቸገሩ ነበር ። ማለትም ሰው ሲወለድ ክርስትና የሚያስነሱበት ፣ ሲሞትም የሚቀብሩበት ቤ/ክ በቅርበት አልነበረምና ፣
#እነኚህንና እንደ ተክሊል ፣ ንስሃ ፣ ስጋወደሙን ለሌሎችንም መንፈሳዊ አገልግሎቶች ለማግኘት እንዳሁኑ ዘመናዊ ተሽከርካሪ የለምና በበቅሎ ፣ በፈረስ ካልሆነም በእግር እሩቅ ቦታ መጓዝ ግዳቸው ነበር።
#በ1882 ዓ/ም ቡሌ ስላሴ ሲተከል ጥቂት ርቀቱን ቢቀንስላቸውም ግን ከ3 እና 4 ሰዓት በላይ መጓዙ አልቀረላቸውም ነበር።
#ይህ ችግር ያንገፈገፋቸው በወቅቱ የነበሩት የአካባቢው ታላላቅ ሰዎች እርስ በእርስ በጪጩ አካባቢ ቤተክርስቲያን ስለማነጽና ታቦት የማምጣት ሀሳብ ያስቡ ፣ ይመክሩ ጀመር .....ይቀጥላል .....
#የዚህ ተዓምረኛ ስፍራ ታሪክ ለብዙዎች እንዲደርስ ሼር ስለምታደርጉ አብሳሪው መልዓክ የጸሎታችሁን መልስ ያብስራችሁ !!!
@Yahiwenesei
BY ያህዌ ንሲ (እግዚአብሔር ዓላማዬ ነው)
Share with your friend now:
tgoop.com/Yahiwenesei/2461